The Home of all የሁሉም ቤት


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Edutainment


Well come to the home of all in this channel all things about human being life post every day
* Motivate for free
* learn for free
* earn more for free
Buy ads: https://telega.io/c/+LiBy-b_3bjIyMjk0
══════❁✿❁═════════

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Edutainment
Statistics
Posts filter


"መማር ምን ይሰራል" እያላችሁ አታናንቁ፤ የሆነ ጊዜ አለመማርም እንዲሁ የተናቀ ነገር ነበር፤ ይሄው ቀን ወጣለት!

🔊 Alex Abrham


እሺ ቀኑን እየጠበቅን ነው


Good morning

እሰከ አምና ድረስ ተማሪ እያለሁ ቅዳሜን በጣም ነበር የምወዳት አንድም ትምህርት የልም ሁለተኛ ኳስ አለ ሶስተኛ የገበያ ቀን ነው የሆነ ነገር ይገዛልናል (ልጅ እያለን) አሁን ግን ቅዳሜ እንደሌሎች ቀን ነው፣ እኔ አሁን ገና ከእንቅልፌ ተነሳሁ 😭 በነገራችን ላይ "ስራ ላለው ሰው አረፍዶ መነሳት እና ስራ ለሌለው ሰው በጥዋቱ መነሳት እኩል ነው የሚያናድዱት" እና ስራ ላጣን ስራ ይስጠን ከዚህ ከኢትዮጵያ ብርር ብለን መውጣት የምንፈልግ ደግሞ እናት ሃገር ዩጋንዳም ብትሆን ትጥራን😘 እስኪ እንደኔ ከ አውሮፓ እሰከ ኤስያ ለስደት በማጣራት መንገድ ሁሉ እዚህ ሆኖ የሄድ እቺ ምልክት 🔥 ነካ ያድርግ ብቻ መልካም ቀን ይሁንልን family.


///እናት ቀን የላትም///

ቀንሽን በሙሉ ለልጆችሽ ሰጥተሽ፣
የኔ የምትይው እናት ምን ቀን አለሽ።

ስለዚህም እኔ!

ላንች ቀን ተቆርጦ ቀኗ ነው ቢሉኝም፣
እናቴን ነው እንጅ ቀኗን አላከብርም።

ለምን ካላችሁኝ!

እድሜዋን በሙሉ ሳትሰስት ስትሰጠኝ፣
እሷ እየተራበች እኔን ስታጎርሰኝ።

የኖርኩ እኔ ልጇ!

ብዙ እልፍ ስቃዮች እንዳለፈች ባውቅም፣
ለኔ የምትለው እናት ቀን የላትም።

ገጣሚ ጊዜአለው ...✍️


❤እናቴ❤

አልገጥሽ እያሉ ቃላትና ቅኔ፣
ስላንች ስናገር ይዘጋል ልሳኔ።

እናቴ እወድሻለሁ❤
እናት ያላችሁ እድሜዋን ያርዝምላችሁ!


ሁሌም የናቶች ቀን ነው


Introduction መተዋወቅ

ሜሮን እባላለሁ የዚህ ምርጥ ቻነል Admin ስለሆንኩ ደስታዬ ወሰን የለዉም ከዛሬ ጀምሮ አሪፍ ቆይታ ይኖረናል ብየ አስባለሁ በ ድምፅ program ይኖረናል ብቻ የሁሉም ቤት የሁሉም መገኛ ነው ጠብቁን😍


ከዛሬ ጀምሮ የሚገርሙ Program ይጀመራል......


Female Admin approved


ግጥሜን አንብባችሁ፣
መጽሐፍ አውርዳችሁ፣

ላይክ ለገጫችሁ፣
እግዜር ይባርካችሁ።

ነገር ግን ...

ግጥሜን አንብባችሁ፣
ላይክ ያልገጫችሁ፣
ኩላሊት ተውሳ ...
አላውቅም የምትል ፍቅረኛ ይስጣችሁ፣

ብዬ አልራገምም አይደለውም ክፉ፣
ይልቅስ በፀጋ በሀብት ተትረፍረፉ።

በሉ ለይኩ😂

አወንታዊም ይሁን አሉታዊ አስተያየትችን በፀጋና ቀደስታ እቀበላለሁ። comment ስር አስቀምጥሉኝ


አረፍ....?


