የሊቢያ ብሔራዊ ቡድን ቅጣት ተጣለበት !
ሊቢያ በቅርቡ ከቤኒን ጋር ቤንጋዚ ላይ በነበራት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የተፈጠረውን ክስተት ተከትሎ ከካፍ ቅጣት ተጥሎባታል።
የቤኒን ብሔራዊ ቡድን ከሊቢያ ጋር በነበረው የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ ወቅት ጥቃት እንደደረሰበት አስታውቆ ነበር።
የቤኒን ብሔራዊ ቡድን ከሊቢያ ጋር ካደረገው ጨዋታ በኋላ የሊቢያ ፖሊሶች ተጨዋቾቹ እና አሰልጣኙን ባስ ውስጥ አስገብተው በዱላ መደብደባቸው ተገልጾ ነበር።
አሁን ላይ ካፍ የሊቢያ ደጋፊዎች እና ባለስልጣናት በጨዋታው እና ከጨዋታው በኋላ ባሳዩት ያልተገባ ባህሪ ምክንያት ደንብ መጣሳቸውን ገልጿል።
በዚህም ምክንያት የሊቢያ ብሔራዊ ቡድን በቀጣይ ሁለት ጨዋታዎችን በዝግ ስታዲየም እንዲያደርግ ከካፍ የቅጣት ውሳኔ እንደተላለፍበት ተነግሯል።
ሊቢያ በቅርቡ በናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን ላይ ባደረጉት ያልተገባ ድርጊት በፎርፌ ሶስት ነጥብ እና ሶስት ጎል እንደተሰጠባቸው አይዘነጋም።
@tikvahethsport @kidusyoftahe