እርቅና ይቅርታ ለምን? ከማን ጋር?
(መላኩ አላምረው)
...
‹‹አጥብቀን የምንሻ - ከአምላክ ምህረቱን
ይቅር ካልተባባልን - አናየውም ፊቱን››
.
አንዴ ፍቀዱልኝማ..... ስለ እርቅና ይቅርታ ልሰብካችሁ ነው፡፡
(በዚያውም ሰባኪነት የሚያዋጣኝ ከሆነ ጠቁሙኝማ ያው
ሰባኪነት በነጻ የሚሰጡት መንፈሳዊ አገልግሎት ሳይሆን የትልቅ
እንጀራ ምንጭ እየሆነም አይደል )
ዕድሜና ጊዜ በፈቀደልኝ መጠን ካነበብኋቸው መጻሕፍትም ሆነ
እንዲሁ በእእምሮዬ መርምሬ የተረዳሁት ቁም ነገር ቢኖር... ሰው
እርቅንና ይቅርታን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ አምኖ ሊቀበለውና
ሊተገብረው ይገባል፡፡ ምክንያቱም በምንም መመዘኛ እርቅና ይቅርታ
ጥቅሙ ለራስ ነውና፡፡ እርቅና ይቅርታን የማይቀበልና የማይተገብር
ሰው ሰላማዊ ኑሮን ገንዘቡ አያደርጋትም፡፡
ሰው መታረቅ ያለበት እርቅ የነፍስ መድኅን የአእምሮም ነፃነት ስለሆነ
ነው። ጥላቻ ነፍዝን ያቆስላል። አእምሮን ያቆሽሻል። ሰው መታረቅ
ያለበት እርቅ የሰላምና የመረጋጋት ምንጭ ስለሆነ ነው።
ሰው ይቅር መባባል ያለበት የትኛውንም የጥፋትና የበደል ዓይነት
ነው። ለጥፋትና በደል ደረጃ አውጥተን ይህንን ይቅር እንበል...
ይህኛው ግን ይቅር ሊሉት ይከብዳል አንበል። በደል በደል ነው።
ይብዛም ይነስም በእርቅና ይቅርታ ካልተወገደ በሽታ ነውና ሰብዓዊ
ጤንነትን ያዛባል። "ይቅርታ አይገባውም" የምንለው የበደል ዓይነትና
መጠን ሊኖር አይገባም። እንደዚያ ካልን እኛም በየግላችን ይቅር
ሊባል የማይገባ ጥፋት ሊኖርብንና ያለ ምህረት ልንኖር ነው ማለት
ነው።
ሰው እርቅን መፈጸም ያለበት መተማመንን ለመመለስ እንጅ
ለይስሙላ አይደለም። ሰው በደሉን አምኖ ይቅርታ ከጠየቀ በኋላ
የቀድሞ ጥፋቱ ለነገ ሕይወቱ ተጠያቂ ሊያደርገው አይገባም። ያንንማ
ጥፋት መሆኑን አምኖና ይቅርታ ጠይቆበት ጥሎት መጥቷል። ሰው
መታረቅ ያለበት አንድነትን ለማምጣት ነው። እርቅና ይቅርታ
የአንድነትና የመረጋጋት ምሥጢሮች ናቸው። የነፍስና የሥጋ አንድነት፣
የሐሳብና የተግባር መመሳሰል፣ የእርስ በርስ መግባባትና
መተማመን... በጥል ይጠፋሉ - በእርቅና ይቅርታም ይመለሳሉ።
ሰው ይቅር መባባል ያለበት አምላኩን ለማስደሰትና ውለታ መላሽነቱን
ለማሳየት ነው። ሰው እንኳንስ እርስ በርሱ ከፈጣሪው ጋርም እንኳን
በየሰዓቱ ይጣላል። ፈጣሪው ግን በደሉን ሳይቆጥርበት ይቅር
ይለዋል። ሰው ጥፋቱን አምኖና ከልቡ ተጸጽቶ "በድያለሁ፣ ይቅር
በለኝ አምላኬ" ባለበት ቅጽበት መረጋጋትን የማግኘቱ ምሥጢር
የአምላክ ይቅር ባይነት ነው። ታዲያ በየቀኑ ይቅር የሚለውን አምላክ
ውለታ በምን ይመልሰው? ሌላውን ይቅር በማለት ብቻ። ይቅር
የማይሉ ይቅርታን መጠየቅ እንደምን ይችላሉ?
