ኡስታዝ ኸይረዲን ሀሰን ረሂመሁሏሁ ራህመተን ዋሲኣ~~~~~~~~~~~~~~~~
ለትውስታ ዱአ አድረጉለት ውድ የሱና እህት ወንድሞቸ!!
By ቅድሚያ ለተውሂድ
===========
ይህን ታላቅ ወንድማችንን ካወቅኩበት ግዜ ጀምሮ ባለፉት 23 ዓመታት ውስጥ በአካል ባገኘሁት ቁጥር ወይም መልእክቱን በሰማሁት አጋጣሚ እንዲሁም ከአንዳንድ ወንድሞች ጋር ስለሱ የዳእዋ ውስጥ ተሳትፎና የአኗኗር ዘይቤ ስናወጋ እንደታዘብኩት ታላቅ የሆነ የተግባር ሰው ነበር። አላህም ወፈቀውና እየተነገረለት ባለው ሁኔታ ይህችን አለም ኖራት። በዚያም ላይ ተለያት። ረሂመሁላሁ ራህመተን ዋሲኣ።
ወንድማችን ኸይረዲንን እንደታዘብኩት…
ንግግረ አጭር
መልእክተ ሠፊ
በሉ … ስሩ ብቻ ሳይሆን
ቀድሞ ተሰላፊ
ተስፋን ሚያለመልም
ሀሳብን ገፋፊ
ቀልዱ ቁምነገሩ
ልብ ላይ አራፊ።
ነበር!
ቋንቋ ቀይሮ እንኳን
ሀሳቡ የሚገባህ
የማትቃወመው
ከልብ የሚነግርህ
በመልካም ሚታወቅ
በበጎ የሚወሳ
ለገጠሩ የሚጮህ
ምንጩን የማይረሳ
ከከተሜው የሚኖር
ለኸይር ሚያነሳሳ
እንደኔ እንዳንተ ስራ ቤቴ ሳይል
ለዳዕዋ እንደሳሳ
ገጠሩን ለማንቃት
ለኪሱ ሳይሳሳ
ይኸው ዛሬ ሄደ
የጉዞው ቀን ደርሳ
በአቋሙ እንደፀና
ተግባራዊው አንበሳ።
እርግጥ
ምሉእ ሰው ባይኖርም
ከነቢያት በቀር
ሚደነቅ ባይኖርም
በሰሃቦች ወደር
ካለው ህዝብ መሃል
ለየት ያለ ሲኖር
ቢወሳ መልካሙ
ሳይበዛ ቢነገር
ማካበድ አይሆንም
አልፎ ከመማማር።
እሱስ ከስራው ጋር ይኸው ተገናኘ
ከኛስ ሚጠበቀው በወቅቱ ተገኘ?
የሰራውን ኸይራት
አላህ ይቀበለው
ስህተቱን ግድፈቱን
ሁሉንም ይለፈው
ወንጀል ሀጢኣቱን
ይተወው ይማረው
ከቀብር ስቃይም
ከአዛብ ያርቀው
ያቺ የለፋላትን
ምኞቱን ያድርሰው
ጀነተል ፊርደውስን
ሸልሞ ያስገባው
ልጅ ቤተሰቦቹንም
ፅናትን ይስጣቸው።
ከዱንያ ሃሳብ ከኣኺራ ስጋት
እሱ ይታደጋቸው።
ተተኪ ወገንም ረዳት ያርግላቸው።
እኛም ኸይር እንሸምት
ሰበቡ ሳያልፈን
ሂሳቡን በመዝጋት
የቁም እስረኛ እንዳይሆን
ዕዳው እስኪነሳለት
የቻለ በቻለው ካሁኑ ይሩጥለት።
የኡስታዝ ኸይረዲን ሀሰን ምክሮችና ግጥሞች
Http://t.me/ustaztokichaw