#AAU
ሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (NGAT) ለመውሰድ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን እንደ ፈተና ማዕከል መርጣችሁ ለነበራችሁ ተፈታኞች ፈተናው ለሌላ ጊዜ መተላለፉን ትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቁ ይታወሳል፡፡
ፈተናው መስከረም 3 እና 4/2017 ዓ.ም በሚከተሉት ሰባት ተቋማት ውስጥ ይሰጣል፦
1. በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣
2. በኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣
3. በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ፣
4. በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኢንስቲትዩት፣
5. በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርስቲ፣
6. በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና
7. በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ፡፡
የተሰጣችሁን የመፈተኛ ስም (Username) ተጠቅማችሁ በሚደርሳችሁ የመፈተኛ ማዕከል እና የፈተና ሰዓት (Exam Session) መሰረት ፈተናው ይሰጣል፡፡
ትምህርት ሚኒስቴር ✅
✅ ተጨማሪ ትምህርታዊ መረጃ ለማግኘት ቻናላችን ይቀላቀሉ
🔻
https://t.me/Tmhrt_Ministers🔻
https://t.me/Tmhrt_Ministers