ይቅር ባይነት አምላክን የምንመስልበት ምሥጢር ነው፡፡ ሰው ይቅር
ማለት ያለበት የበደሉትን ነው። የበደላቸውንማ ግዴታው ነው። ሰው
እልምላኩን የሚመስለው የበደሉትን ይቅር ሲል ብቻ ነው። የበደለማ
ይቅርታን ይጠይቃል እንጅ ይቅርታ አድራጊ አይደለም።
...
በእርቅና ይቅርታ ላይ ጥናት ያደረጉ ጸሐፍት አንድ ሰው ከ4 ነገሮች
ጋር እርቅ መፈጸም እንዳለበት ያትታሉ፡፡
1ኛ. ከራሱ ጋር፡-
ሰው ከምንም በፊት መታረቅ ያለበት ከራሱ ጋር ነው። ከራሱ ጋር
ያልታረቀ ከሌላው ጋር እንዴት ሊታረቅ ይችላል? ከራሱ ጋር እርቅ
የፈጸመ ሰው ከሰውም ከአምላኩም ከተፈጥሮም ጋር ለመታረቅ
አይከብደውም። ከሕሊናው ጋር ሲሟገት የሚኖር እርሱ ከራሱ ጋር
እርቅ ያልፈጸመና ከልቡ ሐሳብ ጋር ስምምነት የሌለው የራሱ ጠላት
ነው፡፡
2ኛ. ከሌላው ጋር፡-
ከራሱ ጋር እርቅና ይቅርታ የፈጠረ ሰው ከሌላውም ጋር ይስማማል፡፡
ምክንያቱም ጣዕሙን ቀምሶታልና፡፡ በእርቅና ስምምነት የሚገኘውን
ሰላም አይቷልና፡፡ ከራሱም ከሰውም ጋር የሚታረቅና የሚስማማ
እርሱ የተባረከ ነው፡፡ ኑሮውም ሰላምና ደስታ ይሞላበታል፡፡ ሰውን
ይቅር የማይል እርሱ ለራሱም ሰላም የማያስብ ነው፡፡ ሌላውን አሳዝኖ
መደሰት የማይታሰብ ነው፡፡
3ኛ. ከአምላኩ ጋር፡-
ሰው ከአምላኩ ጋር ለመታረቅ አስቀድሞ ከራሱና ከወንድሙ ጋር
መታረቅ አለበት፡፡ ከራሱ ጋር ያልተስማማና ወንድሙንም የበደለ ሰው
የአምላክን ይቅርታ በትጋት ቢፈልግም አያገኛትም፡፡ ሁለቱን እርቆች
ቀድሞ የፈጸመ ግን በዚያው ቅጽበት ከአምላኩ ጋር ይታረቃል፡፡
ወንድሙን ይቅር ለሚል ለእርሱ አምላኩ ከእርሱ ጋር ነው፡፡ ሰዎችን
በሚወድበት መጠን ፈጣሪው ይወደዋል፡፡ ሰው ከአምላኩ ጋር
የሚኖረው እርቅና ይቅርታ ከራሱም ሆነ ከወንድሙ ጋር በሚያደርገው
እርቅና ይቅርታ ይወሰናል፡፡ ከራስ ጋር ሳይታረቁና ወንድምን ይቅር
ሳይሉ ከአምላክ ዘንድ ምህረትን መጠበቅ በራሱ ግብዝነት ነው፡፡
4ኛ. ከተፈጥሮ ጋር፡-
የሰው ልጅ ምንም እንኳን እርስ በርሱ ቢስማማና ከአምላክ ጋር ነው
የምኖረው ብሎ ቢያምን.... ከተፈጥሮ ጋርም ስምምነት ካልፈጠረ
በቀር ምድራዊ ሰላሙ ምሉዕ አይሆንም፡፡ አካባቢውን በክሎ ንጹህ
አየርን መመኘት የዋህነት ነው፡፡ አትክልትና ዛፎችንም አጥፍቶ
አረንጓዴና ለዓይን ማራኪ ምድርን መመኘት እብደት ነው፡፡ ከተፈጥሮ
ጋር ለመታረቅ ሰው ለተፈጥሮ መስጠት ያለበትን መስጠት ግድ ነው፡፡
ከተፈጥሮ በመቀበል ላይ ብቻ የተመሠረተ የዓለም ጉዞ ወደ ጥፋት
እንጅ ወደ ልማት ሊመጣ አይችልምና፡፡
@wegoch