💛 የ መዝሙር ግáŒĨሞá‰Ŋ 💛


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


đŸ‡Ē🇹 የáŠĸá‰ĩዮáŒĩá‹Ģ áŠĻርá‰ļá‹ļክáˆĩ ተዋሕá‹ļ ቤተክርáˆĩቲá‹Ģን  አáˆĩተምህሮ ና áˆĩርአá‰ĩን የጠበቁ ቆየá‰ĩ á‹Ģሉና አá‹ŗዲáˆĩ👇👇
👏 የቸá‰Ĩቸá‰Ļ መዝሙáˆĢá‰ĩ đŸŽģ የበገና መዝሙáˆĢá‰ĩ  
👑 የቅዱáˆŗ መዝሙáˆĢá‰ĩ â›Ēī¸ የንግáˆĩ መዝሙáˆĢá‰ĩ
💍 የሠርግ መዝሙáˆĢá‰ĩ đŸŒĻ ወቅá‰ŗዊ መዝሙáˆĢá‰ĩ መገኛ

đŸ“ĸለ ማáˆĩá‰ŗወቂá‹Ģ áˆĩáˆĢዎá‰Ŋ @Miki_Mako

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


đŸŒē ሰላም፡ለáŠĩልክሙáĸ áŠĨነሆ ግáŠĨዝን በዐá‰ĸይ ጾም በሚል ልዩ ግáŠĨዝን የምንማማርበá‰ĩ ዝግጅá‰ĩ ተመለáˆĩንáĸ

📜 በመሆኑም ግáŠĨዝ ቋንቋን ቀለል á‰Ŗለና ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለመáˆĩጠá‰ĩ ቅá‹ĩመ ዝግጅá‰ŗá‰Ŋንን አጠናቀናል ከá‰ŗá‰Ŋ በተቀመጠው ሊንክ በመመዝገá‰Ĩ áŒĨንá‰ŗዊና ውዱ ቋንቋá‰Ŋንን áŠĨናáŒĨና áĨ ዕንወቅáĸ

📖 á‰ĩምህርቱን ከ14 ዓመá‰ĩ ዕá‹ĩሜ በላይ የሆነ ማንኛውም ሰው ፤  áˆĩልክáŖ ላፕá‰ļፕ ወይም ዴáˆĩክá‰ļፕ በመጠቀም መማር ይá‰ģላልáĸ

✅ ምዝገá‰Ŗውን ለማáŠĢሄá‹ĩ በዚህ ውáˆĩáŒĨ ሙሉ áˆĩም áŠĨና áˆĩልክ ቁáŒĨር በመላክ የመማማáˆĒá‹Ģ á‰Ļá‰ŗዎá‰Ŋን መቀበል ነው ✅
@Geez202
@Geez202
@Geez202 👈
                

â›ŗī¸ ለበለጠ መረጃ በምዝገá‰Ŗው ይደርáˆĩዎá‰ŗልáĸ áŒĨá‹Ģቄ ሲኖር ከá‰ŗá‰Ŋ በተቀመጠው በáˆĩልክ á‹Ģግኙንáĸ ሠናይ፡ጊዜáĸ

đŸ—Ŗ ለሌሎá‰Ŋም áˆŧር በማá‹ĩረግ áŠĨንá‹ĩናá‹ŗርáˆĩ በአክá‰Ĩሎá‰ĩ áŠĨንጠይቃለንáĸ
đŸŒē መሠረተ፡ግáŠĨዝ đŸŒē
@MesereteGeez - 0977682046


ፈውáˆĩ መንፈáˆŗዊ
👇👇👇👇👇
https://youtube.com/@fewus_menfesawi_aba_gebrekidan?si=bxcN3DD1LN3S8oNM


✞ሰላም አላገኝም✞

ሰላም አላገኝም ከáŠĨርሹ ተለይá‰ŧ
ሁሌ ላመáˆĩግነው ከቤቱ ገá‰Ĩá‰ŧ
ምሕረቱ á‰Ĩዙ ነው ጌá‰ŗ ውለá‰ŗው
ለáŠĨኔ á‹Ģደረገው ልዩ ነው áˆĨáˆĢው

á‰Ĩርሃን ተሰውሮኝ ከá‰Ļኝ ጨለማው
በáŠĸá‹ĢáˆĒኮ መንገá‹ĩ አየኝ በግርማው
የá‹ŗዊá‰ĩ ልጅ ማረኝ á‰Ĩá‹Ŧ ለመንኩá‰ĩ
á‰Ĩርሃኔን አበáˆĢ áŠĨኔም አመንኩá‰ĩ
     አዝ= = = = =
በአውáˆŦ መኖáˆĒá‹Ģ በዋáˆģ ሲáŒĨሉኝ
አዘዘ አናá‰Ĩáˆĩቱን አንዲጠá‰Ĩቁኝ
ተáˆĩፋá‹Ŧን ቀጠለ ደርáˆļ መá‹ŗኛá‹Ŧ
ከሞá‰ĩ አá‹ŗነኝ ቸሩ አረኛá‹Ŧ
   አዝ= = = = =
áˆĻáˆĩá‰ĩ ቀን á‹Ģደረው በዓáˆŖ ተውáŒĻ
á‹ĩኖ ቆሟል ወáŒĨá‰ļ á‰ŗáˆĒክ ተለውáŒĻ
የነነዌ ሰዎá‰Ŋ ዮናáˆĩ ሰá‰ŖáŠĒው
ምሕረá‰ĩን አግኝá‰ļ ከቸር ፈáŒŖáˆĒው
   አዝ= = = = =
ለá‰Ĩዙ ዘመናá‰ĩ በደዌ ተይዤ
áˆĩተኛ ነበረ áˆĩቃይ ተሞልá‰ŧ
አምላáŠŦ ፈቀደ ተነáˆŖሁ ከአልጋ
ፈውáˆļ አቆመኝ ይኸው á‹Ģለዋጋ

መዝሙር
ዲá‹Ģቆን ሙሉጌá‰ŗ ማሞ
  
ማር ፲áĨáĩፎ
╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯




✞áŠĨኔ ግን በምህረá‰ĩህ á‰Ĩዛá‰ĩ✞

áŠĨኔ ግን በምሕረá‰ĩህ á‰Ĩዛá‰ĩ
áŠĨኔ ግን በይቅርá‰ŗህ á‰Ĩዛá‰ĩ
ወደ ቤá‰ĩህ áŠĨገá‰Ŗለሁ
አመልክሃለው áŠĨዘምርልሃለሁ

