የቅዱሳን ታሪካቸው ህይወታቸው ትምህርቶች


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


⛪️1ኛ ቆሮንቶስ 6÷2፤ቅዱሳን፡በዓለም፡ላይ፡እንዲፈርዱ፡አታውቁምን፧በዓለምስ፡ላይ፡ብትፈርዱ፡ከዅሉ፡ይልቅ፡ትንሽ፡
ስለሚኾን፡ነገር፡ልትፈርዱ፡አትበቁምን፧
@Brkeyazew
@Brkeyazew
https://t.me/yekidusantarikachewhiywetachew

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


1⃣7⃣ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ


⁉️ጥያቄና መልስ
🌺🌺🌺🌺

'https://t.me/addlist/33Faa1YThXUwMjU0' rel='nofollow'>❤️፩. ኦርቶዶክስ ማለት ምን ማለት ነው?❤️

፪. ጌታ ለምን ድንግል ከሆነች ማርያም 'https://t.me/addlist/33Faa1YThXUwMjU0' rel='nofollow'>ተወለደ? (ለምን በድንግልና ተወለደ?)


⛪️የአባታችን የአቡነ #ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታሪክ

🥀 #ተራኪ ወንድም #ዘለአለም

💦የአባታችን የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከት አይለየን አሜን

🌹መልካም ቆይታ👂👆

https://t.me/yekidusantarikachewhiywetachew


"ሰላም ለልሳንከ ጽድቀ ሃይማኖት
ዘነበበ፤ ወለቃልከ ሰላም እንተ ያቀልል
ዕፀበ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለከ
መንግሥተ ሰማያት ተውህበ፤ እስመ
ኮንከ አባ ከመ አርዌ ምድር ጠቢበ፤
ወበይዋሄከ ተመሰልከ ርግበ፡፡

ሰላም ለእስትንፋስከ ሱታፌ
ማሕየዊ እስትንፋሱ፤ ልሳነ ዕፍረት
ጳውሎስ ፈዋሴ ዱያን በጽንፈ ልብሱ፤
ገብረ ኢየሱስ ክርስቶስ ወገብረ ቅዱስ
መንፈሱ፤ ይቶሳሕ በንፍሐትየ
ለእስትንፋስከ ጢሱ፤ ከመ ያንጽሐኒ
ለዓለም እምኵሉ ደነሱ፡፡"

አባቴ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ! እውነተኛውን
የክርስቶስን ሃይማኖት ለአስተማረ አንደበትህና ችግርን
ለሚያቃልል ሥልጣነ ቃልህ ሰላም እላለሁ፤ ቅዱሱ አባት ሆይ!
መንግሥተ ሰማያት ለአንተ ፈጽማ የተዘጋጀች ናት፤ በጠላት
ዲያብሎስ ዘንድ እንደ እባብ ብልህ ስትሆንበት በቅዱሳን
በኩል ልክ እንደ ርግብ የዋህ ሆነህ ተገኝተሃልና፡፡

ሰላም ለእስትንፋስከ

አባቴ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ!
ለሕሙማን በልብሱ ዘርፍ ፈውስ የሚሰጥ አንደበቱ ከመዓር
ከወተት የሚጣፍጥ በአምላኩ ኀይል አዳኝ ከሚሆን ከጳውሎስ
እስትንፋስ የማዳኑ ተባባሪ ለሚሆን እስትንፋስህ ሰላም
እላለሁ፤ ቅዱሱ አባት ሆይ! የኢየሱስ ክርስቶስና የባሕርይ
አባቱ የአብ የባሕርይ ሕይወቱ የመንፈስ ቅዱስ ታማኝ
አገልጋይ ነህና፡፡ ከዚኽ ዓለም ኀጢአት ንጹሕ ያደርገኝ ዘንድ
የእስትንፋስህ  ከእስትንፋሴ ጋር አንድነትን ይፍጠሩ፡፡ "

(መልክዐ ገብረ ሕይወት ገብረ መንፈስ ቅዱስ )

እንኳን አደረሳችሁ 🌹❤️


Forward from: 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤
እንኳን ለጻድቁ አባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደርሳቹ❗️

ጥቅምት 5-ኑሮአቸው እንደሰው ያይደለ በምድረ በዳ እንደመላእክት የኖሩትና በዝቋላ ተራራ ባለው ባሕር ውስጥ 100 ዓመት ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ሰዎች ምሕረትን የለመኑት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታላቅ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ዕለት ነው፡፡ 

