ያሲን ኑሩ️️ YASIN NURU


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Blogs


የ ያሲን ኑሩ ሐዲሶች
Yasin Nuru
"ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራውን ሰው ያህል አጅር ያገኛል" ረሱል (ﷺ)
"የበጎ ስራ ምላሹ በጎ እንጂ ሌላ አይደለም "  
የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሰራ ሰው ያገኘዋል :>> { አል -ዘልዘለህ 7}
This is not official
ለአስተያየት👇👇
@Hasabbbbot

ሀዲሶችን ከፈለጋችሁ👇👇
@yasin_nuru_hadis

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Blogs
Statistics
Posts filter


ስድስቱ የተውበት መስፈርቶች

በህይወታችን ብዙ ጊዜ ወንጀሎችን እንፈፅማለን። አላህ ያደለው በወንጀሉ አላህ ፊትእንዳይጠየቅ ተውበት ማድረግን ያስባል። ግን ስንቱ ነው ተውበቱ መስፈርቶችን የሚያሟላ እንዲሆን የሚጨነቀው?  እራሳችንን በሚገባ ጠይቀን እናውቃለን?!

ለመሆኑ መስፈርቶቹን ምን ያህሎቻችን በሚገባ እንለያቸዋለን?  ለማያውቁ ጥቆማ፣ ለሚያውቁ ማስታወሻ ይሆን ዘንድ እጠቅሳለሁ። የተውበት መስፈርቶች ስድስት ናቸው። እነሱም:-

→1 ኢኽላስ: – አላህን ብቻ በማሰብ ነው ተውበቱን ማድረግ ያለበት።  አንድ ሰው ወንጀልን የሚተወው ዱንያዊ ጥቅሞችን አስቦ ከሆነ የመጀመሪያውን የተውበት መስፈርት አላሟላም፡፡

→2 ወንጀሉን ማቆም:– አንድ ሰው የሚፈፅመውን ወንጀል ባላቋረጠበት ሁኔታ "ቶብቻለሁ" ቢል ቀልድ ነው የሚሆነው። ስለዚህ ተውበት ያሰበ ሰው ጥፋቱን በቀጠሮ ሳይሆን ወዲያው ሊያቆም ይገባል።

→3 ወደ ጥፋቱ ዳግም ላይመለሱ ቁርጠኛ ውሳኔ ላይ መድረስ። አንድ ሰው ከወር ቡሀላ እንደሚመለስ እያሰበ ረመዳን ሊገባ ሲል አንድን ወንጀል ቢተው መስፈርት ስላላሟላ ተውበት አድርጓል ማለት አይቻልም።

→4 በወንጀሉ መፀፀት። ሰውየው ሲፈፅመው በቆየው ወንጀል ላይ ደንታ ቢስ ከሆነ ተውበቱ የእውነት አይደለም።  ፀፀቱ "ሰው ምን ይለኛል" ወይም "ክብሬ ጎደፈ" በሚል ሳይሆን የጌታውን ህግ በመጣሱ ሊሆን ይገባል፡፡ለምሳሌ ብዙ ሰዎች ዝሙት ፈፅመው ጌታቸው ዘንድ ካለው ሂሳብ ይልቅ ዱንያ ላይ ያለው የሰው ወሬ ሲያስጨንቃቸው ይፀፀታሉ።
እንዲህ አይነት ፀፀት የተውበትን መስፈርት አያሟላም። ይልቅ ከዛሬው የበዛ ህዝብ ፊት ነገ በአኺራ መዋረድ ከመምጣቱ በፊት ትክክለኛውን ፀፀት እዚሁ ልናስገኝ ይገባል።

→5 ተውበቱ ወቅቱን የጠበቀ መሆን፡፡ይህም ማለት ሞት አፋፍ ላይ ከመድረሱ በፊት እና ፀሀይ በመጥለቂያዋ ከመውጣቷ በፊት መሆኑ ነው።

→6 ወንጀሉ የሰው ሐቅ መግፋት ከሆነ ሐቁን ሊመልስ ወይም ይቅርታውን ሊያገኝ
ይገባል። ወይም ኢስቲግፋርና ኸይር ስራ ሊያበዛ ይገባል፡፡
         🍂    🍂     🍂

አላህ ከመሞታችን በፊት ንፁህ የሆነች ተውበት ይወፍቀን።

ጥራት ይገባው ሰዎችን ለተውበት የገጠመ እግሮችንም በመንገዱ ላይ ያፀና ካንተ ውጭ አስጠጊ የለኝም ጌታየ በይቅርታህ ከቅጣትን እጠበቃለሁ  ብትቀጣኝ በፍትህ ብትምረኝ አንተ ለሱ የተገባህ ነህ።

   አቤት የተውበተኞች ደስታ በአላህ ፍቅር። አላህ ተውበት አድራጊዎችን ይወዳል ተጥራሪዎችንም ይወዳል።

  አላህ ሆይ አንተ ጌታየ ነህ ካንተ ውጭ አምላክ የለም ፈጠርከኝም ባሪያህ አድርገህ እኔ የቻልኩትን ያክል በትዕዛዛቶችህ ላይ ነኝ ከሰራሃው መጥፎ ነገር ሁሉ ባንተ እጠበቃለሁ

በኔ ላይም በዋልከው ፀጋ እውቅና እሰጣለሁ ወንጀሌንም እናዘዛለሁ ማረኝ!! ካንተ ውጭ ወንጀል የሚምር የለምና።

እንቻኮል ወደ አላህ አላህ ይባርካችሁ

ሼር ይደረግ ለመልካም ነገር እንሽቀዳደም

@yasin_nuru   @yasin_nuru


አስገራሚ ቂሷ!

ሱባሀን አሏህ መጨረሻ ሲያምር!!

ዒሻእ ሰላት ተሰግዶ ጥቂት ደቂቃዎች እንዳለፉ አንድ ወጣት ከወደ ውጭ በኩል ይጮህና የመስጅዱን ጀማዓ ይጠራል።

ሰዉ ግር ብሎ ልጁን ተከትሎ ሲወጣ አንድ እድሜው 20 ማይሞላ ልጅ ባቡር ገጭቶት አካሉን ለሁለት ከፍሎታል (ሱብሀን አላህ) ግን ሩሁ አልወጣችም ሊሞት ጣር ላይ ነበር በዚህ ሁኔታ ላይ ሳለ ከተሰበሰቡት አንዱ ጎንበስ ብሎ የልጁን ጭንቅላት በእግሩ ላይ አስቀመጠው።

"ላ ኢላሀ ኢለላህ በል... ላ ኢላሀ ኢለላህ በል"
ይለውም ጀመር... ልጁ ሩሁ ልትወጣ ጥድፊያ ላይ ናት ይፈራገጣል...እናም የአላህ ተውፊቅ ሆነና ልጁ " ላ ኢላሀ ኢለላህ ሙሀመዱን ረሱሉላህ" እንዳለ ሰውነቱ ቀዘቀዘ ትንፋሹ ዳግም ላይመለስ ተቋረጠ ነፍሱም ወደ
ፈጣሪዋ አመራች።

(ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን)

ተባብረው ልጁን ሰዎች ወደሚበዙበት አካባቢ ወሰዱት ቤተሰቡን ለማፈላለግ... ሌሊቱ ጨለማማ ነበር ፅልመቱ ያስፈራል ብርሀናማ ቦታ ሁነው ልጁን የሚገልፁ ነገሮችን ልብሶቹን በመጠቀም ቤተሰቡን ያፈላልጉ ጀመር...

ድንገት በቦታው ከነበሩት አንዱ የአስክሬኑን እጅ ይዞ ፦"ይህ ልጅ ክርስቲያን ነው አንገቱ ላይ መስቀል ይኸው..." እያለ ጮኸ። ሁሉም ግራ ተጋባ "ይህ ልጅ በተውሂድ ነው የሞተው ታድያ እኛው በሙስሊሞች መቃብር እንቅበረው ወይስ ለቤተሰቦቹ አስረክበን በክርስቲያኖች መቃብር ይቅበሩት?" እያሉ ይወያዩ ጀመር..

ቤተስቦቹ ጋ ለመውሰድ ይወስኑና ተሸክመውት በእንባ ወደቤተሰቦቹ ጉዞ ጀመሩ። ልጁ መስጅድ አካባቢ ስለሞተ አስክሬኑን ያጀቡት ሁሉም ሙስሊሞች ነበሩ።

ተሸክመውት ከአከባቢው ሲደርሱ አባቱም የልጁን ማረፍ ሰምቶ ሲገሰግስ አገኙት አባትየውም ሲያያቸው ተንሰቅስቆ ያለቅስ ጀመር (እንዴት አያልቅስ ተስፋ ይሆነኛል፣ረዳት ይሆነኛል፣መመኪያ ይሆነኛል ብሎ የሚጠብቀው ልጁ ከሰዎች ትከሻ ላይ ተጭኖ ሲመጣለት...) ልጁን አቅፎ አምርሮ ያለቅሳል...

ይህ ሁሉ ሙስሊም ልጁን ተሸክሞ መምጣቱ ያስገረመው አባት እያለቀሰ ለተሰበሰበው ሰው እንዲህ አላቸው፦ "ይህን ስነግራችሁ በህፍረት ነው...ልጄ እንዲው ቁርአን መስማት ይወዳል። አዎ ልጄ በርግጥ ክርስቲያን ነው ነገር ግን የሙስሊሞችን ቁርአን መስማት ይወዳል። ዘውትር ክፍሉ ስገባ ኢርፎን/earphone ከጆሮው አያለው...

"ምንድነው ምትሰማው?" ስለው "ዘፈን ነው"ይለኛል ከጆሮው ነቅዬ ሳዳምጥ ግን ቁርአን ነው። በጣምም እቆጣው ነበር ይሄን መስማት ካልተውክ እገድልሀለሁ እያልኩ ሁሌም አስጠነቅቀውም ነበር... "ባባ እኔን መግደል አትችልም ቁርአን መስማትም አትከልክለኝ" ይለኝ ነበር..

በቦታው ያሉት ሁሉ እየተያዩ ይለቃቀሱ ነበር። "ልጅህ እኮ በሸሀዳ ነው የሞተው" ብለው ሲነግሩት...

ያ የልጁ መሞት ቅስሙን የሰበረው አባት ያ የልጁን ሬሳ አቅፎ ቁጭ ያለው አባት እንባውን እያረገፈ ልጁን በስስት እያየ እንዲህ አለ፦ "ልጄ በመሰከረው ነገር እኔም እመሰክራለሁ ከአላህ ሌላ አምላክ እንደሌለ ሙሀመድም የ አላህ መልዕክተኛ እንደሆኑ እመስክራለሁ"

ከዚያም ሁሉም ጀማዓ ጀናዛውን ይዘው ወደ ሙስሊሞች መቃብር "ላ ኢላሀ ኢለላህ... ላ ኢላሀ ኢለላህ.... ላ ኢላሀ ኢለላህ" እያሉ አጅበው ወስደው ቀበሩት።
__
ሙስ
ሊም ሆኖ ኖሮ በኩፍር መሞትም አለና ካፊር ሆኖ ኖሮ በተውሂድ መሞትም አለና "አላህ ካቲማችንን ያሳምርልን"

ምንጭ፦ ﻫﻨﺎ ﺃﺑﻨﺎﺀ ﻋﺎﺋﺸﺔ ﺃﻡ ﺍﻟﻤﺆﻣﻨﻴﻦ !!

@yasin_nuru     @yasin_nuru

5.3k 0 97 55 269

የመሬት መንቀጥቀጥ በድጋሚ ተከስቷል

ዛሬ ጠዋት ከደቂቃዎች በፊት 1:38 በአዋሽ ከተማ ባለፈው ሳምንት ከተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ ጨመር ያለ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን እየተነገረ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪ በአደስ አበባ በአዳማ ከተማም ተመሳሳይ ንዝረት መሰማቱን በርካታ ሰዎች እየገለፁ ይገኛል።

ሱራ99: 1-----8
إِذَا زُلْزِلَتِ الْأَرْضُ زِلْزَالَهَا

ምድር (በኀይል) መንቀጥቀጥዋን በተንቀጠቀጠች ጊዜ፤

وَأَخْرَجَتِ الْأَرْضُ أَثْقَالَهَا

ምድር ሸክሞችዋን ባወጣችም ጊዜ፤
وَقَالَ الْإِنسَانُ مَا لَهَا

ሰውም ምን ኾነች? ባለ ጊዜ፤
يَوْمَئِذٍ تُحَدِّثُ أَخْبَارَهَا

በዚያ ቀን ወሬዎችዋን ትናገራለች፡፡
بِأَنَّ رَبَّكَ أَوْحَىٰ لَهَا

ጌታህ ለእርሷ በማሳወቁ ምክንያት፡፡
يَوْمَئِذٍ يَصْدُرُ النَّاسُ أَشْتَاتًا لِّيُرَوْا أَعْمَالَهُمْ

በዚያ ቀን ሰዎች ሥራዎቻቸውን (ምንዳዋን) እንዲያዩ ይደረጉ ዘንድ (እንደየሥራቸው) የተለያዩ ኾነው (ከመቆሚያው ስፍራ) ይመለሳሉ፡፡
فَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ خَيْرًا يَرَهُ

የብናኝ ክብደት ያክልም መልካምን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡
وَمَن يَعْمَلْ مِثْقَالَ ذَرَّةٍ شَرًّا يَرَهُ

የብናኝ ክብደት ያክልም ክፉን የሠራ ሰው ያገኘዋል፡፡

@yasin_nuru @yasin_nuru

6.2k 0 60 33 237

ما هي صلاة التوبه

የተውበት ሶላት ምንድነው?

وكيف نُصَلِّيها ؟

እንዴትስ ነው ምንሰግደው?

የተውበት ሶላት ማለት

صلاة التوبه هي الصلاة التي يؤديها المسلم بعد الذنب ...

አንድ ሙስሊም ከወንጀል ቡሃላ የሚሰግደው ሶላት ነው።

ለወንጀል መማሪያ ሰበብ ይሆናል በአላህ ፍቃድ

وتكون سببا في غفران الذنب
< < باذن الله > >

ሶላተ አተውባ(ወደአላህ የመመለሻ) ሶላት

صلاة التوبة
ركعتان
2ረከዐ ነው

وذلك بعد أن يتطهر المسلم كجاهزيتة الصلاة المفروضة

ከዛም አንድ ሙስሊም ጦሀራ እንሚሆነው ልክ ለዋጅብ ሶላት እንደሚዘጋጀው ይዘጋጃል።

በመጀመሪያው ረከዐ ፋቲሃ ከተቀራ ቡሃላ ከሱረቱል ኢምራን 135ተኛውን አያ መቅራት።

وَالَّذِينَ إِذَا فَعَلُوا فَاحِشَةً أَوْ ظَلَمُوا أَنفُسَهُمْ ذَكَرُوا اللَّهَ فَاسْتَغْفَرُوا لِذُنُوبِهِمْ وَمَن يَغْفِرُ الذُّنُوبَ إِلَّا اللَّهُ وَلَمْ يُصِرُّوا عَلَى مَافَعَلُوا وَهُمْ يَعْلَمُونَ )

በ2ለተኛው ረከዐ ሱረቱል ፋቲሃን መቅራት ከዛ ከታች ያለውን ከሱረቱ ኒሳእ 110ረኛውን አያ መቅራት።

سورة النساء
وَمَن يَعْمَلْ سُوءًا أَوْ يَظْلِمُ نَفْسَهُ، ثُمَّ يَسْتَغْفِرِ اللَّهَ يَجِدِ اللَّهَ غَفُورًا رحِيمًا )

ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል قال رسول الله ﷺ

ما من عبد يذنب ذنباً فيحسن الطهور ثم يقوم فيصلي ركعتين ثم يستغفر الله إلا غفر له

አንድ ባሪያ ጦሀራውን አሳምሮ ከዛም ተነስቶ ሁለት ረከዐ ሰግዶ አላህን ይቅርታ ከጠየቀው አላህ ይቅር ይለዋል።

በመጨረሻም

وا في الاخير

ያአላህ ወዳንተ ከተመለሱት ከጦሀራዎች አድርገን።

اللهم اجعلنا من التوابين المتطهرين
سبحان الله وبحمده سبحان الله العظيم

ሱብሃነላህ ወቢሃምዲህ
ሱብሀነላሁ ልዐዚም

ወንጀሉ ትንሸም ቢሆን ትልቅ አዲስም ይሁን የቆየ ይህን የተውበት ሰላት በማንኛውም ሰአት መስገድ ይችላል።

ወቢላሂ ተውፊቅ ወሰላሙአለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱህ።

@yasin_nuru @yasin_nuru

6.9k 0 158 18 160

🔰 የሙስሊሞች መጀመሪያ 🔰

በአላህ ፈቃድ ሙስሊም ያልሆኑ ግለሰቦች የመጀመሪያ ሙስሊም ነቢዩ ሙሀመድ ሰላሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ናቸው ብለው የሚጠቅሷቸው ሹቡሃ እናያለን።
የሚያነሱት አንቀፅ👇

قُلْ إِنَّنِي هَدَانِي رَبِّي إِلَىٰ صِرَاطٍ مُّسْتَقِيمٍ دِينًا قِيَمًا مِّلَّةَ إِبْرَاهِيمَ حَنِيفًا ۚ وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ
📚 6፥161 *«እኔ ጌታዬ ወደ ቀጥተኛው መንገድ ትክክለኛን ሃይማኖት ወደ እውነት አዘንባይ ሲኾን የአብርሃምን መንገድ መራኝ፥ እርሱም ከአጋሪዎቹ አልነበረም» በል"*፡፡

قُلْ إِنَّ صَلَاتِي وَنُسُكِي وَمَحْيَايَ وَمَمَاتِي لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ
6፥162 «ሶላቴ፣ መስዋዕቴም፣ ሕይወቴም፣ ሞቴም ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ነው» በል፡፡

لَا شَرِيكَ لَهُ ۖ وَبِذَٰلِكَ أُمِرْتُ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُسْلِمِينَ

6:163 «ለእርሱ ተጋሪ የለውም፡፡ በዚህም (በማጥራት) ታዘዝኩ፡፡ እኔም የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ» (በል)፡፡

➰ የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ *በል" የሚለውን በመያዝ የመጀመሪያ ሙስሊም ነቢዩ ሙሀመድ ናቸው በማለት ይሟገታሉ።

ለዚህ ሹቡሀ መልሳችን

➤➤ በተጠቀሰው አንቀፅ ላይ ነቢዩ ዓለይሂ ሰላቱ ወሰላም * የአብርሃምን መንገድ መራኝ*፥ እርሱም ከአጋሪዎቹ አልነበረም» በል"* በማለት የኢብራሂምን ሃይማኖት እንዲከተሉ ታዘዋል።
የኢብራሂም ሃይማኖት ምን ነበር ከተባለ 
ما كَانَ إِبْرَاهِيمُ يَهُودِيًّا وَلَا نَصْرَانِيًّا وَلَـٰكِن كَانَ حَنِيفًا مُّسْلِمًا وَمَا كَانَ مِنَ الْمُشْرِكِينَ

