የአጠቃላይ ትምህርት ፈተና እና ምዘና ዳይሬክቶሬት የ2017 ዓ.ም የ6 ወር እቅድ አፈጻጸም ገመገመ።
(ታህሳስ 18/2017 ዓ.ም) በመርሀግብሩ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የዘርፉ አስተባባሪዎችን ጨምሮ የቢሮው እና የክፍለ ከተማ የፈተና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ በመርሀግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የአጠቃላይ ትምህርት ፈተና እና ምዘና ዳይሬክቶሬት በ2017 ዓ.ም ስድስት ወራት የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን ገልጸው የዛሬው ውይይት በአፈጻጸም ሂደት የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልም ሆነ በሂደት የተስተዋሉ ችግሮችን በመቅረፍ በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት በሚያስችሉ ሀሳቦች ላይ ለመወያየት መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
የቢሮው የአጠቃላይ ትምህርት ፈተና እና ምዘና ቡድን መሪ አቶ ተሾመ ደገፋ የዳይሬክቶሬቱን የ2017 ዓ.ም የ6 ወር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን በቀረበው የአፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከተሳታፊዎች ለተነሱ አስተያየቶችና ጥያቄዎች ምላሽ ተሰቷል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!
What Sapp: -
https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2DYou Tube:
https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728TikTok፡-
tiktok.com/@aaeducationbureauTelegram ፡
https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureauTwitter ፡
https://twitter.com/aacaebcFace book:
https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication