✞ ጋሜል - የመዝሙር ግጥሞች ✞


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


✟ የኦርቶዶክሳውያን መንፈሳዊ የምስጋና ቤት ✟
ቤተ ክርስቲያንን አንተውም ከቶ
የሰጠንን አምላክ በደሙ መስርቶ
የሰጠንን ጌታ በመስቀሉ ሞቶ
የአምላካችንን ቤት አንተውም ከቶ
ለማስታወቂያ ሥራ➝ @Naolviva
💿 የተዋሕዶ የመዝሙር ግጥሞች 💿
   ✍ / ትምህርቶችን ለማግኘት ✍
👇👇👇
https://t.me/maedot_ze_orthodox

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


✞ ማርያም ብዬ ✞

ማርያም ብዬ እዘምራለው
እንደ አባቶቼ እጠራታለው
በያሬድ ዜማ በአዲሱ ቅኔ
ልዘምርላት በዕድሜ ዘመኔ (፪)



ማርያም ብዬ በእሳት መታጠቂያ ታጥቋል ባለቅኔ
ማርያም ብዬ መንፈስ ይማርካል ማኅሌት ገንቦ
ማርያም ብዬ በወርቁ ፅናላይ አርጓል ፀሎቴ
ማርያም ብዬ ባአማኑኤል እናት በአንቺው በእመቤቴ

           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

ማርያም ብዬ በክብር ደመና ተሞልቷል መቅደሱ
ማርያም ብዬ ድንግል የአንቺ ምልጃ ስቦናል ወደሱ
ማርያም ብዬ ሆነሽ ተገኝተሻል ሁለተኛ ሰማይ
ማርያም ብዬ ጌታ ከአንቺ ወቷል የጽድቃችን ፀሐይ

           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

ማርያም ብዬ አልጠግብም ስጠራሽ ማር ነሽ ለከንፈሬ
ማርያም ብዬ ሳሊለነ እያልኩሽ አለው እስከዛሬ
ማርያም ብዬ ፀጋሽ ቤቴን ሞልቶ ተትረፈረፈልኝ
ማርያም ብዬ ሐዘን እና ለቅሶ ከኋላ ቀረልኝ

           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►

ማርያም ብዬ የባለጋራዬ ምሽጉ ፈረሰ
ማርያም ብዬ በመስቀል ስር ክብሬ እንባዬ ታበሰ
ማርያም ብዬ አልፈራም ከንግዲ አለችኝ መከታ
ማርያም ብዬ ቁስሌን የምትፈውስ እስሬን የምትፈታ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ማርያም ተዐቢ ✞

ማርያም ተዐቢ እምኲሉ ፍጥረት [፪]
ኢያውዐያ እሳተ መለኮት [፪]

መላእክት በሰማይ ፊቱ የሚቆሙት
ክንፋቸውን ለብሰው የሚሸፈኑት
ባይችሉ ነው የአምላክን ፊት ማየት
ማርያም ግን ችላዋለች በእውነት

ኢያውዐያ እሳተ መለኮት [፪]

ልብሱ እሳት የኾነ ቀሚሱ እሳት
አጅግ የከበረ ኃያል መለኮት
ተዘረጋ ሰባቱ መጋረጃ
በሆድሽ ውስጥ የሰላም መታወጃ

ኢያውዐያ እሳተ መለኮት [፪]

ሙሴ በተራራ ጫማውን አውልቆ
ለመቆም ተስኖት ነበረ ተደንቆ
ዕፀ ጳጦስ አንቺ ነሽ በሐዲስ ኪዳን
የታቀፍሽው አሳተ መለኮትን

ኢያውዐያ እሳተ መለኮት [፪]

ሙሴ እግዚአብሔርን ስላነጋገረ
ሕዝቡ ፊቱን ሊያየው እጅግ ተቸገረ
ድንግል አንቺ ታቀፍሽ ይህን መለኮት
እንዴት ልቻል ብሩህ ፊትሽን ለማየት

ኢያውዐያ እሳተ መለኮት [፪]

ማርያም ተዐቢ እምኲሉ ፍጥረት [፪]
ኢያውዐያ አሳተ መለኮት [፪]

             መዝሙር|
        የአእላፋት ዝማሬ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ
!

