የደብረምጥማቅ ፃድቃኔ ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል እና ህንፃ ቤተክርስቲያን ምርቃት ዛሬ ተከብሮ ውሏል።
በሰሜን ሸዋ ዞን ሞጃና ወደራ ወረዳ የምትገኘው የደብረምጥማቅ ፃድቃኔ ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል እና አስር አመታት የግንባታ ሂደትን የወሰደው ህንፃ ቤተክርስቲያን ምርቃት በሰላም ተከብሮ መጠናቀቁን ወረዳው አስታውቋል።
ከእስከዛሬዉ ለየት ባለ መልኩ ሰፊ ቁጥር ያለዉ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች መታደማቸውን የገለጹት የወረዳዉ ሠላምና ድህነት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሸዋፈረዉ ግርማ በዓሉ በድምቀት አክብረዉ ዉለዋል ሲሉ ገልጸዋል።
ኃላፊው ክብረ በዓሉም በሰላም መጠናቀቁን ተከትሎ ምዕመናኑ ወደ ቤታቸዉ የመሸኘቱ ስራ እየተከናወነ መሆኑን አስታውቀዋል።
❤ t.me/tikvahethmagazine