📚 (ሱረቱ አሊ-ዒምራን - 67)
ኢብራሂም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም፡፡ ግን ወደ ቀጥተኛው ሃይማኖት የተዘነበለ ሙስሊም ነበረ፡፡ ከአጋሪዎችም አልነበረም፡፡

➰ ነቢዩ ሙሀመድ ዐለይሂ ሰላቱ ወሰላም የነቢዩ ኢብራሂም ሃይማኖት(እስልምናን) እንዲከተሉ ከታዘዙ በእስልምና የቀደማቸው ነቢዩ ኢብራሂም እና ሌሎች ነቢያት ስላሉ ነቢዩ ሙሀመድ የመጀመሪያ ሙስሊም ሊሆኑ አይችሉም።

እንደዛ ከሆነ ታዲያ ነቢዩ  የሙስሊሞች መጀመሪያ ነኝ» (በል) ተብለው የታዘዙትስ  ምን ማለት ነው?? ከተባለ
➤➤➤➤እዚህ አንቀፅ ላይ የተፈለገው "أولية الزمانية" አንፃራዊ መጀመሪያነት  ነው።
ማለትም ከተላኩበት ህዝብ አንፃር የመጀመሪያ ናቸው።
ቀደምት ሰለፎቻችንም የተረዱት እንዲህ ነው።

📚 ተፍሲር ኢብኑ ከሲርአልበገዊይአጥጠበሪይ..  ሱራ 6:163 ላይ ታላቁ ሙፈሲር ቀታዳህ ረሂመሁላህ" መጀመሪያነቱ የተፈለገው ከዚህ ከተላኩበት ኡመት(ህዝብ) አንፃር ነው" በማለት ፈስሮታል

📚 ተፍሲር አልጀላለይን እና አስሰዕዲይም ከዚህ ኡመት(ህዝብ) ማለት ነው በማለት ፈስረውታል።

➤➤ ልክንደዚነሁ ሙሳ ዐለይሂ ሰላምም የምዕመናን መጀመሪያ ተብሏል
لَمَّا جَاءَ مُوسَىٰ لِمِيقَاتِنَا وَكَلَّمَهُ رَبُّهُ قَالَ رَبِّ أَرِنِي أَنظُرْ إِلَيْكَ ۚ قَالَ لَن تَرَانِي وَلَٰكِنِ انظُرْ إِلَى الْجَبَلِ فَإِنِ اسْتَقَرَّ مَكَانَهُ فَسَوْفَ تَرَانِي ۚ فَلَمَّا تَجَلَّىٰ رَبُّهُ لِلْجَبَلِ جَعَلَهُ دَكًّا وَخَرَّ مُوسَىٰ صَعِقًا ۚ فَلَمَّا أَفَاقَ قَالَ سُبْحَانَكَ تُبْتُ إِلَيْكَ وَأَنَا أَوَّلُ الْمُؤْمِنِينَ
📚 ሱራ 7:143
ሙሳም ለቀጠሯችን በመጣና ጌታውም ባነጋገረው ጊዜ፡- «ጌታዬ ሆይ! (ነፍስህን) አሳየኝ ወደ አንተ እመለከታለሁና» አለ፡፡ (አላህም)፡- «በፍጹም አታየኝም ግን ወደ ተራራው ተመልከት፡፡ በስፍራውም ቢረጋ በእርግጥ ታየኛለህ» አለው፡፡ ጌታው ለተራራው በተገለጸ ጊዜ እንኩትኩት አደረገው፡፡ ሙሳም ጮሆ ወደቀ፡፡ በአንሰራራም ጊዜ «ጥራት ይገባህ፡፡ ወዳንተ ተመለስኩ፡፡ እኔም (በወቅቱ) የምእምናን መጀመሪያ ነኝ» አለ፡፡

☝️እዚህ አንቀፅ ላይ ሙሳ ዐለይሂ ሰላም የአማኞች መጀመሪያ መባሉ ከነኢብራሂም ከነ ኑህ በፊት ነበረ ወይም የመጀመሪያ አማኝ እሱ ነው ማለት ነውን??
በፍፁም አይደለም የተፈለገበት ከተላከበት ህዝቦቹ አንፃር የመጀመሪያ አማኝ ነው።
📚 ኢብኑ ከሲር ሱራ 7:143 ላይ ታላቁ ሙፈሲር ሶሀቢይ ኢብኑ ዐባስ እና ሙጃሂድ "" ከተላከበት ከእስራኤል ልጆች ነው"" በማለት ፈስረውታል
📚 አልበገዊይም ከሙጃሂድና ከሱድይ በመዘገብ፣ አጥጠበሪይም ከሙጃሂድ ከህዝቦቼ የመጀመሪያ አማኝ ማለት ነው በማለት ፈስረውታል።
📚 ተፍሲሩል ጀላለይን ሱራ 7:143 ላይ ከዘመኔ ሰዎች የመጀመሪያ አማኝ ነኝ ማለት ነው በማለት ተርጉመውታል

➤➤ በሙሳ ዐለይሂ ሰላም ዘመን የነበሩ ደጋሚዎችም የመጀመሪያ አማኝ ነን ብለዋል

إِنَّا نَطْمَعُ أَن يَغْفِرَ لَنَا رَبُّنَا خَطَايَانَا أَن كُنَّا أَوَّلَ الْمُؤْمِنِينَ

«እኛ የምእምናን መጀመሪያ በመኾናችን ጌታችን ኀጢአቶቻችንን ለእኛ ሊምር እንከጅላለን፡፡»
ሹዐራእ 26:51
ይህ ማለት ከሙሳ በፊት አምነው ነበር ማለት ሳይሆን ከህዝቦቻቸው አንፃር ነው
📚 ተፍሲሩል ጀላለይን ሱራ 26:51
📚 ተፍሲሩል ሙየሰር ሱራ 26:51

🌺 ልክንደዚሁ ነቢዩ ሰላሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የሙስሊም መጀመሪያ መባላቸው ከተላኩበት ህዝብ አንፃር ነው።

ሼር አርጉ ለሂዳያ ሰበብ ሁኑ

@yasin_nuru @yasin_nuru


≈••የጁምአ ቀን••≈

ነብዩ(ሰ.አ.ወ) ስለ ጁምአ ቀን ታላቅነት ሲናገሩ

የጁምአ ቀን የቀኖች ሁሉ ንጉስ ነው እነዚህ 5 ነገሮች የጁምአ ቀን ተከስተዋል ብለዋል።

1አላህ አደምን የፈጠረው በጁምአ ቀን ነው፤

2 አደም ከጀነት የወጡትም በጁምአ ቀን ነዉ፤

3 አደም የሞተውም በጁምአ ቀን ነው፤

4 ቂያማ የምትቆመው በጁምአ ቀን ነው፤

5 በጁምአ ቀን የሆነች ሰአት አለች።

አንድ የአላህ ባሪያ አላህን የጠየቀውን ነገር ይሰጠዋል.ያችን ሰአት ካገኛት ሀራም ነገር እስካልጠየቀ ድረስ አላህ ይቀበለዋል።

6.2k 0 71 24 126

🚫ይህን ደኢፍ ሐዲስ ከማሰራጨት ተቆጠቡ!!

"📌ነብዩ ሶለሏሁ አለይሂ ወሰልም አንድ ግዜ #ለአሊይ እንዲህ አሉት:—
አንተ አልይ ሆይ #ከመተኛትህ በፊት እነዚህን #አምስት ነገሮች ተግብር ፡፡
1, ስትተኛ አራት ሺህ ድናር #ሰደቃ ስጥ 

2, ሙሉ ቁርአን #አኽትም

3, #ለጀነት ዋጋዋን ክፈል፡፡

4, ሁለት ሰወች #አስታርቅ

5, ከዚያም አንድ ጌዜ #ሀጅ አድርገህ ተኛ አሉ ፡

✅ዐልይ ረ.ዐ አሉ ያረሱለላህ እሄን #በአንድ ለሌት እንዴት ማድረግ ይቻላል ? እንዴት ነው ማድረግ  የምንችለው ? ከዚያም ረሱል ሰ.ዐ.ወ የሚከተለው ተናገሩ፡፡

1) 4ጌዜ ሱረቱል #ፋቲሓ አልሐምዱሊላሂ የሚለውን የቀራ ከ4000 ድናር #ሰደቃ ጋር እኩል ነው 

2), ሶስት ጌዜ ሱረቱል #ኢኽላስ  የቀራ ሙሉ ቁርአን $እንዳከተመ ይቆጠርለታል ፡፡

3), #ላሃውላወላቁወተ ኢላ ቢላህ አልዪል አዚምን ሶስት ጌዜ ያለ #ጀነት ዋጋውን ከፍሏል 

4), አስር ጌዜ #አስግፉርላህ ያለ ሰው ሁለት ሰዎችን #እንደማስታረቅ

5), አራት ጌዜ #ሸሀዳ የደረገ ሰው አንድ ጌዜ #ሀጅ እንዳደረገ ነው፡፡ ከዛም ዐልይ ረ.ዐ ከአልጋ መሄድ #በፊት አደርገዋለሁ አሉ።"

📌ይህ ሀዲስ ትክክለኛነቱ እንዴት ነው⁉️

✅መልስ ✅
✅ይህ ሀዲስ መሰረት የሌለው #የተቀጠፈ ሀዲስ ነው። በየትኛውም የሀዲስ ኪታብ ላይ #የሌለ በመሆኑ ይህን ሀዲስ #መሰራጨትም ሆነ ማስተላለፍ አይቻልም‼️