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ ​​የብርሀን ደጅ ናት ✞

የብርሀን ደጅ ናት ድንግል እናታችን
ከሰማይ እያበራች ደስ አለው ልባችን
ፍቅርሽን ሰላምሽን ድኅነት ይኹነን ኦኦ
ፍጥረት /በሙሉ/[፪] ፊትሽ ይወድቃሉ
ፀጋሽ ይድረሰን[፪] ይሰጠን እያሉ


        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
የእኔ ልብ ምን ጽድቅ አለው አንቺ ለማስተናገድ
የኃጢአት ጎተራ ነው የተሞላው በስስት
ኧረ እንዴት[፪] ድንግል ትኑርበት ኦኦ
አትጸየፍም የእኔ ልብ ታሰናዳዋለች
ስለኃጥአቴ የእኔ እናት ምልጃ ታቀርባለች

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ልባቸውን የዘጉ ድንግልን ለማስገባት
ሕሊናቸው ይመለስ እንጸልይ ለዚህ ጥፋት
አምላክን ይዛ ነው ድንግል የምትመጣው ኦኦ
እሷን ስንመልስ ጌታን ነው የምናስቀይመው

             መዝሙር|
        የአእላፋት ዝማሬ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ
!

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ ቂርቆስ ለወዳጁ ✞

ለወዳጁ ቂርቆስ ለወዳጁ
ያነሳዋል ላደገ ከደጁ
በብርቱ ሰልፍ ለእኔ ሆኖ ብርቱ
ሰው አርጎኛል በምልጃው ሰማዕቱ(፪)


እንደ ቤተልሔም ቤቱ ነው ልደቴ
ማረፊያዬም እርሱ ናዝሬት ሰገነቴ
አንዳች ያልነበራት ቤቴ ተጎብኝታ
አወጀች ለክብሩ የድሉን እልልታ
    ውበት ማዕረጌ
    ቆምኩኝ አደግድጌ
    ቂርቆስ ቂርቆስ ብዬ
    ታብሷል እንባዬ


       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ግሩም ቃልኪዳኑ በውስጤ እየሰራ
ሜዳ ያረግ ነበር ግዙፉን መከራ
አበባ ነው ስሙ ዕፍራን የተባለ
ስንቱን አልፎ አየው ቂርቆስ ቂርቆስ ያለ
    ውበት ማዕረጌ
    ቆምኩኝ አደግድጌ
    ቂርቆስ ቂርቆስ ብዬ
    ታብሷል እንባዬ


       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በወዳጅ ንክሻ ሲዛነፍ ሰላሜ
ገድሉን እየሰማሁ ቀለለ ሸክሜ
በናቀኝ ዓለም ፊት  አርጎኝ ባለዋጋ
ጨለማውን ይኸው ሰማዕቱ አነጋ
    ውበት ማዕረጌ
    ቆምኩኝ አደግድጌ
    ቂርቆስ ቂርቆስ ብዬ
    ታብሷል እንባዬ


       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ከማውጀው ቃላት ንግግር በላይ ነው
በመውጣት መውረዴ ቂርቆስ ያደረገው
ዛሬን ለመዋጀት መሠረት ሆነና
መጽሐፈ ዜናውን ቃኘው እንደገና
    ውበት ማዕረጌ
    ቆምኩኝ አደግድጌ
    ቂርቆስ ቂርቆስ ብዬ
    ታብሷል እንባዬ


       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ውለታውን ሳስብ እንባ ካይኔ ይፈሳል
ስለ እርሱም ስከትብ ብዕሬ ኅይል ያጣል
ከመቅደሱ ጽድቅን ታጥቄ በረከት
አጉራሼ ሰማዕቱ ይታያል በኔ ፊት
    ውበት ማዕረጌ
    ቆምኩኝ አደግድጌ
    ቂርቆስ ቂርቆስ ብዬ
    ታብሷል እንባዬ


