የፍቅር ቴሌግራም ❤️‍🔥™


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


𝐖𝐞𝐥𝐜𝐨𝐦𝐞 t̑̈ȏ̈ የፍቅር ቴሌግራም™ ❤
💙በዚ 𝐂𝐡𝐚𝐧𝐧𝐞𝐥 ላይ
💜ድርሰቶች
💚የፍቅር ግጥሞች
💛ጣፋጭ ታሪኮች
❤️ምክሮች ...
አልፎ አልፎ ቀልዶች ይለቀቁበታል 😂

Since 2016 e.c
❤️ከናተ ሚጠበቀው 𝐉𝐨𝐢𝐧 to request በማረግ ብቻ መከታተል ነው ❤️
👇👇👇

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


Betty እባላለሁ እድሜ  23 ነው በጣም ቆንጆ  እና ለ kiss የሚገፋፋ ከንፈር አለኝ ስራዬ የ ሆቴል  አስተናጋጅ ነኝ
በምሰራበት ሆቴል በጣም ብዙ ደምበኞች ነበሩኝ  ቀኑን ባላስታውስም ወደ 2:30 አካባቢ ይሆናል ከደንበኞቼ አንዱ መኝታ ቤቱ ድረስ ቢራ እንዳመጣለት ይጠይቀኛል እኔም ቢራዉን ወሰድኩለት ክፍሉ ስገባ ግን ያልጠበኩት
see more....


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
🎁 መሸለም ልንጀምር ነው 🎁

ይሄ መልዕክት ከ20 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል

ቀድመው እነዚን ቻናል ለተቀላቀሉ 20 ሰዎች የ50 ብር ካርድ ልሸልም ነው ቶሎ ይቀላቀሉ።


Squid Game Season 2 (2022)

በጉጉት ሲበጠቅ የነበረው Squid Game Season 2 ተለቀቀ አሁኑኑ ቻናላችንን JOIN በማረግ ፊልሙን ያውርዱ👇
https://t.me/addlist/Hi8NJ3zE-GA2N2Nk
https://t.me/addlist/Hi8NJ3zE-GA2N2Nk


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ

                        ክፍል  
1️⃣1️⃣


ምንም ነገር ሳልነግራት ዝም ብዬ ተነስቼ መውጣት ፈልጌ ነበር ግን ለማንም አውርቼ ማላቀውን ሚስጥሬን ለመንገር ወሰንኩ ምናልባት ትንሽ ልቧ ላይ ያለውን ጥላቻ ማብረድ ከቻልኩ ብዬ አስቤ ስለነበር ነው ንግግሬን ሳልጀምር ማላቀው ስልክ ተደወለልኝ አላነሳሁትም ስልኬን ሳይለንት አድርጌ ኪሴ ከተትኩትና ለፋኖስ ከልጅነቴ ጀምሮ የተፈጠረውን መተረክ ጀመርኩ።

እኔ የተወለድኩት እዚሁ ነው።
እኔ ስወለድ እናቴ መውለድ ሳትፈልግ በድንገት ነው የተረገዝኩት ለማስወረድ ብዙ ብትሞክርም ፈጣሪ ስላልፈቀደው ሳይሳካላት ቀረ  አባቴ የልጅ ፍቅሩ በጣም ከፍ ያለ ስለነበር በእናቴ ማርገዝ ደስታው ጣራ ነክቶ ነበር።
እሷ ስትወልድ እንዳትሳቀቅ ብሎ ሰፊ ቤት ተከራየላት እሷ ሌሊት ወጥቶ ማታ እየገባ እሷን አንድም ስራ እንድትሰራ አይፈቅድላትም ሰራተኛ ቀጠረላት ከመሬት እቃ ስታነሳ ሁላ ሚከፋው አባት ነበረኝ።

እኔም ተወለድኩ ስራ እረፍት ጠይቆ እንደ እናት አረሳት እሷ ምንም ዘመድ ስላልነበራት ሚጠይቃት ሰው እንኳን የላትም።
ብቻ ምን አደከመሽ እኔ ተወልጄ ሁለት አመት ከሆነኝ ቡሀላ እሱ እንደአራዊት ሌሊት እየወጣ ሌሊት እየገባ አንቀባሮ ሲያኖራት እናቴ ጠገበችና እዛው ግቢ ተከራይቶ ከሚኖር ወንደላጤጋ መማገጥ ጀመረች።

አባቴ ተደጋጋሚ ጊዜ ወሬ ቢደርሰውም ንቆ ያልፈው ነበር።
የሆነ ቀን ግን እጅ ከፍንጅ ያዛት እና ተጣሉ እራሷ አኩርፋ ከቤት ጥላ ወጣች ከወር ቡሀላ ግን እኔ እየተጎዳሁ እንደሆነ ስላሰበ መልሶ እራሱ ለምኖ ታረቃት እሷ ግን ይቅርታ አድርጎላት እንኳን አመሏን አልተወችም አባቴ ደሞ ከምልሽ በላይ ይወዳት ያፈቅራት ነበር ከሷ ሌላ ሴት ምድር ላይ የተፈጠረች አይመስለውም እሷን አጥቶ መኖር መተንፈስ እንደሚችል አያምንም።
ብቻ በጣም ብዙ ጊዜ እየታረቁ እየተጣሉ ቆዩ በመጨረሻም አታስገድደኝ እኔ ከሌላ ሰው ፍቅር ይዞኛል አንተንም ልጄንም አልፈልጋችሁም አለችው።
አባቴ ተስፋ አልቆረጠም ያለማቋረጥ ሽማግሌ እየላከ ሰላም ሲነሳት ወደሌላ ከተማ አድራሻዋን አጥፍታ ጠፋች አባቴ በሷ ናፍቆት ብዙ ተሰቃየ እሷ ልቴድበት ትችላለች ብሎ ያሰበው ቦታ በሙሉ እኔን እየያዘ እየዞረ ይፈልጋት ነበር በሷ ምክንያት ከስራ ተባረረ።
የምንበላው አጣን አባቴ ግን በዛን ሰአት የምንበላው ከማጣታችን በላይ የሷ ካጠገቡ መራቅ አብዝቶ ያሳስበው ነበር እኔንም በጣም ስለሚወደኝ ለደቂቃ ካይኑ ዞር እንድል አይፈልግም።

የሆነ ቀን የድሮ አከራያችን የት እንዳለች ነገረችው እኔን ይዞ ከአክስቴ ብር ተበድሮ ያለችበት ይዞኝ ሄደ እናቴ ከሌላ ሰው አርግዛ ለመውለድ ተቃርባ ነበር ያንን የተመለከተው አባቴ እህቱጋ ሄዶ አደራ ሰቷት እሱ ሄዶ እራሱን አጠፋ ።

በሰአቱ አክስቴ መሀን ስለነበረች  እኔን እንደልጇ ተቀበለችኝ እናትም አባትም ሆና አሳደገችኝ።
ግን እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ ስለናቴ ምሰማው ነገር ሴትን ልጅ እንድጠላና ፍቅር ሚባለው ነገር በራሱ የሰው ልጅ የመሞቿ ገመድ እንደሆነ እያሰብኩ ነው ያደኩት።መንገድ ላይ ወንድና ሴት ተቃቅፈው ሲሄድ የወንዱ መሞቻ ቀን መች ይሆን እያልኩ ነው የኖርኩት።
ገባሽ ሴትን ልጅ አደለም ለፍቅር ለጓደኞነት እራሱ ለመቅረብ አስቤ ሞክሬ አላቅም ሁሉም ሴቶች እንደናቴ ይመስሉኛል ልክ እናቴ አባቴን ለሞት እንደዳረገችው እኔም ባፈቀርኳት ሴት የምጠፋ ይመስለኛል ።
ለዛ ነው እራሴን ከሴት ልጅና ከፍቅር ማርቀው።
ደሞ የዛን ቀን እህትሽ ከነዩኒፎርሟ መጥታ እወድሀለሁ ተረዳኝ ስትለኝ ገና ህፃን እይደሆነችና አርፋ ትምህርቷን እንድትማር ስነግራት እሷ ግን ግግም ብላ ስልክህን ስጠኝ ስትለኝ ገና በዛ እድሜዋ ለዛውም ከነዪኒፎርሟ እንደዛ መሆኗ አናዶኝ ነው በጥፊ የመታኋት እንጂ እኔ እንድትሞት አደለም ከልቤ ፀፅቶኛል አስተዳደጌ ነው እንደዚህ ያደረገኝ አልኳት።
አደል አትርሳ አሳዳጊህምኮ ሴት ናት ለሴት ልጅ ጥላቻ ካለህ እሷን እንዴት በዚህ ልክ ልትወዳት ቻልክ አለችኝ።

ንግግሯ አናደደኝ እማዬንማ የምወዳት ከልቧ ሴት ስለሆነች ነው ገባሽ ለኔ ላልወለደችው ልጇ ህይወቷን ለመስጠት ስለማታመነታ ነው።
ጠያቂ ዘመድ ባጣሁ ሰአት እሷ ብቻዋን ዘመድ አዝማድ ሆና ስላሳደገችኝ ነው።
አንድም ቀን የናትና አባቴን አለመኖር እንዳስታውለው እድል ስላልሰጠችኝ ነው



ይቀጥላል...