አባታችን አራት ሺህ እልፍ እየሰገዱ፣ 300 ጊዜ የቀኝ 300 ጊዜ ደግሞ የግራ ፊታቸውን በድንጋይ እየመቱ፣ መዝሙረ ዳዊትን እየደገሙ፣ 15ቱን መኅልየ ነቢያት፣ መኅልየ ሰለምንንና ውዳሴ ማርያም እየጸለዩ ለኃጥአን ምሕረትን ሲለምኑ ዕንባቸው እንደ ውኃ ይፈስ ነበር፡፡ ጌታችንም ‹‹በተወለድሁባት፣ በተጠመቅሁባትና ከሞት በተነሣሁባት ዕለት እልፍ እልፍ ነፍሳትን እምርልሃለሁ›› የሚል ቃል ኪዳን ሰጣቸዉ

አምላካችን በቃል ኪዳናቸው ይማረን


✝️#ድምፀ_ተዋህዶ ✝️


Forward from: 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤
“አሁን ባለን የአስተዳደር ክፍተቶችና በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጎደላቸው አሠራሮች ለአገልግሎታችን እንቅፋት እየሆኑብን ነው”ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ገለጹ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት 43ኛው ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ለተገኙ ተሳታፊዎች መልእክት አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አሁን ባለን የአስተዳደር ክፍተቶችና በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጎደላቸው አሠራሮች ለአገልግሎታችን እንቅፋት እየሆኑብን ነው። በዚህ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን የሚታየውን  ችግር ለመፍታት በጥናት ላይ የተመሠረተ መፍትሔ ማምጣት ይገባል ሲሉ አፅዕኖት ሰጥተዋል፡፡

ቅዱስነታቸው ጨምረው እንደገለጹት ቅዱስ ሲኖዶስ ተግባራዊ እንዲሆን የወሰነውን የቤተ ክርስቲያን የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ ውጤታማ ለማድረግ ሁላችንም በትብብር መሥራት ይገባናል ብለዋል።

በዛሬው ዕለት የተጀመረው 43ኛው አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ከሀገር ውስጥ እና ውጪ ከሚገኙ አህጉረ ስብከቶች፣ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት እና ገዳማት እንዲሁም ከተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት የተወከሉ ተሳታፊዎች በተገኙበት እየተከናወነ ይገኛል።

#ድምፀ_ተዋህዶ


"" ባልንጀራዬ ማን ነው? "" (ሉቃ. ፲:፳፱)

(መስከረም 2017)


ወርሓዊ የጸሎት መርሐ ግብር ጥቅምት ፬/፪/፳፻፲፯ ዓ/ም ምሽት ፪ ሰዓት በጊዜ እንገናኝ ::
መርሐ ግብሩ
-ጸሎት
-ስንክሳር
-ካነበብኩት ላካፍላችሁ
-መዝሙር
- ጥያቄ እና መልስ

"ናሁ ሠናይ ወናሁ አዳም
ሶበ ይሄልዉ አኃው ኅቡረ
ከመ ዕፍረት ዘይውኅዝ እምርእሱ እስከ ጽሕሙ"

(መዝሙረ ዳዊት ፻፴፪)

https://t.me/felege_haymanott


✝አጭር መልእክት ፥ በገዳማት ጉዳይ፦


"" ልባችሁን አታጽኑ! "" (መዝ. ፺፬:፰)

"ዝክረ ቅዱስ ዳዊት ዘወርኀ መስከረም"

(መስከረም 23 - 2017)




Forward from: 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤
"በሰማይ የምትኖር ሆይ፥ ዓይኖቼን ወደ አንተ አነሣሁ፤ እነሆ፥ የባሪያዎች ዓይኖች ወደ ጌታቸው እጅ እንደ ሆኑ፥ የባሪያይቱም ዓይን ወደ እመቤትዋ እጅ እንደ ሆነ፥ እንዲሁ እስኪምረን ድረስ፡ ዓይናችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ነው'' መዝ. 122:1-3

#ድምፀ_ተዋህዶ

▫️https://t.me/dmtse_tewaedo


#መጋባት_ይሻላል

        
#ቀሲስ ፋሲል

8ላላገቡና ለመበለቶች ግን እላለሁ። እንደ እኔ ቢኖሩ ለእነርሱ መልካም ነው፤

9ነገር ግን በምኞት ከመቃጠል መጋባት ይሻላልና ራሳቸውን መግዛት ባይችሉ ያግቡ።

https://youtu.be/DbyfVE2xUqs?si=8z4ot-YgTpki0igd

@yekidusantarikachewhiywetachew


"" ጥበበኛስ ማን ነው? "" (፩ ቆሮ. ፩:፳)