            መዝሙር|
  ዘማሪ ዲያቆን ገዛኸኝ ኤርባ

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ ድንግል ሆይ ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ ✞

ድንግል ሆይ ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆናል
እመቤቴ ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እንዴት ይሆናል
ደካማ ነኝ እኔ ምግባር ይጎድለኛል [፪]

ወደ ተራራማው ይሁዳ ከተማ
ፈጥነሽ ስትመጪ ድምፅሽ የተሰማ
የኤልሳቤጥ ዘመድ የዘካርያስ
ድምፅሽን አሰሚኝ በአንቺ ልቀደስ

          አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በማኀፀንሽ ይዘሽ የሰማይ እንግዳ
አንዴት ትመጫለሽ ከታናሽዋ ጓደ
አንዴት ልቀበልሽ እምላኬን ይዘሽ
መንፈስ ቤቴን ሞላው ሲሰማ ድምፅሽ

          አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በሥጋዊ ሳይሆን በመንፈስ ዓይኖቼ
ለማየት እሻለሁ ከልቤ ጓጉቼ
ሥራዬ የከፋ መሆኑን አውቃለሁ
ድምፅሽን ለመስማት አጅግ እፈራለሁ

          አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
አንቺ ቡርክት ነሽ ቡሩክ የአንቺ ፍሬ
ላመንሽዋ ብፅዕት ትዘምር ከንፈሬ
ፅንሰን ደስ አሰኘ የድምፅሽ ሰላምታ
ለዚህ ታላቅ ነገር ይገባል እልልታ

          አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በሁሉ የሞላው ዙፋኑ ቢያደርግሽ
የመላእክት መዝሙር ተሰማ ከሆድሽ
ሁለተኛ ሰማይ ድንግል ማርያም
በአንቺ ድንቅ አድርጓል መድኃኔዓለም

             መዝሙር|
        የአእላፋት ዝማሬ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ
!

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ እንተ በምድር ✞

እንተ በምድር ሥርዊሃ ወበሰማይ አዕጹቂሃ (፪)
ሐረገወይን(፪) ድንግል ሐረገወይን


ትርጉም፦
ሥርችዋ በምድር ጫፎችዋ በሰማይ የሆነ
የወይን ሐረግ ድንግል ማርያም ናት



✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ
!

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ ቃል በቃሉ ተናገራት ✞

ሥጋዋን አንጽቶ በማርያሞ አደረ
ቃሉን በነቢያት ቀድሞ ያናገረ
ቃሉን በነቢያት ቀድሞ ያናገረ
ቀድሞ ያናገረ

ቃል በቃሉ ተናገራት [፪]
ማርያምን አከበራት
እግዚአብሔር መረጣት
ቃል ተናገራት


        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ፍጥረታት በሙሉ ያመሰግኑሻል
የሕይወታችን በር ድንግል ናት ይሉሻል
የሕይወታችን በር ድንግል ናት ይሉሻል
ድንግል ናት ይሉሻል
        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
እግዚአብሔር አብ ላከ አንድያ ልጁን
የአንቺን ሥጋ ለብሶ እኛን እንዲያድን
የአንቺን ሥጋ ለብሶ እኛን እንዲያድን
እኛን እንዲያድን
        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ድንግል ሰገዱልሽ መላእክት በራማ
በአንቺ ላይ ስላለ የመኮት ግርማ
በአንቺ ላይ ስላለ የመለኮት ግርማ
የመለኮት ግርማ
        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ዓለሙን ያዳነ ያንቺን ሥጋ ለብሦ
ዘለዓለም ኗሪ ነው በሰማያት ነግሦ
ዘለዓለም ኗሪ ነው በሰማያት ነግሦ
በሰማያት ነግሦ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ
!

