የነፍሴ ጥያቄዎች


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


✋እንኩዋን ወደ ቻናላችን በሰላም መጡ

በዚ ቻናል ውስጥ ከእሰላም ወገኖቻችን የሚነሱ ጥያቄዎችን እንመልሳለን እንተነትናለን እባክዎን ልቦን ክፍት አድርገው ይከታተሉ👍
ለአስተያየት ለጥያቄ ለምክር @yenebsebot ይጠቀሙ
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
.
አስተያየት ካለ ያሳውቁን እንጂ Live ብለው ማግኘት ያለቦትን እንዳያጡ!!

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ከሆነ ቦታ ወደ ሆነ ቦታ እየሄድኩ የተከፈተው ለሙሀመድ የተዘፈነው ዘፈን ደስ ሲል። አሁን አሁን የምታወጧቸው ነሺዳዎች ግን ሙሀመድን ከአላህ እኩል ያደረጉ ይመስላሉ ስለ አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ስናወራ መቃወምን ማቆም ያለባቹ ይመስለኛል ምክንያቱም እናንተም ሁለት አምላክ ወደ ማምለክ እየሄዳቹ ነው ሙሀመድን እና አላህን፤የኛው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ብለን አንድ አምላክ ነው የምንለው አንድ አምላክ አሀዱ አምላክ ነው። የናንተው ሁለት አምላክ መሰለኝ አላህ አንደኛው አምላክ ከአላህ ያነሰው ሁለተኛው አምላክ ሙሀመድ።

@yenebsetiyakewoch


የ tiktok አብዱሎች የሚጠይቁትን ጥያቄ በ tiktok ለመመለስ ስል ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት tiktok account ከፈትኩ እና እስኪ ፈቃዳቹ ከሆነ እየገባቹ follow አድርጉ🙏

tiktok.com/@ewenetn

ይቅር በዚሁ ይበቃል የምትሉ 👎 እቺን
በዛም ያስፈልጋል ምትሉ 👍 እቺን እየነካቹ ሄዳቹም follow አድርጉ


"ለምንድነው የምትፆመው?"

ይሄን ጥያቄ የሚጠይቁ ሰዎች አሉ፤ይህን ጥያቄ ክርስትያን ነኝ ከሚል ሰው መስማት ያሳዝናል።

ለምንድነው ምፆመው? ሞት እየነገሰ ሰው እንዴት ይህን ጥያቄ የመጠየቅን ድፍረት ሊያገኝ ይችላል? ወደ ግራ እና ወደቀኝ ዞር ዞር ብለን እንመልከት እስኪ ምን ይታይሀል? ምንስ ይታይሻል? በሽታ፣ሱሰኝነት፣ኑፋቄ...ወደልጆቻችሁ ክፍል ብትገቡ ምን ታያላቹ? ብትቀርቡዋቸው አብራቹ ብትቀመጡ እና ውስጣቸውን ብትረዱ ያሉበትን ሁኔታ የሚያጨሱትን የሚያዩትን ብትመለከቱ ደምስሮቻቸው ላይ ምን ሰክተው በምን እንደሚጦዙ ጓደኞቻቸው እነማን እንደሆኑ ብታውቁ፤TV ከፍታቹ ብትመለከቱ ራሳችሁን ብታደምጡ የምትሰሙት ጦርነት የምታዩት ሴሰኝነት የምትረግጡት መሬት በደም የራሰ ተስፋ የሚያስቆርጥ እንደሆነ ይገባቹዋል።

ከዛ ለምን መፆም እንዳለብን ይገለጥላቹዋል ለምን እንደምንፆም ይገባቹዋል። ተስፋ ላለመቁረጥ ስንል እንፆማለን፤በንፋስ የሚሰበር ሸንበቆ ላለመሆን ስንል እንፆማለን።

አለማዊ ለስላሳ ልብስን አንፈልግ!
በቁም ሬሳዎች የተሞሉ ትላልቅ ቤቶችን አንፈልግ!
ሰይጣናዊ ዝሙታዊ ጭፈራዎችን አንፈልግ!
👉ወደ መጥምቁ ዮሀንስ የንስሀ ጥሪ እንመለስ!
👉ሊመጣ ያለውን በመላእክት ታጅቦ የሚመጣውን ንጉሱን ለመቀበል እንዘጋጅ!
👉የምንፆመውም ለዛ ነው!
👉ከመንግስቱ እንዳንጎድል ነው በንስሀ የምንኖረው!
👉መስቀሉን እና ስቃዩን እናስብ ለአለም ችግር የኛ ፆም እና ስግደት ፀሎታችን መፍትሄ አለው ለዛም እንፆማለን!

