የ "ቶ"መስቀል ምስጢር
***
# ETHIOPIA | “ቶ” የግዕዝ ሠባተኛዋ ፊደል ነች፡፡ ሠባት ቁጥር ትልቅ ትርጉም ያላት ነች ፍፁምነትን የምታመለክት ነች፡፡ ሠባተኛው ዙፋን የጌታ እንደሆነ፣ ሠባተኛው ቀን ሠንበት እንደሆነች፣ 7 ቁጥር ብዙ ሚስጥር አላት፡፡ “ቶ” ሠባተኛዋ ቁጥር በመሆኗ ፍፁምነትን የምታመለክት ነች፡፡ ክርስቶስን የምትወክል ነች፡፡ ክርስቶስ ለኛ ሲል በቀራኒዮ መስቀል ላይ ራቁቱን መሠቀሉን የምታመለክት ነች። ትልቁ ከዚህ በላይ ያለው ሚስጥር አባቶቻችን ከመፅሐፍ ቅዱስ ትርጔሜ ሲተነትኑ በሰማይ መላዕክት ዘንድ ውጊያ ሆነ ቅዱስ ሚካኤል ቅዱስ ገብርኤል ከሣጥናኤል ጋር ሲዋጉ ሁለት ጊዜ ተሸንፈዋል፡ በሶስተኛው እንዲያሸንፉ ሲልካቸው ይህን ቀስተደመና ቀርፆ፣ ይህን ምልክት የኮከቡን ቅርፅ የ“ቶ” ቅርፅ ያለው መስቀል በየክንፋቸው ቀርፆላቸዋል። "ኤል"የሚለውንም ሚስጢራዊ ስም አትሞባቸዋል።ይህን ካደረገላቸው በኋላ ተመልሰው ወደ ውጊያው ቢሄዱ ሳጥናኤል ሀይላቸውን ሊቋቋመው አልቻለም ውድቀቱ ፈጠነ ሽንፈቱ የከፋ ሆነበት ፅልመትን አልብሰው ወደ በርባኖስ ውስጥ ጥልቅ ጨለማ ላይ ወረወሩት። የአምላክ ክንድ ፅኑ መሆኗን ሳጥናኤል ያውቃልና በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላሴን ስሉስ ቅዱስ እያለ እየተንቀጠቀጠ ይገዛል ይላል። ሆኖም ምግባር ስለሌለው ፅድቅን አያያትም። ሰወች "ቶ"ን የህይወት ምልክት አድርገዉ
የሚወስዱት ለኢትዮጵያዉያን ብቻ ነዉ::የሚገርመዉ ደግሞ ይህ ምልክት አገልግሎት ላይ የዋለዉ ከክርስቶስ ልደት በፊት 3000 አመታት ቀደም ብሎ ጥንት ግብፃዉያን ቶርኔተር (የፑንት ምድር) ብለዉ በሚጠሯት ሀገር ነዉ:: ግብፃዉያን እንደሚሉት የፒራሚድ ግንባታ ጥበብን የተማሩት ከቶርኔተር (የአሁኗ ኢትዮጵያ) ሰወችና አማልክቶች ነዉ:: በ670 አ.አ በኢትዮጵያ ነግሶ የነበረዉ ንጉስ ቲርሀቅ እየሩሳሌም የኦሶር ንጉስ በሆነዉ በሰናክሬም ስትወረር
ለእየሩሳሌም መከታ ሆኖ ሲዘምት ሀያላን ከሚባሉ ወታደሮች ጋሻ ላይ የ "ቶ" ምልክት እንደተቀረፀና ንጉሱም በ"ቶ" ቅርፅ የተሰራ መስቀል ማሰሩን የሚያስረዱ የድንጋይ ላይ ፅሁፎች ተገኝተዋል:: .
የ"ቶ" ምልክት የተፈጠረዉ በቅርብ ግዜ ነዉ ለሚሉ ሰወች "ቶ "የተፈጠረዉ አለም ሲፈጠር ነዉ ብል እዉነት እንጅ ዉሸት አይሆንም::ለዚህ ማስረጃየ ደግሞ የሰዉ ልጅ የተፈጠረዉ በ"ቶ" ቀመር መሆኑ ነዉ:: . ይህ ምልክት ግብፅ በሚገኙ የዋሻ ስእሎች ላይ የህይወትን ገፀ ባህሪ ይዞ እንደነበር የሚያስረዳ ሲሆን ይህ
ምልክት አገልግሎት የጀመረዉ ኢትዮጵያ ላይ ከሆነ ግብፅ ላይ እንዴት ተገኘ? ብሎ ለሚጠይቅ ግብፅ ላይ የነገሱት 18 ኢትዮጵያዊ ንጉሶች ተጠቃሽ ናቸዉ:: ሜምኖን የተባለዉ ኢትዮጵያዊ የግብፅ ንጉስ ከ1320 አ.አ እስከ ሴፕዩምስኬኩረስ 170 አ.ም የቆመ ሀዉልት እንደነበረዉና ሀዉልቱም ጠዋት ጠዋት ፀሀይ ሲያርፍበት የክራር ድምፅ ያሰማ እንደነበር ሄሮዱተስ በፓፒረስ ወረቀት ላይ አስፍሮት ይገኛል::ክራር ደግሞ የኢትዮጵያ የባህል መሳሪያ መሆኑ አጀብ ያስብላል:: በሳባዉያን የዋሻ ላይ ስእሎችና ማህተሞች ላይ "ቶ" ተመስሎ ጣቱን የቀሰረ ምስል እንዳለ (አስቻለዉ ከበደ የተባለ ፀሀፊ ከርከቤዴል ሳዶፍ) በሚል መፅሀፉ አስፍሮታል::ሳባዉያን ሰዉን ለመሳል "ቶ"ን መጠቀማቸዉ ይታወሳል፡፡
ይቆየን
@yaltenegeru_mistroch