ትዝታዊ🐣


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Books


ስላላቹ አመሰግናለው !!
ለሃሳብና አስተያየታቹ . . . . @tiztawe1_bot ይጠቀሙ

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Books
Statistics
Posts filter


🦋
………………
በጊዜ ብዛት የማያዋጣትን የሆነች የማያዘልቃትን መሰብሰብ የያዘች ከአሁን አሁን አያትና ወደፊት እንደሷ እንዳልሆን እሰጋለሁ……

እሷንስ መኖር አይደል እንደዚህ ያደረጋት፣ እድሜ አይደል ጎራ ያስለያት ፣ ጊዜ አይደል የጣላት……
.
.
ማን ያቃል እኔም እንደሷ መጠንከር ያቃታት ያቺ ሴት እሆን ይሆናል……

ጊዜ ብዙ ያስተምረናል ፣ አዙሮ አዙሮ ግን ያየነውን ፣ የታዘብነውን ያንኑ ያደርገናል………


💫………

. .. ሰማዩ ወግጎ አይን ለብርሃን ቅርብ ነው ሁሉም ጠርቶ ይታየዋል. . . በዚህ ሰዓት ከአካል ሁሉ አዋቂ እሱ ይመስለዋል ፣ ጥያቄ ሳያሻ እደፈለገ ሲያሽከረክር ጎህ ይቀዳል. . .(የፍቅሩ ጠዋት)

. .  ምድር የሰማይ  ሞላሰስ ተደፍቶባት ስታሴር
ዓይን ማስተዋልን መዋስ ይፈልጋል ከመጣበት ለመመለስ ወይም ወደሚሄድበት ለመቀጠል ሚመክረው ሚጠቁመው የናቀውን ወዳጃ ይለማመጣል. . . . (. በፍቅሩ ምሽት.   ልቤ ሸሸ)

በስቃይ መሃል ነው ትክክለኝነት ሚወለደው አልኩ . . .እንኳን ሄደ

ያልኩት ዐ.ነገር ውሸቴን ይሁን እውነቴን እስካሁን አላወኩም !

@tiztawe/tizta


ድሮ…………🖤

"ናፍቀሽኛል ፎቶሽን ላኪልኝ " ይለኝና በስንት ልመናና ትግል ልክለታለው ፣

እስካኮርፍ ድረስ ይስቅና ፣
"የድሮ የእነ እማዬ ዘመን  ፎቶ አነሳስ እኮ ነው …………" አይጨርሰውም ይስቃል

"እኔ እኮ ፎቶ አልወድም ፣ አነሳስ አልችልም ፣ አይወጣልኝም " እያልኩ እነጫነጫለው
:
:
"ውብ ነሽ የኔ ሚስት " ኩርፊያዬን ያቆማታል

ቢሆንም ቢሆንም ነግቶም ፎቶ ይጠይቀኛል ፣ እኔም በብዙ ልመና ልካለው ፣ እሱም መሳቁን አያቆምም ………

ዛሬ🐥

እኔ ፎቶ ስወድ ፣ ደሞም ሲወጣልኝ ……… ሚለምነኝ ምልክለት እሱ የለም …… ልቤ
ውስጥ ስላለችው  ያቺ አደይ በልጅነቷ የኮተኮታት ፣ የፍቅር ፀሃዩን የሰጣት ፣ እውነቱን ያጠጣት እሱ ሳያጌጥባት ፣ ሌላ ያምርባታል ………

እናም አልኩ
የመጀመርያ ፍቅር እንደ ልጅነት ነው ………

@tiztawe/tizta


❤️💫

" አየሽው ኣ አገባ " እጇ ላይ አጥብቃ ከያዘችው ስልኳ ላይ የሙሽሮቹን ፎቶ ታሳየኛለች……

"ያምራሉ ……የተባረከ ይሁንላቸው !"

"ከምርሽን ነው ኣ "

"ምኑን ሪም "

"የምታፈቅሪው ሰው እኮ ነው ……!

"እና ?"