🔻ክፍል1️⃣2️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ የፍቅር ጥግ ክፍል 11 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ

                        ክፍል  
1️⃣0️⃣


ጥሩ እንዴት ማለት አሪፍ ነው ምን መሰለህ እህቴ ምትማረው ከእናት መስሪያ ቤት አስፋልት ተሻግሮ ያለው የሀብታም ትምህርት ቤት ነው ።
እና እሷ ወደትምህርት ቤት ባባቴ መኪና እየሄደች አንተ ከtaxi ወርደህ ወደስራ ቦታህ እየሄድክ ታይሀለች ምንህን እንደወደደችው ባላቅም ብቻ ባንድ እይታ ፍቅር ያዛት አባቴ ትምህርት ቤት በር ላይ አድርሷት ሲመለስ እሷ ተደብቃ አስፋልት ተሻግራ ቆማ አንተ ስራ ቦታህ እስክትመጣ ቆማ ትጠብቅሀለች አንተ ወደስራ ቦታ ለመግባት ስለምታረፍድ አንተን  ጥበቃ እየቆየች እሷም ክላስ አርፍዳ ትገባለች ተደጋጋሚ ጊዜ በማርፈዷ ምክንያት ለአባቴ ተደውሎ ለምን እንደምታረፍድ ጥያቄ ቀረበበት አባቴ ደሞ ሁሌ በጊዜ ነው ክላስ አድርሷት የሚመመለሰው በዛ ምክንያት ግራ ስለገባው እህቴን አብዝቶ ተቆጣት ድጋሜ በማርፈድ ቅሬታ ከቀረበባት እዚሁ ለቤታችን ቅርብ የሆነ ሌላ ትምህርት ቤት እንደሚያስገባት ሲነግራት ሁለታችንም ደነገጥን ምክንያቱም እኔ ስላንተ ሁሉንም ነገር ጠንቅቄ ስለማቅ ነው።  ለህቴ ከኔ በላይ ቅርብ ሰው የላትም ምንም ነገር ሳደብቅ ትነግረኛለች ስምህን እንኳን ሳታቀው ስላንተ ስታወራ አይኗ ይበራ ነበር አንዴ በሳቀች ብለን ምጠብቃት ልጅ ስላንተ ስታወራ ግን ፊቷ እንደፀሀይ እያበራ ሳቅ በሳቅ ሆና ነበር ምታወራኝ።

በመጨረሻም ሁሉንም እውነት ላንተ ነግራህ ሰአት አመቻችታችሁ እንድትገናኙ እሷም ክላስ ሳታረፍድ ወይ ስትወጣ እንድታይህ ካልሆነም ማታ ላይ ከስራ ሰአትህ ቡሀላ እየመጣን ልናገኝህ ወሰንና ለእህቴ ሁሉንም እውነት አፍረጥርጣ እንድትነግርህ ሌሊቱን ሙሉ ስመክራት አደርኩ እሷም ተስማማች ።
በነጋታው ስልኳን ይዛ ወደትምህርት ቤት መጣች ያንተን ስልክ ተቀብላ በዛውም ለኔ ምን እንዳልካት ደውላ ለመናገር ስለፈለገች ነበር ስልክ የያዘችው።

አይገርምም አንተ ጢባራሙ እእ አንተ ብቻ ወንድ የተፈጠርክ የሚመስልህ አንተ ግን እንደምትወድህ ስትነግርህ በጥፊ ብለህ ሸኘሀት።
እህቴ በሰአቱ እያለቀሰች እጅህን እንዳነሳህባትና በህይወቷ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደተመታች በዛም ምን ያህል እንደከፋት እያዞራት እንደሆነና ትምህርት ቤት መጥቼ እንድወስዳት እየነገረችኝ ነበር ንግግሯን እንኳን ሳትጨርስ እህቴ የመኪና ሰለባ የሆነችው የቤታችንን ድመቀት ነው የቀማኸን ሳቃችንን ነው ያሳጣኸን የናትና አባቴን ትዳር ነው የበተንከው ገባህ ባይኔ ሙሉ ስላየኋት ምትሟሟብኝ የሚመስለኝን እህቴን በመኪና አደጋ እንዳጣት ያደረከኝ ታስታውሳለህ አደል አስክሬኗ እንኳን ከመሬት ተለቅሞ ነው የተቀበረችው የሚሰቀጥጥ የመኪና አደጋ ነው የደረሰባት እሷን ካጣሁ ቡሀላ ከልቤ ስቄ አላቅም ከእናትና አባቴ ቤት ወጥቼ ነው ምኖረው እናቴ ጤነኛ አደለችም ባንዴ ልጇንም ትዳሯንም ነው ያጣችው አባቴ ከስንት አንዴ ነው ስልክ እንኳን ሚያነሳልን የት እንዳለ የት እንደሚኖር አናቅም።

አንተ ካደረከን ነገር አንፃር እኔ ምንም አላደረኩህም ሰው ፊት ብቻ ነው ያዋረድኩህ ማፍቀር እንዴት እንደሆነ ስቃዩ እንድትረዳ ስለምፈልግ ነው እስካሁንም የታገስኩህ እንጂ እንደኔማ ቢሆን ገና የመጀመሪያ የተገናኘን ቀን መጥህ ውስጥ መርዝ አድርጌ ብገልህ ምኞቴ ነበር ስታቅፈኝ እንዳባ ጨጓሬ ነው ምትኮሰኩሰኝ ሳይህ ፊቴ ላይ ቀድሞ ሚመጣው ነፍሰገዳይነትህ ነው ምን ያህል ትግስተኛ እንደሆንኩ የገባኝ አንድ አመት ሙሉ አንተን መታገሴን ሳስበው ነው።
እህቴ ምን ጥሎባት አንተን እንደወደደችህ አላቅም አንተን እንኳን ማፍቀር ለትንሽ ቀን አብሮ ጊዜ ማሳለፍ እራሱ ይከብዳል ምትቀፍ ሰው ነህ ምንህም አይስብም።

ይታይሀል ከነሱጋ የተቀመጠው ሰው ፍቅረኛዬ ነው የአራት አመት ፍቅረኛዬ አሁን አብረን ነው ምንኖረው በከፋኝ ሰአት ከጎኔ የነበረው እሱ ነው አለችኝ።

አንዳንዴ የምንሰማውን ነገር ማመን አቅቶን ፈጣሪን በቃ ከህልሜ ቀስቅሰኝ እንጂ እስካሁንኮ አልነቃንም ብለነው አናቅም እኔ በሰአቱ እንደዛ ነው ያልኩት።

ፋኖስ ይሄን ሁላ ነገር ስትነግረኝ እያለቀሰች ስለነበር አሳዘነችኝ ውስጤ ተላወሰ እራሴን ጠላሁት በእህቷ ፈንታ እኔ በነበርኩ ብዬ ተመኘሁ።



ይቀጥላል...