♻️ምንጭ: 📚የሳኡዲ የዒልም ጥናትና የፈትዋ ቋሚ ኮሚቴ እና 📚ኢብን ኡሰይሚን ረሂመሁሏህ

@yasin_nuru @yasin_nuru

7.8k 0 89 40 157

የለሊት ሶላት እና የአሰጋገድ ሁኔታው‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
✍ሶላት በእስልምና የመጀመሪያውና ዋነኛው
አላህ በባሮቹ ላይ የደነገገው ተግባር ነው።
||
የሌሊት ሶላት አንዱ የተረጋገጠ ሱና እና ትልቅ ፋይዳ ያለውና ከምርጥ ኢባዳዎች አንዱ ነው ከሌሊቱ መጀመሪያ ጀምሮ እስከ ሱብሒ ሶላት ድረስ ከመስገድ በፊት በመጨረሻው አንድ ሶስተኛው ላይ ቢገኝ ይመረጣል።
*
የለሊት ሶላት እና አሰጋገዱ:
✔️ በየሁለት ረከዓው እያሰላመቱ የቻሉትን የፈለጉትን ያክል ይሰግዱና መጨረሻ ላይ አንድ ረከዓ ብቻ በመጨመር በዊትር ያጠናቅቃሉ።
*
የ"ለይል" (ለሊት) ሶላት ተብሎ በውስጥ "ተነይቶ" (ታስቦ) ፋቲሓ ይቀራል።
ከፋቲሓ በኋላ የቻሉትን ሱራ ይቀራል። "ሓፊዝ የሆነ ስው በሒፍዙ አርዝሞ ይቀራል፤ "ሓፊዝ ያልሆነ ስው የሚችለውን ይደጋግማል ካልሆነ ደግሞ ቁርኣን ይዞ መቅራት ይችላል።

በዚህ መልኩ ሁለት ረከዓ ከሰገዱ በኋላ - እንደ "ቀብልያ"፣ "ባዕዲያ" ሱንና ሶላቶች ማለት ነው - አተሕያቱ ቀርተው ማሰላመት ነው።
°
✅ ከዛም በኋላ በዚሁ መስረት የቻሉትን ያክል ሁለት ሁለት ረከዓ እየሰገዱ አስርም ይሁን፣ አስራ ሁለትም፣ አስራ አራትም፣ አስራ ስድስትም፣ ሃያ እና ሃያ ሁለትም ሰግደው  መጨረሻ ላይ አንድ ነጠላ ቁጥር በመስገድ ዊትር አድርገው ማጠናቀቅ።
ዊትር ማለት ደግሞ ኢ—ተጋማሽ ቁጥሮች ማለት ነው (1፣3፣5፣7...) ማለትም 1 ረካዓ ሰግደው ተሽሁድን በመቅራት ሶላቱን ዊተር አድርገው ማጠናቀቅ ይችላሉ።
:
እንደው ጠቅለል ሲደረግ ሶላተል-ለይል ማለት ከኢሻ በኃላ እስከ ፈጅር ድረስ ባለው ወቅት ውስጥ የሚሰገድ፣ ቁርአን በዛ ተደርጎ የሚቀራበት ትርፍ የሆነ የሌሊት ሶላት ሲሆን ይህ ሶላት ተራዊህ ወይም ተሀጁድ ተብሎ ሊጠራ ይችላል።
:
ለዛም ነው የሌሊቱ መጀመሪያም ይሁን መካከል ይሁን መጨረሻ ላይ መስገድ ቢቻልም በላጩ ግን የሌሊቱ የመጨረሻው አንድ ሶስተኛ ላይ መስገድ በላጭ ነው።
*
ምክንያቱም በዚህ ወቅት በሀዲስ እንደተገለፀው አላህ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ የሚወርድበትና "ማን ነው የሚለምነኝ የምቀበለው⁉️ ማን ነው የሚጠይቀኝ የምሰጠው⁉️  ማን ነው ማሀርታን የሚጠይቀኝ የምምረው⁉️" የሚልበት ሰአት በመሆኑና በርካታ ኡለሞች ዘንድ ከተኙ ቡኃላ ተነስቶ መስገድ በላጭ ስለሆነ ይህን ሱና ለማግኘት ሲባል ነው።
ﻳَﻨْﺰِﻝُ ﺭَﺑُّﻨﺎ ﺗَﺒﺎﺭَﻙَ ﻭﺗَﻌﺎﻟَﻰ ﻛُﻞَّ ﻟَﻴْﻠﺔٍ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﺴَّﻤﺎﺀِ ﺍﻟﺪُّﻧْﻴﺎ ﺣِﻴﻦَ ﻳَﺒْﻘَﻰ ﺛُﻠُﺚُ ﺍﻟﻠَّﻴْﻞِ ﺍﻵﺧِﺮُ، ﻳﻘﻮﻝُ : ﻣَﻦ ﻳَﺪْﻋُﻮﻧِﻲ، ﻓﺄﺳْﺘَﺠِﻴﺐَ ﻟﻪ؟ ﻣَﻦ ﻳَﺴْﺄَﻟُﻨِﻲ ﻓﺄُﻋْﻄِﻴَﻪُ؟ ﻣَﻦ ﻳَﺴﺘَﻐْﻔِﺮُﻧﻲ ﻓﺄﻏْﻔِﺮَ ﻟﻪ؟
ﺍﻟﺮﺍﻭﻱ : ﺃﺑﻮ ﻫﺮﻳﺮﺓ - ﺍﻟﻤﺤﺪﺙ :
ﺍﻟﻤﺼﺪﺭ : ﺻﺤﻴﺢ
📒ﻣﺴﻠم ‏(758)
በተጨማሪም ይህ የቁርአን አንቀፅ የሚያመለክተው ሁሉንም የሌሊት ሶላቶች ነው።
”وَمِنَ اللَّيْلِ فَتَهَجَّدْ بِهِ نَافِلَةً لَّكَ عَسَىٰ أَن يَبْعَثَكَ رَبُّكَ مَقَامًا مَّحْمُودًا“
"ከሌሊትም ላንተ ተጨማሪ የሆነችን ሶላት በርሱ (በቁርአን) ስገድ፣ ጌታህ ምስጉን በሆነ ስፍራ በእርግጥ ያቆምሃል።"
📒ሱረቱል ኢስራእ [79]
*
በመጨረሻም እስከ ሌሊቱ አጋማሽ በሗላ (ማለትም ከ 7 ሰዐት በሗላ) እንቅልፍ በተለያዩ ስራዎችና ምክንያቶች ሳትተኙ ከቀራችሁ ሁለት ረካዓና አንድ ውትር ወትራችሁ ሀጃም ያላችሁ ዱዓችሁን አድርጋችሁ ብትተኙ ለስኬታችሁ ቁልፍ፣ ለኢማናችሁ ትርፍ፣ ወንጀልን ለማርገፍ፣ ለጭንቃችሁ መውጫ እና ከአላህ ጋር ያላችሁን ግንኙነት ለማጠናከር የተመረጠ ግዜ ነውና ተጠቀሙበት።
||
ሌሎች አንብበው ከሰገዱ የአጅሩ ተካፋይ ናችሁና፤
መልክቱን ለሌሎችም እንዲደርስ ሁላችሁም ሼር አድርጉት‼️

@yasin_nuru @yasin_nuru

10.5k 0 210 12 177

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው! የአላህ እዝነትና ሰላም በውዱ ነቢያችን ላይ ይሁን!

🌹🌹 #አቂሚ_ሰላት 🌹🌹

🥀🥀ሶላትን የመተው መዘዞች🥀🥀


#ሰላትን በአግባቡ አለመስገድ ያለውን መዘዝ እናያለን።


አላህ በክቡር ቃሉ እንዲህ ይላል፦

فَخَلَفَ مِن بَعدِهِم خَلفٌ أَضاعُوا الصَّلاةَ وَاتَّبَعُوا الشَّهَواتِ فَسَوفَ يَلقَونَ غَيًّا ﴿٥٩﴾ إِلّا مَن تابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ صالِحًا فَأُولئِكَ يَدخُلونَ الجَنَّةَ وَلا يُظلَمونَ شَيئًا ﴿٦٠﴾

ከእነርሱም በኋላ ሶላትን ያጓደሉ (የተው) ፍላጎቶችን የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ። ግን የተጸጸተነም በጎንም ሥራ የሠራ ሰው እነዚህ ገነትን ይገባሉ። አንዳችም አይበደሉም።

ቁርአን ሱራ መርየም (19:59-60)


አላህ ቱልዶችን ጠቅሷል በትሉዶች የተተኩ። እንዚህም የተተኩት ተተኪዎች እኛ #ከሰለፎች በኋላ ያለን ነን። እነሱም የተባሉት ሰለፎች ናቸው። ታድያ እነዚህ አሁን የተተኩት ተተኪዎች ምን አይነት ናቸው ብላችሁ ከጠየቃችሁኝ እኔ ሳልሆን ቁርአን እራሱ የምልሳል እንዲህ በማለት፦

فَخَلَفَ مِن بَعدِهِم خَلفٌ أَضاعُوا الصَّلاةَ وَاتَّبَعُوا الشَّهَواتِ فَسَوفَ يَلقَونَ غَيًّا ﴿٥٩﴾

ከእነርሱም በኋላ ሶላትን ያጓደሉ (የተው) ፍላጎቶችን የተከተሉ መጥፎ ምትኮች ተተኩ! የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ።

ቁርአን ሱራ መርየም (19:59)

እነዚህም ተተኪዎች
1.#ሰላትን በአግባቡ የማይግዱ ወይም ከናካቴው እርግፍ አርገው የተው።

2. ስሜቶቻቸውን የሚከተሉ ናቸው። እነዚህ አላህ የጠቀሰው ሁለቱ ምሳሌዎች በእኛ ዘመን ጎልተው ታይተዋል እየታዩም ነው።

ምክኒያቱም #ሰላትን በአግባቡ የማይሰግድ ብዙ ነው ይባስ ብሎ ከነ የማይሰግዱ ብዙ ናቸው። አላህ እውነትን አልተናገረም? በእርግጥ እውነትን ተናግሯል! ምክኒያቱም በዚህ ዘመን #ሰላትን እንደቀላል እያየናት ነው በአግባቡም እየሰገድን አይደለም።  በዚህ ዘመን ስሜታችንን የተከተልን ብዙወቻችን ነን ይሄ ለማንም ግልፅ ነው ሰላትን ለመስገድ ጊዜ የለንም ለሌላ ነገር ግን ነፃ ነን። ለምን? ቁርአን ይመልሳል፦

وَاتَّبَعُوا الشَّهَواتِ ...