"አልከፋሽም "

"ለምን ይከፋኛል ?"

"በሷ ቦታ ብሆን ብለሽ አልተመኘሽም ?"

…………የሙሽሪትን ቦታ አየሁት ግንባሯ ከግንባሩ ላይ ነው ፣ እሱ አይኑን ጨፍኖዋል ፣ እሷ የሚያምር ፈገግታ ውስጥ ናት ……… ነፍሳቸው ይስቃል ………

……… አሰብኩ በምንም ሁኔታ ቦታውን የመፈለግ ስሜት አልተሰማኝም ………

" አልተመኘውም ……"

"ጤነኛ አትመስይኝም "………ጥላኝ ሄደች

፣
፣
ማልመውን ሁሉ መኖር አለብኝ ብዬ የመድረቅ ነፃነት ለነፍሴ እያስተማርኳት አልመጣውም ፣ መልቀቅ ያለብኝንም ደስ እያለኝ መልቀቅ እችልበታለው፣

ለቦታው እሷ ውብ ናት አሳምራዋለች ፣ ለሱ የተፈጠረቹ እሷ ናት ……… ስለደስታው ደስ ነው ያለኝ……… አንድ አንዴ ድሉ የእኛ ሳይሆን የምናሸንፍበት ታሪክ ይኖረናል …………


@tiztawe/tizta


🦋……
………ምን አልባት እላለው ቢራቢሮ ያልጨረሰቸው የጠፈጥሮ እድገት ቢኖርስ ፣ እኛ ባወቅነው ልክ ጨርሰንላት ቢሆንስ


🦋❤️……!

tizta/@tiztawe


💫🦋…………

ስኖር ላደርጋቸው ከምፈልጋቸው ነገሮች ውስጥ አንዱን በዚህ ሳምንት ውስጥ ፈጣሪ ረድቶኝ ሆኖልኛል ………

ከአመታት በፊት**

እለቱ 21 የማርያም ቀን ነውና አያቴ ቤተክርስትያን አርፍዳ ስትመለስ ቅጠሎቹ ግቢውን አበላሹት ተብሎ በተቆረጠ ዛፍ ላይ ወጥቼ የቴዲን ዘፈን እዘፍናለው በሰዓቱ ሚሰማኝ ብዙ ሰው ባዘጋጀውት ኮንሰርት ላይ ተገኝቶ ስዘፋን እየተመለከተ ያለ ይመስለኛል ፣ ደሞ ለቴዲ አፍሮ ያለኝ ፍቅር እምም …… "የሱን ዘፈኖች እደሸመደድሻቸው የፈጣሪን ቃል ብሸመድጂ ክንፍ ይኖርሽ ነበር " ትለኛለች እየተከታተለች ጥፋቴን ማስዋብ ምትፈልክ አክስቴ ፣ እናላቹ አያቴ "ምን እየሆንሽ ነው ?" አለችኝ ከንግግሯ ውጪ ፊቷ ላይ ቁጣም ደስታም አይነበብም ነበር ………

"ኮንሰርት ነው አያቴ ኮንሰርት ፣ ከቴዲ ጋር እኮ ነኝ አስበሽዋል "

"ተይ ሆድዬ ሰው አጥብቆ የፈለገውን ነው ሚኖረው ፣ መፅሐፈ ምሳሌ ላይ ምዕራፍ 13 ላይ ደሞ እንዲህ ይላል 'አፉን የሚጠብቅ ነፍሱን ይጠብቃል ፣ከንፈሩን የሚያሞጠሙጥ ግን ጥፋትን ያገኘዋል ' በአፍሽ ክፉ ምኞትን አትመኚ ፣ ሙላቱን ትኖሪዎልሽ "

"የአፌን ሙላት ?"