አንድ አባት የመለሱትን መልስ ከራሴ ጋር አዋህጄ ፃፍኩላቹ ፆማችን መፍትሄ አለው!
share👇join👇share
@yenebsetiyakewoch
@yenebsetiyakewoch


በእንተ ቆላስይስ 1፥16

የአይሁዳውያን መሠረተ እምነት ከሆኑት ዶግማዎች መካከል በቀዳሚነት የሚሰለፈው የእግዚአብሔር ብቸኛ ፈጣሪነት ነው። የብሉይ ኪዳንም የመጀመሪያ ክፍል የእግዚአብሔርን አስገኚነት በመናገር የሚጀምረው በዚህ አግባብ ነው(ዘፍ 1፥1)። ኢሳይያስም በትንቢቱ የዘፍጥረት 1፥1 ምንባብ በሚያጸና መልኩ ይኽን ይላል፣ “ብቻዬን ሰማያትን የዘረጋሁ፣ ምድርን ያንጣለልሁ፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤”(ኢሳ. 44፡24)። ወደ አዲስ ኪዳን ስንመጣ ደግሞ ሁሉም ነገር የተፈጠረው በእግዚአብሔር ልጅ በክርስቶስ ኢየሱስ እንደሆነ ንዋይ ሕሩይ ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ በማለት ያረጋግጥልናል፦

“ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ በሰማይና በምድር ያሉ፣ የሚታዩና የማይታዩ፣ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኀይላት፣ ገዦች ቢሆኑ ወይም ባለ ሥልጣናት፣ ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል።”
— ቆላስይስ 1፥16

ከላይ ባለው በጥቅሱ ውስጥ ሐዋርያው “ሁሉ በእርሱ ተፈጥረዋል”(ἐν αὐτῷ ἐκτίσθη τὰ πάντα ) ይለናል፡፡ ይኸውም በእግዚአብሔር አብ ልጅ ዓለማት መፈጠሩን እናም ልጁ ኢየሱስ ልክ እንደ አባቱ የአምላክነት ተግባርን ይከውን እንደነበር ያስገነዝበናል። ሆኖም የክርስቶስን አምላክነት የማይቀበሉ ወገኖች በሚከተለው ሙግት በቆላስይስ 1፥16 የተጠቀሰውን የጌታችንን ፈጣሪነት ለማስተባበል ይሞክራሉ። ይኸውም፤ “' ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል' የሚለው አዲስ ፍጥረትን የሚያመለክት እንጂ ክርስቶስ ፍጥረታትን ካለመኖር ወደ መኖር ማምጣቱን የሚያመለክት አይደለም” የሚል ነው።

ከላይ የሚገኘው ሙግት ቢያንስ ሶስት መሠረታዊ ነጥቦችን ያላገናዘበ ነው። ይኸውም፤

1ኛ. መና*ቃን ይህ ትርጓሜያቸው የቋንቋ (Linguistic approach) ድጋፍን መሠረት ያላደረገ ነው። ምክንያቱም ἐκτίσθη “ኤክቲስቴ” የሚለው ቃል ቊማዊ ፍጥረትን እንጂ በፍጹም ተምሳሌታዊ ገለጻን ለማመልከት ግልጋሎት ላይ አይውልም[1]። ይህ ማለት የመና*ቃን ሙግት ከጅምሩ ወንዝ የማያሻግር ሆኖ ይቀራል ማለት ነው።

2ኛ.ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ 11፥36 የአብ ፈጣሪነትን የገለጠበትን ምንባብ ከቆላስያስ 1፥16 ጋር በትይዩ ተመልከት፤

አብ፦
“#ሁሉም(τὰ πάντα) ከእርሱ፣ #በእርሱ(δι’ αὐτοῦ)፣ #ለእርሱ(εἰς αὐτὸν) ነውና፤ ለእርሱ ለዘላለም ክብር ይሁን፤ አሜን።”
— ሮሜ 11፥36 (አዲሱ መ.ት)

ወልድ፦
“ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ በሰማይና በምድር ያሉ፣ የሚታዩና የማይታዩ፣ ዙፋናት ቢሆኑ ወይም ኀይላት፣ ገዦች ቢሆኑ ወይም ባለ ሥልጣናት፣ #ሁሉም(τὰ πάντα) ነገር #በእርሱና(δι’ αὐτοῦ) #ለእርሱ(εἰς αὐτὸν) ተፈጥሮአል።”
— ቆላስይስ 1፥16 (አዲሱ መ.ት)

በሁለቱም ጥቅሶች ውስጥ “ሁሉም” (τὰ πάντα “ታ ፓንታ”) ፤ “በእርሱ” ( δι’ αὐτοῦ ዲ አውቱ)፤ “ለእርሱ” (εἰς αὐτὸν ሔይስ አውቶን)፤ የሚሉትን ቃላቶችን ተጠቅሞአል። ስለዚህ ቆላስይስ 1፥16 ላይ የወልድን ፈጣሪነት አያሳይም ካሉን፣ በተመሣሣይ የሮሜ 11፥36 ምንባብም እንዲሁ የአብን ፈጣሪነት አያሳይም ብለው መደምደም ይኖርባቸዋል። ምክንያቱም ሐዋርያው ለሁለቱም አካላት ተመሣሣይ ሰዋስዋዊ ውቅር ተጠቅሞአልና።

3ኛ.የመና*ቃን ችግር ሐዋርያው በክርስቶስ ተፈጠሩ የሚለን በሰማይ የሚኖሩ ገዢዎች እና ሥልጣናትን መሆኑን አለማስተዋል ነው።

“ሁሉ ነገር በእርሱ ተፈጥሮአል፤ በሰማይና በምድር ያሉ፣ የሚታዩና የማይታዩ፣ ዙፋናት፣ ቢሆኑ ወይም ኀይላት፣ *ገዦች*(ἄρχαι) ቢሆኑ ወይም *ባለ ሥልጣናት*(ἐξουσίαι)፣ ሁሉም ነገር በእርሱና ለእርሱ ተፈጥሮአል።”
— ቆላስይስ 1፥16

ጳውሎስ በሌላ ጽሑፉ ላይ ክርስቲያኖችን የሚዋጉ ዓመፀኛ መናፍስት ፍጥረታትን በሚመለከት “ገዦች ” እና “ሥልጣናት” የሚሉትን ቃላት ተጠቅሟል።

“ምክንያቱም ተጋድሎአችን ከሥጋና ከደም ጋር ሳይሆን ከዚህ ከጨለማ ዓለም *ገዦች*(τὰς ἀρχάς)፣ *ከሥልጣናትና*(τὰς ἐξουσίας) ከኀይላት እንዲሁም በሰማያዊ ስፍራ ካሉ ከርኩሳን መናፍስት ሰራዊት ጋር ነው።”
— ኤፌሶን 6፥12 (አዲሱ መ.ት)

ይኽም ማለት ኢየሱስ ቅዱሳን ሆነ እርኩሳን መናፍስትን የፈጠረ አምላክ መሆኑን በግልጽ ያመለክታል።በአጠቃላይ ቅዱስ ጳውሎስ የክርስቶስን የበላይነት፣ አድራጊ ፈጣሪ መሆኑን በግልፅ እየተረከልን ነው። እርሱ ተራ መልአክ ወይም ተራ ሰው አይደለም፣ ነገር ግን ከሁሉም በላይ የሆነ፣ ሊመለክ የሚገባው ፈጣሪ ነው። ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘለዓለም ክብር ይሁን! የሚያመልከው አሜን ይላል።

[1] መጽሐፈ ጥበብ 1፥14፤ 10፥1፤ 11፥18፤ ዘዳግም 4፥32፤ ዘፍጥረት 6፥7; ሲራክ 24፥9፣ ሲራክ 15፥14፤ መጽሐፈ ኢዮብ 13፥18፤1 ቆሮንቶስ 11፥9፤ ኤፌሶን 3፥9፤ ሮሜ 1፥25፤ ራእይ 10፥6፣ ራእ 14፥7

(በወንድም ሚናስ)

Share👇join👇share
@yenebsetiyakewoch
@yenebsetiyakewoch


ብዙ ሙስሊሞች ክርስትናን ዲዳት እና ዛኪረ በነገሩዋቸው ልክ ነው የሚያውቁት!

መፅሀፍ ቅዱስን ማንበብ ማለት የዲዳት እና የዛኪርን የቆዩ ተመልሰው ያለፉ ጥያቄዎችን እንደአዲስ ማስጮህ ይመስላቸዋል።

ተወዳጆች ሆይ መፅሀፍ ቅዱስን በሰዎች ወይም በእስልምና መነፅር ከምታነቡ ባታነቡ ይሻላችዋል ይልቁንስ እውነትን ከፈለክ ከዘፍጥረት እስከ ራእይ በትክክለኛው መንገድ በአውዱ መሰረት አንብበው እመነኝ የዛኔ ክርስትና ትገለጥልሀለች።


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
እንዲ አይነት ወጣቶችን አበረታቱት ጥቂት ለማለት ያክል..

ዘሌዋውያን አብይ ሀሳቡን ቅድስናን አድርጎ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ በአሮን ልጆች የክህነት አገልግሎት የሚካሄደውን እና በሌዋውያን የሚታዘዘውን ስርአት የሚያሳይ ነው።

ልጅቱዋ ወደ ምትለው ዘሌዋውናን 21 ስንመጣ ወንድሜ ጥሩ አድርጎ መልሶላታል ተባረክ። አንድ ጥቅስ ይዛቹ አትጋልቡ ስለማን ስለምንድነው ክፍሉ ሚያወራው ብላቹ ጠይቁ በመገናኛው ድንኩዋን መስዋእቱም ሰዊውም ንፁህ መሆን ይጠበቅባቸዋል። ካህን አልሆኑም ማለት ከእግዚያብሄር ህዝብነት ጎደሉ ተቆረጡ ተካዱ ማለት አይደለም ካዳቸው ያልሻቸውን ሰዎች እግዜርም ህዝቤ ብሎ የጠራቸው በድንቅ ተአምራት ከግብፅ ባርነት አስወጥቶ የመራቸው እሱ ነው ይህን ስርአት የሰጠው!