ፍላጎቶችን የተከተሉ ...

ታድያ በዚህ ተግባራችን አላህ እንዲህ ሲል ጠራን መጥፎ ምትኮች ተተኩ...

መጥፎ ምትኮች ተባልን ለምን? እኛ ሰላትን በአግባቡ የማንሰግድ ሰላትን የተውን ህዝቦች ሰለሆንን! እንዲሁም ስሜታችንን በመከተል ከአላህ ስለራቅን እሱን በአግባቡ  አለመገዛታችን ነው። ታድያ አላህ ለዚህ ተግባራችን መጥፎ ምትኮች ብቻ ብሎ አለተወንም በአኪራም የሚጠብቀን ታላቅ ቅጣት አዘጋጅቶልናል ይሄንንም እንዲህ ሲል ገልፆልናል፦

فَسَوفَ يَلقَونَ غَيًّا ﴿٥٩﴾

የገሀነምንም ሸለቆ በእርግጥ ያገኛሉ።

አላህ አኺራም በዚህ ተግባራችን የገሀነምን #ሸለቆ እንደምንገባ ነግሮናል። አላህ የለውን የሚፈፅም ጌታ ነው። ታድያ ከዚህ መጥፎ ተብለው ከተጠሩት ሕዝቦችን ላለመሆንና የጀሐነምን #ሸለቆ እንዳናገኝ ምን እናድርግ ካላችሁኝ እኔ ሳልሆን አላህ እራሱ ይመልሳል እንዲህ ሲል፦

إِلّا مَن تابَ وَآمَنَ وَعَمِلَ صالِحًا فَأُولئِكَ يَدخُلونَ الجَنَّةَ وَلا يُظلَمونَ شَيئًا ﴿٦٠﴾

ግን የተጸጸተነም በጎንም ሥራ የሠራ ሰው እነዚህ ገነትን ይገባሉ። አንዳችም አይበደሉም።

ቁርአን ሱራ መርየም (19:60)

ታድያ አላህ እነዚህን ነገሮች ካደረግን

#መጥፎ_ተተኪዎች ከሚባሉት እንደዚሁም #ከጀሐነም ሸለቆም ለመዳን ወይም የጀሐነም ሸለቆ እንዳያገኘን እንዲሁም ምንም #ሳንበደል ጀነት የምንገባበትን መንገዶች ነግሮናል እነሱም

1. #ተውባ (ወደ አላህ መመለስ)

2. #ኢማናችንን_ማደስ
3. #መልካም (በጎ) ሥራን መሥራት እነዚህን ሶሰት ነገሮች ምንም ያህል ሰላትን በአግባቡ ባንሰግድ እንዚሁም ምንም ያህል ስሜታችንን ብንከተል ግን እነዚህን አላህ የጠቀሳቸውን #ሶስት ነገሮች ካደረግን #ምንም አንበደለም እንደዚሁም ጀነትን እንገባለን። በአላህ እዝነትና ፍቃድ! ሰለዚህ አደራ! ሁላችንም ሶላትን አጥብቀን በአግባቡ እንስገድ ከተመላሾም፤ መልካም ከሚሰሩት፤ከማይበደሉት #ጀነትን ከሚገቡት ያድርገን!

ወንድም ያሲን✍

አላህ ባነበቡት ከሚጠቀሙት ያድርገን!
ለአላህ ብለን እንወዳችኋለን!

@yasin_nuru @yasin_nuru

9.1k 0 83 19 134

መቼም ሰው ነንና ፈራሽ እንደሆንን እናውቃለን። እንደ ሙስሊም ከሞት በኋላ ህይወት እንዳለ እናምናለን። ስለሆነም የአኺራችን ጉዳይ ያስጨንቀናል። ለዚህም ሲባል በጌታችን ህግ ለመኖር፣ ትእዛዛቱን ለመፈፀም ክልከላውን ለመራቅ፣ ስለ ድክመታችን ተውበት ለማድረግ እንሞክራለን። ሆኖም ግን አንድ በቀላል ጥረት ብዙ ትርፍ የምንሸምትበትን ነገር ስንዘነጋ እንስተዋላለን።

አዎ ስራሽን እየሰራሽ፣ መኪናህን እየሾፈርክ፣ ወረፋ እየጠበቃችሁ፣ በመኪና እየተጓዝክ፣ ሰው እየጠበቅሽ፣ በእግራችን እየተንቀሳቀስን፣… ዚክር ቢደረግ በየእለቱ ስንትና ስንት አጅር በሰበሰብን ነበር። ዚክር ከምናስበው እጅግ የላቀ ፋይዳ አለው። ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–

"أَلَا أُنَبِّئُكُمْ بِخَيْرِ أَعْمَالِكُمْ، وَأَزْكَاهَا عِنْدَ مَلِيكِكُمْ، وَأَرْفَعِهَا فِي دَرَجَاتِكُمْ، وَخَيْرٌ لَكُمْ مِنْ إِنْفَاقِ الذَّهَبِ وَالْوَرِقِ، وَخَيْرٌ لَكُمْ مِنْ أَنْ تَلْقَوْا عَدُوَّكُمْ، فَتَضْرِبُوا أَعْنَاقَهُمْ، وَيَضْرِبُوا أَعْنَاقَكُمْ ".
قَالُوا : بَلَى.
قَالَ : " ذِكْرُ اللَّهِ تَعَالَى".
* "ከ(መልካም) ስራዎቻችሁ በላጭ፣
* ከንጉሳችሁ ዘንድ የጠራ፣
* ደረጃዎቻችሁን ከፍ የሚያደርግ፣
* ወርቅና ብር ከመለገስ የሚሻላችሁ፣
* ጠላቶቻችሁን አግኝታችሁ አንገቶቻቸውን ከምትመቱና አንገቶቻችሁን ከሚመቱ (ከጂሃድ) የሚበልጥባችሁን አልነግራችሁምን?"

√ (ሶሐቦች):– "እንዴታ! (ይንገሩን) የአላህ መልእክተኛ ሆይ" አሉ።

* "አሸናፊና የላቀውን አላህ ማውሳት" አሉ።
[ቲርሚዚ ዘግበውታል: 3377]

ትልልቅ ምንዳ ያላቸው አጫጭር ዚክሮች
~
① ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–

(مَن قال: سبحان الله وبحمده، في يوم مائة مرة، حُطَّت خطاياه وإن كانت مثل زبد البحر)؛
"በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ‘ሱብሓነላ፞ሂ ወቢሐምዲሂ’ ያለ ሰው ወንጀሎቹ እንደ ባህር አረፋ ቢሆኑ እንኳን ይረግፉለታል።" [ቡኻሪ]

② እናታችን ጁወይሪያህ ቢንቲል ሓሪሥ ረዲየላ፞ሁ ዐንሃ ባስተላለፈችው በአንድ ወቅት ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም ሱብሕን ከሰገዱ በኋላ ማለዳ ላይ ከሷ ዘንድ ወጡ። እሷ መስገጃዋ ላይ ተቀምጣ ዚክር ላይ ነች። እዚያው እንደተቀመጠች ረፋድ ላይ ተመለሱ።
"ካንቺ ከተለየሁ ጊዜ አንስቶ እስካሁን በተለየሁብሽ ሁኔታ ላይ ከመሆን አልተወገድሽም?" አሏት።
"አዎ" አለች።
በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉ:–
" لَقَدْ قُلْتُ بَعْدَكِ أَرْبَعَ كَلِمَاتٍ ثَلَاثَ مَرَّاتٍ، لَوْ وُزِنَتْ بِمَا قُلْتِ مُنْذُ الْيَوْمِ لَوَزَنَتْهُنَّ : سُبْحَانَ اللَّهِ وَبِحَمْدِهِ عَدَدَ خَلْقِهِ، وَرِضَا نَفْسِهِ، وَزِنَةَ عَرْشِهِ، وَمِدَادَ كَلِمَاتِهِ ".
"በእርግጥም ካንቺ በኋላ አራት ንግግሮችን ሶስት ጊዜ ተናግሬያለሁ። ከንጋት ጀምሮ አንቺ ካልሺው ጋር ቢመዘኑ (እኔ ያልኳቸው) ይመዝናሉ።
* ሱብሓነላ፞ሂ ወቢ ሐምዲሁ ዐደደ ኸልቂሁ፣
* ወሪዷ ነፍሲሂ፣
* ወዚነተ ዐርሺሂ፣
* ወሚዳደ ከሊማቲሂ።" [ሙስሊም የዘገቡት]

③ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(كلمتان خفيفَتان على اللسان، ثقيلَتان في الميزان، حبيبَتان إلى الرحمن: سُبحان الله وبحمده، سبحان الله العظيم)؛
"ምላስ ላይ የቀለሉ፣ ሚዛን ላይ የከበዱ እና አረ፞ሕማን ዘንድ የተወደዱ ሁለት ንግግሮች አሉ። ‘ሱብሓነላ፞ሂ ወቢሐምዲሂ፣ ሱብሓነላ፞ሂል ዐዚም።" [ቡኻሪና ሙስሊም]

④ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም ከጀነት ድልብ ሃብቶች ውስጥ እንደሆነ የገለፁት የዚክር አይነት
(لا حول ولا قوة إلا بالله)؛
"ላ ሐውለ ወላ ቁወ፞ተ ኢላ፞ ቢላ፞ህ" [ኢብኑ ሒባ፞ን]

⑤ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(مَن قال: لا إله إلا الله وحده لا شريك له، له الملك وله الحمد وهو على كل شيء قدير - عشر مرات - كان كمَن أعتق أربعة أنفُسٍ مِن ولد إسماعيل)

"አስር ጊዜ ’ላ ኢላሀ ኢለ፞ላ፞ህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ። ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ። ወሁወ ዐላ ኩሊ፞ ሸይኢን ቀዲር’ ያለ ሰው ከኢስማዒል ልጆች አራት ነፍሶችን ነፃ እንዳወጣ ነው።" [ሙስሊም]

⑥ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(سيِّد الاستغفار أن تقول: (اللهمَّ أنت ربي، لا إله إلا أنت، خلقتَني وأنا عبدُك، وأنا على عهدك ووعدك ما استطعتُ، أعوذ بك من شرِّ ما صنعتُ، أبوء لك بنعمتك عليَّ، وأبوء لك بذنبي، فاغفر لي، فإنه لا يغفر الذنوب إلا أنت، قال: ومَن قالها من النهار موقنًا بها، فمات من يومه قبل أن يُمسي فهو مِن أهل الجنَّة، ومَن قالها من الليل وهو مُوقن بها، فماتَ قبْل أن يُصبح، فهو مِن أهل الجنَّة)؛
"የኢስቲግፋር ሁሉ አለቃ ‘አላ፞ሁመ፞ አንተ ረቢ፞ ላ ኢላሀ ኢላ፞ አንተ። ኸለቅተኒ። ወአነ ዐብዱከ። ወአነ ዐላ ዐህዲከ ወወዕዲከ መ’ስተጦዕቱ። አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ፞ ማ ሶነዕቱ። አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለየ፞። ወአቡኡ ለከ ቢዘንቢ። ፈግፊር ሊ። ፈኢነ፞ሁ ላ የግፊሩ ዙ፞ኑበ ኢላ፞ አንተ’ የሚለው ነው።
በሷ አረጋግጦ በቀኑ ካላት በኋላ ሳያመሽ በእለቱ የሞተ ሰው እርሱ ከጀነት ሰዎች ነው። በሷ አረጋግጦ በሌሊት ካላት በኋላ ሳያነጋ የሞተ ሰው እርሱ ከጀነት ሰዎች ነው።" [ቡኻሪ]

እነዚህ ምሳሌዎች ብቻ ናቸው። ሌሎችም ብዙ አሉ። ከነዚህ በተጓዳኝ ከውዱእ በኋላ፣ ከአዛን በኋላ፣ መስጂድ ስትገባ፣ ከመስጂድ ስትወጣ፣ ከሶላት በኋላ፣ ከምግብ በኋላ፣ ስትተኛ፣ ስትነሳ፣ ወዘተ ያሉትን ብትል ቆጥረህ የማትዘልቀው አጅር አለህ።
በጥቅሉ ጊዜህን መድበህ ዚክርን የህይወትህ አካል አድርገው። ለዚህ ከተቸገርክ እየሰራህ፣ እየተጓዝክ ብዙ መፈፀም ትችላለህ። ዚክር ትኩረት እንጂ የረባ ጥረት አይጠይቅህም። መልእክተኛው ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዳሉት "ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ።"

@yasin_nuru @yasin_nuru

9.5k 0 101 23 155

😢እንዲህ በምሽቱ ሐብት ንብረት አስጥሎ ያስወጣ ልጅ ታቅፎ ከቤት ያስፈረጠጠ እመጫት ሳትቀር ከአልጋዋ የተነሳችበት ክስተት በእርግጥም ያስደነግጣል።

⁉️ይህ ከአምላክ ዘንድ የተላከ ማስጠንቀቂያ ነው።
መሬት በመነቅነቅ የተሰደደ የማንቂያ ደውል!
አዎ በኢትዮጵያ ምድር የተከሰተው ይህ ነው። የመሬት መስመጥና የምድር መንቀጥቀጥ ወንጀል ሲበራከት፣ አምላክን መፍራት ሲጠፋ የሚከሰት የአምላክ ቁጣ!

🙌ንቁ የሚል መልዕክት ወደኔ ተመለሱ የሚል ተግሳፅ አለዚያ ቁጣዬ ብርቱ ቅጣቴም አሳማሚ ነው እያለን ነው።ቀልድም ለከት አለው ከቀልዶቻችን እንቆጠብ!!

ሁሉም በየእምነቱ ወደ ፈጣሪው ይመለስ 🙏😢

የመሬት መንቀጥቀጥ መብዛቱ…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لا تَقُومُ السّاعَةُ حتّى يُقْبَضَ العِلْمُ، وتَكْثُرَ الزَّلازِلُ﴾

«ሰዓቲቱ (ትንሳዔ) አትቆምም፤ ዕውቀት እስከሚነሳና የመሬት መንቀጥቀጥ እስከሚበዛ ድረስ።»

[አል-ቡኻሪይ: 1036]

@yasin_nuru @yasin_nuru

9.8k 0 86 63 192

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ ፊዚክስ እና ስፔስ ሳይንስ ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ኤልያስ ሌዊ ስለ መሬት መንቀጥቀጡ እና ከዚህ በሁዋላ ከተከሰተም መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎች የሰጡትን መግለጫ ከላይ ባለው ድምፅ ቅጂ መከታተል ትችላላችሁ !

@yasin_nuru @yasin_nuru

8.5k 0 65 10 65

ከ4.5 እስከ 4.9 ይሆናል በተባለ መጠን የመሬት መንቀጥቀጥ በአዲስ አበባ ከተማ ተከስቷል

በበርካታ የከተማው አካባቢዎች የሚገኙ ነዋሪዎች በስጋት ላይ እንደሚገኙ ተረድተናል።

አከባቢያችሁ አሁን ተረጋግቷል አህባቢ?

@yasin_nuru @yasin_nuru

9.8k 0 46 15 70

ከደቂቃዎች በፊት (ከምሽቱ 2:10) ላይ በአዲስ አበባ፣ መስቀል አደባባይ፣ ካዛንቺስ እና ሌሎች የከተማዋ አካባቢዎች የተከሰተው አነስተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ የፈጠረው ንዝረት ህንጻዎችን ለተወሰኑ ሰከንዶች አንቀጥቅጦ ነበር።

@yasin_nuru @yasin_nuru

9.6k 0 87 61 119

   ዱዳው ለማኝ

   እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በ1976 በፍልስጤም ነፃ አውጪዎችና በክርስቲያኖች የገዘፈ ተጽዕኖ ስር ትመራ በነበረችው ሉብናን መካከል ጦርነት ተፋፍሞ ሀገሪቷን ያምሳት ይዟል። አንድ ለማኝ በቤሩት ጎዳናዎች መሐል በነፃነት ይርመሰመሳል። ሰውነቱ ቆሽሾ አካሉ ይከረፋል። በባዶ እግሩ የሚራመድ ፀጉርና ፂሙ የተንጨበረረ ነው። መናገር የማይችል ዱዳ አዎ! ዝም ነው ማውራት አይችልም። አስተዋይ ነው ነገሮችን በጥልቅ ይመለከታል። ግና ከአንደበቱ ቃላት አፍልቆ መናገርን ተነፍጓል። በስሌትና በብዜት ክስተቶችን ይመረምራል። በበጋም ሆነ በክረምት ከደረበው ረዝሞ ከደከረተ፣ ጎስቁሎ ከተቀደደ ጥቁር ካፖርት ውጪ ሌላ የሚለብሰው ነገር የለም።

   የቤሩት ደጋግ ሰዎች ያላቸውን ያካፍሉታል። ሲበዛ ሚስኪን ነውና ካላቸው ላይ ቀንሰው ያካፍሉታል። ከትልቁም ከትንሹም ጋር በምልክት እየተግባባ ይጫወታል። ድርጊቶቹ ያንሰፈስፋሉ። አንድ ቂጣ እንጂ የበዛ ዳቦ አይቀበልም። የሚበቃውን የእለት ጉርሱን እንጂ የተትረፈረፈ ነገር አይፈልግም።

የሚጠራበትም ስም የለውም። ዱዳው በሚል መጠርያ እንጂ አይታወቅም። ሰው ላይ አይደርስም። ማንንም አይበድልም። እጁንም በሰው ሐቅ ላይ አይዘረጋም። ሰማዩን እንደ ጣራ ምድርን እንደፍራሽ እየተገለገለ ለሽ ይላል። ብርዱን እየማገ የቅዝቃዜ ጋቢን ደርቦ ከመንገዱ ጥግ ይተኛል።