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ እግዚአብሔር ፈዋሽ ✞

እግዚአብሔር ፈዋሽ የስምህ ትርጉም
ፈታሔ ማህፀን ሩፋኤል ግሩም
ለአንተ አለኝ ምስጋና የመንገዴ መሪ ነህና[፪]

      
ይውረድ ከሰማይ የምሕረት ጠል
ሩፋኤል አሳደገኝ ልበል
ከልጅነቴ ያኖርከኝ በክብር
ሩፋኤል ለአንተ ልዘምር [፪]

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
የመብረቅ ጋሻ የእሳት ጦር ይዘህ
ከንፋስ ይልቅ ትፈጥናለህ
መራሄ ፍኖት ናልኝ ወደ እኔ
ጦቢት ነኝ ይብራልኝ አይኔ [፪]

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ተሾምክ በኃይላት አለቃ ሆነህ
ሰሚነህ ሩፋኤል ለዓለም
ሲወልዱ እናቶች እንዳይጨንቃቸው
ማህፀን ከፋች ሆንካቸው [፪]

        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
እኔ የአንተ ልጅ ለአንተ ልዘምር
ስላየሁ የአንተን ልዩ ፍቅር
በደረስኩበት የማትለየኝ
ስለአንተ ምለው ብዙ አለኝ
ስለአንተ ገና ብዙ አለኝ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ዘርዓ ብሩክ ✞

አባ ዘርዓብሩክ ጻድቁ አባታችን
ክብርኽ ይሁነን ግርማ ሞገሳችን
ፀጋኸ ይድረሰን በረከት ይሙላብን
ከመድኃኒዓለም በምልጃኽ አቅርበን


ተግቶ የፀለየ ....... ዘርዓብሩክ
ገና በህፃንነት ...... ዘርዓብሩክ
አይኑን ያሳወረ ..... ዘርዓብሩክ
በእምነት በፀሎት ..ዘርዓብሩክ
   ልዩነው ታምሩ
   ልዩ ነው ስራው


አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ባላ አደራ አባይ ......... ዘርዓብሩክ
መፃፍህን ተፋ ........... ዘርዓብሩክ
ዲያቢሎስ በመፍራት ...ዘርዓብሩክ
በፊትህ ተደፋ .............ዘርዓብሩክ
   ልዩነው ታምሩ
   ልዩ ነው ስራው


 አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ፀሐይን ያቆመ .........  ዘርዓብሩክ
ለአምስት አመታት .....  ዘርዓብሩክ
የአክናፍ ባለቤት ....... ዘርዓብሩክ
የፀጋዎች አባት ........ ዘርዓብሩክ
   ልዩነው ታምሩ
   ልዩ ነው ስራው


አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
እንኳን ሰው ይቅርና ........ ዘርዓብሩክ
ዘንዶ ያስታረቀው ........... ዘርዓብሩክ
ዘርዓብሩክ ኃያል ........... ዘርዓብሩክ
ግሩም ነው ገድላቸው ..... ዘርዓብሩክ
   ልዩነው ታምሩ
   ልዩ ነው ስራው


አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ብረር በክንፎችኽ ......... ዘርዓብሩክ
ዙራት ይህቺን ዓለም ..... ዘርዓብሩክ
አማልዳት ኢትዮጵያን...... ዘርዓብሩክ
ከመድኃኒዓለም..............ዘርዓብሩክ
   ልዩነው ታምሩ
   ልዩ ነው ስራው


          መዝሙር|
  በዘማሪ| የአብስራ ሲሳይ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ ✞

አባ ሳሙኤል ዘዋልድባ
መነኮሰ ኃያል ቤቴ ግባ
ታስባርካለህ ሰውን ምድር
ቅርብ ነህ አንተ ለእግዚአብሔር (፪)


           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
የበረሀ መናኝ ግሩም ነው ገድልህ
ምድር አስባርከሀል ከፍ አርገህ በእጅህ
ታምር ነው ገዳምህን ላየ
እረድኤት በረከት ገበየ
ልጆችህ በገዳሙ ውስጥ ያሉ
ሳሙኤል ሳሙኤል ይላሉ

           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
አይሻገርብሽ እህልም ኃጢአት
ጌታንችን ብሏታል ዋልድባን መሬት
ትርመት ይዘው ልጆቹ በሙሉ
ቋርፍ ነው ዘወትር የሚበሉት
የጣመ የላመ አተን
ዮርዳኖስ ጸበል ምግብ ሆነልን

           አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
አስኬማውን ለብሶ በገዳም ሲኖር
የትሕትና አባት ነው የሕግ መምህር
ሀሌሉያን ሄደን አይተን
አብረን ከአንተ እንኖራለን
ሀሌሉያ ሄደን አይተን
አብረን ከአንተ እንኖራለን

          መዝሙር|
ቀሲስ እንግዳወርቅ በቀለ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት
ወሰላም በምድር ለዘሠሞሮ ለሰብእ (፬)


ትርጉም፦
በሰማያት ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን
ሰውን ለወደደው ለእርሱ በምድር ሰላም ይሁን


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ
!

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
      @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ በምን ደስ ላሰኝህ ✞

በምን ደስ ላሰኝህ ጌታዬ ሆይ
በምን ደስ ላሰኝህ አምላኬ ሆይ
ዓለምና መላው የአንተው አይደለም ወይ
የፈጠርከው ሁሉ የአንተው አይደለም ወይ(፪)


       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ኪሩቤል ሱራፌል ቅዱስ ስሉስ ያሉህ
መላእክት በራማ የሚያመሰግኑህ
ድንቅ መካር ኃያል ኤልሻዳይ ነህና
ትቢያ ነኝ ምን ልስጥህ ምንስ አለኝና/፪/

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ቅዱሱን መስዋዕት ልዑል ስለሚወድ
ምን ይዤ ልምጣና ከአምላኬ ፊት ልስገድ
ወደላይ በሰማይ ወደታች በጥልቀት
አምላኬ የታለ የማትገኝበት
ጌታ ሆይ የታለ የማትገኝበት

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በኪዳን በጸሎት ቅዳሴ ሰዓታት
አንተ የሰጠኸን የመንፈስ ቅዱስ ሐብት
መልሰን ወደ አንተ ብንሰጥ ምንድነው
ተወው ጉዳችንን ስስታችን ይኸው/፪/

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ሐብት እና ንብረቴስ ጉልበቴስ ምንድነው
ጤናን የሰጠኸኝ ከአንተ በቀር ማንነው
በሰጠኸኝ እድሜ በሕይወት ዘመኔ
ከገላዬስ ቢሆን የትኛው ነው የእኔ
ከአካላቴስ ቢሆን የትኛው ነው የእኔ

                መዝሙር|
      በዘማሪ| ዳግማዊ ደርቤ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ብፁዕ ነህ ያሬድ ሆይ ✞

ብፅዕት ከርስ እንተ ፆረተከ
ወብፁዓት አጥባት እለ ሐፀናከ
ብፁዕ ነህ ያሬድ ሆይ የተመሰገንህ
ሰማያዊ ዜማን ለምድር ያሰማህ (፪)


ቀዳሚሃ ለጽዮን ሰማየ ሣረረ
ከጽዮን ቀድሞ ሰማይን ፈጠረ
ያለ የነበረ ዘላለም የሚኖር
የሁሉ አስገኚ ስብሐት ለእግዚአብሔር
መዓዛ ሠናይ ለእግዚአብሔር ካህኑ
ትርድአነ ነዓ በህየ መካኑ(፪)


        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በታቦተ ጽዮን ራሱን አቅንቶ
ወደ ምስራቅ ዞሮ እጆቹን ዘርግቶ
ሃሌ ሉያ አለ በአክሱም አደባባይ
በአውደ ምሕረቱ በዜማ አራራይ
መዓዛ ሠናይ ለእግዚአብሔር ካህኑ
ትርድአነ ነዓ በህየ መካኑ(፪)


        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በአራራይ ዜማ መንፈስ ገለጠለት
በሙራደ ቃል ዜማው ሰመረለት
አርያም ምስጋና ከሰማይ ተገኘች
እርሷም ለዘላለም እንዲሁ ትኖራለች
መዓዛ ሠናይ ለእግዚአብሔር ካህኑ
ትርድአነ ነዓ በህየ መካኑ(፪)


        አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በመሰንቆው ጣዕም በበገናው ንዝረት
በቅኔ በእንዚራ በመለከት ድምፀት
ምስጋናን ሲያቀርቡ መላእክት በአንድነት
ለያሬድ ዜማዎች ሆነዋል አብነት
መዓዛ ሠናይ ለእግዚአብሔር ካህኑ
ትርድአነ ነዓ በህየ መካኑ(፪)


           ፈረንሳይ አቦ
  መካነ ሕይወት ሰ/ት/ቤት

"እግዚአብሔርን አመስግኑ መዝሙር መልካም ነውና"
                መዝ፻፵፯፥፩
✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ እልል እልል እልል ✞

እልል እልል እልል
ደስ ይበለን ሁላችን
አምላካችን መልካም አደረገልን
ደስም አለን የሠራዊት ጌታ ክበር ተመስገን (፪)


ልመናን ይሰማል ................. እልል
እግዚአብሔር ይረዳል .......... እልል
ከመንገድ አንወድቅም .......... እልል
እርሱ ይደግፈናል ................ እልል

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ሰውና መላእክት .......... እልል
በአንድነት ዘመሩ .......... እልል
የአምላክ ትሕትና .......... እልል
ለሰው ሆነ ክብሩ .......... እልል

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው...... እልል
ማን ይቃወመናል ................... እልል
ማዕበሉም ጸጥ ይላል ............. እልል
እግዚአብሔር ከፍ ይላል .......... እልል

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
እረኞቹ መጡ ................. እልል
መልእክቱን አይተው ......... እልል
ሰብእ ሰገል መጡ ............ እልል
በኮከብ ተመርተው ........... እልል

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ቆሜ ዘምሬያለሁ ............... እልል
ጌታ ለልደትህ .................. እልል
አቁመኝ በቀኝህ ................ እልል
በክብር በመንግሥትህ....... እልል


✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ
!

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
      @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ ✞

ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ [፪]
ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ
የፍቅርን ሕይወት እንድትለብሱ
ኑ በብርሃኑ ተመላለሱ


       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ሁሉን በሚችል በአምላክ ጥላ
በእረፍት ውኃ ስር አርፈናልና
ሰላምና ፍቅር ሕይወት በሚሰጥ
ወደ ጌታችን እንሂድ እንሩጥ

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ምሕረትና ፍርድ በእጁ የያዘው
የሰላም አባት መድኅኔዓለም ነው
ሕይወት የሆነን በመስቀል ውሎ
ብርሃንን ሰጠን ጨለማን ሽሮ

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
የሚያስደነግጥ የሚያስጨንቀን
ይጠፋልና እርሱን ተማጽነን
በቀን ከሚበር ፍላጻ ሁሉ
ይታደገናል በቅዱስ ቃሉ

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
እግርህ በድንጋይ እንዳይመታ
በፈተና ውስጥ እንድትበረታ
መቅሠፍት ከቤትህ እንዲከለከል
ይጠብቅሃል ሌሊትና ቀን

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ስሙን ያወቀ ሕይወት መሆኑን
ይመላለሳል ከኀይል ወደ ኀይል
ረጅም ዕድሜ ይጠግባል እርሱ
ብርሃን ይሆናል የጸጋ ልብሱ

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
አቤቱ አንተ ተስፋ ነህና
የምትመግብ የፍቅር መና
ማዳንህ እኛን አስደስቶናል
እንዲህ ያለ ክብር ከየት ይገኛል

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ
!