በሕይወቴ ዘመን አንዲá‰ĩ ነገር áˆģá‰ĩኩኝ
በቤá‰ĩህ ተáŒĨá‹Ŧ መኖáˆŦን መረáŒĨኩኝ
ከኃáŒĸአá‰ĩ á‹ĩንáŠŗን የአንተን ደጅ ይáˆģላል
áŠĨረፍቴ ጌá‰ŗá‹Ŧ áŠĨቅፍህ ይሞቃል(áĒ)
አዝ= = = = =
የክá‰Ĩርህን áˆĨፍáˆĢ ማደርá‹Ģ ወደá‹ĩኩá‰ĩ
መቅደáˆĩህ ቀደሰኝ ዙፋኔን ጠላሁá‰ĩ
ከዚህá‰Ŋ ለምለም áˆĩፍáˆĢ ወዴá‰ĩ áŠĨወáŒŖለሁ
የተሰበረ ልá‰Ĩ ይዤልህ áŠĨመáŒŖለሁ
አዝ= = = = =
በመከáˆĢá‹Ŧ ቀን የተናገርኩá‰ĩን
ከደጅህ መáŒĨá‰ŧ ከንፈሮá‰ŧ á‹Ģሉá‰ĩን
áˆĩዕለቴን ልፈፅም ማልጄ áŠĨነáˆŖለሁ
የአምልኮ መáˆĩዋዕቴን áŠĨሰዋልሃለው(áĒ)
አዝ= = = = =
áŠĨንደ ሰá‰Ĩአ ሰገል ይዤ ወርቅ ዕáŒŖኔን
አምሃ አኮቴá‰ĩ መá‰Ŗá‹Ŧን ከርቤá‹Ŧን
ልቤን አየሰዋሁ áŠĨሰግá‹ĩልሃለው
áŠĻሜጋ አልፋ ነህ áŠĨቀኝልሀለው

        መዝሙር
  ቀሲáˆĩ ምንá‹ŗá‹Ŧ á‰Ĩርሃኑ

"áŠĨኔ ግን በምሕረá‰ĩህ á‰Ĩዛá‰ĩ ወደ ቤá‰ĩህ áŠĨገá‰Ŗለሁ፤ አንተን በመፍáˆĢá‰ĩ ወደ ቅá‹ĩáˆĩናህ መቅደáˆĩ áŠĨሰግá‹ŗለሁáĸ"
መዝ፭áĨ፯
╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯


✞ና ና አማኑኤል✞

ና ና አማኑኤል ና መá‹ĩኃኒቴ
áŒŊá‹ĩቅህን አልá‰Ĩሰኝ ይቅር መáˆĢቆቴ

የምህረá‰ĩ አá‰Ŗá‰ĩ - - አማኑኤል
የቸርነá‰ĩ ጌá‰ŗ - - አማኑኤል
ፊá‰ĩህ የተመላ - - አማኑኤል
ሁሌ በይቅርá‰ŗ - - አማኑኤል
áŠĢለው ፍቅር በላይ - - አማኑኤል
አá‰Ŗá‰ĩ ለአንá‹ĩ ልጁ - - አማኑኤል
አምላክ ይወደናል - - አማኑኤል
አይáŒĨለንም ከáŠĨጁ- -  አማኑኤል
አዝ= = = = =
መá‹ĩኃኒቴ ልበል - - አማኑኤል
á‹ĩኛለው በሞá‰ĩህ - - አማኑኤል
ቁáˆĩሌ ተፈውሷል - - አማኑኤል
በቁáˆĩልህ በሞá‰ĩህ - - አማኑኤል
áˆĩሸáŒĨህ አቀፍከኝ - - አማኑኤል
áˆĩወጋህ አይኔ በáˆĢ - - አማኑኤል
በፍቅርህ አወáŒŖኸኝ - - አማኑኤል
ከዚá‹Ģ ከመከáˆĢ - - አማኑኤል
አዝ= = = = =
አንተ ከኔ ጋር ነህ - - አማኑኤል
አዎ ከኔ ጋáˆĢ - - አማኑኤል
á‹ĩል አርገህልኛል - - አማኑኤል
የጭንቄን ተáˆĢáˆĢ - - አማኑኤል
በጉá‰Ŗኤ መሃል - - አማኑኤል
አፌ አንተን አወጀ - - አማኑኤል
የከበረ ደምህ - - አማኑኤል
ነፍሴን áˆĩለዋጀ - - አማኑኤል
አዝ= = = = =
የá‹ĩንግሏ ፍáˆŦ - - አማኑኤል
የá‰Ĩላቴናዋ - - አማኑኤል
የቤቴ ምሰáˆļ - -  አማኑኤል
የነፍሴ ቤዛዋ - - አማኑኤል
መሰረቴ አንተ ነህ - - አማኑኤል
á‹Ģáˆŗደገኝ áŠĨጅህ - - አማኑኤል
አá‰ĩተወኝም አንተ - - አማኑኤል
áˆĩለሆንኩኝ ልጅህ - - አማኑኤል

መዝሙር
ሲáˆĩተር ሕይወá‰ĩ ተፈáˆĒ

"áŠĨነሆáĨ á‹ĩንግል á‰ĩፀንáˆŗለá‰ŊáĨ ወንá‹ĩ ልጅም á‰ĩወልá‹ŗለá‰ŊáĨ áˆĩሙንም አማኑኤል á‰Ĩላ á‰ĩጠáˆĢዋለá‰Ŋáĸ"
                 áŠĸáˆŗ፯áĨ፲áŦ
╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯

23k 0 534 195

💍የጋá‰Ĩá‰ģ ዓላማ💍

ይህ ምáˆĩáŒĸር á‰ŗላቅ ነው áŠĨንá‹ŗለው መáŒŊሐፍ
መኝá‰ŗውም ንጹሕ የለበá‰ĩም áŠĨá‹ĩፍ(áĒ)