"አዎ የአፍሽን ሙላት "…… ወደ ፊት እራመድ ካለች በኃላ የሆነ ነገር እንደረሳ ሰው እያሰበች " ነይ በይ ምግብ እንብላ "

………

ከራሴ በጣም የምወደው ነገር ማንኛውንም የሰዎች ንግግር እንደተራ ወይም እንደቀልድ አልመለከታቸውም ፣ የደረሰኝን ቁጣም ፣ ነቀፋም ፣ ሙገሳም ወይም ምክር ወዘተዎች በትክክል ውስጤ ውስጥ አመላልሳቸዋለው ፣ ምን አልባት ለራሴ ምፈልገውን ደስታ የሰጠሁት ለዚህ ይሆናል /ለራሴ ነው ያልኩት/

ይኽን ንግግሯን ለራሴ ብዬ ብዬው እጅግ ሳምንበት " እንግድያውስ ከአፌ ፍሬ መልካምን ምበላ ከሆነ ፣ ምርጡን ነገሮች ልመኝ ……… የነፍሴ ወረቀት ላይ ፃፍኩ ከቴዲ አፍሮ ጋር ከመዝፈን በላይ እጅግ ውብ ምኞቶች ያሉሽ ሴት ነሽ ይላል ጅማሪው ፣ አንደኛ አንቺ ምንም ጥሩ ድምፅ የሌለሽ ዘፈን በደረሰበት ማደርሺ ሴትዬ ነሽ ስለዚህ ዘፋኝ አትሆኚ ፣ በዛ ላይ ቴዲ አፍሮን አገኘሽም አላገኘሽም ህይወትሽ ውስጥ ሚጨምርም ሚቀንስም ነገር የለም ፣ እና ወይዘሪት ህይወትሽ ውስጥ ሚጨምር ነገር ተመኚ ለሱም በርትተሽ ትጊ ……… ባይሳካም እንኳን ጥሩ ተመኝተሽ እሱን ለማግኘት የሄድሽበት መንገድ ደስ የሚል ደስታ ይሰጥሻል ………


……… "አያቴ ተመኘው እኮ " አልኳት ከብዙ ቀናት በኃላ

"ምን ተመኘሽ "

ብዙ ነገር እስከነማብራርያው ዘረዘርኩላት ከዛ ሁሉ ውስጥ ግን አንዱ ላይ አቁማ አጥብቃ ጠየቀችኝ " የሰው ልጆች እንደ ልጆችሽ ማሳደግ ትፈልጊያለሽ ?"

"አዎ "

" አንቺ አትወልጂም ?"

"ብዙ ወላጅ አልባ ህፃናት አሉ እኮ ፣ ወላጅ የሌለው ሞልቶ ሌላ ወላጅ ሚፈልግ ማምጣት ግፍ ነው "

" ምኞትሽን አስፊ "

"ምን አርጊው "

"አንድን ጥሩ ተግባር ለማከናወን ሌላ ጥሩ ነገርን መተው አይገባም "

"እሺ ፣ ሁኔታዎች መልስ አላቸው "
:
:
ከዓመታት በኃላ አንዲት የጡት ካንሰር ታካሚ ሆስፒታል ውስጥ ህክምናዋን ስትከታተል ታቅፋው ማያት ህፃን ነበር

"ህፃኑ አንቺን ይመስላል " ይሉኛል የስራ ባልደረቦቼ

እኔም የልጅ ነገር አይሆንልኝም ባገኘሁት ቁጥር እስመዋለው ይዛው መምጣቷ ግን ምቾት አይሰጠኝም ገና አራስነቱን ያልጨረሰ ጨቅላ እላለው በውስጤ ፣

እራሷ የሆነ ቀን

"አባቱ የሁለት ወር እርጉዝ ሆኜ ነው የሞተው፣ሁለታችንም በማደጎ ነው ያደግነው ቤተሰብ የለንም ፣ማርገዜ አደጋለው ተብዬ ነበር እራስ ወዳድነት መሆኑን ባውቅም ለባለቤቴ ቤተሰብ ልሰጠው ፈለኩ ግን አምላኬ አልፈቀደም ………"

በሌላ ቀን አቅፌ እየሳምኩት

"አንቺን ይመስላል ፣ ብሞት እናቱ ትሆኚያለሽ ?"………
*
*
*

…………እናት ሆንኩ !