🔻ክፍል1️⃣1️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ የፍቅር ጥግ ክፍል 10 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ

                        ክፍል  
9️⃣

አይን አይኗን መመልከቱን ተያያዝኩት።
ልእልት መጥታ ካጠገቤ ቆማ መሬት መሬት እያየች ፋኖስን ሄደህ ምን እንደተፈጠረ ማውራት ከፈለክ እኔ ከእቴቴ አጠገብ እሆናለሁ እኔ አለሁ ለሷ አለችኝ።

አመሰግናለሁ ግን ጥያት አሌድም ከምንም ነገር በላይ እናቴ ናት ለኔ አስፈላጊዋ አልኳት።
እናቴ ፈገግ ብላ አየችኝና በቃ አሁን ደና ሆኛለሁ ሂድ አናግራትና ና እኔም ልቤ እርፍ ይበልልኝ እኔኮ አሞኝ ስለቆየሁ ድንጋጤ ንዴት ጭንቀት ሲያጋጥመኝ ስለሚጥለኝ ነው እንጂ ደና ነኝ ሂድ እስቲ መቼስ በጤናዋ እንዲህ አላደረገችም ምክንያቷን ጠይቃት ለወደፊት መማሪያ ይሆንሀል ሂድ አለችኝ።

እዛ ተቀምጬ የባሰ ጭንቀት ልሆንባት ስላልፈለኩ ተነስቼ ወጣሁ ልእልት እስከበር እየተከተለች እንዳትቆይ እሺ አደራ እቴቴ ደና አትመስለኝም አደራ አደራ አለችኝ።
ዞሬ እንኳን ላያት ስላልፈለኩ በእጄ ወደዛ ሂጂ የሚል ምልክት ሰጥቻት ግቢውን ለቅቄ ወጣሁ።
ፋኖስጋ ተደጋጋሚ ጊዜ ደወልኩ አታነሳም በመልእክት አንዴ እንኳን እንድታናግረኝ ለመንኳት ጭራሽ አትመልስም ሲጨንቀኝ ጓደኛዋጋ ደወልኩና ቢያንስ ምክንያቷን ብቻ ትንገረኝ ለሌላ ጊዜም ትምህርት ይሆነኛል በናትሽ ብዬ ተማፀንኳት ና በቃ የተለመደው ቤት ነን አለችኝ።

እንደ እብድ እያደረገኝ የነገረችኝ ቦታ ሄድኩኝ ስደርስ ሁሉም ተሰብስበው ቆዝመው ተቀምጠዋል።

ሁሉም እኔን ሲያዩ ተነስተው ብቻዋን ትተዋት ቦታ ቀይረው ተቀመጡ የሆነ ወንድ አብሯቸው አለ።

ከፊት ለፊቷ ሄጄ ቁጭ ስል እልህ ውስጤን ተናንቆኝ ሰውነቴ መንቀጥቀጥ ጀመረ።

ምንም ሌላ ነገር ልልሽ አደለም ግን ምክንያትሽን ብቻ ንገሪኝ አልኳት።

የፌዝ ሳቅ ፈገግ አለችና ታስታውሳለህ ከአመት በፊት የሆነች ቀይ እንቡጥ ለማየት ምታሳሳ ፀጉሯ በጀርባዋ የተነሰነሰ አደለም ለመምታት ለማየት ምታሳሳ ያያት ወንድ ሁሉ የሚመኛት አንዴ በሳቀች ብሎ ሰው ሁሉ የሚጠብቃት ልጅ እእ ለኛ ቤተሰብ ደሞ የመሳቃችን ምክንያት እሷ ነበረች።
እናትና አባቴ ለመፋታት ጫፍ ደርሰው እሷ በመረገዟ ምክንያት ትዳራቸው ስለቆየ ስጦታ ብለው ስም አወጡላት በቃ ለቤታችን ስጦታ ናት እሷ ከተወለደች ጀምሮ ቤታችን በረከት በበረከት ሆኖ ነበር።
ያ ለመፍረስ ጫፍ የደረሰው ትዳር እንዳዲስ የሰው ምሳሌ የሚያስቀና ትዳር ሆኖ ነበር።

ሁሉም ነገር ግን ነበር ለምን አትለኝም ባንተ ምክንያት ነው ለችኝ የሚፈሰውን እንባዋን ካይኗ ላይ እየጠረገች።

እንዴት??? ነገሮች ይበልጥ ተወሳስበውብኝ በአግራሞት እየተመለከትኳት ነበር።



ይቀጥላል...



🔻ክፍል1️⃣0️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ የፍቅር ጥግ ክፍል 9 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ

                        ክፍል  
8️⃣


በነጋታው ልክ ከፋኖስጋ እንደተገናኘን የጓደኛዋን ስልክ ሰበብ ፈልጌ ወሰድኩባትና ጓደኛዋን ማውራት ጀመርኩ።
ልደቷ በሚቀጥለው ወር ላይ እንደሆነ ነገረችኝ አጋጣሚ ሆኖ ሚውለው እሁድ ቀን ነበር በደስታ ብዛት ላብድ ምንም አልቀረኝም።
ቀጣዮቹን ጊዜዎች እንዴት ወጥሬ ሰርቼ
ለሷ ፕሮግራሙን እንደማዘጋጅላት እያሰብኩ መተኛት መነሳቱን ተያያዝኩት።
ወሩ ሁላ ረዘመብኝ ፋኖስ ሁሌ ምትሄድበት ቤት ስላለ እዛ ይዛኝ ሄዳ ቁጭ ብለን እያወራን የልደቷን ቀን እንዴት ማሳለፍ እንደምትፈልግ ጠየኳት።
ልደት የማክበር ልምድ ስለሌለኝ ተኝቼ ነው ምውለው ስትለኝ ይበልጥ ደስ አለኝ ካላሰበችበት እንደውም ለኔ ጥሩ ሰርፕራይዝ  ይሆንልኛል ብዬ ተደሳሰትኩ።
ለሷ ፕሮግራሙን እንደማዘጋጅላት እያሰብኩ መተኛት መነሳቱን ተያያዝኩት።
ወሩ ሁላ ረዘመብኝ ፋኖስ ሁሌ ምትሄድበት ቤት ስላለ እዛ ይዛኝ ሄዳ ቁጭ ብለን እያወራን የልደቷን ቀን እንዴት ማሳለፍ እንደምትፈልግ ጠየኳት።
ልደት የማክበር ልምድ ስለሌለኝ ተኝቼ ነው ምውለው ስትለኝ ይበልጥ ደስ አለኝ ካላሰበችበት እንደውም ለኔ ጥሩ ሰርፕራይዝ  ይሆንልኛል ብዬ ተደሳሰትኩ።

ለእናቴና ለጓደኞቼ ነገርኳቸው ሁሉም ያንን ቀን በጉጉት እንደሚጠብቁ ነገሩኝ።
የሷንም ጓደኞች የዛን ቀን ሰርፕራይዝ እንደምናረጋት ነገርኳቸው ሁሉም ደስተኞች ነበሩ።
እናቴ ቤት እናዘጋጅላት ፈጣሪ ይመስገን ቤታችን ቆንጆ ነው አያሳፍርም አደል እንዴ አለችኝ።
በደስታ ተስማምቼ ፕሮግራሙን ቤት ለማድረግ ወሰንና ቀኑ ሲደርስ ቤት ዝግጅቱን ጀመርን።
እኔ ቀኑ እስከሚደርስበት አምስት ቀናት ውስጥ እንቅልፍ አልወሰደኝም ሁሉም ነገር ብርቅ ሆነብኝ አንዳንዴ ሌሊት ላይ እየተነሳሁ እንዴት እንደምንበረከክ ሁላ እየተለማመድኩ ብቻዬን እስቃለሁ።

የፕሮግራሙ ቀን 8 ሰአት ላይ ቤት እንድትመጣ ነገርኳት ልእልት ከዋዜማው ጀምሮ ከኔ በላይ ከእናቴጋ እየተጋገዘች ሁሉንም ነገር ስትሰራራ ነበር።

የፋኖስ ጓደኞች ከሷ ቀደም ብለው መጡ የኔም የስራ ባልደረቦች ተገኙ።
እኔ የሆነ ጭንቀት ውስጤን ተናነቀኝ።
ዝም ብዬ መቅበዝበዜን ያየችው እናቴ እቅፍ አደረገችኝና ልጄ እራስህን እያየኸው ነው አደል እንደልጅ እየተቅበዘበዝክኮ ነው አለችኝ። ፈገግ ብቻ ብዬ ዝም አልኳት።

ሰአቱ ደረሰ ፋኖስ ደውላ እየመጣች እንደሆነ ነገረችኝ።
መጣች። መጀመሪያ ዝምብለን ልደቷን ሰርፕራይዝ ያደረግናት እንዲመስላት ስትገባ ቀለል አድርገን ሰርፕራይዝ አልናት በፍፁም እንዳልጠበቀችና ደስ እንዳላት ሆና አለቀሰች። አቅፌ አባበልኳት።
ለልደቷ የተዘጋጀውን ኬክ ከመቁረሷ በፊት እኔ የጋብቻ ጥያቄዬን ማቅረብ ስለነበረብኝ ሁሉም በአይናቸው አሁን አሁን ጠይቃት የሚል ምልክት ሲሰጡኝ
ሳታስበው ከኋላዋ ተንበርክኬ በፍርሀት ውስጥ እንዳለሁ ታገቢኛለሽ ብዬ ጠየኳት።

በውስጤ የልጅነት ህልሟን የሁልጊዜ ፍላጎቷን ስላሳካሁላት ምን ያህል እድለኛ ወንድ እንደሆንኩ እያሰብኩ ነበር።

እሷ ግን ልክ ከፊት ለፊቷ ተንበርክኬ ጥያቄውን ሳቀርብላት ቃል ካፏ ሳይወጣ ወደጓደኞቿ ዞረችና ከት ብላ ሳቀች ጓደኞቿም አላስቻላቸውም አብረዋት ሳቁ..........