áŠĨውቀá‰ĩን áŒĨበá‰Ĩን ጎናáŒŊፎá‰ĩ ለአá‹ŗም
ሁሉን áŠĨንዲገዛ አሰልáŒĨኖá‰ĩ በዓለም
ከጎኑ አáŒĨንá‰ĩ ወáˆĩá‹ļ በረቂቅ ምáˆĩáŒĸሊ
አáˆĩማምá‰ļ ፈጠáˆĢá‰ĩ ሔዋንን ለክá‰Ĩሊ(áĒ)
አዝ= = = = =
ዘርን ለመተáŠĢá‰ĩ á‰ĩውልá‹ĩ áŠĨንዲቀáŒĨል
በá‰ĩዕዛዘ አምላክ ከአá‰ĨáˆĢክ የሚከፈል
በሕግ áŠĨና áˆĨርዓá‰ĩ በቤቱ ለኖሩá‰ĩ የተሰጠ ጸጋ የምáˆĨáŒĸር አንá‹ĩነá‰ĩ (áĒ)
አዝ= = = = =
በጸሎá‰ĩ ለመá‰ĩጋá‰ĩ በአንá‹ĩነá‰ĩ ተá‰Ŗá‰Ĩሎ መንግáˆĨቱን ለመውረáˆĩ ሕጉንም አክá‰Ĩሎ
ከዝሙá‰ĩ áŠĨርቆ ሕይወá‰ĩን ለመምáˆĢá‰ĩ
ፈáŒŖáˆĒ ለሰው ልጅ á‹Ģበጀው áˆĨርዓá‰ĩ(áĒ)
  አዝ= = = = =
በምá‹ĩáˆĢዊ ኑሮ በመውáŒŖá‰ĩ መግá‰Ŗቱ
áŠĨየተረá‹ŗዱ በአንá‹ĩ áŠĨንዲበረቱ
የቤተክርáˆĩቲá‹Ģንን áˆĨርዓá‰ĩ ጠá‰Ĩቀው
ለክá‰Ĩር áŠĨንዲበቁ የተሰጠ ሕግ ነው(áĒ)
አዝ= = = = =
ዘወá‰ĩር ይá‰ŗወጅ የጋá‰Ĩá‰ģ ዓላማ
ሙáˆŊሎá‰Ŋ ልበሱ ፍቅርን áŠĨንደ ሸማ
የነፍáˆĩ ዋጋን á‰ĩተን ለáˆĨጋ በማá‹ĩላá‰ĩ
ከመንገá‹ĩ áŠĨንá‹ŗንርቅ áŠĨንá‰ĩጋ ለጸሎá‰ĩ(áĒ)

      መዝሙር
  በማኅበረ ቅዱáˆŗን

"...áˆĩለዚህ ሰው አá‰Ŗቱንና áŠĨናቱን ይተዋል ከሚáˆĩቱም ጋር ይተá‰ŖበáˆĢል ሁለቱም አንá‹ĩ áˆĨጋ ይሆናሉáĸይህ ምáˆĨáŒĸር á‰ŗላቅ ነውáĨ"
ኤፌ ፭áĨ፴áĒ
╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯


#ተጋá‰Ĩኡ
ተጋá‰Ĩኡ በቅáŒŊበá‰ĩ ለግንዘተ áŠĨሙ ቅá‹ĩáˆĩá‰ĩ
á‰Ĩጹአን(፭)ሐዋርá‹Ģá‰ĩ
#á‰ĩርጉም
ቅá‹ĩáˆĩá‰ĩ áŠĨናቱን ለመገነዝ á‰Ĩጹአን ሐዋርá‹Ģá‰ĩ በቅáŒŊበá‰ĩ ተሰበሰቡ

✞


#ጊዜ_áŠĨረፍá‰ŗ
ጊዜ áŠĨረፍá‰ŗ(áĒ) ለáˆļልá‹Ģና
ወረደ ወልá‹ĩ(áŦ)ወልá‹ĩ áŠĨም ዲበ ልዕልና
#á‰ĩርጉም
በማርá‹Ģም áŠĨረፍá‰ĩ ጊዜ ወልá‹ĩ ከሰማይ ወረደ

✞


#ለዛቲ_á‹ĩንግል
ለዛቲ á‹ĩንግል(áĒ)
ወአግአዛ(áĒ)ለዛቲ á‹ĩንግል(áĒ)
#á‰ĩርጉም
á‹ĩንግልን ከዓለም á‹ĩáŠĢም ነáŒģ አወáŒŖá‰ĩ

✞


#ዘá‹ĩንግል
ዘá‹ĩንግል መናáˆĩግተ áŠĸá‹Ģርኂዎ
áŠĸá‹Ģርኂዎ ዘáŠĒሩቤል áŠĸርáŠĨዮ(áĒ)
#á‰ĩርጉም
áŠĒሊá‰Ĩ በማይመረምረው ምáˆĩáŒĸር የá‹ĩንግል ማህተመ á‹ĩንግልናን áˆŗይከፍá‰ĩ

✞


#አንáŒēሆ_áˆĨጋሃ
አንáŒēሆ áˆĨጋሃ ቀዲáˆļ áŠĒá‹Ģሃ
ወረደ(áŦ) ሃደረ ላዕሌሃ
#á‰ĩርጉም
áˆĩጋዋን አንáŒŊá‰ļ/ ከሃáŒĸአá‰ĩ ጠá‰Ĩቆ áŠĨሷን ለይá‰ļ/አክá‰Ĩሎ ከሷ  ሰው ሆነáĸ

✞


#áŠĨáˆĩመ_áŠĨም_ዘርዐ_á‹ŗዊá‰ĩ
áŠĨáˆĩመ áŠĨም ዘርዐ á‹ŗዊá‰ĩ ዘመáŒŊአ
በቤተልሄም ዘይሁá‹ŗ(áĒ)
#á‰ĩርጉም
ከá‹ŗዊá‰ĩ ዘር በይሁá‹ŗ áŠĨáŒŖ በምá‰ĩሆን በቤተ ልሄም ሰው ሁኗልና..

╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯


#ወልá‹ĩáŠĒ_ይáŒŧውአáŠĒ
       
ወልá‹ĩáŠĒ ይáŒŧውአáŠĒ(áĒ)
ውáˆĩተ ሕይወá‰ĩ ወመንግáˆĨተ ክá‰Ĩር (áĒ)
ልጅáˆŊ ይጠáˆĢáˆģል(áĒ)
ወደ ሕይወá‰ĩና ወደ ክá‰Ĩር መንግáˆĨá‰ĩ(áĒ)

╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯


✞አይዞህ á‹ļáŠĒማáˆĩ✞

አይዞህ á‹ļáŠĒማáˆĩ ሆይ á‰ĸá‹Ģልቅም ወይን ጠጁ
áŠĨá‹ĩምተኛው á‰ĸጎርፍ á‰ĸሞላ በደጁ
ንግáˆĨቷ áˆĩላለá‰Ŋ በáŠĨá‹ĩምተኛው መሃል
á‹Ģለቀው መጠáŒĨህ ይጨመርልሃል

ወይኑ አለቀ á‰Ĩለህ áˆĩá‰ĩጨነቅ በáŠĨፍረá‰ĩ
ሰውም á‰ĸáˆĩቅá‰Ĩህ á‰ĸá‹Ģደርግህ ለተረá‰ĩ
የጠáˆĢáŠģá‰ĩ  ንግáˆĨá‰ĩ ልጇ ጋር á‹Ģለá‰Ŋው
ከáŠĨፍረá‰ĩ አá‹ŗነá‰Ŋህ ጋኑን áŠĨáˆĩሞላá‰Ŋው
አዝ= = = = =
áˆĩá‹ĩáˆĩቱ መáŒĨመቂá‹Ģ ተሟáŒĨáŒĻ ከáˆĩሊ
á‹ļáŠĒማáˆĩ ደንግáŒĻ ሲጓዝ በግንá‰Ŗሊ
የአማኑኤል áŠĨናá‰ĩ የክá‰Ĩር áŠĨንግá‹ŗ
አá‰ĩረፈረፈá‰Ŋው á‹Ģለቀውን ጓá‹ŗ
አዝ= = = = =
የጓá‹ŗህ áˆĩá‰ĨáˆĢá‰ĩ  ተጠግኖልሃል
ጎá‹ļሎህ በሙሉ á‹ŗግም ሞልá‰ļልሃል
ተá‰ĩረፈረፈልህ በደáˆĩá‰ŗ ላይ ደáˆĩá‰ŗ
ሠርግህ ላይ áˆĩላለ የሠáˆĢዊá‰ĩ ጌá‰ŗ
አዝ= = = = =
የተáˆĢቆá‰ŗá‰Ŋሁ ጸጋá‰Ŋሁ á‹Ģለቀ
የሕይወá‰ŗá‰Ŋሁ ወይን ዛáˆŦም የደረቀ
የልá‰Ŗá‰Ŋሁ áˆĩፍáˆĢ ይደልደል ይዘርጋ
ክፈቱ áŠĨና አáˆĩገቧá‰ĩ ንግáˆĨቷን ልጇ ጋ

መዝሙር
በኮምá‰Ļልá‰ģ ደá‰Ĩረ ምሕረá‰ĩ ቅ/ገ/ሰ/á‰ĩ/ቤá‰ĩ
ዘርዓይ ደርቤ áŠĨና á‰Ĩዙአየሁ ተክሉ

ዮሐáĒáĨፊ-፲፭
╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯

35k 0 113 101

Forward from: 💛 የ መዝሙር ግáŒĨሞá‰Ŋ 💛
"በáˆĻáˆĩተኛውም ቀን በገሊላ ቃና ሰርግ ነበረáĨ የáŠĸየሱáˆĩም áŠĨናá‰ĩ በዚá‹Ģ ነበረá‰Ŋ፤
áŠĸየሱáˆĩም ደግሞ ደቀ መዛሙርቱም ወደ ሰርጉ á‰ŗደሙáĸ
የወይን ጠጅም á‰Ŗለቀ ጊዜ የáŠĸየሱáˆĩ áŠĨናá‰ĩáĸ የወይን ጠጅ áŠĨኮ የላቸውም አለá‰Ŋውáĸ
áŠĸየሱáˆĩምáĸ አንá‰ē ሴá‰ĩáĨ ከአንá‰ē ጋር ምን አለኝ? ጊዜá‹Ŧ ገና አልደረሰም አላá‰ĩáĸ
áŠĨናቱም ለአገልጋዮቹáĸ የሚላá‰Ŋሁን ሁሉ አá‹ĩርጉ አለá‰ģቸውáĸ
አይሁá‹ĩም áŠĨንደሚá‹Ģደርጉá‰ĩ የማንáŒģá‰ĩ ልማá‹ĩ áˆĩá‹ĩáˆĩá‰ĩ የá‹ĩንጋይ ጋኖá‰Ŋ በዚá‹Ģ ተቀምጠው ነበርáĨ áŠĨá‹Ģንá‹ŗንá‹ŗቸውም ሁለá‰ĩ ወይም áˆĻáˆĩá‰ĩ áŠĨንáˆĩáˆĢ ይይዙ ነበርáĸ
áŠĸየሱáˆĩምáĸ ጋኖቹን ውኃ ሙሉአቸው አላቸውáĸ áŠĨáˆĩከ አፋቸውም ሙሉአቸው አላቸውáĸ áŠĨáˆĩከ አፋቸውም ሞሉአቸውáĸ
አሁን ቀá‹ĩá‰ŗá‰Ŋሁ ለአáˆŗá‹ŗáˆĒው áˆĩጡá‰ĩ አላቸው፤ ሰጡá‰ĩምáĸ
አáˆŗá‹ŗáˆĒውም የወይን ጠጅ የሆነውን ውሃ በቀመሰ ጊዜ ከወዴá‰ĩ áŠĨንደ መáŒŖ አላወቀም፤ ውኃውን የቀዱá‰ĩ አገልጋዮá‰Ŋ ግን á‹Ģውቁ ነበር፤ አáˆŗá‹ŗáˆĒው ሙáˆŊáˆĢውን ጠርá‰ļáĸ
ሰው ሁሉ አáˆĩቀá‹ĩሞ መልáŠĢሙን የወይን ጠጅ á‹Ģቀርá‰ŖልáĨ ከሰከሩም በኋላ መናኛውን፤ አንተáˆĩ መልáŠĢሙን የወይን ጠጅ áŠĨáˆĩከ አሁን አቆይተሃል አለውáĸ
áŠĸየሱáˆĩ ይህን የምልክá‰ļá‰Ŋ መጀመáˆĒá‹Ģ በገሊላ ቃና አደረገ፤ ክá‰Ĩሩንም ገለጠáĨ ደቀ መዛሙርቱም በáŠĨርሹ አመኑáĸ

ዮሐ áĒáĨፊ-፲፩
╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
    @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯


#ክርáˆĩá‰ļáˆĩ_ተጠመቀ

ክርáˆĩá‰ļáˆĩ ተወለደ ተጠመቀ ክርሰá‰ļáˆĩ
á‹ŗግመኛ ወለደን ከውሃ ከመንፈáˆĩቅዱáˆĩ(áĒ)


ዮሐ áĢáĨ፭


መዝሙር
የናዝáˆŦá‰ĩ ደá‰Ĩረ ፀሐይ ቅá‹ĩáˆĩá‰ĩ ማርá‹Ģም ሰ/á‰ĩ/ቤá‰ĩ

╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯




Forward from: 💛 የ መዝሙር ግáŒĨሞá‰Ŋ 💛
â›Ēī¸ መልáŠĢም የ áŒĨምቀá‰ĩ በዓል á‹Ģá‹ĩርግልን â›Ēī¸
╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ ══╯


​​✞áŒĨምቀተ ክርáˆĩá‰ļáˆĩ ✞


✝በሊቀ ሊቃውንá‰ĩ ዕዝáˆĢ ሓዲáˆĩ✝

✍ áŒĨምቀá‰ĩ ማለá‰ĩ ምን ማለá‰ĩ ነው?

