የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ስኮላርሽፕ ቃለመጠይቅ እና ፈተና ከሀሙስ ግንቦት 24 /9/2015 ጀምሮ ይሰጣል።
....................................................
የሚሠጡት ፈተናዎች በሂሳብ፣እንግሊዘኛ እና ፊዚክስ የትምህርት መስኮች ላይ ያተኮሩ መሆናቸውም ተገልጿል
ግንቦት 21/2015 ዓም.(የትምህርት ሚኒስቴር) የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ስኮላርሽፕ ቃለመጠይቅ እና ፈተና ከሀሙስ ግንቦት 24 /9/2015 ጀምሮ ይሰጣል።
ምዝገባውን ያከናወኑ እና አስፈላጊውን መረጃ አሟልተው በኢትዮጵያ የተባበሩት አረብ ኢሜሬትስ ኢምባሲ በኩል ተቀባይነት ያገኙ 499 ተማሪዎች ከሀሙስ ግንቦት 24/9/2015 ጀምሮ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ጊቢ ለቃለመጠይቅ እና ፈተና እንደሚቀርቡ ተገልጿል።
በትምህርት ሚኒስቴር የአለማቀፋዊነትና ስኮላርሺፕ ዴስክ ሀላፊ ዶ/ር ኢዶሳ ተርፋሳ ጉዳዩን አስመልክቶ በሠጡት ማብራሪያ የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግስት በ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት ዕድል ለመስጠት በፈቀደው መሰረት ቀደም ሲል ከ09/08/2015 እስከ 15/08/2015 ድረስ በበይነ መረብ ምዝገባ መከናወኑን እና መረጃዎችን የማጥራት ስራዎች ሲከናወን መቆየቱን ገልጸዋል፡፡