ግራ ገባኝ ምን እየተካሄደ እንዳለ እኔ ከተንበረከኩበት ሳልነሳ የሁሉንም አይን በየተራ እያየሁ ምንድነው ፋኖስ ታገቢኛለሽ ብዬ እየጠየኩሽ ነውኮ አልኳት።
እሱኮ ነው ያሳቀኝ አየህ አደረኩት ፊት ለፊቴ አንበረከኩህ ይቺን ቀን ለማየት አመት ከምናምን መጠበቄ እራሱ ቆጭቶኛል ግን አደረጉት አንበረከኩህ ብላ በእልህ እየተናገረች እንባዋ ካይኗ ጠብ ጠብ አለ።
ጓደኞቿ እኔን በግልምጫ እያነሱ እየጣሉ እሷን አየሽ አንቺ አውርተሽ አልተውሽውም አሳካሽውኮ ጀግና ነሽ በቃ ለምን ታለቅሻለሽ እያሉ ይዘዋት ወጡ እኔ ነገሩ ህልም እየመሰለኝ ዝም ብዬ እናቴን አይን አይኗን እያየሁ ቆምኩኝ።
ወዲያው ተመልሳ መጣችና ለሌላ ጊዜህ ግን ሰዎች ላይ አትበጣጠስ ምድር ላይ ያለሁት ወንድ እኔ ብቻ ነኝ አትበል እሺ የምድራችን ባዶው ወንድ አንተ ነህ ብላ ተመልሳ ወጣች እኔ እየሮጥኩ ተከተልኳትና ምን እያወራች እንዳለች ጠየኳት ላንተ ማብራራት የለብኝም ምክንያቱም አንተ ለኔ ምንም ነህ ብላ ጥላኝ ወጣች የሚተናነቀኝን እንባ ዋጥ አድርጌ ወደቤት ተመልሼ ገባሁ ።

እናቴ መሬት ላይ ወድቃ ከበዋት እንድትረጋጋ እየነገሯት ነበር እሷ ዝም ብላ ታቃስታለች  እየሮጥኩ ሄጄ እማዬ እማዬ እያልኩ ከወደቀችበት ለማንሳት ስሞክር ልጄ በሰው ፊት አዋረደችህ አደል እኔ ባይኔ ሙሉ ለማየት የምሳሳልህን ልጄን ሰው ፊት አንበርክካ ጥላህ ሄደች ምን አርገሀት ነው ልጄ አንተ ለሰው ክፉ አታስብ ምን ሴጣን አሳስቶህ ምን ጥፋት ሰርተህ ነው አለችኝ እያለቀሰች የእናቴን ንግግር ስሰማ እኔ ሳግ እየተናነቀኝ አብሪያት ማልቀስ ጀመርኩ።  
አንስተን ወደመኝታ ቤት ወስደን አስተኛናት ዶክተር ልጥራ ወይ ሀኪም ቤት ልውሰድሽ ስላትም አሻፈረኝ ስትል ምንም ማድረግ አልቻልኩም።
ጓደኞቼ ምንም አታረጉም ሂዱ በቃ ብያቸው መቆየት ቢፈልጉም አስኬድኳቸው።

እኔ ከእናቴ አጠገብ ቁጭ ብዬ አስሬ ትንፋሿን ቼክ እያደረኩ.....



ይቀጥላል...



🔻ክፍል 9️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ የፍቅር ጥግ ክፍል 8 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ

                        ክፍል  
7️⃣
 

ጥሩ በቃ ተጫወቱ እማዬ እኔ ልተኛ ነው ብያት ብድግ አልኩ እናቴ ግን እጄን ያዘችና አስቀመጠችኝ።
ምነው እማ ፈለግሽኝ አልኳት።

አዎ አንድ ነገር ልነግርህ ነው ባንተ ፊት ቃል ላስገባት ነው አለችኝ።
ማንን???
እስካሁን ስሟን እንኳን አታቀውም አደል ልእልት ትባላለች ።
ልጄ እኔ አንድ ቃል የማስገባችሁ ነገር ቢኖር እኔ የሆነ ነገር ብሆን አይበለውና ብሞት እሷን ጓደኛ ጎረቤት እናት አድርገህ ትከሻዋን ተደገፋት አንቺም ልእልቴ በምትወጃት እናትሽ ይዤሻለሁ ልጄን ተቆጣኝ ገላመጠኝ ብለሽ ፊቲሽን እንዳታዞሪበት ምንም ሁኔታ ውስጥ ቢሆን አደራዬን ላንቺ ነው የሰጠሁት በምድር የሰጠሁሽን ቃል በሰማይ እቀበልሻለሁ ይሄንን ቃሌን እንዳትረሱ አለች።
እናቴ ተናግራ እስክትጨርስ እኔ ቀድሞ እንባዬ ፈሶ አለቀ።
በጣም ስለተናደድኩ ተነስቼ ተቻት ወጣሁና አልጋዬ ላይ ተዘረርኩ አላስችልህ ሲለኝ ደሞ ተመልሼ ሄድኩና እማዬ ሁለተኛ ይሄ እኔ ብሞት ወይ የሆነ ነገር ብሆን የምትይውን ነገር ደግመሽ ከተናገርሽው እንጣላለን ሁለተኛ እንደዚህ ስትይ ከሰማሁሽ ደግመሽ ፊትን አታይውም ቆይ እኔ ተጨንቄ እንድሞት ነው እንዴ ምትፈልጊው ደሞስ ቆይ ካልጠፋ ሰው ለዚች ዘገምት ነው አደራ ምትሰጭኝ እእ እኔኮ ፍቅረኛ አለኝ በቅርቡ ሚስቴ ላደርጋት ነው ታዲያ ይቺ ምን ቤት ናት ደሞ እሷን ብሎ ልእልት በስርአት ማውራት እራሱ አትችልምኮ ብያት ተመልሼ ወጣሁና ሳሎን ቁጭ ብዬ ቴሌቪዥን መመልከት ጀመርኩ።
ትንሽ ቆየት ብለው እናቴና ልጅቷ ተያይዘው መጡ እናቴ ተነስና ትምህርት ቤት አድርሰሀት ና አንተጋ መኪና እያለ ለምን taxi ትጠብቃለች አለችኝ።

ውስጤ ቅጥል እያለ ቢሆንም እሺ ብያት ቁልፈን አንስቼ  ወጣሁ ።
ልጅቷ ቅርፍፍ እያለች መጣችና ጋቢና ገብታ ቁጭ አለች።

ልክ ከግቢ እንደወጣን ውረጂና በእግርሽ ሂጂ ልላት ፈልጌ ነበር ግን እናቴ ስትሰማ ምን እንደሚሰማት አሰብኩና እዛው ትምህርት ቤቷ አደረስኳት።

ስትወርድ ፊቴን እንኳን አላየችውም ቻው ወይም አመሰግናለሁ እንኳን አላለችኝም።
ይባስ እየተናደድኩ ወደቤት ለመመለስ መኪናውን እያዞርኩ እናቴ ደወለችና አንድ ክላስ ብቻ ነው ያላት ቢበዛ 45 ደቂቃ ነው በዛው ይዘሀት ና አለችኝ ።
እየማልኩ አላረገውም እማዬ አልኳት።
እሷ ግን ግግም አለች ልጄ ትራንስፖርት የያዘችውን ብር ቅድም ለኔ ቡና ገዛዝታበት መጣች እሰጥሻለሁ ብያት እረስቼውኮ ነው አለችኝ።

እየሳኩ አይ እማ ቤቱን የሞላው ቡና አደል እንዴ ያ ሁሉ ቡና እያለ ለምንድነው ምትገዛልሽ ብዬ መለስኩላት።

አደለምኮ ልጄ የሌለኝ መስሏት ነው እንጂ እኔ አጥቼ አደለምኮ አሁን 45 ደቂቃ መጠበቅ ከብዶህ ነው ይሁን በቃ አንተ እንደፈለክ አላስቸግረህ ተወው አለችኝ።