"መፅሀፍ ቅዱስ የእግዝያብሄር ቃል ነው ወይ?" የሚለውን "የተበረዘው መፅሀፍ ቅዱስ ወይስ ቁርአን?" በሚል ርእስ በተከታታይ ክፍሎች ለቀን ነበር ጋብዙልኝማ።

@yenebsetiyakewoch
@yenebsetiyakewoch


ትልቅ ማን ነው?



(ማቴ 11÷9-11)

ለማኙ የባለጠጋውን ቤት አልፎ የድሃዋ በር ላይ ቆሞ፡- ‹‹በእንተ ማርያም›› እያለ ይለምናል፡፡ ድሃዋም፡- ‹‹ይህን ትልቅ ቤት አልፈህ እንዴት እኔ በር ላይ ትለምናለህ?›› ይሉታል፡፡ ለማኙም፡- ‹‹አይ እሜቴ ትልቁ ቤት ትልቅ ሰው የለበትም›› አላቸው ይባላል፡፡ ድህነትን እንደ አመል በመቊጠር የባለጠጎችን ቤት ስናይ የደህና ሰው ቤት ነው እንላለን፡፡ የሰውዬውን ትልቅነት በቤቱ እንመዝነዋለን፡፡ ቤት የትልቅነት መለኪያ ሆኗል፡፡

አለቃ ገብረ ሃና እንደነገሩ ለብሰው ወደ ተጠሩበት ድግስ ይሄዳሉ፡፡ በሩ ላይ የቆመው ዘብም አላስገባም ብሎ ይመልሳቸዋል፡፡ እርሳቸውም በልብሳቸው እንደ ተመዘኑ ገብቷቸው ደህና ልብስ ለብሰው ተመልሰው ቢመጡ እጅ ነሥቶ አስገባቸው፡፡ እርሳቸውም ከእንጀራው ላይ ወጡን እያነሡ ልብሳቸውን መለቅለቅ ጀመሩ፡፡ ሰዎቹም ምነው አለቃ ምን ነካዎት? ቢሏቸው፡- ‹‹የተጠራሁት እኔ ሳልሆን ልብሴ ነው›› አሉ ይባላል፡፡ አለባበስ የትልቅነት መለኪያ ሆኗል፡፡ ከአባባሉም፡- ‹‹ኖር ለልብሱ›› ነው፡፡ እኛም ሰዎች ሲለብሱና ሳይለብሱ የማንቆጣጠረው ማንነታችን ሁለት ሰው ያደርገናል፡፡ ውሾች ሱፍ የለበሰ ላይ አይጮኹም፣ ለማኙን ደግሞ ወርረው ያጣድፉታል፡፡ ይህ ነገር ምንድነው ብዬ አንድ ወዳጄን ብጠይቀው፡- ‹‹ፍርፋሪያቸውን የሚወስድባቸው ስለሚመስላቸው ነው›› ብሎኛል፡፡ እኔስ ከእኛ ተምረው ይመስለኝ ነበር፡፡

የሚያስደስተን የሚበቃን ኑሮ ስላለን ሳይሆን ከሌሎች በመብለጣችን ነው፡፡ ትልቅነት ትልቅ መከራ እንዳለው በቃላት አይገባንም፡፡ ለትልቅነት መሥራትና ትልቅ ሥራ መሥራት ይለያያሉ፡፡ ለትልቅነት የሚሠሩ በሌሎች ላይ ይራመዳሉ፡፡ ትልቅ ሥራ የሚሠራ ግን መሥዋዕት ይሆናሉ፡፡ ብዙ ትልልቅ ሰዎች ያልበደሉ ልጆቻቸው እንኳ አገር የለሽ ሆነዋል፡፡ የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ልጆችና የልጅ ልጆች ምንድነው በደላቸው? ትልቅ ኑሮ ትልቅ ጉድ እንዳለው እግዚአብሔር ብቻ ያውቃል፡፡ በየመንደሩ ይዞር የነበረው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በየቤቱ ያለው ድብቅ ልቅሶ ይሰማው ነበር፡፡ ያለ ልቅሶ የማይኖሩ ቤቶች እንደሌሉ እርሱ ብቻ ያውቅ ነበር፡፡

