ትምህርት ሚኒስቴር


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


ተጨማሪ መረጃዎችን
በዌብሳይት - www.moe.gov.et

በሊንክዲን - https://www.linkedin.com/company/ministry-of-education-ethiopia
በትዊተር - http://twitter.com/fdremoe
በፌስቡክ -https://www.facebook.com/fdremoe/
በቴሌግራም-https://t.me/timihert_minister
ይከታተሉ።

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


ማስታወቂያ
የድህረምረቃ ፕሮግራሞች (NGAT) የመግቢያ ፈተና ለመውሰድ የተመዘጋባችሁ በሙሉ ይህንን ሊንክ ( https://ngat.ethernet.edu.et) በመጫን መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።


በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ የማህበረሰብ ጉድኝት ሥራዎች የህብረተሰቡን ፍላጎት መሠረት ያደረጉና ችግር ፈቺ ሊሆኑ እንደሚገባ ተጠቆመ፡። (ታህሳስ 26/04/2017 ዓ.ም) ከ47 ዩኒቨርስቲዎች ለተውጣጡ የማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክተሮች ስልጠና ተሰጥቷል። በትምህርት ሚኒስቴር የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች ተወካይ መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሠራዊት ሃንዲሶ በስልጠናው ወቅት እንደገለጹት የማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎች የህብረተሰቡን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ ፣ ሙያዊ ፣ ሳይንሳዊና ችግሮችንም በአግባቡ የሚፈቱ ሊሆን ይገባል። ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአካባቢያቸው ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫና የንቅናቄ ስራዎችን በማከናወን በማህበረሰብ ጉድኝት ስራዎች የተቆጠረ ተከታታይነትና ወጥነት ያለው ውጤት እንዲመዘገብ በትጋት መስራት እንደሚጠበቅባቸውም ዶ/ር ሠራዊት ተናግረዋል፡፡
የማህበረሰብ ጉድኝት እና አገር በቀል እዉቀት ዴስክ ሃላፊ ወ/ሮ ሰላም አለሙ በበኩላቸው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሚከናወኑ ቁልፍ ተልዕኮዎች መካከል የማህበረሰብ ጉድኝት ሥራ አንደኛው መሆኑን አመልክተው ተቋማቱ የአካባቢያቸውን ማህበረሰብ በማሳተፍ ችግሮች እንዲቀረፉ በትጋት መስራትና የማህበራዊ ሀላፊነታውን መወጣት እንደሚገባቸው ተናግረዋል። የስልጠናው ዓላማም አሳሳቢ እየሆኑ በመጡና ተለይተው በተቀመጡ ማህበራዊ ጉዳዮች ማለትም የአእምሮ ጤናና አደንዛዥ እጽ፣ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት፣ ህገወጥ ስደትና የሰዎች ዝውውር ላይ የምርምርና ግብዛቤ ፈጠራ ስራ እንዲሰሩ ለማስቻል መሆኑን አመልክተዋል።። ተቋማቱ የትምህርት ጥራትን ለማሳደግ በአካባቢያቸው ያሉ ትምህርት ቤቶችን እንዲደግፉ ፣ የማህበረሰቡ ዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ግንዛቤ እንዲያሳዳድጉ እና እንዲያግዙ ማስቻልም ሌላኛው አላማ መሆኑን ጠቅሰዋል። በስልጠናው ላይ ሁሉም የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች የማህበረሰብ ጉድኝት ዳይሬክተሮች የተሳተፉ ሲሆን ከትምህርት ሚኒስቴር ፤ ከጤና ሚኒስቴር ፣ከመንገድ ደህንትና መድህን ፈንድ ፣ ከስደተኖች ጉዳይ አስተዳደር እና ከጅማ ዩኒቨርስቲ በመጡ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷቸዋል።




የትምህርት ሚኒስቴር ከICDL Africa እና kepler ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረመ፡፡
-------------------------- // ----------------------------
(ታህሳስ 04/2017 ዓ.ም) ስምምነቱ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ምሩቃንን የዲጂታልና ሶፍት ሰኪል በማጎልበት ብቁና ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ድጋፍ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

በሂደትም የዩኒቨርሲቲ እና ኢንዱስትሪ ትብብርን በማሳደግ ምሩቃን የተሻለ ክህሎት እና የስራ እድል የሚያገኙበትን ሁኔታዎች ለማመቻቸት እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ባደረጉት ንግግር የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ምሩቃን ያለባቸውን የዲጂታልና ሶፍት ስኪል ክህሎት ክፍተቶች በመለየት ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል መሆኑን አብራርተዋል።