ሴት አላጣም ብለህ ከሚስትህ አትኳረፍ
                ተይ........!
ወንድ ሞልቷል ብለሽ ከባልሽ አትለይ

አንተም ሴት ባታጣ ፈላጊሽ ቢበዛም
ወርቅ እየተሸጠ መዳብ አይገዛም።

  .....✍ ታሮስ


በ17 አመትህ በጣም የወደድከው ሰው 25 ሲሞላህ ግድ አይሰጥህም፤ Freshman year የወደክበት ፈተና የመጨረሻው አመት ላይ ሆነህ ልትመረቅ ስትቃረብ ዋጋ አይኖረውም።

ዛሬ የሚያጋጥሙህ ችግሮች የዓለም ፍጻሜ ሊመስሉህ ይችላሉ ነገር ግን ምንም እንደማይከሰትና በዓመት ውስጥ ለውጥ እንደማያመጡ እርግጠኛ ሁን። ደህና ትሆናለህ..


         -መሐመድ አሊ


የ Spain ሙዚቃ ነው ካልተሳሳትኩ

Money heist film ያያችሁ እስኪ react


🥀.....አንቺ'ና ቁንጅናሽ.....👱‍♀
      
        እኔም ለኔ❤️‍🔥 ስልሽ
   ሌላም ሠው😌 ሢመኝሽ
    ተወዳድርኩ🥹 እኔም
      የግሌ 🥰ላደርግሽ
    ግና ምን😔 ያደርጋል
    መስፈርትሽ🤷 ይከብዳል
    እንኩዋን 🙋እኔ ቀርቶ
  እብዱም ደግሞ ያብዳል💔።


ዝምታዬን አንብብ!

(ሂወት ዘውዴ✍️)

ባሳየኸኝ መንገድ ብዙ ጊዜ ተጓዝኩ፣
ከህይወት ገጽህ ላይ ደስታዬን አተረፍኩ።

ፈካሁ እንደኮከብ ውስጤን ሃሴት ገባው፣
በመኖርህ ስሌት መኖሬን ገነባው።

እናም አንተ ማለት!
መንገዴ ደስታዬ መኖርና ህልሜ፣
ትላንቴ ዛሬዬ አልፎም ዘላለሜ።

የውስጤ ድምቀት ነህ የውበቴ ፀዳል፣
እንዳንተ ተደርጎ ማን ሰው ይወደዳል።

ምናምን እያልኩኝ ፍቅሬን ባልገልጥልህ፣
ታላቅ ሰው ነህና...
በዝምታዬ ውስጥ መውደዴን ታያለህ


የሊስትሮ እቃዬ

ረሀቤ ቢከሰኝ ~ ባዶ ሆዴን አይቶ
አፌ መሰከረ ~ ችሎት ላይ አዛግቶ

በህይወት ፍርድ ቤት...
የተሾሙት ዳኛ ~ መፃፉን ሲገልፁ
ያልሰራ አይብላ ~ ይል ነበር አንቀፁ

ይህንን ስትሰማ...
ፈጥና መጣችና ~ ሆና ጠበቃዬ
ከፍርድ አዳነችኝ ~ የሊስትሮ እቃዬ

እኔም እሱዋን ይዤ...
አንገቴን ለስራ ~ ጎንበስ እንዳረኩት
ችግሬን በብሩሽ ~ ሲጠረግ አየሁት

የኩራቴን በትር...
ወርውሬ ስጥለው ~ ከጄ ላይ ወደዛ
እንኳን የሰው ጫማ ~ የኔም ፊቴ ወዛ

ካመታት ቀጠሮ...
ከጊዜ በኃላ ~ የዋለው ችሎት
ጥረቴን አየና ~ ቢፈርድልኝ ሀብት
ከትቢያ ተነስተው ~ እንዲሉ ከማማ
እኔም በተራዬ...
ከላይ ተቀምጬ ~ አስጠረኩኝ ጫማ