"ነገረ መስቀሉ"

"ተግሣጽ - ክፍል ፪/2"

(መስከረም 21 - 2017)


❀ስንክሳር
"ዘወርኀ መስከረም ፳፯/27"

"❀ኦ ማርያም (መዝሙር)"

"❀ጸሎተ ምቅናይ"

(መስከረም 26 - 2017)








Forward from: 🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤
#እንኳን #ለፆመ_ጽጌ በሳላም አደረሳቹህ

✤ወርኃ ጽጌ 40 ቀናት ነው፤ መስከረም 26 ተጀምሮ ኅዳር 5 ያልቃል፤ ጾመ ጽጌ የፈቃድ ጾም ነው (ከሰዓትም ቅዳሴ የሚቀደሰስባቸው አካባቢዎች አሉ (ጎንደር )፡፡
በግዕዝ ጸገየ ማለት   አበበ ፤ አፈራ ፣ በውበት ተንቆጠቆጠ ማለት ነው፡፡ 
በማኀሌቱም ወቅትን እመቤታቸንን 3 ዓመት ከ6 ወር እስከ ግብፅ ከዚያም የአሥራት ሀገሯ  በሆነችው በኢትዮጵያ የተሰደደችበትን ወቅት በማሰብ  በጽጌና በአበባ እመቤታቸንን እና ጌታቸንን በመመሰል ሲያመሰግኗት ፣  ከልጇ ጋር ያየችውን መከራ  እያሰቡ  እና  ምልጃዋን ሲለምኑ ያድራሉ ፡፡

✤እምግብጽ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን፤ ለቅዱሳን ክብር ልጄን ከግብጽ ጠራሁት››
በማለት ነቢዩ ሆሴዕ በምዕራፍ ፲፩ ቍጥር ፩ እና ፪ ላይ አስቀድሞ እንደ ተናገረው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በልጅነቱ ወደ ምድረ #ግብጽ (ምስር) የተሰደደው የነቢያት ትንቢት ይፈጽም ዘንድ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሕፃናትን በመፍጀት ከሚታወቀው ከአረመኔው ንጉሥ ከሄሮድስ ለማምለጥ ነው፡፡ አምላካችን ክርስቶስ ያለጊዜው (ዕለተ ዓርብ) #ደሙ #አይፈስምና፡፡ ስለዚህም ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ምድረ ግብጽ ሽሽ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ለመግደል ይፈልጋልና›› ብሎ መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል ለዮሴፍ በነገረው ቃል መሠረት ሕፃኑንና እናቱን ይዞ በሌሊት ወደ ግብጽ ምድር ተሰደደ፡፡ ይህንን ስደት አስመልክቶ #ሰቆቃወ ድንግል የሚባለውን ቃለ እግዚአብሔር ካህናቱ በሚያሳዝን ዜማ ያደርሳሉ፤ ያቀርባሉ፡፡

#በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ሕፃናትን ሄሮድስ አስፈጅቷል፡፡ ‹‹ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ለቅሶና ብዙ ዋይታ፡፡ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፡፡ መጽናናትም አልወደደችም፤ የሉምና›› የሚለው ትንቢትም ተፈጸሟል፡፡

#ከሦስት ዓመት ከመንፈቅ የግብጽ ስደት በኋላ ሊቃውንቱ፡- ‹‹ተመየጢ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፣ በላዕሌኪ አልቦ ዘያበጽሕ ሁከተ፣ ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፣ ዘየኀሥሦ ለወልድኪ ይእዜሰ ሞተ፣ በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ›› እያሉ ከስደት መመለሷን ያበሥራሉ፡፡ ትርጉሙም፡- ‹‹ማርያም ሆይ! ወደ ሀገርሽ ወደ ናዝሬት ተመለሺ፡፡ በአንቺ ላይ ሁከት የሚያመጣ ማንም የለም፡፡ ቤት እንደሌለሽ ሁሉ በግብጽ አትቆይ፡፡ ለዮሴፍ በሕልሙ መልአክ እንደ ነገረው የሕፃኑን ነፍስ የፈለገው (ጠላት ሄሮድስ) ሞቷልና›› ማለት ነው፡፡ የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በዐርባው ቀን (በዘመነ ጽጌ) ወቅት የማርያምን የሽሽትና የመመለስ (የሚጠት) ታሪክ እያነሡ ውዳሴ የሚያቀርቡትና ማኅሌት የሚቆሙት በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ በዚህ ወቅት ለእመቤታችን ክብር ሲባል የፈቃድ ጾም የሚጾሙ ምዕመናንና ምዕመናትም ብዙዎች ናቸው በመሃል ኢትዮጵያ  በፈቃድ ጾምነት ሲጾም ; በሰሜኑ አካባቢ ተጹሞ ከሰዓት ይቀደሳል ሌሎች ጋር ግን ጠዋት ያበቃል፡፡