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
      @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ እኔ እራሴን ካልጣልኩ ✞

እኔ እራሴን ካልጣልኩ አታውቅም ጥለኸኝ(፪)
ፍቅር ነህ ጌታዬ በፍቅር የምታየኝ
ፍቅር ነህ አባቴ በፍቅር እምታየኝ


       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ኃጢአቴ ነው እንጂ ከአንተ የሚያሸሸኝ
በደሌ በዝቶ እንጂ አንገት የሚያስደፋኝ
አምላኬ ይዞኛል ሰፊው መዳፍህ
በበዛው ቸርነት ምሕረት ይቅርታህ

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ዛሬ ይቅር ብለኸኝ ዛሬ እንኳን ባጠፋ
አምላኬ በእኔ ላይ አትቆርጥም ተስፋ
እኔ እየሸሸው ትከተለኛለህ
ጀርባዬን ስሰጥህ ልጄ ትለኛለህ

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
መመለሴን እንጂ ስለማትወድ ሞቴን
መጣህልኝ ብለህ አቀፍከኝ አንገቴን
በአንተ ተጀምሮ ስለማያልቅ በሰው
አምላኬ በአንተ ላይ ተስፋዬ ብዙ ነው

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
እኔ እያጠፋሁኝ እኔው ስበድልህ
ፍሪዳውን ማረድ አንተ ግን ነው ልምድህ
የጠፋው ተገኝቷል ተነስቷል የሞተው
ትላለህ አምላኬ ማዳንህ ድንቅ ነው

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በአስለመድከኝ ምሕረት በአስለመድከኝ ፍቅር
ከእኔ ጋር ነህና ተመስገን እግዚአብሔር
ስለሆንከኝ አንተ መጠጊያ ከለላ
ክፉውን አልፈራም መሄድ በሞት ጥላ

                    መዝሙር|
|ሊቀ መዘምራን ዲ/ን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ አጥቷል ጎሎበታል ✞

አጥቷል ጎሎበታል ብለህ ሳትንቀኝ
ለዚህ ያደረስከኝ ጌታዬ እኔ ማነኝ
ይሞላል አይቀርም በአንተ ሸለቆዬ
ጠብቃለሁና ቀንህን ጌታዬ(፪)


       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ሐዘን ፅልመት ክፉ ዘመን
ቢገጥመኝም እንኴን
ያልፋል ሁሉም ታሪክ ሆኖ
በፊትህ ሲለካ
ማን ጎደለ ማን አፈረ አንተን የጠበቀ
ጸና ልቤ በእግዚአብሔር ይሄን እያወቀ

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በዓለም ስፍራ ባይኖረኝም
ብሆንም ጎስቇላ
አምላኬ ሆይ ከአንተ በቀር
አልሄድ ወደ ሌላ
ጌታዬ ሆይ በፍለጋ ወጣሁ ከመቃብር
ስመሰክር እኖራለሁ ስራህን ስናገር

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ቀን ለክተህ ጊዜን አይተህ
ሰውን የማትከዳ
ያለ ወረት ትመጣለህ እኔን ልትረዳ
ከእነ ኤልያስ ወንድሞቼ ባልስተካከልም
ማማ ሆነህ ከፍ አረከኝ አንተ ሰው አጥልም

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
እንደ እናት ልጅ እንዳልቆጥርህ
ከዚህም ትበልጣለህ
ከአንተ በቀር ያፈቀረኝ
በምድር ስለሌለ ስለ
ስምህ መነቀፌ ክብሬ ነው ማረጌ
በምን መንገድ ላስደስትህ እንደምን አድርጌ

               መዝሙር|
ዘማሪ| ቀሲስ አሸናፊ ገ/ማርያም

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE


https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem
https://t.me/yemezmur_gexem

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥


✞ ሣር ቅጠሉ ሠርዶው ✞

ሣር ቅጠሉ ሠርዶው ሰንበሌጥ ቀጤማው
በዚያች ቀን በዚያች ወር ለምልሞ የነበረው
በእልልታ ዘመሩ በደስታ ተሞልተው
ጌታ መወለዱን የምሥራች ሰምተው

እልል በይ ቤተልሔም ሃሌ ሃሌ ሉያ
የፍቅር የሰላም ነሽና ገበያ [፪]

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ያ ትሑት እረኛ ሳለ በትጋት
ብርሃንን ለበሰ በእኩለ ሌሊት
ጥሪ ተደርጐለት ከሰማይ ሠራዊት
ለመመልከት በቃ የጌታውን ልደት

እልል በይ ቤተልሔም ሃሌ ሃሌ ሉያ
የፍቅር የሰላም ነሽና ገበያ [፪]

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
የእረኝነት ሥራ ተንቆ እዲቀር
ብሎ ሰው በልማድ ደንግጎ ነበር
የብዙ ሰው ራስ መሆኑን እረኛ
ክርስቶስ ሲወለድ ተረዳነው እኛ

እልል በይ ቤተልሔም ሃሌ ሃሌ ሉያ
የፍቅር የሰላም ነሽና ገበያ [፪]

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ
!