ጌታ ኢየሱስ ስለ እነ እስክንድር ወይም ስለ እነ ኔሮን ታላቅነት አልተናገረም፡፡ ስለ ዮሐንስና ጴጥሮስም የትልቅነት ክርክር ዕጣ አልጣለም፡፡ ሕፃን አምጥቶ ትልቅ ይህ መሆኑን ነገራቸው (ማቴ. 18÷1-4)፡፡ ሕጻን ትንሽ መሆኑን ሁሉም ያምናሉ፡፡ የተከበሩ ሰዎች ሕጻናትን ያከብራሉ፡፡ የዛሬው ሳይሆን የወደፊቱ ማንነቱ እየታያቸው ስፍራ ይሰጡታል፡፡ ሰው እንደ አሁኑ ሆኖ አይቀርም፡፡ የሕጻን ትልቅነቱ ስህተቱን ለመቀበል አያፍርም፣ ፍቅርን ይሰጣል እንጂ ለብድር ኑሮ አይኖርም፣ መቀበል ይችላል እንጂ አይግደረደርም፣ ራሱን ዝቅ ያደርጋል፣ ለማወቅ ይጥራል፣ ያልገባውን አስመስሎ ማለፍ አይችልም፣ በደልን በቶሎ ይረሳል፣ ምን እበላለሁ? ምን እለብሳለሁ? የማይል መንፈሳዊ ነው፡፡ የትልቅነት መስፈርቱ እንደ ሕጻናት መሆን ነው፡፡

ትልቅ ለመሆን በፖለቲካ ውስጥ ብዙዎች ይሽሎኮለካሉ፡፡ ዝነኛ ለመሆን ከሰማይ ጠቀስ ፎቅና ከታወቁ ድልድዮች ብዙዎች ራሳቸውን ይጥላሉ፡፡ እስከ ዛሬ ትልቅነት ያደክም ነበር፡፡ ዛሬ ደግሞ ይገድላል፡፡ ግን ለትልቅነት ብለው የሠሩት ትልቅ ያደርጋል? ትልቅነት እኛ እንፈልገዋለን ወይስ ይመጣል?

ዮሐንስ መጥምቅ ትልቅ ሰው እንደ ሆነ የመሰከረው ጌታችን ነው (ማቴ. 11÷9-11)፡፡ ጌታችን ዮሐንስን ትልቅ ያለው የዓለምን መመዘኛ ፍጹም በመጣል ነው፡፡ ዓለም ትልቅ ለማለት አራት ነገሮች እንደሚያስፈልጉ ታምናለች፡፡

1. ቤት፡- ቤቱን ብቻ በማየት ይህ የትልቅ ሰው ቤት ነው እንላለን፡፡ በመላው ዓለም የተሟላ ቤት ያላቸው ትልቅ ይባላሉ፡፡ ዮሐንስ ግን ቤት ያልነበረው በበረሃ የሚኖር ሰው ነበር (ማቴ. 3÷1-2)

2. ልብስ፡- ቀድመን የምናየው ሰውዬውን ሳይሆን ልብሱን ነው፡፡ ፕሮቶኮሉን ያልጠበቀ ሰው የማይገባባቸውና የማይሠራባቸው ስፍራዎች አሉ፡፡ ፖሊስ ቀድሞ የሚያነሣው ደህና ለብሶ የወደቀውን ነው፡፡ ዮሐንስ ግን ልብሱ የግመል ጠጉር፣ መታጠቂያውም ጠፈር ነበር (ማር. 1÷6)፡፡

3. ምግብ፡- ሁላችንም ቆመን ብንሄድም ለየት ያለ ምግቦችን በውድ ዋጋ፣ በደረጃ የሚመገቡ ሰዎች ትልቅ ሰዎች ይባላሉ፡፡ የሕንድ ባለጠጋ ለምሳ ለንደን ይሄዳል ይባላል፡፡ የታወቁ ወጥ ቤቶች የሠሩትም ሆነ ሌላው ምግብ ክብሩ ከጉሮሮ እስኪያልፍ ነው፡፡ ዮሐንስ ግን ምግቡ አንበጣና የበረሃ ማር ነበር (ማር. 1÷6)፡፡

4. የንግግር ችሎታ፡- ዛሬ የዓለምን የሥልጣን በትር የጨበጡ ሰዎች በንግግር ችሎታቸው የታወቁና ጥሩ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ዮሐንስ ግን የማንንም ወዳጅነት ሳይፈልግ በደልን የሚያጋልጥ ነበር (ሉቃ. 3÷7)፡፡ ግን ትልቅ ነበር፡፡

ታድያ ትልቅ ማን ነው

ከድንግል ማርያም ልጆች ቻናል የተወሰደ

@yenebsetiyakewoch
@yenebsetiyakewoch


ሙሀመድ ነብይ ሊባል የሚችለው ከፊት ለፊቱ ሀሰተኛ የሚል ቅፅል ካለው ብቻ ነው !!


ሰላም ለእናንተ ይሁን ወንድሞቼ እና እህቶቼ ይህንን የምታነቡ በሙሉ የእግዚያብሔር ሰላም በሁላችሁ ላይ ይሁን🙏


" በዚችም ዓለት ላይ ቤተ ክርስቲያኔን እሠራለሁ፥ የገሃነም ደጆችም አይችሉአትም።"
(የማቴዎስ ወንጌል 16:18)

ቤተ ክርስትያንን የገሀነብ ደጆች አይችሉዋትም የገሀነብ ደጆችም ትግልን ይታገላሉ ቤተክርስትያንም ታሸንፋለች! ቤተክርስትያንን ከፖለቲካ ጋር የምታያይዙ የከበረውን ከቀለለው ባታዋድዱ እላለው እሱዋ ከፖለቲካ በላይ ነችና!