ጦርነቱ እንደቀጠለ ነበር። ወሬው ሁሉ ስለ ዘመቻው ዜናው ሁሉ ስለእልቂቱ ሆኗል።
     የእስራኤል ጦር ዘመናዊ መሳርያን ታጥቆ ወደ ቤሩት በሰልፍ ይገባ ይዟል። በግስጋሴው መሐል ከጀግና ተዋጊዎች ብርቱ ተቃውሞ ቢገጥመውም የቤሩትን ህዝብ በአሰቃቂ የቦምብ ድብደባ እያረገፈ፣ በአስፈሪ መሳርያና በአውዳሚ ዛጎሎች እየረፈረፈ በሬሳቸው ላይ በመራመው ወደ ውስጥ መዝለቁን ቀጥሏል። ዱዳው ለማኝ በሌላ አለም ውስጥ ከንፎ በራሱ ዛቢያ ይሽከረከራል። ይነሳል ይተኛል። ይለምናል ይመገባል።

    የነበልባል እሳቶች እየተምዘገዘጉ ዷ ደሽ ጓ የሚሉ ድምጾችን ያስተናግዱ ጀምረዋል። የእሳት አረሮች ይወነጨፋሉ። ከባባድ መሳርያዎች እየተተኮሱ የቂያማን ክስተት ያስታውሳል። ሁኔታው በእጅጉ ያስፈራል።

  የእስራኤል ጦር ዱዳው ወደሚተኛበት ጎዳና አቅራቢያ ሲጠጋ አንዳንድ ፍልስጤማዊያን ሊያስጠጉት ሞከሩ። ግና እሱ ፈቃደኛ አልነበረም። በምእራብ ቤሩት ውስጥ የተንከራተተባቸውና የተኛባቸው መንገዶች እንደሚያድኑት እያመነ አስባልት ዳር ኩርምት ብሎ መቀመጡን መረጠ።

   የእስራኤል ጦር ወደ ምእራብ ቤሩት ሲደርስ ሰዎች ተስፋ በመቁረጥ ብቻውን ትተውት ነፍሳቸውን ለማዳን ሩጫ ጀመሩ። ከፊሎቹም ከመንገዱ ጥግ ካለው የፈራረሰ ህንፃ ስር ተሸጉጠው ቆሙ። ከሚጠብቃቸውን የግድያ ዕጣ ፈንታ ለማምለጥ ተሸሸጉ። ዱዳው ላይ አንዳች ነገር እንዳይደርስበትም ሰግተዋል። ከንቱ የሆነ እዝነት!

    የእስራኤል ጦረኞችን የያዘ ወታደራዊ መኪና ከዱዳው አቅራቢያ በሚገኘው ትይዩ መንገድ ላይ ቆመ። ሶስት የባለ ሙሉ ማዕረግ መኮንኖች ከመኪናው ወረዱ። ሁለት አጃቢዎች መሳርያቸውን ደቅነው ከኋላ ተከተሉ።

ጣታቸውን የመሳርያው ምላጭ ላይ አድርገው በጥንቃቄ ተጓዙ። በድምሩ አምስት ወታደሮች ነበሩ። ከኋላቸው በርካታ የታጠቁ ተሽከርካሪዎች በወታደር ተሞልተው ቆመዋል።

  ቦታው አስፈሪ ድባብ የሚፍስበት፣ በሞቱ ሰዎች ሬሳ የተጨማለቀ፣ የደም ሽታና በሚያጥን በባሩድ ጭስ የተሞላ ነበር። ወታደሮቹ ወደ ዱዳው ቀረቡ። እሱ መሬት ላይ ተዘርግቶ በዙሪያው ስላለው ነገር ሁሉ ደንታ ቢስ ነበር። በራሱ አለም ውስጥ እየዋለለ ሲጋራውን ቡን ያደርጋል።

  መኮንኖቹ እርሱ ዘንድ ለመድረስ ሁለት እርምጃ  ሲቀራቸው ሞትን በደስታ እንደሚቀበል ሰው ከተቀመጠበት ብድግ አለ። የእስራኤሉ ዋና አዛዥ ኮሎኔል እጁን ወዳናቱ አንሥቶ ሰላምታን አቀረበለትና በዕብራይስጥኛ እንዲህ አለ "በእስራኤል መከላከያ ሰራዊት ስም ሰላም እላለሁ ኮሎኔል እስራኤልን ለማገልገል ላደረጋችሁት ቁርጠኛ ትግል በኔና በእስራኤል መንግስት ስም እናመሰግናለን። ያለ እርስዎ ቤሩት አንገባም ነበር"
ዲዳው ለማኝ ያንኑ ቃል በረጋ መንፈስ ከአንደበቱ አውጥቶ ሰላምታውን መለሰ። ፊቱ ላይ ለስላሳ ፈገግታ ይታያል።

በዕብራይስጠኛም በቀልድ መልክ "ትንሽ ዘገያችሁ" እያለ ወደ መኪናው ተሰቀለ። ዘመናዊ መሳርያን እስከ አፍንጫው የታጠቀው ወታደራዊ መኪና ከኋላ እየተከተላቸው ጉዟቸውን ቀጠሉ። የዕብራይስጥ ቋንቋ ጠንቅቀው የሚያውቁ ፍልስጤማዊያን ለቦታው ቅርብ ነበሩ። ውይይቱን ሰምተው ኖሯልና ተደናገጡ። ለካ ከጉያቸው ሸሽገው ሲቀልቡት የኖሩት የገዛ ጠላታቸውን ነበር። እስራኤላዊው ሰላይ የኖረበትን ስፍራ እየተመለከተ የቤሩት ነዋሪያንን እየገላመጠ ሀገሩን ለቆ ተጓዘ።

- በአገራችንስ ይህን ዱዳ የመሳሰሉ በዳኢነት ስም የተሸጎጡ ስንትና ስንት መሻኢኾችና ዳኢዎች አሉ?

- ይህን የመሰሉ ስንት ዱዳ ለማኞች የማህበረ ቅዱሳንን የቤተ ክርስቲያንን ተልዕኮ ለማስፈፀም በከፍተኛ የመንግስት መዋቅር ላይ ይገኛሉ?

- ንፁህ ለብሶ፣ ሥጋው ደልቦ ኢስላምን ለማጥፋት የሚኳትንስ ስንትና ስንት ይህን ዱዳ መሳይ አለ? አላህ ይጠብቀን።

ጌታዬ ሆይ! ባልሰራበት እንኳ ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሚያገኘውን አጅር አታሳጣኝ

@yasin_nuru @yasin_nuru

10.7k 0 81 16 130

ጥፍጥና ቆራጭ የሆነችውን ሞት አስታውስ


ጨቅነው አፈር አልብስው ተቆልፎብህ መሬቱ፣

አብሮህ የሚቆይ አይኖርም ሰው ይመለሳል ከቤቱ🥺🥺

@yasin_nuru @yasin_nuru

8.5k 0 34 10 87

🔰 የነቢያት ሃይማኖት 🔰

በመጀመሪያ ኢስላም أسلم "አስለመ" ከሚል ግስ የተያዘ ሲሆን ትርጉሙ " ታዘዘ"  እጅ ሰጠ" ማለት ሲሆን ኢስላም ለሀያሉ አምላክ በመታዘዝ ለሱ እጅ በመስጠት እሱን ብቻ ማምለክ ማለት ነው።

አላህ ሱብሀነሁ ወተዐላ ስለ ኢብራሂም ሲተርክልን እንዲህ ይላል

إِذْ قَالَ لَهُ رَبُّهُ أَسْلِمْ ۖ قَالَ أَسْلَمْتُ لِرَبِّ الْعَالَمِينَ
ጌታው ለርሱ ታዘዝ ባለው ጊዜ (መረጠው)፡፡ ለዓለማት ጌታ ታዘዝኩ አለ፡፡ [Qur'an 2:131]

💍 በጥቅሉ ኢስላም ማለት ሀያሉ አምላክን መታዘዝና ለሱ እጅ በመስጠት እሱን ብቻ ማምለክ መሆኑን ከተስማማን
💡 ቀደምት ነቢያት(እነ አዳም,ኖህ"አብረሀም'ሙሴ'ኢሳ/እየሱስ/ ..) ለሀያሉ አምላክ ታዛዦች ስለነበሩ ሙስሊም ነበሩ ማለት ነው።

🌺 ነቢዩ ኑሕ(ኖህ) ሙስሊም ነበረ

🏆23:23 ኑሕንም ወደ ሕዝቦቹ በእርግጥ ላክነው፡፡ ወዲያውም «ሕዝቦቼ ሆይ! አላህን አምልኩ፡፡ ከእርሱ ሌላ ምንም አምላክ የላችሁም፡፡ አትጠነቀቁምን» አላቸው፡፡

10፥72 “ብትሸሹም አትጎዱኝም ፣ከምንዳም ምንንም አለምናችሁም፡፡ምንዳዬም በአላህ ላይ እንጂ በሌላ አይደለም፣*"ከሙስሊሞችም እሆን ዘንድ ታዝዣለሁኝ"
*” فَإِن تَوَلَّيْتُمْ فَمَا سَأَلْتُكُم مِّنْ أَجْرٍ ۖ إِنْ أَجْرِىَ إِلَّا عَلَى ٱللَّهِ ۖ وَأُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ مِنَ ٱلْمُسْلِمِينَ