✍ ጌá‰ŗá‰Ŋን áŒĨምቀቱን ለምን በዮርá‹ŗኖáˆĩ አደረገ?

✍ ጌá‰ŗá‰Ŋን ሲጠመቅ መንፈáˆĩቅዱáˆĩ ለምን በርግá‰Ĩ አምáˆŗል ወረደ?

✍ ጌá‰ŗá‰Ŋን ለምን በውሃ ተጠመቀ?

✍ ለምን መንፈáˆĩቅዱáˆĩ ጌá‰ŗá‰Ŋን ተጠምቆ ከá‰Ŗሕሩ ከወáŒŖ በኋላ ወረደ?

✍ ጌá‰ŗá‰Ŋን  ለመጠመቅ ለምን ወደ ዮሐንáˆĩ ሄደ?

✍ ዮሐንáˆĩ ጌá‰ŗá‰Ŋንን ምን áŠĨá‹Ģለ አጠመቀው?

✍ ጌá‰ŗá‰Ŋን ለምን በለሊá‰ĩ ተጠመቀ?.

✍ ጌá‰ŗá‰Ŋን ለምን በሠላáˆŗ ዓመቱ ተጠመቀ?

✍ ቃና ዘገሊላ ምንá‹ĩን ነው?

ሊቀ ሊቃውንá‰ĩ ዕዝáˆĢ ሓዲáˆĩ በሰፊው አáˆĩተምረውናልáĸ


በአምáˆĩá‰ĩ ክፍል ተáŒŊፏልáĸ

የጌá‰ŗá‰Ŋን የመá‹ĩኃኒá‰ŗá‰Ŋን የáŠĸየሱáˆĩ ክርáˆĩá‰ļáˆĩን áŒĨምቀá‰ĩ áˆĩናከá‰Ĩር ይህንን ሁሉ ተረá‹ĩተን áŠĨንዲሆን áŠĨá‹Ģáˆŗሰá‰Ĩንáĸ

 🎊መልáŠĢም  የáŒĨምቀá‰ĩ በዓል á‹Ģá‹ĩርግልንáĸ🎊

╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯


ከሰማá‹Ģá‰ĩ ወርá‹ļ
                
            ● ጸሐፌ á‰ĩዕዛዝ ●
    ♡ዲ/ን á‰ŗዴዎáˆĩ ግርማ♡
╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯


​​✞ከሰማá‹Ģá‰ĩ ወርá‹ļ✞  
                
ከሰማá‹Ģá‰ĩ ወርá‹ļ ከá‹ĩንግል ተወልá‹ļ        
ተገኘ በበረá‰ĩ áˆĢሱን አዋርá‹ļ       
       
የነገáˆĨá‰ŗá‰ĩ ንጉáˆĨ - - - ተገኘ በበረá‰ĩ       
ቤዛ ኲሉ ዓለም - - - ተገኘ በበረá‰ĩ    
መá‹ĩኅን ተወለደ - - - ተገኘ በበረá‰ĩ      
በቤተልሔም - - - ተገኘ በበረá‰ĩ   
አáˆĢቀልን ከáŠĨኛ - - - ተገኘ በበረá‰ĩ    
ቁáŒŖን በá‰ĩዕግáˆĩቱ - - - ተገኘ በበረá‰ĩ    
á‰ŗላቅ ነው ከሁሉ - - - ተገኘ በበረá‰ĩ     
የጌá‰ŗ ልደቱ - - - ተገኘ በበረá‰ĩ   
    አዝ= = = = =   
ለቅዱáˆŗን ክá‰Ĩር - - - ተገኘ በበረá‰ĩ     
ጸጋን ሊá‹Ģለá‰Ĩáˆŗቸው - - - ተገኘ በበረá‰ĩ     
መáŒŖ ወልደ አምላክ - - - ተገኘ በበረá‰ĩ    
ከመáŠĢከላቸው  - - - ተገኘ በበረá‰ĩ
የጠፋው አá‹ŗምን - - - ተገኘ በበረá‰ĩ 
ከá‰Ļá‰ŗው መልáˆļ - - - ተገኘ በበረá‰ĩ      
የተገፈፈውን - - - ተገኘ በበረá‰ĩ     
ጸጋውን አልá‰Ĩáˆļ - - - ተገኘ በበረá‰ĩ    
በበረá‰ĩ ተገኘ - - - ተገኘ በበረá‰ĩ    
ኮá‰Ŗ ቅጠል ለá‰Ĩáˆļ - - - ተገኘ በበረá‰ĩ    
  አዝ= = = = =      
የጠፋ አá‹ŗምን - - - ተገኘ በበረá‰ĩ       
ከውá‹ĩቀá‰ĩ ሊá‹ĢነáˆŖ - - - ተገኘ በበረá‰ĩ    
ተገኘ አምላáŠĢá‰Ŋን - - - ተገኘ በበረá‰ĩ    
በቤተ áŠĨንáˆĩáˆŗ  - - - ተገኘ በበረá‰ĩ     
መላáŠĨክá‰ĩ መጡ - - - ተገኘ በበረá‰ĩ    
áŠĨረኞá‰Ŋ ዘመሩ  - - - ተገኘ በበረá‰ĩ         
የአጋንንá‰ĩ ሰáˆĢዊá‰ĩ - - - ተገኘ በበረá‰ĩ    
በሙሉ አፈሩ - - - ተገኘ በበረá‰ĩ
   አዝ= = = = =
ከልዑል መንበሩ - - - ተገኘ በበረá‰ĩ         
ከዙፋኑ ወርá‹ļ  - - - ተገኘ በበረá‰ĩ     
á‰ĩሕá‰ĩናን ሰበከ - - - ተገኘ በበረá‰ĩ    
በበረá‰ĩ ተወልá‹ļ      - - - ተገኘ በበረá‰ĩ    
ቁáŒŖ ሞá‰ĩን áˆŊሎ  - - - ተገኘ በበረá‰ĩ    
áŒŊá‹ĩቅን አበሰረ  - - - ተገኘ በበረá‰ĩ     
ሰይáŒŖን á‹ĩል ተነáˆŖ   - - - ተገኘ በበረá‰ĩ      
መርገምም ተáˆģረ - - - ተገኘ በበረá‰ĩ    