@tiztawe ………/#


" የሁላችንም እቅፍ ውስጥ ' ያ ዘመን ' የምንለው  ዝምተኛ ጊዜ አለ ……! "

tizta/@tiztawe


🦋……………


ሚጨንቀኝ ትላንት ፣ ምፈራው ነገ የለኝም ………እስከነ ስህተቴ ትላንትን ወደዋለው ፣ ጥፋቴ ላይ የመቆየት ትግስት የለኝም አንድ አንዴ ጥፋት መሆኑን አውቄው ሳይሆን እንዲው ይሰለቸኝና ተወዋለው ከዛን  ካለፈ በኃላ ፈገግ እልና ለካ ስሳሳት ነበር የምልባቸው ጊዜያቶች ብዙ አሉ።

ለራሴ ስነግረው ያደኩት ነገር "ለተፈጠረ ነገር ባርያ አደለሽም " ለዚህም ምንም ነገር አይጨንቀኝም ፣ ህይወቴ ውስጥ ለሚመጡም ለሚሄዱም ነገሮች ግድ ኖሮኝ አያውቅም ፣ እስካሉ የእውነት ወዳቸዋለው  ሲሄዱ እንደነበሩኝ እንኳን ለማስታወስ ዘነጋቸዋለው …… ዝናቡ ቢያበሰብሰኝም ማንም ጥላ ይዞ እንዲመጣልኝ ጠብቄም ፈልጌም አላውቅም ።

አሁን ግን ፍርሃት ሲወረኝ ይሰማኛል ፣ መቶ እንደ ልጅ አቅፎ ውስጡ እንዲሸሽገኝ እመኛለው ……" በቃ አልሄድኩም ፣ ትቼሽ አልሄድም "  ሚለውን ቃል ናፍቃለው ………

አብረን ሆነን የምጠጣው ቡና  ሚጣፍጠኝ እኔ ጎበዝ ቡና አፊይ ስለሆንኩ እንጂ ከሱ ጋር ስለምጠጣው አይመስለኝም ነበር ፣ ቀልዶ ስስቅ ቀልድ አዋቂ ስለሆነ እንጂ እሱ ስላወራው እንደሆነ አልገባኝም ፣ሰላም ሚተነፍሰው ማንነቱን የማደንቀው ሚደነቅ ሆኖብኝ እንጂ ልቤን በተለየ እንደሚያንጫጫት አልተረዳውም

ትሁት ነፍሱ ውብ ልቡን ያዞርብኛል ብዬ ስለማላስብ ግድ የለሽንነቴን አላስተዋልኩትም ፣ ምን አልባትም ለሱ ሚሰማኝ ስሜት የፍቅር አይመስለኝም ነበር ፣ የህይወቴን ስም ባጣው ሰዓት አብሮኝ ስለነበር በየእርምጃዎቼ ስለተከተለኝ ውለታው የያዘኝ መስሎኝ  ነበር………

ግን ከዛች ጠዋት በኃላ ፈርቼ ማላውቀው ፍርሃት አለት ነፍሴን ሲርዳት ተሰማኝ ………

"ልሄድ ነው ካናዳ "

"ለስንት ጊዜ "

" አመት ወይም አመታት "

"እህ ፣ እዚህ ያለው ስራስ "

" አንቺ ስላለሽ እንጂ ፣ ቤተሰቤም ስራዬም እኮ እዛ ነው "

"ወደ ጁሩ አርሴማ ልታሰራ ስላሰብከው ጤናጣብያስ ?"