ቻናሉን በቅርብ ቀን አስተካክለን በአዲስ መልክ እንማማራለን እስከዛው በማስታወቂያ እንዳትሰለቹ❤ ካሁን በፊት የነበረውን bot እየተቆጣጠርነው ስላላይደለ አዲስ bot እናሳውቃችዃለን። ቻናሉንም በአዲስ መልክ ምንጀምረው ይሆናል እስከዛው መልካም ገዜ


በምድር ላይ የምኩራራበት ትልቁ ንብረቴ ክርስትናዬ ብቻ ነው ክርስትና መስቀሉን መከራውን በመሸከም ከሱ ጋር የምናደርገው ጉዞ ነው❤


እግዚአብሔር ምላጭ ተከራየ?

ኢሳይያስ 7:20 “በዚያን ቀን፤ እግዚአብሔር ከወንዝ ማዶ በተከራየው ምላጭ በአሦር ንጉሥ፤ የራሱንና የእግሩን ጠጉር ይላጨዋል፤ ምላጩም ጢሙን ደግሞ ይበላል” ይላል፡፡ አምላክ ምላጭ ይከራያልን? ሁሉን የፈጠረና ዓለሙ ሁሉ የርሱስ አይደለምን? ጸጉር ይላጫልን? ተራ የሰው ማህበራ ድርጊቶቹን ሁሉ የፈጣሪ እለታዊ ድርጊት እንደሆኑ አድርጎ መግለፅ ለፈጣሪ ያለንን እሳቤ በብዥታ የተሞላ አያደርግምን?

“ምላጭ” የተባለው የአሦር ንጉሥ መሆኑ በግልፅ እየታየ ይህ ጥያቄ መነሳቱ በራሱ በእጅጉ የሚያስገርም ነው፡፡ ይህ ቃል እግዚአብሔር እርሱን በማያቀውቀው፣ ጣዖት አምላኪ በሆነው የአሦር ንጉሥ ተጠቅሞ የይሁዳ ንጉሥ የአካዝ ጠላት የሆነውን ኤፍሬምን እንደሚያዋርድ የተነገረ ዘይቤያዊ ንግግር ነው፡፡ (መላጨት የኀዘንና የውርደት ምልክት ነው 2ሳሙኤል 10፡4፣ ኤርምያስ 41፡5፡፡) ይህ ነጥብ የሙግት ሐሳብ ሆኖ መቅረቡ በራሱ እጅግ አስቂኝ ነው፡፡ በሌላ ወገን ደግሞ ሙስሊም ወገኖች ይህንን ነጥብ “ከጠንካራ” ሙግቶቻቸው መካከል እንደ አንዱ በመቁጠር በተደጋጋሚ ማንሳታቸው በእጅጉ የሚያሳዝን ነው፡፡ ብዙ ሙስሊሞች አንዱ የጻፈውን በመያዝ በደመነፍስና በድርቅና ከመከራከር በዘለለ ክፍሉን አውጥቶ የማንበብ ልማድ የላቸውም፡፡

 እውነት ለሁሉ
share👇join👇sharw
@yenebsetiyakewoch
@yenebsetiyakewoch


(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች ምዕ. 1)
----------
3፤ ከእግዚአብሔር ከአባታችን ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።

4፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ስላመናችሁ በተሰጣችሁ በእግዚአብሔር ጸጋ ምክንያት ሁልጊዜ ስለ እናንተ አምላክን አመሰግናለሁ፤

5-6፤ ለክርስቶስ መመስከሬ በእናንተ ዘንድ እንደ ጸና፥ በነገር ሁሉ በቃልም ሁሉ በእውቀትም ሁሉ በእርሱ ባለ ጠጎች እንድትሆኑ ተደርጋችኋልና።

7፤ እንደዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ ስትጠባበቁ አንድ የጸጋ ስጦታ እንኳ አይጎድልባችሁም፤

8፤ እርሱም ደግሞ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ቀን ያለ ነቀፋ እንድትሆኑ እስከ ፍጻሜ ድረስ ያጸናችኋል።

9፤ ወደ ልጁ ወደ ጌታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ ኅብረት የጠራችሁ እግዚአብሔር የታመነ ነው።

10፤ ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሁላችሁ አንድ ንግግር እንድትናገሩ በአንድ ልብና በአንድ አሳብም የተባበራችሁ እንድትሆኑ እንጂ መለያየት በመካከላችሁ እንዳይሆን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እለምናችኋለሁ።

መልካም ሰንበት
@yenebsetiyakewoch


ኢየሱስ ሁሉን አዋቂ ነው ወይ?