       ጸሐፌ á‰ĩዕዛዝ
  ዲ/ን á‰ŗዴዎáˆĩ ግርማ
╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
   @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯


#አሰርግዉኒ

አሰርግዉኒ áˆĨላሴ በቀጠንተ ምáŒŊዋá‰ĩ ሠናይ
áŠĨምነ ልማዱ á‰Ĩሉይ ለነዌ ጊጉይ
áŠĨንዘ በዴዴሁ ይግáŠĨር አልአዛርን ነá‹ŗይ

áˆĨሉáˆĩ ቅዱáˆĩ  ሸልመኝ መልáŠĢሙን የርኅáˆĢኄ ሃር
áŠĨንደ ነዌ አርጅቷል ቆልፎ የልቡናውን በር
በደጃፉ ቆሞ ሲማጸን ሲለምን አልአዛር

╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
  @yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯


በáˆĩመአá‰Ĩ ወወልá‹ĩ ወመንፈáˆĩቅዱáˆĩ አሐዱ አምላክ አሜን

"ከሁሉ አáˆĩቀá‹ĩመን በአáŠĢል ልዩ በክá‰Ĩር አንá‹ĩ የሆነውን áˆĻáˆĩá‰ĩነቱን áŠĨንሰá‰ĨáŠĢለን
áŠĨነሱም አá‰Ĩ ወልá‹ĩ መንፈáˆĩቅዱáˆĩ ናቸውáĸ"

     ሃይማኖተ አበው ዘጎርጎርዮáˆĩ ...

✞መቅá‹ĩመ ኲሉ✞

መቅá‹ĩመ ኲሉ ንሰá‰Ĩክ áˆĨላሴ ዕሩየ
ወንዌáŒĨን ሎቱ አኮቴተ ዕሩየ
የዝማáˆŦ አልፋ የአገልግሎá‰ĩ መቅá‹ĩም
áˆĨላሴን ማወደáˆĩ á‰Ĩለን አንá‹ĩም áˆĻáˆĩá‰ĩም

መሠረተ ሃይማኖá‰ĩ áŠĨርሱም በኩረ  አáŠĨማá‹ĩ
ምáˆĩáŒĸረ áˆĨላሴን ማጉላá‰ĩ በአበው ልማá‹ĩ
ተምረናልና በየ መáŒģሕፍቱ
ወጠነ áˆĩá‰Ĩሐተ በáˆĩመ ሠለáˆĨቱ
አዝ= = = = =
በáˆĩም በአáŠĢል በግá‰Ĩር በከዊን áˆĻáˆĩá‰ĩ á‰Ĩለን
ወáŠĨንዘ ሠለáˆĨቱ አሐዱ ነው አሚን
አይደርáˆĩበá‰ĩ ጠá‰ĸá‰Ĩ የተመáˆĢመረም
á‰Ĩሎ á‹Ģደንቃል áŠĨንጂ á‰ĩá‰ĩነከር á‰ĩá‰ĩረመም
አዝ= = = = =
ንግበር ሰá‰Ĩአ á‰Ĩለው በአርአá‹Ģ በአምáˆŗል
መልክአ áˆĨላሴ በማኅጸን ሲáˆŗል
የሰው ልጆá‰Ŋ ሆነን የተፈጠርን ሁሉ
ንበል áˆĩá‰Ĩሐá‰ĩ ወክá‰Ĩር ለáˆĨሉáˆĩ ይደሉ
አዝ= = = = =
አá‹ĩá‰ŖáˆĢቱ መምáˆŦ á‹ĩንáŠŗን ሆኖ መቅደáˆĩ
አá‰Ĩርሃም áŠĢህኑ áŠĨንá‹ŗገኘ ሞገáˆĩ
አሐዱ አá‰Ĩ ሲá‰Ŗል ተገለáŒĨ áˆĨላሴ
በረከá‰ĩህን ላክ በጊዜ ቅá‹ŗሴ

በገነተ áŠĸየሱáˆĩ ገነተ ማርá‹Ģም
መሠረተ ሃይማኖá‰ĩ ሰ/á‰ĩ/ቤá‰ĩ
╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ  ══╯


Forward from: 💛 የ መዝሙር ግáŒĨሞá‰Ŋ 💛
​​በáˆĩመአá‰Ĩ ወወልá‹ĩ ወመንፈáˆĩቅዱáˆĩ አሐዱ አምላክ አሜን!

በዓለ ግዝረá‰ĩ

ከርáŠĨሰ ደá‰Ĩር á‰Ĩርሃኑ አáŠĢል

ጌá‰ŗá‰Ŋን መá‹ĩኃኒá‰ŗá‰Ŋን áŠĸየሱáˆĩ ክርáˆĩá‰ļáˆĩ ቅá‹ĩመ ዓለም በህሊና á‹Ģሰበውን፤ á‹ĩኅረ ዓለም በነá‰ĸá‹Ģá‰ĩ á‹Ģናገረውን ለመፈጸም ሰው ሆነáŖ áˆĨጋ ለበሰ፤ ሕግ ጠá‰Ŗá‹Ģዊን ሕግ መáŒŊሐፋዊን áŠĨየፈጸመ በáŒĨቂቱ አደገáĸ ሕግ ጠá‰Ŗá‹Ģዊ፤ አበáŖ áŠĨመ ማለá‰ĩáŖ ለዘመá‹ĩ መá‰ŗዘዝáŖ በየáŒĨቂቱ ማደግ ነውáĸ "ወልህቀ በበኅቅ áŠĨንዘይá‰ĩኤዘዝ ለአዝማዲሁ ወለይáŠĨቲ áŠĨሙ"áŠĨንዲልáĸ