እንደከፋት ስለገባኝ እሺ በቃ እማዬ በሰው መኪና እኔ ምን እንቢ አስባለኝ በቃ ይዣት እመጣለሁ ቻው ብያት ስልኩና ዘጋሁትና ተመልሼ ያወረድኳት ቦታ ላይ ቆምኩኝ።

ፋኖስጋ ደውዬ ማውራት ጀመርን እንደለመድነው ምን እንዳወራን እንኳን በቅጡ ሳላውቅ 1ሰአት ከሀያ አውርተናል እኔ 10 ደቂቃ እራሱ ያወራኋት አልመሰለኝም ነበር።
ልክ ልጅቷ መጥታ መኪናዬ ፊት ለፊት ስትቆም ነው ያወራነውን ሁላ የተመለከትኩት።

ፋኖስን ተሰናብቻት ስልኩና ዘጋሁትና ከፍቼ አስገባኋት ።
እየተመለስን ምነው 45 ደቂቃ ነው ምትቆየው ብላኝ ነበርኮ እማ አንቺ ስንት ሰአት እንደቆየሽ ታውቆሻል አልኳት።

ዝም አለችኝ።
ንቀቷ ከምንም በላይ አናደደኝና ጥጌን ይዤ ቆሜ ውረጂ ከመኪናው ጭራሽ እኔን ማውራት እየደበረሽ ነው አብረሽኝ ምቴጂው አልኳት።

እንዳጎነበሰች ይቅርታ አለችኝ።
በፈጣሪ ስም ስንት አይነት አድርቅ ሰው አለ የሷ ግን ይለያል ።
ቤት ስንደርስ ከመቼው ከመኪናው ወረዳ እናቴጋ ሄዳ መሳሳቅ እንደጀመሩ አላውቅም ብቻ ግን መኪናውን እንኳን በስርአት እስካቆም የጠበቀችኝ አይመስለኝም ።

እኔም ችግሯ በትክክል ከኔጋ እንደሆነ ስለገባኝ ትቻቸው ገብቼ ለጥ አልኩኝ ።
ተኝቼ ሳስበው የነበረው ለፋኖስ ቀለበት ማስርላት መቼ ነው እንዴት አድርጌ ግሮግራሙን ላዘጋጀው ሚለውን እያሰብኩ ነበር እንቅልፍ የወሰደኝ።





ይቀጥላል...



🔻ክፍል 8️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ የፍቅር ጥግ ክፍል 7 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ

                        ክፍል  
6️⃣
 

በደስታ ተስማማች እንደ እብድ አደረጋት አለምን የገዛች ያህል እንደተሰማት ነገረችኝ።
እኔም ወስጄ ከእናቴጋ አስተዋወኳት እናቴና እሷ እረጅም አመት እንደሚተዋወቅ ሰው በአንዴ ተግባቡ እኔም ያንን ደስታቸውን ሳይ በጣም ደስ ብሎኝ በፈገግታ እየተመለከትኳቸው ነበር።
ፋኖስ ልክ ፈጣሪ የጨለመው ህይወቴን አይቶ ብርሀን ትሆነኝ ዘንድ እሷን ስለላከልኝ አመሰገንኩት የመጀመሪያዬ ስለሆነ ይሁን ወይ የኔ የተለየ ፍቅር ሆኖ አላቅም ግን አብረን ውለን ባንለያይ ደስታዬ ነው ሳገኛት አይኔን ካይኗ ላይ ለደቂቃ መንቀል አልፈልግም አስቸኳይ ስራ ኖሮኝ እሷ ከደወለችልኝ ትቼ ወደሷጋ ነው ምሄደው በየቀኑ ማለት በሚያስችል ሁኔታ ከሷ የሆነ ስጦታ ይሰጠኛል።

ፍቅር እብድም ጅልም ነው ሞኝ ያደርገናል ምንም ነገር እንዳይታየን እውር የሚያደርገንም ነገር አለ።
እኔ ከስራ ቀርቼ እሷም ከስራ ቀርታ ቀኑን ሙሉ አብረን እንውላለን እንደዛም ሆኖ እኔ አልጠግባትም ቤት ገብቼ ሌሊቱን ሙሉ ለእናቴ ስለሷ እያወራሁላት ባድር ደስታዬ ነው።

ጠዋት ላይ ከእንቅልፌ ተነስቼ ወደስራ በመሄድ ፋንታ እሷ ወዳለችበት መሄድ ነው ምፈልገው።
አንድ ወንድ ከሴት ልጅ የሚመኘውን በሙሉ ሰታኛለች ህይወት ውስጥ በነበረኝ ደስታ ላይ እጥፍ ደስታን ጨምራልኛለች ብቻ ለምን አስከዛሬ ሳላፍቅር ቆየሁ ፍቅር እንደዚህ ደስ ይላል እንዴ ብዬ እስክገረም ድረስ ለኔ ልዩ ሴት ነበረች በፍቅሯ አብጃለሁ ለማለት ስድስት ወር ብቻ ነበር የበቃኝ በነዛ ወራት ውስጥ እኔ ስወለድ አብራኝ ተወልዳ አብራኝ አድጋ ሁሌም ከጎኔ የነበረች ሴት እንደሆነች ያህል ነበር  የተሰማኝ ።

ገና ስንገናኝ ፊቷን አይቼ ስሜቷን አቀዋለሁ እሷም እንደዛው ሰው ፊት ሳናወራ ተያይተን ብቻ እንግባባለን።

ልክ ከእናቴጋ ስሆን የሚሰማኝን ነፃነት እሷጋም አገኘዋለሁ ብር ቢኖረኝ ባይኖረኝ ግዴላትም የኛ ዋናው ነገር መተያየታችን ብቻ ነው ።

ብቻ እናቴ በኔ ፀባይ እስክትገረም ድረስ  በወጣሁ በገባሁ ቁጥር አፈዘዘችህ አደል እያለች መቀመጫ እስክታሳጣኝ ከልቤ አፈቀርኳት።

ፋኖስ ሁሌ ምትነግረኝ አንድ ነገር ከለ ጓደኞቼ በተሰበሰቡበት ያንተም ጓደኞች ተሰብስብው ተንበርክከህ ታገቢኛለሽ ብለህ ስጠይቀኝ ያለውን ደስታ ሳስበው በቃ እኔጃ ያንን ቀን አይቼ ብሞትም አይቆጨኝም ለኔ ምድር ላይ ሚያጓጓኝ ያ ቀን ብቻ ነው ትለኛለች ይሄ ንግግሯ በተገናኘን ቁጥር ካፏ ጠፍቶ አያቅም እኔም እንደምንም ብዬ ለሷ ቀለበት ለማሰር መሯሯጥ ጀመርኩ ።


ቀኑ እሮብ ነበር ፋኖስ አሞኛል አንገናኝም ስትለኝ በጣም ደብሮኝ ስለነበር የሚሰራውን የከስተመር መኪና ይዤ ወደቤት ሄድኩ ሰአቱ ሰባት ወይ ስምንት ቢሆን ነው።
ስደርስ እናቴ ከጎረቤታችን ልጅጋ የሞቀ ጨዋታ ይዘው ፍንድቅድቅ እያሉ ይሳሳቃሉ ።
እናቴ አልጋ ላይ ጋደም ብላለች።
ልጅቷ ደሞ ሙሉ እቃውን መኝታ ቤት አስገባብታ ቡናዋን እያፈላች  ከአልጋው ስር ካጠገቧ ቁጭ ብላለች ።

ልክ ስገባ እናቴ እርፍ ብላ እንደዛ እየተፍለቀለቀች ሳያት ደስ አለኝና ሄጄ ሳምኳት ሁሌም እንደዚህ ሳቂልኝ እሺ ብያት አጠገቧ ቁጭ አልኩ።

እናቴ ገልመጥ አድርጋኝ ሰላም በላት እንጂ አላየሀትም እንዴ አለችኝ።
የውሸት ፈገግ እያልኩ ውይ ይቅርታ አላየሁሽም ነበር ደናነሽ የጎረቤቴ ልጅ አልኳት።
አንገቷን ደፍታ ደና ነኝ አለችኝ።




ይቀጥላል...