ዝም አለኝ

"እውነት ልትሄድ ነው " አልኩት ቃላቶቼን እያንቀጠቀትኩ……

" ስለምታፈቅሪው አይደል ሲመለስም የተቀበልሽው ፣ እርግጠኛ አልነበርሽ ስለሱ ስትነግሪኝ ፣ ታድያ ምን እሰራለው እዚህ ደስታሽ እሱ ከሆነ ደስታሽ ነው ደስታዬ ፣ " ምንም አልመለስኩለትም አይኖቼ በጭንቀት ካዘጋጀው ሻንጣ ላይ ተክዘዋል ………

"አፈቅርሻለው ፣ ግን ከልብሽ ጋር ታግዬ አይደለም በንፅፅር የኔ እድትሆኚ አልፈልግም ፣ ወደምትፈልጊው አቅጣጫ ብረሪልኝ "

" ባረኩት ነገር አልፀፀትም ፣ እሱን በማፍቀሬ ፣ ሲመጣም በማውራቴ ……… የትኛውም ነገር አይፀፅተኝም ፣ " አልኩት

አዎ አልፀፀትም "ባላወራው እንዴት አውቅ ነበር አንተን እንደምወድህ "ለራሴ ነው ያልኩት

"ሰላም ግባ " ቦርሳዬን ከአልጋው ላይ አንስቼ ወደመውጫው ተሳብኩ ፣

"አሚን "

እንደቆረጠ ገባኝ ………

ይሂድ ግን ተመልሶ ይመጣ ይሁን ?… ለመጀመርያ ጊዜ ፍርሃት 'ነገዬን ' ሲኮረኩመው ተሰማኝ ………

ትዝታ /@tiztawe


መሄድ ……ቻዎ መባል …መሸኘት … ደስ ይላል።… መንገድ እኮ ያምራል … መሄድ ደሞ መምጣት ከዛን መሄድ ……… ህይወት በመመላለስ ውስጥ ታምረኛለች !

ትዝታ /@tiztawe


"ንጋቴ ሲተነፍስ ይሰማኛል ፣ ያኔ ጨለማዬን አውልቄ ጠዋቴን ነፍሴ ላይ አርከፈክፋለው "

tizta/@tiztawe




💫…………

የሚስብ መልክ እማ በሀገሩ ሞልትል
ለኔ እንዳቺ ቆንጆ ማግኘት ተስኖኛል
ስፈልግ ያጣሁሽ አንቺን አይደለም ወይ
ሴቱ እማ ሞልቶቷል ምድሩ ሴት አይደል ወይ....

..  .እኔ.....

ናት አይደለች እያልኩ በፍቅር ሚዛን ቀመር
ነብስ ካወኩ ወዲህ ስጠብቅሽ ነበር

ግና

አገሩን ሳካልል ስወጣ ስወርደው
አይን አይከለከል ስት አይነቷን አየው።

ምን ያህሉን ግዜ እጠብቅሻለው
ለኔ ውብነትሽ ዛሬም ልቤ ላይ ነው
የት ትሆኚ ይሆን የቱጋ ነው ያለሽ
አንቺን እየፈለኩ ዝምብዬ ስባክን  ዝም ብለሽ ታያለሽ

ኧረ *3

እረ ተይ ጡር አለው
እዚህ ጋር ነኝ በይኝ ስከንፍ እመጣለው


ሳላገኝሽ ብሞት እኔ የለሁበት
ፀፀትሽ ከባድ ነው እንዳትሞችበት !!