ሕግ መáŒŊሐፋዊ በáˆĩምንá‰ĩ ቀን ቤተ ግዝረá‰ĩ በአርá‰Ŗ ቀን ዕጉለ ርግá‰Ĩ ዘውገ ማዕነቅ ይዞ ቤተ መቅደáˆĩ መግá‰Ŗá‰ĩ የመáˆŗሰሉá‰ĩ ናቸው፤ በማለá‰ĩ የመáŒģሕፍተ ሐዲáˆĩ áŠĒá‹ŗን ሊቃውንá‰ĩ በሐዲáˆĩ áŠĒá‹ŗን á‰ĩርጓሜ መግá‰ĸá‹Ģ ላይ á‹ĢመሰáŒĨáˆĢሉáŖ á‹ĢáˆĩተምáˆĢሉáĸ

ቅዱáˆĩ ሉቃáˆĩ በáŒģፈው የጌá‰ŗá‰Ŋን የመá‹ĩኃኒá‰ŗá‰Ŋን áŠĸየሱáˆĩ ክርáˆĩá‰ļáˆĩ ቅዱáˆĩ ወንጌል ምዕáˆĢፍ ፊ ቁáŒĨር áļ፱ ላይ ዘግá‰Ļልን áŠĨንደምናገኘው፤ በዘመነ á‰Ĩሉይ ወንá‹ĩ ልጅ በተወለደ በáˆĩምንተኛው ቀን ሲገረዝ áˆĩም ይወáŒŖለá‰ĩ ነበርáĸበመሆኑም ግዝረá‰ĩ የáˆĨጋ ሸለፈá‰ĩ መቆረáŒĨን á‹Ģመለክá‰ŗልáĸ

የግዝረá‰ĩ áˆĨርዓá‰ĩ ዝም á‰Ĩሎ የመáŒŖ áˆŗይሆን áŠĨግዚአá‰Ĩሔር ለአá‰Ĩርሃም የሰጠው የቃል áŠĒá‹ŗኑ ምልክá‰ĩ ነውáĸ á‹˜áá˛á¯ áĨ ፯-፲áŦ

በሙሴ የመáˆĒነá‰ĩ ዘመንም ለáŠĨáˆĩáˆĢኤል ህዝá‰Ĩ ምልክá‰ĩና መለá‹Ģ ነበርáĸ
ዘፀ ፲áĒáĨáĩáĢ

ፈáˆĒáˆŗውá‹Ģን ግን ከአá‰Ĩርሃም የመáŒŖ መሆኑን áˆŗይረዱ በሙሴ áŠĨንደተሰጠ ሕጋዊና ሕዝá‰Ŗዊ ምልክá‰ĩ አá‹ĩርገው á‹Ģምኑ ነበርáĸየሐዋ፲፭áĨ፲-፭

ጌá‰ŗá‰Ŋን መá‹ĩኃኒá‰ŗá‰Ŋን áŠĸየሱáˆĩ ክርáˆĩá‰ļáˆĩ ግን፤ መጀመáˆĒá‹Ģ áˆĢሹ የሰጠው ለአá‰Ĩርሃም áŠĨንደነበርና መንፈáˆŗዊ ምልክá‰ĩም áŠĨንደሆነ አáˆĩረá‹ĩቷቸው ነበርáĸዮሐ ፯áĨáŗáĒ

የሚከተሉá‰ĩ áˆĻáˆĩá‰ĩ ነáŒĨá‰Ļá‰Ŋ የግዝረá‰ĩ ዋና ዋና ዓላማዎá‰Ŋ ናቸውáĸ

ፊ.áŠĨግዚአá‰Ĩሔር የተገረዘውን ሰው ለáˆĢሹ መርጧልና አምላኩ ነውáĸ ዘፍ á˛á¯áĨ፰

áĒ.የተገረዙá‰ĩ የáŠĨግዚአá‰Ĩሔር ህዝá‰Ļá‰Ŋ ናቸውና ክፋá‰ĩንም ከህይወá‰ŗቸው ማáˆĩወገá‹ĩ አለá‰Ŗቸውáĸ ዘጸ፲áĨ፲፮

áĢ.áŠĨግዚአá‰Ĩሔር በáŠĨምነá‰ĩ áˆĩለተቀበላቸው የáŒŊá‹ĩቃቸው መሠረá‰ĩ ነውáĸ ሮሜáŦáĨ፲፩

ሆኖም በሐዲáˆĩ áŠĒá‹ŗን áˆĨርዓá‰ĩ áˆŖይሆን፤ የሚá‹Ģá‹ĩነው የáŠĨግዚአá‰Ĩሔር ህግ መሆኑን ቅዱáˆĩ áŒŗውሎáˆĩ á‹Ģá‰ĨáˆĢáˆĢልáĸ
ሮሜáĒáĨáŗ፭

ዋናው ነገር የáˆĨጋ ሸለፈá‰ĩ መገረዝ áˆŗይሆን የልá‰Ĩ መለወáŒĨና በáŠĨግዚአá‰Ĩሔር ማመን ሕጉንም መፈጸም ነውáŖ ሲል ቅዱáˆĩ áŒŗውሎáˆĩ ምዕመናኑን በመንፈáˆĩ የተገረዙ መሆናቸውንም ጨምሮ አá‰ĨáˆĢርቷልáĸፊሊáŒĩ áĢáĨ፴

በተለይም ህዝá‰Ĩና አህዛá‰Ĩ ማለá‰ĩም á‰ĩንá‰ĸá‰ĩ የተነገረላቸውáŖ ተáˆĩፋ የተነገáˆĢቸው áŠĨáˆĩáˆĢኤላውá‹Ģን áŠĨና ከአህዛá‰Ĩ ወገን የመጡá‰ĩ ሁለቱም የክርáˆĩá‰ĩና አማኞá‰Ŋ በግዝረá‰ĩ ምክንá‹Ģá‰ĩ á‹Ģáˆĩነሱá‰ĩን አለመግá‰Ŗá‰Ŗá‰ĩ አáˆĩመልክá‰ļ በáŒģፈው መልáŠĨክቱ በሐዲáˆĩ áŠĒá‹ŗን ዘመን áŒĨምቀá‰ĩ በግዝረá‰ĩ ፋንá‰ŗ መተáŠĢቱን á‹Ģáˆĩረá‹ŗልáĸቆላáĒáĨ፲፩