🔻ክፍል 7️⃣1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔


ክፍል 6 ሊለቀቅ ነው ከታች ያለውን ሊንክ start ያላደረጋችሁ ፍጠኑ start አድርጉት

http://t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref930303744


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

       ❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ ❤️

ፀሀፊ ✍️ ማኔ

                        ክፍል  
5️⃣
 
እንዲሁ እየተወዛገብኩ ካሁን ካሁን ደወለች ወይ መልእክት ላከች ብዬ ስልኬን እያየሁ ቤት ደረስኩ።
ቤት ስገባ የጎረቤታችን ልጅ ከእማዬጋ ቁጭ ብለው ከት ብለው ይሳሳቃሉ እኔ ስገባ ግን ልጅቷ ሳቋም ጥፍት አለ ከተቀመጠችበት ብድግ አለችና በቃ ክላስ እረፈደብኝ እቴቴ ቻው ብላት ቀና ብላ እንኳን ሳታየኝ ወጣች ከመጀመሪያውም ተናድጄ ስለነበር ለእናቴ ቆይ ይቺ ዘገምተኛ ልጅ ግን ያማታል እንዴ ምንድነው እኔ ስገባ እያሮጠ ሚያስወጣት ልጠልዛት እንዴ አልኳት።

አይ እንግዲ ስርአት በሷ ቀልድ የለም ልጄ እንደው እስከዛሬ ብዙ ሰው አውቃለሁ ግን እንደሷ ንፁህ ልብ ያለው ምስኪን ልጅ አይቼ አላቅም ልቧ ከእንቁ የከበረ ነው ውስጧ እንደወተት ነጭ ነው ክፋት አይቶት አያቅም አደራህን እንደው ካፍህ ክፉ ቃል ወጥቶ እንዳታስቀይማት አደራ አለችኝ።

እሺ በቃ ልተኛ ነው ብዬ ልገባ ስል ና ቁጭ በል በምን ተናደህ ነው አለችኝ
ነገሩን ነግሪያት የባሰ ከሷጋ መጨቃጨቅ ስላልፈለኩ  አረ ደክሞኝ ነው እማ እረፍት ላድርግ በናትሽ እእ ትንሽ ብቻ ብያት ገብቼ ተኛሁ ወዲያው ስልኬ ላይ መልእክት ገባልኝ ።
ካሁን ቡሀላ አላስቸግርህም ቃሌ ነው ደህና ሁን ይላል።
አይቼው ዝም አልኩኝ።
ግን ነገሩ ከሶስት ቀን አላለፈም ነበር ደግማ መልእክት ላከች< እውነት ለመናገር ልረብሽህ ፈልጌ አልነበረም ግን ከዚህ በላይ ዝም ማለት አልቻልኩም ከፈለክ አውራኝ ከደበረህ ዝም በለኝ> ብላ ላከችልኝ።

እስከማታ ዝም ብያት ቆየሁና እኔ ዝም ብልሽ አንቺ ዝም ትይኛለሽ አልኳት።
አይ እኔ ዝም አልልህም እስከሞት ድረስ ላንተ እፋለማለሁ አለችኝ።
በቃ ያንን መልእክት ካየሁ ቡሀላ መሳቅ ማቆም አቃተኝ በትርፍ ሰአትሽ ኮሜዲ ትሰሪ ነበር እንዴ ብዬ መለስኩላት።

ከብዙ መዘጋጋት ከዛ መልሶ ማውራት ቦቻ ከብዙ ልመና ቡሀላ እኔም እየለመድኳት መጣሁ ።
ተቀጣጠርንና በድጋሜ ተገናኘን እንደተለመደው ውብ ሆና ነበር የመጣችው ቁጭ አድርጌ  ሁሉንም አወራኋት ከልጅነቴ ጀምሮ ፍቅረኛ ኖሮኝ እንደማያቅ እናቴ ኮራ ጀነን ያልኩ ወንድ እንድሆን አድርጋ እንዳሳደገችኝ በህይወቼ አንድም ቀን አፍቅሬ ወይም የፍቅር ስሜት ተሰምቶኝ እንደማያቅ ነገርኳት።

በቃ የልብህን ድንግልና ለኔ ስጠኝና ዘላለሜን እንደፋኖስ እያበራሁልህ አብረን እንኑር አለችኝ።
እንደዚህ ስተለኝ በድጋሜ ከት ብዬ ሳኩና ልብም ድንግልና አለው እንዴ አልኳት።

ቀላል አሁን ምላሽህን ንገረኝ አለች።
ባሁን ሰአት ምንም ልላት እንደማልችልና ግን እንደስከዛሬው እንደማልዘጋት እንደጓደኛ እንደምቀርባት ምናልባት ለሷ የፍቅር ስሜት እንዲሰማኝ ካደረገች አብሪያት እንደምሆንና ያንን ማድረግ ካልቻለች ግን እንደምንለያይ ነገርኳት።

በራሷ በጣም እርግጠኛ ነበረች አታስብ ማመን እስኪያቅትህ ድረስ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ነው ፍቅር የሚይዝህ አለችኝ።

ኮንፊደንሷ ደስ እንደሚል ነግሪያት አብረን ጊዜ አሳለፍን።

ከዛ ቀን ቡሃላ ጠዋት በእናቴ ፈንታ ከእንቅልፌ ምትቀሰቅሰኝ እሷ ሆነች ምሳ ሰአት እንኳን ምሳ መብላት እንዳለብኝ ምታስታውሰኝ እሷ ሆነች።
በተገናኘን ቁጥር የሆነ ስጦታ ይዛልኝ ትመጣለች ።
በፍፁም ያልተገባ ነገር አታደርግም ረጋ ያለች ናት ከኔጋ አብራኝ እየሄደች በተአምር አይኗ ሌላ ወንድ ላይ አያርፍም።
አክብሮቷ ላቅ ያለ ነው እኔ አጥፍቼ ቀድማ ይቅርታ ምትጠይቀኝ እሷ ናት አትወደኝም እንዴ ብዬ እስክጠራጠር ድረስ ትልቅም ትንሽም ጥፋት ባጠፋ ቀድማ ይቅርታ ትጠይቀኝና ሼም ታሲዘኛለች።

ስራ ቦታ ካሉት ጓደኞቼጋ  ካስተዋወኳት ጊዜ ጀምሮ ሁሉም ጓደኞቼ በጣም ነው ሚወዷት ስትመጣ በፍቅር ነው ሚቀበሏት እኔም እንዳለችው እሷን ለማፍቀር ብዙ ጊዜ አልፈጀብኝም ነበሮ ግን የፍቅር ስሜት በራሱ ምን እንደሆነ ስለማላቅ ከራሴ ስሜትጋ እየታገልኩ ነበር የቆየሁት።

በመጨረሻም እኔ እራሴ አብረን እንድንሆን ጠየኳት።
(እናቴ ከልጅነቴ ጀምሮ የሰው ልጅ አጥብቆ የፈለገው ነገር መጥፊያው ነው ትለኝ ነበር)
.
.
.
ይቀጥላል

10 ሰው ከታች ያለውን ሊንክ start ካደረጋችሁ ክፍል 6 አሁን ይለቀቃል ፍጠኑ

(ሊንኩ ምንድን ነው ለምትሉ አዲስ game ነው መስራት እምትፈልጉ ይጠቅማችዃል ስሩ መስራት እማትፈልጉ ደግሞ start በማድረግ አብሮነታችሁን አሳዩን)

http://t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref930303744



🔻ክፍል
6️⃣ከ 1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀

💔 
https://t.me/yefikirtelegramet 💔


እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ የፍቅር ጥግ ክፍል 5 ሊለቀቅ ነው አላችሁ ወይ?


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ

                        ክፍል  
4️⃣
 

ቆሜ ማወራው ነገር ግራ እንደገባኝ አለቃዬ መጣና በቃ እንሂድ አሪፍ ነው የሰራነው ዛሬ መኪናው እኔጋ ይደር በዛውም ልሸኝል አለኝ።

እሺ ብዬ ትቻት ልገባ ስል አሳዘነችኝና የት ነው ቤትሽ እንሸኝሽ አልኳት።
ነገረችን እኔም እሷም ከኋላ ገባን ንዴቴ ስላልበረደልኝ እየደጋገምኩ ድጋሜ እዚህ ቆመሽ እንዳታመሽ ሰፈሩ እንኳን ለሴት ለወንድ ያስፈራል አልኳት።

እንደዛ ከሆነ ስልኬን ከብሎክ አውጣው አልጨቀጭቅህም አላስቸግርህም አንዳንዴ ብቻ ድምፅህን እንድሰማው ነው ብላ ስትለምነኝ እሺ ብዬ ስልኳን ከብሎክ አወጣሁት በዛውም ሰፈሯ ደርሰን ስለነበር ተሰናብታኝ ከመኪናው ወረደች።

