Wolkite University Registrar


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


It is the official telegram channel of Wolkite University Registrar Directorate.

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter






We are excited to announce that the Higher Education Institutions' Electronic Learning Implementation Directive has been approved by the Ministry of Education and is registered by the Federal Attorney General, Ministry of Justice










Summer Exit Exam Schedule (የካቲት 01)








የተስተካከለ የጥር 30 መውጫ ፈተና REVISED EXIT EXAM SCHEDULE (ጥር 30)


#ይነበብ

ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመራቸው ስራዎች አንዱ የሆነ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከነገ ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ/ም ይጀምራል።

ለመሆኑ በዚህ ፈተና ወቅት ከተማሪዎች እንዲሁም ከፈታኞች ምን እጠበቃል ?

[ ከተፈታኞች የሚጠበቅ ]

- ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍል ሲመጡ ማንኛውም አይነት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት ፣ ላፕቶፕና ... ወዘተ ተመሳሳይ ኤክትሮኒክ ቁሳቁስ መያዝ በፍፁም የተከለከለ ነው።  (ይዞ የተገኘ ፈተናው /ውጤቱ ተሰርዞበት በቀጣይ ጊዜ እንዲቀመጥ ይደርጋል)

- ፈተና ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት መፈተኛ ክፍል መገኘት አለባቸው ይህም ማለት ከጥዋቱ 2፡00 በፊት ፤ ከሰዓት ደግሞ ከ8፡00 በፊት ተፈታኞች መገኘት አለባቸው።

- ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ID መያዝ ያለባቸው ሲሆን User Name እና Password lower-case and upper-case ፊደላትን
ለይተው በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው።

- ተፈታኞች ፈተና ከተጀመረ በኃላ ከ30 ደቂቃ በፊት ከፈተናው ክፍል መውጣት የለባቸውም።

- ተፈታኞች ፤ ፈተናውን የሚያስፈትኑ መምህራን በሚያሳዩት ቦታ ብቻ መቀመጥ አለባቸው።

- ሁሉም ተፈታኝ እንዲቀመጥ የተመደበበት የራሱ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ተቀምጦ መክፈትና መጠቀም አለበት።

- በፈተና ክፍል ውስጥ መነጋገር እና ከቦታ ቦታ መዘዋወር በፍፁም የተከለከለ ነው። እንዲሁም ማንኛውም ተፈታኝ ከጎኑ ያለውን ተማሪ ኮምፒውተር በፍፁም ማየት የለበትም።

- ምንም ዓይነት ወረቀት ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መምጣት አይቻልም።

- ተፈታኞች በምንም ሁኔታ መኮርጅም ሆነ ማስኮርጅ ተግባር ላይ ቢሳተፉ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

- ሁሉም ተፈታኞሽ ለፈታኝ መምህራንና ለአስተባባሪዎች  መታዘዝ ያለባቸው ሲሆን የፈተናው ደንብ እና ስርዓት ተገዢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

NB. ሁሉም ተፈታኞች ወደ መፈኛ ክፍል ተፈትሸው እንዲገቡ የሚደረግ ሲሆን ማንኛውም ተፈታኝ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በፍተሻ ወቅት ይሁን ሥርዓት ለማስያዝ በሚደረግ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆኖ ከተገኘ ከመፈተኛ አከባቢ እንዲገለል ተደርጎ በቀጣዩ የመውጫ ፈተና መስጫ ወቅት እንዲቀመጥ ይፈቀድለታል።

[ ከፈታኝ መምህራን የሚጠበቅ ]

- የተፈታኝ ተማሪዎችን ID በአግባቡ በማረጋገጥ ወደ ክፍል እንዲገቡ ማደረግ ይጠበቅባቸዋል።

- ተፈታኝ ተማሪዎችን በሥም ዝርዝራቸው መሠረት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

- ፈታኝ መምራህን የተማሪዎችን አቴንዳንሰ ይወስዳሉ ፤ ተማሪዎችን ፊርማ ያስፈርማሉ።

- በፈተና ክፍል ውስጥ ደምጽ እንዳይሰማ፣ ተማሪዎች ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወሩ ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው።

- የፈተናው አጠቃለይ ሂደት በትኩረት መከታተል አለባቸው።

- በህመም ምክንያት ተማሪዎች ከክፍል መውጣት ቢፈልጉ ከሱፐርቨዘር ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እርዳታ ያደርጋሉ።

- ተማሪዎች በጎናቸው ያለውን ሌላ ኮምፒውተር እንዳይመለከቱ መቆጣጠር አለባቸው።

- ተማሪዎች ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በፊት እንዳይወጡ መቆጣጠር ይጠበቅባቸዋል።

- ሲኮርጂ ወይንም ሲያስኮርጅ የተገኘ ተማሪ ከመፈተኛ ክፍል እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

- ፈተናው ከጀመረ 15 ደቂቃ በኃላ የሚመጣ ተማሪ እንዲገባ ማድረግ የላባቸውም።

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ: 2017 ዓ/ም






በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የ2017 አጋማሽ የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ከላይ በተያያዘው ፕሮግራም መሰረት የተመደባችሁበትን የፈተና ቀን፣ሰዓት እንዲሁም የመፈተኛ ቦታ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ ስለዚህ ከፈተናው ሰዓት 30 ደቂቃ ቀድማችሁ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፡ ለፈተና ስትመጡ ማንኛውንም የኤለክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ ሰዓት…) መያዝ አይፈቀድም፡፡


EXIT_EXAM_MID_Schedule_2017.pdf
168.4Kb
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የ2017 አጋማሽ የመውጫ ፈተና ፕሮግራም


ማስታወቂያ
የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመዉጫ  ፈተና (Exit Exam) ጊዜን በድጋሚ ስለማሳወቅ
በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ላይ የሚሰጠውን የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም መሆኑን ከዚህን በፊት መግለጻችን ይታወሳል፡፡ በመሆኑም ፈተናውን ለመፈተን የተመዘገባችሁ ተፈታኞች (አዲስና በድጋሚ ለመፈተን ያመለከታችሁ በሙሉ) ፈተናው የሚሰጠው ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ መኑን በድጋሚ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር

18 last posts shown.