የእመቤታችን ምልጃ ና ጸሎት አይለየን

#ማኅሌተ_ጽጌ
✤የማኅሌተ ጽጌ  የሰቈቃወ ድንግል ደራሲ አባ ጽጌ ድንግል ነው ፡፡
  ገዳሙም ትልቅና ሰፊ የኾነ የፍልፍል ዋሻ ሲኾን ወሎ ወግዲ ወለቃ ወንዝ አጠገብ በረሃ ላይ (ከጋሥጫ ገዳም የ4 ሰዓት የእግር መንገድ) ይገኛል፡፡
✤✤ በየዓመቱ ሳይመረገዱ ያመይታለፉ የማይቀሩ፤ ዚቃቸው የማይለወጥ፤
      እጅጉን በምንወደው የማኅሌተ ጽጌ ቁመት ላይ በየዓመቱ ሳይመረገዱ የማይታለፉ የማይቀሩ፤ ዚቃቸው የማይለወጥ
( ከማኅሌተ ጽጌ፤ ጽጌ አስተርአየ(የመጀመሪያው ሳምንት)፣ በከመ ይቤ መጽሐፍ፣ ትመስል እምኪ ማርያም፣ ዘኒ ስብሐተ ወዘኒ ማኅሌተ፣ ኢየሐፍር ቀዊመ ቅድመ ሥዕልኪ እና ኅብር ሐመልሚል (የመጨረሻው ሳምንት)ናቸው፡፡
✤ ከሰቈቃወ ድንግል፤ በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ፣ ብክዩ ኅዙናን፣ እስከ ማዕዜኑ እግዝእትየ እና አብርሂ አብርሂ ናቸው፡፡
✤ከማኅሌተ ጽጌ ውስጥ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ እና ክበበ ጌራ ወርቅ በየሳምንቱ (በኹሉም ዓመታት) ይመረገዳሉ፤ ዚቁ ግን በዓሉን በተመለከተ ይኾናል፡፡
✤ ከላይ ካየናቸው ውጪ የሚገኙት #የማኅሌተ ጽጌና የሰቈቃወ ድንግል ክፍሎች ግን #በየሰባት ዓመት አንዴ ነው የሚመረገዱት፡፡
( የማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤

የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ የማኅሌት ቁመትም የላይ ቤትን አብነት የተከተለ ሲኾን የዚቁ ወረብ ግን የደብሩን የራሱን (የሸዋን) የተከተለ ነው፤
( የላይ ቤት ቁመት የሚቆሙ አድባራት #ዘግምጃ ቤት የሚለውን እንዲከተሉ፤ የታች ቤትን #ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘበዓታ የሚለውን እንዲከተሉ፡፡ የዚቁ ወረብን ግን የቀጨኔ ደብረ ሰላም
የቤቱን ቀለም አስቀድመን ቀጥሎ ደግሞ ዓዲ (ወይም) በማለት የጎንደርን ስላስቀመጥነው እንደ ደብራችሁ ይትበሃል መርጣችሁ  ተጠቀሙ፡፡

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/

    #ድምፀ_ተዋህዶ

https://t.me/dmtse_tewaedo


|°°ለጀማሪ የግእዝ ቋንቋ ወዳጆች ሁሉ
  🙌 ሰላም ጤና ይስጥልን ክቡራት እና ክቡራን የልሳነ ግእዝ ስልጠና በ @lesangeez128 እየሰጠን እንደሆነ ይታወቃል ሆኖም የጀማሪዎች ስልጠና  በቅርቡ በonline ስለሚጀመር በዚህ #ዙር ላይ 20 ተማሪዎች ብቻ ስለሚካተቱ ከወዲሁዠለጀማሪችሁን እንድታዘጋጁና በፍጥነት እንድትመዘገቡ መልእክታችንን እናስተላልፋለን።
#ለሁለት ወር የመማሪያ ክፍያ #250ብር ብቻ ለበለጠ መረጃ በ @asrategabriel ያነጋግሩን አልያም በ +251970908094 ይደውሉልን።

   🤲ሰብሕዎ የልሳነ ግእዝ ማሰልጠኛ ተቋም🧑‍🎓

20 last posts shown.