እንግዲህ አዝናለው...
ባለውለታዬ ~ ክብሬ ነሽ እያልኩዋት
ከታች ያነሳችኝ...
የሊስትሮ እቃየን ~ ከላይ እረገጥኳት

እንግዲህ አዝናለሁ...
ውድዋ…………… የሊስትሮ ዕቃዬ
ምንም እንኩዋን ~ ብትሆኝ ባለውለታዬ

በጫማ ስረግጥሽ ~ አይክፋሽ ግድ የለም
ባታውቂው ነው እንጂ
ለዋለላት ሁሉ ~ እንደዚህ ናት አለም።

ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ)✍️


//// ስዬ ልጨርሰው ✍️


ባያድለኝ ከእግር ቆሜ ባልራመድ፡
በቤት ውስጥ አድጌ ከልጅ ባልዋደድ፡

ባልውል ከ እኩዮቼ ባልቦርቅ ዘልዬ፡
መቆምን ባላውቀው ብሄድም ቁጭ ብዬ፡

ወጉ እንኳን ባይደርሰኝ ጫማ ለመጫመት፡
በምኞት ቢያልፍም እንቡጡ ልጅነት፡

አላጉረመርምም ድምፄንም አውጥቼ፡
ጌታን አልኮንንም ወቀሳን አውርቼ፡

ብቻ እንዲሞላ እግሬ የጎደለው፡
ጠመኔዬን ይዤ ስዬ ልጨርሰው፡

የኔታ ፍቄ✍️

ከተመቻችሁ ለወዳጅ ዘመድ አጋሩት
@yehulum_bet


ማጭድ ይሆነን ዘንድ ምኒሽር ቀለጠ፣

ዳሩ ብረት እንጅ ልብ አልተለወጠ፣

ለሳር ያልነው ማጭድ እልፍ አንገት ቆረጠ።


በእውቀነቱ ስዩም✍️


ግጥሞች loading...


እስኪ like አድርጉ ቤተሰብ ልቀጥል ነው ዛሬ ፈታ እንላለን አብራችሁን ሁኑ 👍😍❤🔥


👖#የሱሪ_ዚኘ_ይዞት_ያስጮኸው_ያቀዋል😆

#ይሄ ህመም በጣም አሰቃቂና ከባድ ነው
በአሜሪካ 17; 000 ወንዶች ብልታቸው
የዙሪ ዚኘ ይዞት ድንገተኛ ክፍል ገብተዋል😇🤣 😂


የወደድኩትን ለእናንተ !!!

በ19 አመቱ በአሜሪካ ሚስጥራዊ አገልግሎት ሰርጎ በመግባት እና ብዙ የሀገሩን ሚስጥሮች ሰርቋል በሚል ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቦ 15 አመት ተፈርዶበት ህይወቱን በእስር ቤት እየመራ ይገኛል ።

አባቱ ብቻቸውን የሚኖሩ አዛውንት ነበሩ ። አንድ ቀን ድንች ለመትከል ፈልገው በእድሚያቸው መግፋት ምክንያት ጥንካሬ አልነበራቸውም ።

ከዚያም ለታሰረው ልጃቸው እንዲህ የሚል መልእክት ላኩ ።

"ውድ ልጄ የአትክልት ስፍራውን ለመቆፈር እና ድንች ለመትከል እንድትረዳኝ አሁን ከእኔ ጋር ብትሆን እመኝ ነበረ ። አሁን የሚረዳኝ የለኝም። "

ከተወሰነ ጊዜ በኋላ አባትየው ከልጃቸው ደብዳቤ ደረሳቸው።

"አባባ እባክህን አትቆፍር ፤ ምክንያቱም አንድ ጠቃሚ ነገር ስለደበቅኩኝ ከእስር ቤት ስወጣ ምን እንደሆነ እነግርሃለሁ።"

የልጃቸው መልእክት በተጻፈ በአንድ ሰአት ውስጥ የምስጢር አገልግሎቱ እና ሰራዊቱ ቤቱን ከበቡ።

በደቂቃዎች ውስጥ የአትክልት ስፍራውን ቆፍረው ሁሉንም ነገር አስወግደው ምንም ነገር ሳያገኙ ቤቱን ለቀው ወጡ።

ከሳምንት በኋላ ከልጃቸው ሌላ ደብዳቤ ደረሳቸው ።

"አባዬ መሬቱ በፖሊስ በደንብ እንደታረሰ ተስፋ አደርጋለሁ አሁን ድንች መትከል ትችላለህ ። ሌላ ነገር ስትፈልግ ኣሳውቀኝ ፤ የእስር ጊዜን ጨርሼ እስክመጣ ድረስ ካንተ ጋር መሆን አልችልም ነገር ግን በምችለው መንገድ ለመደገፍ የተቻለኝን አደርጋለሁ። "

20 last posts shown.