ግዝረá‰ĩም አሁን አይጠቅምም ይለናልáĸ ገላ ፭áĨፎ

ወደ ጌá‰ŗá‰Ŋን መá‹ĩኃኒá‰ŗá‰Ŋን áŠĸየሱáˆĩ ክርáˆĩá‰ļáˆĩ ግዝረá‰ĩ áˆĩንመለáˆĩ ደግሞ፤ በመግá‰ĸá‹Ģው áŠĨንደተገለጸው áŠĻáˆĒá‰ĩና ነá‰ĸá‹Ģá‰ĩን ልፈáŒŊም áŠĨንጂ ልáˆŊáˆĢቸው አልመáŒŖሁም áŠĨንá‹ŗለ፤ ለáˆĩም አጠáˆĢሊ ክá‰Ĩር ይግá‰Ŗውና áŠĨርሹ áˆĢሹ áˆĨርዓቱን ለመፈጸም ከáŠĨመቤá‰ŗá‰Ŋን ከቅá‹ĩáˆĩá‰ĩ á‹ĩንግል ማርá‹Ģም በተወለደ በáˆĩምንተኛው ቀን áŠĨናቱ ወደ ቤተ መቅደáˆĩ ወáˆĩá‹ŗው ሊገረዝ በá‰ŗሰበ ጊዜ በፍጡáˆĢን áŠĨጅ አልተገረዘምáĸ

ምላጩ በገáˆĢዡ áŠĨጅ áŠĨንá‹ŗለ ውኃ ሆኖ ተገኝቷል (መáŒŊሐፈ áˆĩንክáˆŗር áŒĨር áˆĩá‹ĩáˆĩá‰ĩ)áĸይህም በመለኮá‰ŗዊ ኃይሉ ነውáĸ áŠĨርሱም በግá‰Ĩር መንፈáˆĩ ቅዱáˆĩ ተገርዞ ተገኝቷልáĸይህንንም á‹Ģደረገው ሰውን ንቆ áˆĩርዓቱንም ጠልá‰ļ áˆŗይሆን ደመ መለኮቱ á‹Ģለ ዕለተ ዓርá‰Ĩ የማይፈáˆĩ áˆĩለሆነ áŠĨርሹ á‰Ŗወቀ ይህን አደረገ áˆĩሙንም አáˆĩቀá‹ĩሞ በመልአኩ áŠĨንደተነገረ áŠĸየሱáˆĩ አሉá‰ĩáĸ ሉቃáĒ áĨáŗፊ

በዚህም ምክንá‹Ģá‰ĩ ቅá‹ĩáˆĩá‰ĩ ቤተክርáˆĩቲá‹Ģናá‰Ŋንም የጌá‰ŗá‰Ŋን የመá‹ĩኃኒá‰ŗá‰Ŋን የáŠĸየሱáˆĩ ክርáˆĩá‰ļáˆĩን የግዝረá‰ĩ በዓል በየዓመቱ áŒĨር 6 ቀን á‰ŗከá‰ĨáˆĢለá‰Ŋ (መáŒŊሐፈ áˆĩንክáˆŗር áŒĨር áˆĩá‹ĩáˆĩá‰ĩ)áĸ

áˆĩá‰ŗከá‰Ĩርም በግዝረቱ áŠĨለá‰ĩ የተፈጸሙá‰ĩን ተአምáˆĢá‰ĩ በማáˆĩተማርና በማáˆŗወቅ ነውáĸ

ለጌá‰ŗá‰Ŋን መá‹ĩኃኒá‰ŗá‰Ŋን áŠĸየሱáˆĩ ክርáˆĩá‰ļáˆĩ ክá‰Ĩርና ምáˆĩጋና  ይሁን!

አሜን!!!

የአሜáˆĒáŠĢ ማዕከል - በáŠĸ/áŠĻ/ተ/ቤ/ክ ሰ/á‰ĩ/ቤá‰ļá‰Ŋ ማ/መምáˆĒá‹Ģ - ማኅበረ ቅዱáˆŗን

╭══â€ĸ|❀:✧āš‘♥āš‘✧❀|: ══╮
@yamazemur_getemoche
╰══â€ĸāŗ‹â€ĸ✧āš‘♥āš‘✧â€ĸ ══╯

20 last posts shown.

139 136

subscribers
Channel statistics
Popular in the channel

✞አይዞህ á‹ļáŠĒማáˆĩ✞ አይዞህ á‹ļáŠĒማáˆĩ ሆይ á‰ĸá‹Ģልቅም ወይን ጠጁ áŠĨá‹ĩምተኛው á‰ĸጎርፍ á‰ĸሞላ በደጁ ንግáˆĨቷ áˆĩላለá‰Ŋ በáŠĨá‹ĩምተኛው መሃል á‹Ģለቀው መጠáŒĨህ ይጨመርል...
#ተጋá‰Ĩኡ ተጋá‰Ĩኡ በቅáŒŊበá‰ĩ ለግንዘተ áŠĨሙ ቅá‹ĩáˆĩá‰ĩ á‰Ĩጹአን(፭)ሐዋርá‹Ģá‰ĩ #á‰ĩርጉም ቅá‹ĩáˆĩá‰ĩ áŠĨናቱን ለመገነዝ á‰Ĩጹአን ሐዋርá‹Ģá‰ĩ በቅáŒŊበá‰ĩ ተሰበሰቡ ✞ #ጊዜ_...
#ወልá‹ĩáŠĒ_ይáŒŧውአáŠĒ         ወልá‹ĩáŠĒ ይáŒŧውአáŠĒ(áĒ) ውáˆĩተ ሕይወá‰ĩ ወመንግáˆĨተ ክá‰Ĩር (áĒ) ልጅáˆŊ ይጠáˆĢáˆģል(áĒ) ወደ ሕይወá‰ĩና ወደ ክá‰Ĩር መንግáˆĨá‰ĩ(áĒ) ...
✞áŠĨኔ ግን በምህረá‰ĩህ á‰Ĩዛá‰ĩ✞ áŠĨኔ ግን በምሕረá‰ĩህ á‰Ĩዛá‰ĩ áŠĨኔ ግን በይቅርá‰ŗህ á‰Ĩዛá‰ĩ ወደ ቤá‰ĩህ áŠĨገá‰Ŗለሁ አመልክሃለው áŠĨዘምርልሃለሁ በሕይወቴ ዘመን...
💍የጋá‰Ĩá‰ģ ዓላማ💍 ይህ ምáˆĩáŒĸር á‰ŗላቅ ነው áŠĨንá‹ŗለው መáŒŊሐፍ መኝá‰ŗውም ንጹሕ የለበá‰ĩም áŠĨá‹ĩፍ(áĒ) áŠĨውቀá‰ĩን áŒĨበá‰Ĩን ጎናáŒŊፎá‰ĩ ለአá‹ŗም ሁሉን áŠĨንዲገዛ አሰል...