ዳኒኤል vs ኢብኑ አጭር ልውውጥ

አድምጡትማ
share👇join👇share
@yenebsetiyakewoch
@yenebsetiyakewoch


አላህ የፍጡር ስም

ሙስሊም ወገኖቻችን ኢየሱስ የሚለው ስም ለሰዎች መጠርያ ሆኖ ያገለገለባቸው አጋጣሚዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሚገኙ የፍጡር ስም ነው የሚል ሙግት እንደሚያቀርቡ ከዚህ ቀደም ተመልክተናል፤ ምላሻችንንም አስቀምጠናል፡፡ ዛሬ ደግሞ በዚህች አጭር ጽሑፍ የእነርሱኑ ሎጂክ ተጠቅመን አላህ የሚለው ስም የፍጡር ስም መሆኑን እናስረዳለን፡፡

ሙስሊም ወገኖቻችን ትክክለኛው የፈጣሪ ስም አላህ መሆኑን ለማስረዳት ከእብራይስጥና ከአራማይክ ጋር በማገናኘት ሲሞግቱ ይታያሉ፡፡ የተያዩ ምሑራዊ ምንጮችን ስንመለከትም አላህ የሚለው ቃል አል-ኢላህ የሚለው ቃል እጥርጥር መሆኑንና ሴማዊ ስረመሠረት ካላቸው ቃላት ጋር ተያያዥ መሆኑን እንገነዘባለን፡፡ ቃሉም “አምላክ” ተብሎ የሚተረጎም እንጂ የተፀውዖ ስም አለመሆኑን እንረዳለን፡፡ ለምሳሌ ያህል የኢስላም ባሕረ ዕውቀት እንዲህ ይላል፡-

Allah is the Arabic equivalent of the English word God, and is the term employed not only among Arabic-speaking Muslims but by Christians and Jews and in Arabic translations of the Bible. A contraction of al-ilah, meaning “the god,” Allah is cognate with the generic pan-Semitic designation for “God” or “deity” (Israelite/Canaanite El, Akkadian ilu) and is particularly close to the common Hebrew term Elohim and the less frequent Eloah. It is thus, strictly speaking, not a proper name but a title. (Richard C. Martin, Encyclopedia of Islam and the Muslim World, p. 39)

ኤል፣ ኢሉ፣ ኤለሂም፣ ኤሎሃ፣ የሚሉት ሁሉ “አምላክ” የሚል ትርጉም ያላቸው የወል ስሞች አንጂ የተጸውዖ ስሞች አይደሉም፡፡ አላህ ወይም አል-ኢላህ የሚለው ቃል ተመሳሳይ ስረ መሠረት ያለው የወል ስም እንጂ የተጸውዖ ስም አይደም፡፡ ሙስሊም ወገኖቻችን ይህ ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኙት የእብራይስጥና አራማይክ ቃላት ጋር እንደሚገናኝ ዕውቅና መስጠታቸው ቃሉ በብቸኝነት እውነተኛውን አምላክ እንደሚጠቅስ መናገራቸው ስህተት መሆኑን ያሳይል፡፡ ከላይ የተዘረዘሩት “አል-ኢላህ” ከሚለው ቃል ጋር አንድ ስረ መሠረት የሚጋሩት ቃላት እውነተኛውን አምላክ ብቻ ሳይሆን ሰብዓውያን ፈራጆችን፣ መላእክትንና ጣዖታትንም ጭምር ለማመልከት ጥቅም ላይ ውለዋልና፡፡

ቅድመ እስልምና የነበሩት አረቦች ቃሉን ከብዙ አማልክት (ኢላህ) መካከል አንዱና ትለቀኛው አድርገው ለሚያመልኩት አምላክ (አል-ኢላህ) ይጠቀሙት እንደነበረ ምሑራዊ ምንጮች ያሳያሉ፡-

Historical evidence indicates that Allah was the name of an ancient Arabian high god in a pantheon of other gods and goddesses like those found in other ancient Middle Eastern cultures. Worshipping him as the only real god may have started before the seventh century in Arabia, but it was in the Quranic revelations delivered by Muhammad as the prophet of Islam between 610 and 632 that the monotheistic ideal received its first clear expression among Arab peoples. (Campo, Encyclopedia of Islam, p. 34)

ቅድመ እስልምና አረብ ጣዖታውያን ትልቀኛው አምላክ አድርገው ያመልኩ የነበሩትና የካዕባ ትልቀኛው አምላክ ሁባል ነበር፡-

The religion of the pre-Islamic Bedouin was primarily animistic, while urban populations, such as the Meccans, worshiped a supreme God, al-Ilah, and its three daughters, al-Uzza, al-Lat, and Manat. Hubal was the chief deity of the Kaba. (Richard C. Martin, Encyclopedia of Islam and the Muslim World, p. 370)

ቅድመ አረብያ እስልምና አላህ የሚባለው አምላክ ሦስት ሴት ልጆች እንዳሉት ይታወቃል፤ እነዚህም አል-ላት፣ መናትና ኡዛ በመባል ይጠራሉ፡፡ “አል-ላት” “አል-ላህ” የሚለው ቃል ሴቴ ፆታ ሊሆን እንደሚችል ሊቃውንት ይናገራሉ፡-

