አዘጋጅ ®
@elshio_owner
💞ፍቅር ያሸንፋል💕
ክፍል አንድ (1)
✍️...
እውነተኛና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክውድ ጓደኞቼ ጥሩ ያልኩትን አስተማሪ የፍቅር ታሪክ ለናንተ በሚመች መልኩ ማቅረብ ጀምሬአለው እንደምትወዱት አልጠራጠርም እንድታነቡልኝ እጋብዛለሁ፡፡🙏
ያስሚን ሙሐመድ እባላለው የተወለድኩት አማራ ክልል ወሎ ክፍለ
ሀገር ደሴ የምትባል ከተማ ላይ ነው ታድያ ደሴ እናትና አባቴ ጋር ስኖር ደስተኛ ነበርኩ ቤተሰቦቼ ሀብታም ባይባሉም ሌላ ልጅ ስለሌላቸው እኔን በደምብ ይንከባከቡኛል ትምህርትም በግዜ ነበር የገባሁት ፡፡ የልጅነት ህይወቴ ብዙም የተለየ ነገር ስለሌለው ወደ የፍቅር
ህይወቴ ልግባላቹ ልክ በ16 አመቴ የ9ኛ ክፍል ተማሪ ሆንኩ ይሄኔ ነበር የኔም የሰውነት ቅርፅ ለውጥ ያሳየው ከዛም ባለፈ እኔ በባህሪዬ ዝምተኛ ስሆን ከሰውነት ቅርፄ ጀምሮ የብዙሃን ሠው ቀልብ የምስብና በሠዎች አስተያየት ውብ የምባል አይነት ሴት ነበርኩ ፡፡
እኔ የእስልምና ሀይማኖት ተከታይ ነኝ ሆኖም ብዙ የክርስትና እምነት ተከታይ ጓደኞች አሉኝ፡፡ እናም ከነሱጋ ነበር አብዛኛውን ጊዜዬን የማሳልፈው የነበረው አንድ ዓመቱን እንዲ ሆኘ ነበር ያሳለፍኩት አዲሱን ዓመት ተቀብለን ክላስ ጀምረን መማር ጀመርኩ። ከዕታት ባንዱ ቀን ክፍላችን ውስጥ እንግዳ ፊት አየሁ ለኔ ለየት ያለብኝ ደግሞ ልክ ሳየው መደንገጤ ነበር ሁሌም በምናቤ
የምስለው አይነት ወንድ ከለሩ ቸኮሌት ቁመቱ እረዘም ያለ ፀጉሩ የሚያምር ፍሪዝ አስተያየቱ ልብ የሚሰርቅ ባጠቃላይ ውብ ቃሉ የሚያንስበት ልጅ ነው በርግጥ የኔ የተገናኘን ቀን እድሜዬ 17 አካባቢ ነበር እሱ ደግሞ በግምት 19 አካባቢ ይሆነል እኛ ክፍል የገባው ደግሞ ለምን እንደሆነ ለማጣራት ወደ ክፍል ገብቼ ሳይ ለታናሽ እህቱ እቃ ለመስጠት ነበር የመጣው ፡፡ ስሙ ካሌብ ይባላል የግቢያችን የ12ኛ ክፍል ተማሪ ነው ያን ቀን ልቤን እንደወሰደ እስካሁን አልመለሰልኝም እሱን ካየሁበት ቅፅበት ጀምሮ መሉ ሀሳቤ እሱ ነው፡፡ እናም እሱን ለማግኘት ስል መጀመርያ ማድረግ ያለብኝ እህቱን ሜሮንን ተዋወኳት ከሜሪ ጋር በጣም ተግባባን ግን ወንድሟን ማፍቀሬን ፈፅሞ አልነገርኳትም ሁሌም ስናወራ በጣም የማፈቅረው ወንድ
እንዳለ ስነግራት ሁኔታዬን አይታ ታድሎ ያስሚኔ ትለኛለች፡፡ ካሌብ መረብ ኳስ መጫወት ይወዳል ለዛም እሱን ለማየት ከሜሪ ተደብቄ ኳስ ሜዳ እሄድና አየዋለሁ ሁሌም እሱ የሚገኝበት ቦታ እሄዳለው ሳየው ደስስ ይለኛል ካላየሁት ግን እናቷን እንዳጣች ጥጃ ያረገኛል
እነጫነጫለሁ፡፡ ግን አንድ ነገር አውቃለው ከካሌብ ጋር የሀይማኖት ልዩነት አለን ቤተሰቦቼ ደግሞ በሀይማኖት ድርድር አያውቁም ያም ማለት ካሌብን ማፍቀር እንጂ የኔ ማድረግ አልተፈቀደልኝም፡፡ ይህ በንዲህ እንዳለ በተከታታይ 3ቀን ካሌብዬ ትምህርት ቤት ቀረ እሱን ሳላይ ስቀር 3ቱ ቀን አመታት ሆነብኝ ያለኝ ምርጫ ስበብ ፈልጌ ሜሮን ቤታቸው እንድትወስደኝ ዘዴ ማፈላለግ ነበር እናም ተሳክቶልኝ መፅሀፍ ፈልጌ በሚል ሰበብ ከሜር ጋር ቤታቸው ሄድኩ ቤታቸው ያምራል የግቢው በር ተከፍቶ ስንገባ የኔ ካሌብዬ በረንዳው ላይ ቁጭ ብሏል ልክ ሳየው ደርቄ ቀረው ሜሪም ግራ ገብቷት ችግር አለ ያስሚኔ አለችኝ ይሄኔ ነበር ማፍጠጤ የታወቀኝ ካሌብም የታላቅነት ስሜቱ እያንፀባረቀበት ኦኦኦኦኦ ሜሪዬዬ ቆኝጂዬ ጓደኛ አለችሽ አላት እንደሱ ሲላት ይበልጥኑ የደስታ ሲቃ ተናነቀኝ በሱ ደግሞም በምወደው ሰው በካሌብ አፍ ቆንጆ መባሌን ማመን አቃተኝ.......ይቀጥላል
✎ ክፍል 2 ይቀጥላል... አንብበው ሲጨርሱ LIKE ❤️ & Share✅ በማድረግ ታሪኮቹን በፍጥነት ያግኙ።
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
ቶሎ እንዲ🀄️ጥል Like ያድርጉ