እሷ ከወረደች ቡሀላ አለቃዬ እየሳቀ አይ ይች አለም በቃ ፍትሀዊ አደለችማ።
አንተ ሴት አትቀርብ ሴት አጠገብህ ቆማ እራሱ አታስታውላትም ሴቶች ግን አንተን ነው ሚከተሉት ምነው ላንተ ከሚያሽቃብጡ እኛንም ቢመለከቱን አለና ተሳሳቅን።

ሰፈር አድርሶኝ በዛውም እናቴን ገብቶ ሰላም ብሏት ሄደ ደክሞኝ ስለነበር ቶሎ ነበር የተኛሁት።
ጠዋት እንደተለመደው እናቴ ቀስቅሳኝ አርፍጄም ቢሆን ወደስራዬ ሄድኩ ።
ቀኑን ሙሉ ስራ ባይኖርም ውስጥ ቁጭ ብለን ነበር የዋልነው ማታ ላይ ከስራ ስወጣ ልጅቷ መንገድ ላይ እንደምጠብቀኝ ተስፋ አድርጌ ነበር ግን የለችም የሆነ እቃ እንደረሳ ሰው ቅር ቅር አለኝ።
ቤት እንደገባሁ ዛሬኮ ታምሜ ነው ላይህ ያልመጣሁት ይላል መመለስ ስላልፈለኩ ዝም ብያት ተኛሁ።
እንዲሁ ፊልም እንደሰራችብኝ ድጋሜ ሌላ ሳምንታቶች ተቆጠሩ እኔም ልክ ከስራ ስወጣ የሆነ ነገር እንደሚጠብቀኝ ነገር ልቤ ስቅል ይላል ግን ደሞ ስልክ መደወል text መመለስ ወይ ስትደውልልኝ ማንሳት አልፈልግም።

ድንገት ግን ምን እንደተፈጠረ ሳላቅ ለአስራአምስት ቀን ያህል ጠፋች በየቀኑ እንደምትመጣ ተስፋ እያደረኩ ከስራ እወጣለሁ ግን የለችም ከዛሬ ነገ ትደውላለች ብዬ ጠበኩ እሷ በፍፁም መልእክት እራሱ ሳትልክልኝ ስለቆየች ድንገት የሆነ ነገር ተፈጥሮባት ቢሆንስ ብቻ መጨነቅ ጀመርኩ መሰለኝ ለእናቴ ነገርኳት ምነው አንተ በዚህ ልክ ይጨከናል እንዴ የሆነ ነገር ሆና ቢሆንስ ታማም ሊሆን ይችላል ባትወዳት እንኳን ድንገት ምታቀው ሰው እንደዚህ ቢሆን ያስችልሀል በል ደውልላት ብላ ተቆጣችኝ።
እኔ ግን መደወሉ ሞት መስሎ ታየኝ  አልደውልም ብዬ ከተውኩት ቡሀላ የእናቴ ውትወታ አላስቀምጥ ሲለኝ ስልኬን አንስቼ መልእክት ላኩላት

በሰላም ነው የጠፋሽው የሆንሽው ነገር አለ እንዴ ?ብዬ ላኩላት

ፅፌ መጨረሴንና መላኬን እርግጠኛ ባልሆንኩበት ቅፅበት አዎ ደናነኝ ብላ መለሰች።
ዝም አልኳት።
ቀጠለችና  መልእክት በድምፅ መላክ ቢቻል ምን ያህል ደስ እንዳለኝና መልእክቱን ሳየው እንዴት እንደጮኩ ብታይ ደስ ይለኝ ነበሮ አለች።
በድጋሜ አይቼው ዝም አልኩ።

ድጋሜ ሌላ መልእክት።
አለመኖሬን ማስተዋልህ ገርሞኛል እኔኮ ማታ ማታ እዛ ስቆም ብርድ መቶኝ ታምሜ ተኝቼ ነበሮ ከስራም ተባረርኩ ታምሜ ብዙ ቀን በመቅረቴ አባረሩኝ።
በጣም ከፍቶኝ ነበር መልእክትህን ሳየው ልቤ እንዴት እንደመታ
ይላል።

መልእክት ተከታታይ ስትልክ ደበረኝና ደና ደሪ ብዬ ላኩላት።

ደና ደር ከቻልክ ነገ ስራ ከሌለህ እንገናኝ እኔ ማታ መጥቼ እንዳልጠብቅህ ድጋሜ በሽታዬ ይነሳብኛል አለችኝ።

ሲመቸኝ አሳውቅሻለሁ በቃ ድጋሜ መልእክት እንዳትልኪልኝ ብዬ ላኩላት።

በዛው አመረረችና ለሳምንት ያህል ዝም ስትለኝ ድጋሜ በኔ ምክንያት ታማ ይሆን እንዴ ብዬ ሲጨንቀኝ ነገ ቅዳሜ ስለሆነ ከሰአት ስራ አንገባም ከሰአት ላግኝሽ ብዬ መልእክት ላኩላት እሺ ስንት ሰአት አለችኝ 8 ሰአት ብዬ መለስኩላት።

በነጋታው 6.30 ሲል ስራ ቦታህጋ መጥቻለሁ እስክትወጣ እየጠበኩህ ነው ብላ ላከችልኝ።
ስምንስት ሰአት እንደተቀጣጠርንና አሁን ለምን እንደመጣች ጠየኳት።

አይ የምር ልታገኘኝ መሆኑን ስላላመንኩ እዚህ ተቀምጬ ልጠብቅህ ብዬኮ ነው ሀሰብ እንዳትቀይር ፈራሁ ችግር የለም እስከ ስምንት ሰአት እጠብቅሀለሁ ብላ መለሰችልኝ።

ሳቄ መጣ ያማታል እንዴ ይቺ ደሞ ከሁሉም የባሰች ናት ብዬ ከራሴጋ አወራሁና ልብሴን ቀያይሬ ተጣጥቤ ወጣሁ እዛው ቅርብ የነበረ ቤት ይዣት ሄድኩ ፊት ለፊት ለፊት ለፊት ተቀመጥን አይን አይኔን ስታየኝ እኔም ትኩር ብዬ አየኋት።

በጣም ቆንጆ ናት ድርብ ጥርስም አላት ፀጉሯም የራሷ ነው በዛ ላይ በጣም እረጅም ነው በውስጤ እሷን እያደናነኩ ለማውራት ግን ጅንን አልኩባት።
በዛ መሀል አስተናጋጇ መጥታ ምን ልታዘዝ አለችኝ እኔ ምንም አልፈልግም አልኳት እሷ ግን አረ ምሳኮ አልበላሁም አትበላም እንዴ አለችኝ
ውጭ ምግብ በልቼ እንደማላቅ ነገርኳት እሺ በቃ እኔም አልበላም አመሰግናለሁ አለች።

ያምሻል እንዴ አሁን ምሳ አልበላሁም አላልሽም መልሰሽ አልበላም ማለት ምን ማለት ነው አልኳት።
አይ እኔኮ አብረን እንበላለን ብዬ አስቤ ስለመጣሁ ነው አሁን ግን በቃኝ አልበላም አለች።

ለማንኛውም ፈጣሪ ያመመሽን ህመም ያርቅልሽ ደና መሆንሽን ለማወቅ ነው ዛሬ የቀጠርኩሽ በኔ ምክንያት የታመመሽ መስሎኝ ጥሩ ስሜት ስላልተሰማኝ ነው ደና ከሆንሽ ደና ሁኚ በቃ ድጋሜ እንዳትደውይ እኔም መልእክት አልክልሽም በዚህ ሰአት ስራዬ ላይ ማተኮር ነው ምፈልገው አንቺ ደሞ ነፃነቴን እያሳጣሽኝ ነው ብያት በተቀመጠችበት ጥያት ወጣሁ።

አልተከተለችኝም መኪና ውስጥ እየሄድኹ ግን ከራሴጋ ክርክር ጀመርኩ አንዱ ልቤ ደግ አደረክ ይለኛል ሌላኛው ልቤ ደሞ ልክ አላደረክም ወንድ የሆንክ መስሎህ ነው ይለኛል




ይቀጥላል...