ሚኒስተር ድኤታው አክለው እንደገለጹት የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከኢንዱስትሪ ዘርፉ ጋር ያላቸውን ትስስርና ትብብር በተለየ መልኩ ለመደገፍ እገዛ እንደሚኖረውም አብራርተዋል።

የአይሲዲኤል አፍሪካ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሶሎንዥ ኢሚዩሊሳ በበኩላቸው ድርጅታቸው አፍሪካውያን ተገቢውን የዲጂታል ክህሎት የተላበሱ እንዲሆኑ ለማድረግ የሚሰራ ደርጅት መሆኑን በመጥቀስ ባለው አቅም ድጋፍ ለማድረግና አብሮ ለመስራት ፍላጎት ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የኪፕለር ዳይሬክትር በበኩላቸው የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና ምሩቃንን በመደገፍና በማሰልጠን ብቁና ተወዳዳሪ ዜጋ እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።


የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የጀኔራል ዋቁ ጉቱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጎበኙ።
----------------------//--------------

(ታህሳስ 03 / 2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ሮቤ ከተማ የሚገኘውን ጀኔራል ዋቆ ጉቱ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸው ወቅትም ለተማሪዎች ባስተላለፉት መልዕክት ትምህርት የሚፈልገው ጥረት መሆኑን በመገንዘብ ሁሉም ተማሪዎች ጠንክረው መማርና ማጥናት ይኖርባቸዋል ብለዋል።

በትምህርት ሥርዓቱ የፈተና አስተዳደር ስርዓቱን ማስተካከል ያስፈለገው የትምህርት ጥራት እንዲሻሻልና ሀገር የሚረከቡ እውነተኛ ዜጎችን ለማፍራት መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል ብለዋል።

ኩረጃ ለጊዜው የሚጠቅም ሊመስል ይችላል ነገር ግን ሄዶ ሄዶ ራስንም ሀገርንም ይጎዳል ያሉት ሚኒስትሩ ኩረጃን የሚጸየፉ በራሳቸው የሚሰሩና የሚተማመኑ ተማሪዎች መሆን እንዳለበቸውም አሳስበዋል።

የትምህርት ጥራት እንዲሻሻልና ትውልዱ ይህችን ሀገር የመገንባት የወደፊት ሀላፊነቱን በታማኝነት እንዲወጣ የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት በትምህርት ሴክተሩ እየተከናወኑ መሆኑንም አብራርዋል ።

አክለውም ነገ ብቁ ሀገር ተረካቢ ብሎም በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት ተማሪዎች ትምህርታቸው ላይ ብቻ አተኩረው እንዲማሩ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።


በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን ተወሰነ።
------------------- // -------------------

ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎች የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየሰሩ ነው።
ወቅታዊውን የምግብ ዋጋ መጨመር መነሻ በማድረግ ትምህርት ሚኒስቴር ጥናት ያደረገ ሲሆን በጥናቱ ውጤት መነሻነትም የከፍትኛ ትምህርት ተቋማት የምግብ በጀት በቀን ወደ 100 ብር ከፍ እንዲል ተደርጓል። በተደረገው የበጀት ማሻሻያ መሰረት በተቋማቱ የምግብ ሜኑ ተመሳሳይ እንዲሆን በባለሙያዎች ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙ ተገልጿል።
በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሰለሞን አብርሃ ወቅታዊ የምግብ ዋጋ ንረትን ግምት ውስጥ በማስገባት የምግብ በጀት ማሰተካከያ መደረጉን ገልጸዋል።
ዶ/ር ሰለሞን አክለውም በሀገራችን ባሉ ዩኒቨርስቲዎች ያለው የምግብ ሜኑ ተቀራራቢ እንዲሆን እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው በአዲሱ የበጀት ተመን መሰረት ለዩኒቨርስቲዎቹ ባላቸው ተማሪ ቁጥር ልክ ገንዘቡ እንደሚለቀቅላቸው ጠቁመዋል።


#የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ።


(ሕዳር 28/ 2017 ዓ.ም) በትምህርት ሥርዓቱ የሚስተዋለውን የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ችግር ለመቅረፍ በሚቻልበ ጉዳይ ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሂዷል። በምክክር መድረኩ የተገኙት የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ አየለች እሸቴ በእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ላይ የሚስተዋለውን ችግር መቅረፍ ካልተቻለ የሚፈለገውን የትምህርት ጥራት ማረጋገጥና አለም አቀፍ ተወዳደሪ የሆኑ ተማሪዎችን ማፍራት እንደማይቻል ጠቅሰው ሁሉም ባለድርሻ አካላት በትኩርት ሊሰሩ እንደሚገባ ጠቁመዋል። በተለይም ተማሪዎች የሚማሩትን ትምህርት በአግባቡ እንዲረዱና ውጤታማ እንዲሆኑ እንግሊዝኛ ቋንቋን የማንበብ፣ የመጻፍ፣ የመናገርና የማዳመጥ ክህሎታቸውን በሚገባ ማሳደግ ይገባል ብለዋል።

የቀጣዩ ትውልድ እጣ ፈንታ የሚወሰነው አሁን በሚሰራው ሥራ መሆኑን በመገንዘብ የመማር ማስተማር ሥነ - ዘዴውን ማስተካከል እንዲሁም ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበትን ምቹ ሁኔታ በትምህርት ቤቶች መፍጠር ይገባልም ብለዋል። በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) በበኩላቸው የእንግሊዝኛ ቋንቋ በትምህርት ዓይነትና በማስተማሪያ ቋንቋነት በትምህርት ሥርዓቱ እየተሰጠ እንደሚገኝ ጠቅሰው ነገር ግን ከፍተኛ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ችግር መኖሩን የሚያመላክቱ ጥናቶችን አቅርበዋል። በዚህም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ችግር በተማሪዎችና በመምህራን ዘንድ እንደሚስተዋል አንስተው ይህንን ችግር ለመቅረፍ የሚያስችል ትምህርት ቤትን መሰረት ያደረገ ሥልት ቀይሶ መስራት እንደሚገባ ተናግረዋል።

ትምህርት ሚኒስቴርም https://learn-english.moe. gov.et የተሰኘ ያለ ምንም የኢንተርኔት ክፍያ የሚሰራ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ፓርታል አልምቶ ወደ ሥራ ማስገባቱን የጠቀሱት መሪ ሥራ አስፈጻሚው ይህንን ፖርታል ተማሪዎች፣ መምህራን እንዲሁም የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎታቸውን ማሳደግ የሚፈልጉ ዜጎች እንዲጠቀሙበት በሚገባ በማስተዋወቅ ረገድ ሚድያዎችን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። በመድረኩም የተለያዩ ጽሁፎች ቀረበው በተሳታፊዎች ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ተሳታፊዎችም ተማሪዎች በክፍል ውስጥና ከክፍል ውጪ ቋንቋውን እንዲጠቀሙበት እና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ የሚያበረታታ ሁኔታ አለማኖሩ ችግሩን የጎላ እንዳደረገው ገልጸው ይህንን ለመፍታት መምህራንና ተማሪዎች በድፍረት ቋንቋውን እንዲጠቅሙና ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ የሚያደርጉ ስልቶችን መቀየስ እንደሚገባም ተናግረዋል። በመጨረሻም የቋንቋ ክህሎትን በማሳደግ ረገድ የተሰሩ ሥራዎችና ሥልቶችን መሰረት በማድረግ ተሞክሮዎች መቀመርና ማስፋት በተለይም ክልል ከክልል፣ ትምህርት ቤት ከትምህርት ቤት ልምድ የሚለዋውጡበት ሥርዓት መዘርጋት እንደሚገባም ተመላክቷል።

በምክክር መድርኩ ከሁሉም ክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የመጡ አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

https://t.me/timihert_minister




የአምስት የዘርፍ ኢንዱስትሪዎች የትስስር ፎረም ተመሰረተ።
በቀጣይ ሁለት አመታት የየዘርፉን ፎረም የሚመሩ አመራሮችም ተመርጠዋል።

-------------------- // ---------------------

(ሕዳር 27/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በፎረሞቹ ምስረታ ላይ ባደረጉት ንግግር የትምህርትና ስልጠና ተቋማትና የኢንዱስትሪ ትስስር ተወዳዳሪ ዜጋና ሀገርን ለማበልጸግ ቁልፍ ሚና ያላቸው በመሆኑ የዘርፉ ተዋንያኖች ሚናቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል።