/✍ግሩም ብእር.
ለ nuYeAsmck !!/


💫………………*

....ሁልጊዜ ከምተኛበት ሶፋዬ ላይ ተኝቻለሁ።ቀኑን ሁሉ...ከወዲያ ወዲህ ስኳትን ስለዋልኩ  በጣም ደክሞኛል....ከእንቅልፌ የነቃውትም ሰፈራችን ያለው የዘሀራ መስጂድ የ10:00 ሰዐት አዛን ጥሪ ስሰማ ነበር
አይገርምም....እንደ ሰው በስልኬ ማንቂያ (አለርም) ቀጥሬ አለውቅም  ሁሌም በፈለኩት ሰዐት ቀንም ሆነ ለሊት የሚያነቃኝ ይህ የመስጂዳችን አዛን ነው ።
......ዛሬም በዚህ አዛን ነቃሁ...ለምን እንደሆነ እንጃ የሆነ የመደበት ስሜት ተሰማኝና ከሶፋው የመውረድ ስሜቴ ብን ብሎ ጠፋ....ለወትሮው ከጓደኛዬ ጋር ለመገናኘት ተቃጥረናል....እንደምትጠብቀኝ ባውቅም የመሄድ ፍላጎት ከየት ይምጣ...
ይባስ ብዬ ተመቻችቼ በጀርባዬ ተንጋለልኩ....አይኖቼንም ቀጥታ በቤቱ ማዕዘን ላይ ወደ ተሰቀለው ስዕለ አድህኖ ተከልኳቸው.....
ክርስቶስ በቀኝ እጁ ይመስለኛል ባያረጅም ከዘራ ይዟል....ቀይና የተንዘረፈፈ ረጅም ፎጣ ለብሷል...ከስርም ከፎጣው አልፎ የወጣ ወይም በጣም የረዘመ የደመና ከለር ያለው ቀሚሱ እስከ እግሮቹ ጣቶች ደርሷል።ከቆመበት ቤት በር አፍ ላይ አንድ የውሃ መቅጃ ገንቦ ተቀምጧል...ጊቢው በለምለም ሳር የተሞላ ነው።

....በራፉ ላይከፈት የተጠረቀመ ይመስላል....ክርስቶስ ግን ያለ መታከት....በብሩህ ተስፋ ያንኳኳል
ቤቱ ውስጥ ግን ማን ይሆን ያለው??...ምን አይነትስ ፀባይ ይኖረው ይሆን??
ገዳይ ወይስ ቀማኛ፤ዘማዊ ወይስ ሀይማኖተኛ ፤ዘረኛ ወይንስ እንግዳ ተቀባይ....ምን አይነት ሰው ይሆን
ታድሎ....አልኩ ለራሴው
....መች ይሆን የኔን በር የሚያንኳኳው...መቼ ይሆን ተራ የሚደርሰኝ..."አንኳኩ ይከፈትላችኋል ፤ለምኑ ታገኙማላችሁ"ያለው ክርስቶስ...የኔን ማንኳኳት ሳይጠብቅ መቾ ይሆን ደጅአፌን የሚያንኳኳው...አይኖቼ ከስዕለ አድህኖው ላይ አልተነሱም
የክርስቶስን የፊቱን ገፅ አተኩሬ ተመለከትኩት .....ለብዙ ዘመናት ሲያንኳኳ የቆየ መሰለኝ....ግን ደግሞ ከማንኳኳት ብዛት ያልሰለቸ...ምን አልባት እኮ የኔኑን በር ይሆናል የሚያንኳኳው....አልሰማሁት ይሆን????
  የልብ ምቴ ፍጥነቷ ሲጨምር ታወቀኝ...ድንገትም ከየት መጣ የሚሉት የደስታ ስሜት ወረረኝ...
ወዲያው ከሶፋው ብድግ ብዬ ወረድኩ ና ነጠላዬን ከሰነበተችበት ቁምሳጥን አውጥቼ.....ወደ ቤተ ክርስቲያን ከነፍኩ....የልቤን ደጃፍ ልከፍት....

     /ትንሳኤ ዘ ኢትኤል /  @tiztawe


ብዙ ሰዎች ስንብት አይወዱም ፣ በመሄዳቸው ውስጥ ያለው ዝምታን ይንከባከቡታል………

ትዝታ /@tiztawe #ፍትሕ ለሴት ልጆች !