🌺 ነቢዩ ኢብራሂም (አብረሃም) ሙስሊም ነበረ

🏆 3:67 ኢብራሒም ይሁዳዊም ክርስቲያንም አልነበረም ግን ወደ ቀጥተኛዉ ሃይማኖት የተዘነበለ *"ሙስሊም ነበረ"*፤ ከአጋሪዋችም አልነበረም። مَا كَانَ إِبْرَٰهِيمُ يَهُودِيًّۭا وَلَا نَصْرَانِيًّۭا وَلَٰكِن كَانَ حَنِيفًۭا مُّسْلِمًۭا وَمَا كَانَ مِنَ ٱلْمُشْرِكِينَ

🌺 ነቢዩ ያዕቁብ(ያቆብ) እና ልጆቹ ሙስሊም ነበሩ

2:132 በእርሷም በሕግጋቲቱ ኢብራሂም ልጆቹን አዘዘ፡፡ ያዕቁብም እንደዚሁ ልጆቹን አዘዘ፡፡ «ልጆቼ ሆይ! አላህ ለእናንተ ሃይማኖትን መረጠ፤ ስለዚህ እናንተ *"ሙስሊሞች"* ኾናችሁ እንጂ አትሙቱ» አላቸው፡፡ وَوَصَّىٰ بِهَآ إِبْرَٰهِـۧمُ بَنِيهِ وَيَعْقُوبُ يَٰبَنِىَّ إِنَّ ٱللَّهَ ٱصْطَفَىٰ لَكُمُ ٱلدِّينَ فَلَا تَمُوتُنَّ إِلَّا وَأَنتُم مُّسْلِمُون

🌺 ነቢዩላሂ ዩሱፍ(ዮሴፍ) ሙስሊም ነበረ

۞ رَبِّ قَدْ آتَيْتَنِي مِنَ الْمُلْكِ وَعَلَّمْتَنِي مِن تَأْوِيلِ الْأَحَادِيثِ ۚ فَاطِرَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضِ أَنتَ وَلِيِّي فِي الدُّنْيَا وَالْآخِرَةِ ۖ تَوَفَّنِي مُسْلِمًا وَأَلْحِقْنِي بِالصَّالِحِينَ

«ጌታዬ ሆይ! ከንግሥና በእርግጥ ሰጠኸኝ፡፡ ከሕልሞችም ፍች አስተማርከኝ፡፡ የሰማያትና የምድር ፈጣሪ ሆይ! አንተ በቅርቢቱና በመጨረሻይቱ ዓለም ረዳቴ ነህ፡፡ ሙስሊም ሆኘ ግደለኝ፡፡ በመልካሞቹም አስጠጋኝ» (አለ)፡፡ ሱራ ዩሱፍ 12:101

🌺 ነቢዩላሂ ሙሳ(ሙሴ) ሙስሊም ነበረ። ወደ ኢስላም ይጣራ ነበረ።

የዮናስ ምዕራፍ يونس 10:84

وَقَالَ مُوسَىٰ يَا قَوْمِ إِن كُنتُمْ آمَنتُم بِاللَّهِ فَعَلَيْهِ تَوَكَّلُوا إِن كُنتُم مُّسْلِمِينَ

ሙሳም አለ፡- «ሕዝቦቼ ሆይ! በአላህ አምናችሁ እንደ ሆነ በርሱ ላይ ተጠጉ፡፡ ታዛዦች እንደ ሆናችሁ (በአላህ ላይ ትመካላችሁ)፡፡»

@yasin_nuru @yasin_nuru


« ኢሬቻ ላይ ሄዶ የመጣ ሙስሊም ገላውን ታጥቦ ሸሃዳ ይዞ ካልሆነ በስተቀር ወደ መስጂድ መግባት አይችልም»

13.659

ታላቁ ዓሊም ሙፍቲ ሸይኽ አደም ቱላ ( ረሂመሁላሁ ተዓላ)

@yasin_nuru @yasin_nuru

9.8k 0 70 31 216

قال رسول الله ﷺ:

[ ومن كذب علي متعمدًا فليتبوأ مقعده من النار‏]

      📚‏‌رواه البخاري

  

የአላህ መልእክተኛ(ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ:–

[በእኔ ላይ ሆን ብሎ የዋሸ ሰው ከእሳት መቀመጫውን አዘጋጀ።]   

    📚ቡኻሪ ዘግበውታል።

ሰሉ አለ ረሱል

@yasin_nuru @yasin_nuru

10.1k 0 19 28 124

በመላይካ ተመስለህ ነበር

በነጋታው ወደ ሐጅ ሊሄድ ነው። ጓደኞቹን መሰነባበት ስለሚጠበቅበት በውድቅት ሌሊት ከቤቱ ወጣ።

በሌሊት ጨለማ ወደ ጓደኞቹ ቤት ሲሄድ፤ እግሩን ያብረከረከውን፣ ልቡን ያስደነገጠውን...ክስተት ተመለከተ።

አንዲትን ሴት ከቆሻሻ መጣያ ቦታ የሞተ ዶሮ ይዛ ተደብቃ ስትሄድ ነበር የተመለከታት።

አላስቻለውም፦ «አንች ያላህ ባርያ! ምን እየሰራሽ ነው...?» ብሎ ተጣራ።

«አንተ ያላህ ባርያ! የ ፍጥረትን ጉዳይ ለጌታው ተውለት (አትፈላፈል)። አላህ የራሱ የሆነ ዓላማ አለው።» ብላው ልትሄድ ስትል።

«በአላህ ይሁንብሽ፤ ንገሪኝ።» በማለት አስቆማት።
«እንዲያ በአላህ ከለመንከኝማ እነግርሃለሁ።» እንባዋ ጉንጮቿ ላይ ይንጠባጠብ ጀመር።

ከእንባ ትንቅንቅ በፈጠረው በሚቆራረጥ ድምጿ፦ «አላህ ለኛ በክት መብላትን ሀላል አድርጎልናል...።»

ንግግሯን ቀጠለች።
«እኔ አራት ሴት የቲም ልጆችን የማሳድግ ድሃ እናት ነኝ። አባታቸውን ሞት የነጠቀባቸው የቲሞች ረሃብ ሲገርፋቸው፤ የምግብ ያለ ብዬ ብለምን አዛኝ ልቦችን አጣሁ።

እቤቴ አንጀታቸውን ረኃብ ያሳረረባቸው ልጆቼን ሳስብ ከቆሻሻ መጣያም ቢሆን እሚቀመስ ልፈልግላቸው እዚህ መጣሁ። አላህም ይህችን የሞተች ዶሮ ረዘቀኝ፤ ታድያ በክት በላሽ ብለህ ልትከራከረኝ ነው?» በለቅሶ አንደበት ጠየቀችው።

ከፊቷ የቆመው ግርማ ሞገሳሙ ሰው የአዛኝ አባት እንባዎቹን እያፈሰሰ፦ «ይህን አደራ ተቀበይኝ» ብሎ ለሐጅ ጉዞ የያዘውን ገንዘን በሙሉ አስረከባት።

እናት ልቧ በደስታ ፈክቶ ገንዘቡን ይዛ ወደ ልጆቿ ከነፈች።እሱም የሐጅ ገንዘቡን ለተራቡ ጉሮሮዎች ፊዳ አድርጎ ወደ ቤቱ ተመለሰ።

የሐጅ ተጓዦች ጉዞአቸውን ጀመሩ....።

ባለታሪካችን ሐጁን ሰርዞ ሰፈር ሰነበት። ከወራት በኋላም የቀዬው ሰው ሐጁን አጠናቅቆ ሲመለስ ለባለ ታሪካችን የምስጋና ናዳ ያወርዱለት ጀመር።

«የዚህን ዓመት ሐጅ እንዳንተ የኻደመን ሰው የለም፤ ደግሞም እኮ እዝያ ሐጅ ላይ ያደረግክልን ሙሐደራ መቼም የማይረሳ ነው።...ደግሞም እንዳንተ በሐጅ ዒባዳ የጠነከርን አንድም አላየንም...»

ግራ ተጋባ። እሱ ሐጅ ሊሄድ ይቅርና ከቀዬም አልተንቀሳቀሰም፤ እነሱ ሚያወሩት ሌላ ነው። በዝምታ አለፋቸው።

ያን ቀን ባለ ታሪካችን በህልሙ አንድ ከፊቱ ብርሃን የሚፈነጥቅን ሰው ተመለከተ።

ያ ሰውም፦ «አንተ የአላህ ባርያ! ሰላም ባንተ ላይ ይሁን። እኔን ታውቀኛለህ?» ሲል ጠየቀው።

ንግግሩን ቀጠለ፦ «እኔ ሙሐመድ የአላህ መልዕክተኛ ነኝ፣ እኔ የዱንያ ውድህ ነኝ፣ እኔ የአኼራ አማላጅህ ነኝ ለኡመቴ ስለዋልክላት ውለታ አላህ ይመንዳህ።

አላህ ያችን የየቲሞች እናት ሀጃ ስላወጣህ አክብሮሃል፣ ገመናዋንም ስለሸሸግክላት አላህ ገመናህን ሸሽጎልሃል።

አላህም በምስልህ አንድ መልኣክ ፈጥሮ ያንተን ሀጅ ከቀዬህ ሰው ተቀላቅሎ እንዲፈፅምልህ አድርጓል። ለያንዳንዱ ሰው የአንድ ሐጅ ምንዳ ሲመዘገብለት ላንተ የ70 ሰው ሐጅም ተባዝቶ ተመዝግቦልኃል።»

ዐብዱላህ ኢብኑል ሙባረክ ረሒመሁላህ

umma

@yasin_nuru

11.8k 0 124 35 260
20 last posts shown.