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
     
@yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ እልል በሉ ✞

እልል በሉ በአንድነት ዘምሩ
አመስግኑ ለክብሩ ዘምሩለት
እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም የለም በሉ(፪)


       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
በኃጢአት ባርነት ስንኖር ተገዝተን
ከቤቱ ስንርቅ ትእዛዙን አፍርሰን
አይቶ ዝም ላለን ጠላቶቹ ሳለን
ውለተው ብዙ ነው ክብር ለእርሱ ይሁን[፪]

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ራሱን አዋርዶ እኛን አከበረን
ሥጋውና ደሙን ብሉ ጠጡ አለን
መልካም እረኛ ነው የሚያሳጣን የለም
ምስጋና ይድረሰው ለመድኃኔዓለም[፪]

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ሕይወቱን የሰዋ እንደ አምላክ ማን አለ
ለሰው ልጆች ብሎ በመስቀል የዋለ
ፍቅሩ አይለካ አያልቅም ቢወራ
ከሰማያት ወርዶ ሆነ ከእኛ ጋራ [፪]

       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ሥራውን እናድንቅ እንዲህ ለወደደን
ከማያልቀው ፍቅሩ በረከት ላደለን
ለማይነገረው ለአምላክ ስጦታ
ውዳሴን እናቅርብ እንዘምር በእልልታ[፪]

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ
!

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
    @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ ላመስግንህ የእኔ ጌታ ✞

ላመስግንህ የእኔ ጌታ ላመስግንህ
ልቀኝልህ የእኔ ጌታ ልቀኝልህ
ሕይወቴ ነው ዝማሬዬ ትሩፋቴ
የሰጠኸኝ እንዳከብርህ አንተ አባቴ[፪]


       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ከእኔ የሆነ የምሰጥህ ባይኖረኝም
ከሰጠኸኝ ያንተን መስጠት አይከብደኝም
ጥበቤ ነህ የምስጋና መሠረቴ
ዝማሬዬን ያፈሰስከው በሕይወቴ
አንደበቴን የቃኘኸው ለምስጋና
ይኸው ውሰድ ቅኝትህን እንደገና
[፪]
       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ባዶ እኮ ነኝ የእኔ ጌታ ምን ልቅዳልህ
በእጄ ላይ አንዳች የለኝ የምሰጥህ
ለአንተ ክብር የሚመጥን ሕይወት የለኝ
ዝማሬዬን በቸርነት ተቀበለኝ
አንደበቴን የቃኘኸው ለምስጋና
ይኸው ውሰድ ቅኝትህን እንደገና
[፪]
       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ከምድር ላይ ከአፈርህ ስትፈጥረኝ
ከምስጋና የተለየ ምን ሥራ አለኝ
ቀንና ሌት በመቅደስህ እቆማለሁ
አምላኬ ሆይ ሳወድስህ እኖራለሁ
አንደበቴን የቃኘኸው ለምስጋና
ይኸው ውሰድ ቅኝትህን እንደገና
[፪]
       አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
እዝራ ስጠኝ የከበረ መሰንቆህን
ዳዊት ስጠኝ የሚፈውስ በገናህን
መዝሙር ቅኔ ተምሬአለሁ ከአባቶቼ
ዘምራለሁ በአንተ ፍቅር ተነክቼ
አንደበቴን የቃኘኸው ለምስጋና
ይኸው ውሰድ ቅኝትህን እንደገና
[፪]

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ
!

   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
      @yemezmur_gexem
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

20 last posts shown.