ሚንስትር ዴኤታው አያይዘው እንደገለጽት ትስስሩ ሀብትን በጋራ በማመንጨትና በመጠቀም የተሻለ አቅም ለመፍጠር የሚያስችል በመሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ምርምርና ስልጠና ተቋማትና ኢንዱስትሪው ተጣምረው በጋራ መሥራት እንደሚጠበቅባቸው አመላክተዋል።

የከፍተኛ ትምህርት የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች ተ/ መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ሠራዊት ሀንዲሶ በበኩላቸው በዘርፍ የሚቋቋሙት የትስስር ፎረሞች የከፍተኛ ትምህርት ፣ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ፣ ምርምር ተቋማትና ኢንዱስትሪው በመቀናጀትና በመተባበር ሀገር የጣለባቸውን ሃላፊነት እንዲወጡ ለማስቻል ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።

በመጨረሻም የተቋማት ትስስርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዴስክ ሃላፊ አቶ ተሾመ ዳንኤል የፎረሞቹ መቋቋም የከፍተኛ ትምህርት፣ ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ተቋማት፣ ምርምር ተቋማት እና ከኢንዱስትሪው ልምድና ተሞክሮዎችን እንዲቀስሙ የሚያስችል መሆኑን የገለጹ ሲሆን ኢንዱስትሪዎች በተመሳሳይ የሚመነጩ የምርምር ሀብቶችና ቴክኖሎጂዎችን ለመጠቀም የሚያስችላቸው እና የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።




ማስታወቂያ
*

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች   የምዝገባ  ጊዜ ኀዳር 09-10/2017 ዓ.ም መሆኑን ይገልጻል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
• የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ
• የማህበራዊ ሳይንስ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

ማሳሰቢያ፤
ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲመጡ የሚከተሉትን ይዘው መምጣት ይጠበቅባችኋል፡፡
• የ12ኛ ክፍል ፈተና ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
• ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው
• አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
• አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
• የስፖርት ትጥቅ

ማሳሰቢያ:-

ከተጠቀሰው ቀን በፊትም ሆነ በኃላ የሚመጣ ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን በጥብቅ እናሳውቃለን፡፡
     
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት




ትምህርት ሚኒስቴር ከሁዋዌና ሌሎች ተባባሪ አካላት ጋር የሚያዘጋጀው የአይሲቲ ውድድር አበረታች መሆኑ ተገለጸ።

ከሁዋዌ ጋር በመተባበር በተዘጋጀው ሀገር አቀፍ እና አህጉር አቀፍ የአይሲቲ ውድድር ፍጻሜ ለተወዳደሩ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቷል።

ሽልማቱ የተበረከተው የሁዋዌ የ2024/25 አይሲቲ የውድድር ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ሲሆን በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት በትምህርት ሚኒስቴር የአይሲቲ እና ዲጂታል ትምህርት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ዘላለም አሰፋ ባስተላለፉት መልእክት ውድድሩ ለተማሪዎች የስራ እድልን በማመቻቸት እና የስራ ፈጠራ አስተሳሰብን ከማጎልበት አኳያ ሰፊ ሚና ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

ዶ/ር ዘላለም አክለውም ሁዋዌ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተማሪዎችን ክህሎት ለማዳበር እያደረገ ላለው አበርክቶ ምስጋናቸውን ያቀረቡ ሲሆን መሠል ጥረቶችን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አጠናክሮ ማስቀጠል የሚገባ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የሁዋዌ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ በኢትዬጵያ ሚስተር ሊሚንግየ በበኩላቸው ውድድሩ ለወጣቶች ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው በመሆኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።


____________________________
"በእሳቤና በንግግር ከፋፋይ የሆኑ ሀሳቦችን እያጠፉ ሰብሰብ ለማድረግ ይሰራል።
የሚያሰባስቡ የማይለያዩ እሳቤዎችን በታሪክ ትምህርት ካሪኩለም ውስጥ በማካተት ቀጣዩ ትውልድ እንዲገነባው ይደረጋል።"

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ(ዶ/ር) በ6ኛ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የትምህርት ሴክተሩን በተመለከተ የተናገሩት።


የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆኗል።

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስዳችሁ በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታችሁን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባችሁን ማየት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፦

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et

በቴሌግራም 👇
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

15 last posts shown.