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ህክምና ሚጣፍጠኝ ለዚህ ነው ፣ ተፈኩር ታረጋላቹ ……… የአምላክን ጥበብ ታስተነትናላቹ………

ኡፍፍ ❤️


🦋💚…………


"ይሆናል ……! " "አይ አይሆንም! "ይደረጋል……" "አይ አይደረግም "…………

"እያልሽ ነው እራስሽን ያሳደግሽው ፣እናም ባንቺ ደስተኛ ነኝ ፣ ኮራብሻለው "…… ይኽን ሲለኝ ሊሰናበተኝ አርባ አምስት ቀናት ይቀሩት ነበር………

"አሁን እረፍት ይሰማኛል ፣ የምትፈልጊውን ታውቂያለሽ ፣ ለመኖር ዝግጁ ነሽ ፣ ያለኔ ፣ ያለማንም ………"

ተሳስቶዋል ያለሱ ለመኖር ዝግጁ አልነበርኩም ፣ ደስታውን በማየት ውስጥ ነው እራሴ ላይ የሰራሁት ፣ ያበበውን መሰራት አይቶ እየተደሰተ ማይኖርልኝ ከሆነ ታድያ ለምንድነው ምኖረው ?……ምክንያቴ እሱ ነው ……እንደማስበው ፣ እንደሚያስበው ጠንካራ አደለውም …… ላሳካ ስላሰብኩት ነገር ነግሬው ፣ ትችያለሽ በርቺ ብሎ ሳይመልስልኝ በምን ተስፋ እሮጣለው ?…… አዎ ያለማንም መኖር እችላለው ፣ ያለሱ ግን እንዴት ኖራለው ?

እያወራልኝ ማስበው ይኼን ነበር

" ምኞቴ አንቺ ለኔ እንደ ሺ እድቶኚ ሳይሆን ፣ አንቺ ለራስሽ ሺ እንድትሆኚ ነበር…… ከህይወት ምትፈልጊውን እንድታውቂ ፣ እንደ ልጅነትትሽ ጨለማን ብትፈሪም ከጨለማው ለመውጣት ግን እያለቀሽ ሰው ምትጠሪ ሳይሆን እራስሽ ለጨለማው መውጫ መፍትሔ እንድታበጂ ነበር ፍላጎቴ ፣ ያን አይቻለው ……በቃ !"


……ከጨለማው መውጣት ምፈልገው እኮ አንተ ስላለክ ነው ፣ አንተን ለማየት ፣ ስታረጅ ፣ ከልጅ ልጆችህ ጋር ስትጫወት " ኦ ሚገርም አያት እኮ ነው ያለን " ሲሉ ለመስማት ፣ እናታቹ እኮ እያልክ ልጅነቴን ስታወራላቸው ፊትክ ላይ ያለውን ደስታ ለማየት ነው ከድቅድቁ ሚያስመልጡኝን ብዙ ብልሃቶችን የገነባሁት ፣ እንዳልወድቅ  አቋቋሜን ያሳመርኩት ከኔ ቀጥሎ ስላለው ስምክ ስላለኝ ክብር ነው ……… ትላለች ነፍሴ ለራሷ ………ግን ንግግሩን በመልሷ አታቋርጠውም ፤ ያለሱ ጠንካራ መሆኔ ደስታ ከሰጠው ለምን ያን ደስታ ነጥቀዋለው ?
:
:
. ኖሮ ነው ያኖረኝ ፣ እጆቹ እየኮተኮቱኝ ሲሻክሩ ፣ "ለኔ ነው" ይለኛል ላንቺ ነው ብሎ ውለታ እደሆነ ነግሮኝ አያውቅም. .ለሚፈቀር ነፍስ የሚሰራ ሁሉ ለራስ እደሆነ እያስተማረኝ ነበር  . . ታላቅ ዓለም ነው !!

. . .ቃላቶቹ  ከአንደበቱ ሲወጡ የነፍሴ አክናፋት ዙሪያዩን ያቅፉታል ፣ ቃሉ የተስፋ ዜማ ታዜማለች ፣ በአዲስ ብርታት ኃይልም ትሞላለች ። ሁሉን መሆን ይችላል፣ ሁሉንም ማስሆን ይችላል. .

