#UniversityofGonder
በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ
የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ለመከታተል ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች የማመልከቻ ቀናት 👉 ጥር 01 እና 02/2017 ዓ.ም. መሆኑን አሳውቋል።
የምዝገባ ቦታ፡- ለማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ማራኪ ግቢ እና ለተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች አጼ ፋሲል ግቢ መሆኑንም ዩንቨርሲቲው ጨምሮ አሳውቋል።
💥ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ስትሄዱ ከዚህ በታች የተገለጹትን ይዛችሁ እንድትሄዱ
✓ የ8ኛ ክፍል ውጤት ዋናውን እና የማይመለስ ኮፒ
✓ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውን እና የማይመለስ ኮፒ
✓ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ሰርቲፊኬት ዋናን እና የማይመለስ ኮፒ
✓ ሁለት ጉርድ ፎቶ ግራፍ
✓ አንሶላ፣ ብርድ ልብስና የትራስ ልብስ
(ሬጅስትራር ጽ/ቤት)
@Tmhrt_Ministere1@Tmhrt_Ministere1