🔻ክፍል 5️⃣ 1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔

4.2k 0 14 1 198

እንዴት አመሻችሁ ቤተሰብ የፍቅር ጥግ ክፍል 4 ሊለቀቅ ነው
እስከዛው አዲሱን project start እያደረጋችሁ ጠብቁን


‼️Guys  zoo የተባለ አዲስ airdrop መቷል    የ X-empire አጋር project  ነው

‼️ከዚህ በፊት የ x-empire ባለቤት there is something in the future ማለቱ አይዘነጋም

‼️በደንብ ለሰራ X empire  ጥሩ ክፍያ የከፈለ airdrop እንደነበር አይታችሁል

‼️ ገና መጀመሩ ነው ብዙ ሰው ሳይጀምረው  ካሁኑ ጀምሩ አሪፍ ገንዘብ  ታገኙበታላችሁ


👇👇👇👇

t.me/zoo_story_bot/game?startapp=ref930303744


      🔸🔸🔺🔺🔹🔸

      
❤️ የፍቅር ጥግ ❤️

ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ  ታሪክ
❤️

ፀሀፊ
✍️ ማኔ

                        ክፍል  
3️⃣
 

እሷ ተስፋ የቆረጠች አትመስልም በነጋታው ድጋሜ አንድ ወረቀት ሰታኝ ሄደች ከዛሬ ቡሀላ ስራ ስለምጀምር ማታ ማታ ነው ላይህ ምመጣው 11ሰአት ነው ከስራ ምወጣው ከዛ እዚህ መጣለሁ ይላል።
የልጅቷ ጤነኝነት አሳሰበኝ በዛ ላይ እኔ ቋሚ የመውጫ ሰአት የለኝም አንዳንዴ ቀን ወደቤት ልመለስ እችላለሁ አንዳንዴ ደሞ እስከ ምሽቱ ሶስት ሰአትም ልንሰራ እንችላለን የጀመርነው መኪና አስቸኳይ ከሆነና አላልቅ ካለን ሳንጨርስ አንወጣም  ።

በነጋታው አውቄ አስር ሰአት ሲል ወደቤት አመራሁና እማዬን ይዣት ወደቤተክርስቲያን ሄድኩ ቁጭ ብለን የልብ የልባችንን አወራን።

እናቴ ሆድ እየባሳት አንተም ለኔ እኔም ላንተ ብቻኮ ነው ያለነው እኛው ነን ለኛ ያለነው አደል ድንገትኮ አንዳንችን የሆነ ነገር ብንሆን  ብቸኛ ሆነን መኖራችን ነው ለምን ፍቅረኛ አትይዝም ለምን አታገባም ለኔም ቡና ሚያፈላልኝ ሰው እፈልጋለሁ ቀን ቀን ብቻዬን ተኝዬ ስውልኮ እየጨነቀኝ ነው ስራ አለህ ,እንደምታየውም ያማረ ግቢ አለን ልጅኮ በልጅነት ነው አለችኝ።
እሺ ተነሽ ወክ እናድርግ ቤት ላድርስሽና አንድ ቦታ ደርሼ ልምጣ ብያት ወደቤት ተመለስን እሷን ቤት አስገብቼ እኔ ቀጥታ የሰፈራችን ደላላጋ ሄድኩና ለነገ ግዴታ ሰራተኛ ያስፈልገናል ነገ በጠዋት ሰው አምጣልኝ አልኩት።

እሱም አላሳፈርኝም በነጋታው ስራ ቦታ ሆኜ ደወለና ሰው አግቼልሀለሁ   መጥተህ ውሰድ አለኝ ስራ ስላልነበረኝ በፍጥነት ሄድኩና ወደቤት ወስጄ  ከእናቴጋ አስተዋወኳት ይኸው ቀን ቀን ቡና ምታፈላልሽ ምታዋራሽ ልጅ አምጥቼልሻለሁ አልኳት።

እናቴ ክፍት ብሏት አይ አንተ ልጅ እኔ አሁን ሰራተኛ ቅጠርልኝ አልኩህ እእ ቆይ አንድ ቀን ምግብ እንኳን ውጭ በልተህ ማታቅ ልጅ በሌላ ሰው እጅ የተሰራ ምግብ እየበላህ ለመኖር ዝግጁ ነህ አለችኝ።
አዎ እማዬ አሁን አንቺ እረፍት አድርጊ እኔ እለምዳለሁ ምን ችግር አለው ምግብ ምግብ ነው አልኳት።

ጥርሷን ነክሳ ቆይ አንተን በሚመስል አስተያየት እያየችኝ ልጅቷን ጠራችና የወር ደሞዟን ጠየቀቻትና ከደሞዟ በላይ ጨምራ ብር ሰጥታ ይቅርታ ስላስለፋንሽ ግን እኔ ሰራተኛ አልፈልንም እሺ አላድክመሽ በል ሸኝተሀት ና ደላላውጋ ብላ ከቤት አስወጣችን
እኔም ወስጄ ልጅቶን ለደላላው መልሼ በደንብ ይቅርታ ጠይቄ ተመለስኩ።

ቤት ስደርስ በቅጡ እንኳን አስተውያት የማላቃት የጎረቤት ልጅ ከእማዬጋ ቁጭ ብላ ከጣራ በላይ ይሳሳቃሉ።
እኔ ስገባ ልጅቷ አይኗን መሬት ላይ ተክላ ዝም አለች ያ ሁሉ ሳቅ ባንዴ ጥፍት አለ።

እናቴ ጠራችኝና ኑ በደንብ ተዋወቁ እኔ አንድም ቀን ደብሮኝ አያውቅም እሷ ሁሌም ከኔጋ ናት ከፍሪጅ እያወጣሁ አሙቄ ምሰጥህ ምግብ እሷ የሰራችው ነው እንደው ምን እንዳደረካት ባላቅም እንደጦር ነው ምትፈራህ ዛሬ እንኳን ደፍራ አይንህን ትየው በዛውም እኔ ትናት ቀን ቀን አብሮኝ የሚውል ሰው ያልኩህ እንድታገባ ልጫን ፈልጌ እንጂ የምር ደብሮኝ እንዳልሆነ እንድታቀው ነው አለችኝ።

እኔም ልጅቷን ሄጄ ሰላም አልኳት እጇን ስጨብጣት ከመንቀጥቀጡ የተነሳ  ጎንደረኛ እየጨፈረች ሰላም ምትለኝ ሁላ ነበር የመሰለኝ።
እናቴን ስለምትከባከብልኝ እያመሰገንኳት ካፌ ሳልጨርሰው ዝም ብላ እየሮጠች ከቤት ወጥታ ሄደች
ሁኔታው ግራ ገብቶኝ እማዬ ደሞ ምንድነው ከእንደዚች አይነት ህፃንጋ ምትውይው ደሞስ እብድ ናት እንዴ እያወራሁ ምን ያሮጣታል አልኳትና ቁጭ ብለን ማውራት ጀመርን።

በሚቀጥለው ቀን አንድ አስቸጋሪ መኪና ገጥሞን ከጠዋት ጀምሮ እሱን ስንሰራ ዋልን አንዴ ስንገጥም መልሰን ስንፈታ ወገባችን መቆም እስኪያቅተው ሰራን እኔና አለቃዬ ብቻ ስለቀረን ማታ 2,30 አካባቢ ሰርተን ጨረስን እኔ ገብቼ እስክታጠብና ቱታዬን እስክቀይር አንተ ነድተኸው ና ብዬው እሱ መኪናውን ይዞት ወጣ ።
እኔም ጨራርሼ ስወጣ  አስር ጉዳይ ለሶስት ይላል ሰፈሩ ትንሽ መሸት ሲል ሰው ጭር ስለሚል ብዙም ደስ አይልም ድባቡ እስኪመጣ በር ላይ ቆሜ እየጠቀኩት ልጅቷ ጥጓን ይዛ በዛ ጨለማ ቆማ አየኋት በሰአቱ ምን እንደሆንኩ አላቅም እንደእብድ ፈጥኜ የቆመችበትጋ ሄድኩና በጥፊ አጋጨኋት ያምሻል እንዴ በዚህ በምሽት ለዛውም እዚህ ሰፈር ብቻሽን እንዴት እስካሁን ትቆያለሽ ሲጀመር ውስጥ መሆኔን በምን አወቅሽ አልኳት።
11 ሰአትኮ ነው የመጣሁት ቅድም ጓደኞችህን ጠይቄ ነው ውስጥ መሆንህን ያወኩት አለችኝ።
እና ብሆንስ ምን ሆነሻል የሆነ ነገር ብትሆኚስ ሌባ ቢሰርቅሽስ እራስሽን አትወጂውም እንዴ አልኳት።

አንተን ከምወደው በላይ እራሴን አልወደውም አለችኝ።
ቃላት ለማውጣት አፌ ሁላ ተያያዘ...


ይቀጥላል...



🔻ክፍል 4️⃣ 1️⃣5️⃣0️⃣ like በዃላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like💝 ማድረግ አይርሱ።
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀

      ‌‌‌‌‌‌‌      ይ 🀄️ላ🀄️ሉን!
😀

💔 https://t.me/yefikirtelegramet 💔

20 last posts shown.