ከቅርፊቴ በብልሃት ተፈልፍዬ ጫጩነቴን በማስተዋል እዳልፍ መንገድም ሂወትም ሆኖኛል ………

ነፍሴ አደገኛ ተናዳፊ እባብ ከማይደርስባት የመንፈስ ከፍታ ላይ እድትሆን ጥበባዊ ስሪቱ አለበት………

ይኽ ሰው ነው ህይወቴ ላይ የጎደለው ……… ይኽን  አባት ነው  ነፍሴ ያጣቹ ………ይኽን መጠርያ  ነው ሞት የነጠቀባት ………
:
:
እንዳልኩት አበቃልኝ ብዬ ነበር ፣ ግን እሱ እንዳለው ቆምኩ ፣ ሰሪ ከስሪቱ በላይ አዋቂ ነውና ……"ትቆምያለሽ !" አለኝ ቆምኩ

አንዳንዴ ባይኖሩም ፣ ለመኖር ግን አዲስ ሃይል የሚሆኗቹ ታላቅ ነፍሶች አሉ ……… አባቴ !

/ትዝታ / @tiztawe

#ፍትሕ ለሴት ልጆች


"የእኔንትክክለኛ የፍቅር ታሪኬን የኖርኩበት የተሳስተህ ሰው ነህ ፣ እና በስህተት ወደ ህይወትህ የገባሁት ትክክለኛ ሰው ነኝ!"

/የአረብ - ቅኔ ……/@tizatawe/




ትንሽ ነፍስ ፣ ቆንጆ ልብ በነበረኝ ጊዜ ያኔ ትንጥ ሆኜ

"ምን መሆን ትፈልጊያለሽ ስታድጊ " ሲሉኝ

"እንደ አያቴ ፣ እንደ እናቴ ፣ እንደ አባቴ ……… ማደግ ፣ ትልቅ መሆን " እላቸው ነበር

ሳድግ የማደግ ክፍት ውብ ትንሽየዋን ልቤ እንደሚያሰፋብኝ አውቄ ኖሮ ቢሆን

"ማደግ አልፈልግም እዚሁ እንዲው ሆኜ ልቅር" እላቸው  ነበር……


ትዝታ /@tiztawe #ፍትሕ ለሴት ልጆች !


ሲዘንብ  ሁሌም የሚሰማኝ አንድ ድምፅ አለ ፣  ደርቆ እየረጠበ ያለ ያላስገባሁት  ልብስ  ለቅሶ
:
:ያኔ ነው መልፈስፈሴም ፣ መጠንከሬም እኩል ሚሰማኝ …………


ምን አልባት ከፀሃይ በፊት ያለው የዝናብ ውድቀት ይጣፍጠኝ ይሆናል ……

ትዝታ /@tiztawe

20 last posts shown.

4 192

subscribers
Channel statistics
Popular in the channel

❤️💫 " አየሽው ኣ አገባ " እጇ ላይ አጥብቃ ከያዘችው ስልኳ ላይ የሙሽሮቹን ፎቶ ታሳየኛለች…… "ያምራሉ ……የተባረከ ይሁንላቸው !" "ከምርሽን ነ...
🦋…… ………ምን አልባት እላለው ቢራቢሮ ያልጨረሰቸው የጠፈጥሮ እድገት ቢኖርስ ፣ እኛ ባወቅነው ልክ ጨርሰንላት ቢሆንስ 🦋❤️……! tizta/@tiztawe
ድሮ…………🖤 "ናፍቀሽኛል ፎቶሽን ላኪልኝ " ይለኝና በስንት ልመናና ትግል ልክለታለው ፣ እስካኮርፍ ድረስ ይስቅና ፣ "የድሮ የእነ እማዬ ዘመን  ፎ...
💫……… . .. ሰማዩ ወግጎ አይን ለብርሃን ቅርብ ነው ሁሉም ጠርቶ ይታየዋል. . . በዚህ ሰዓት ከአካል ሁሉ አዋቂ እሱ ይመስለዋል ፣ ጥያቄ ሳያሻ እደ...
🦋 ……………… በጊዜ ብዛት የማያዋጣትን የሆነች የማያዘልቃትን መሰብሰብ የያዘች ከአሁን አሁን አያትና ወደፊት እንደሷ እንዳልሆን እሰጋለሁ…… እሷንስ ...