The three most popular goddesses in preIslamic Arabia were al-Lat, Manat, and al-Uzza, sometimes called the daughters of Allah. Al-Lat (possibly the female counterpart of the Arabian high god Allah) was worshipped by Arab tribes in much of the peninsula. (Campo, Encyclopedia of Islam, p. 265)

ከዚህ ምን እንረዳለን? አላህ የሚለው ቃል እውነተኛውን አምላክ ብቻ ሳይሆን ሰዎችን፣ ጣዖታትንና መላእክትን ለማመልከት ጥቅም ላይ ከዋሉት ሴማዊ ቃላት ጋር አንድ ስረ መሠረት የሚጋራ ቃል ነው፡፡ አረብ ጣዖታውያንም ከሁሉም ትልቅ ብለው የሚያስቡትን ጣዖት ለመጥራት ይጠቀሙበት ነበር፡፡ ስለዚህ በሙስሊም ወገኖች ሎጂክ መሠረት አላህ የፈጣሪ ስም ብቻ ሳይሆን የፍጡራንም ስም ነው ማለት ነው፡፡

እውነት ለሁሉ
share👇join👇share
@yenebsetiyakewoch
@yenebsetiyakewoch


ኢየሱስ የፍጡር ስም?

አብዱሎች ኢየሱስ በሚለው ስም የተጠሩ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሚገኙ ኢየሱስ የፍጡር ስም ነው ይሉናል:: ኢየሱስ የስሙ ትርጉም "ያሕዌ አዳኝ" ማለት በመሆኑ ምክንያት ለፈጣሪ ተገቢ የሆነውን ስም ለፈጣሪያቸው ክብር ፍጡራን ተሸከሙት እንጂ በትርጉም ደረጃ ወደ ፍጡራን የሚያመለክት ስም አይደለም:: ሰዎች በዚህ ስም ሲጠሩ ስሙ መታወቂያ ቢሆናቸውም የሚያስተላልፈው መልእክት ወይም ትርጉሙ ወደ ፈጣሪ እንጂ ወደ ፍጡራን አያመለክትም:: ነገር ግን ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ስም ሲጠራ የስሙ ትርጉም ሙሉ በሙሉ እርሱን እንደሚያመለክት አምላክ እንጂ እንደ ፍጡር አይደለም:: ይህ መሆኑ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጽፏል:-

ማቴዎስ 1:21 "ልጅም ትወልዳለች፤ እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ።"

ጌታችን ከኃጢአት ስለሚያድን ነው በዚህ ስም የተጠራው:: ከኃጢአት የሚያድን ደግሞ አምላክ ብቻ ነው:: ስለዚህ ኢየሱስ በዚህ ስም መጠራቱ እርሱ ከኃጢአት የሚያድን ያሕዌ መሆኑን ከማልከት አንጻር ሲሆን ሰዎች በዚህ ስም የተጠሩት ስሙ የተሸከመው ትርጉም ወደ ራሳቸው ሳይሆን ወደ ያሕዌ በሚያመለክት መንገድ ነው::

ከታች የሙስሊሞችን ተመሳሳይ ሎጂክ ተጠቅመን "አላህ የፍጡር ስም" በምትል አጭር ጽሑፍ እለቅላችዋለው::

እውነት ለሁሉ!!

share👇join👇share
@yenebsetiyakewoch
@yenebsetiyakewoch


ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይገባል ዛሬም ነገም እስከለዘላለሙ አሜን!!

መልካም ቀን❤
@yenebsetiyakewoch


ሙስሊም ሰባኪያን ክርስቶስን እናከብረዋለን እንወደዋለን የሚሉት ውሸታቸውን ነው፡፡ ነቢያቸው ሙሐመድም ቢሆን ክርስቶስን በበጎ የጠቀሰው የራሱ “ነቢይነት” ተቀባይነት እንዲኖረው የነበረው ብቸኛ አማራጭ በመሆኑ ነው፡፡ ከክርስቶስ በኋላ “ነቢያት ነን” ብለው የተነሱት ግለሰቦች ሁሉ በተወሰነ መንገድ የራሳቸውን ተልእኮ ከእርሱ ጋር በማያያዝ በእርሱ ሥልጣን ተንተርሰው የራሳቸውን ነቢይነት ተቀባይነት እንዲኖረው ለማድረግ ሲሞክሩ እንመለከታለን፡፡ የክርስቶስ ማንነት የሃቀኝነት፣ የቅድስናና የግብረ ገብነት ጣርያ በመሆኑ እርሱን መቃወም የአንድን ነቢይነ ነኝ ባይ ሐሰተኛነት ከመቅፅበት ገሃድ ያወጣል፡፡ ለዚህ ነው ሙሐመድን ጨምሮ ከክርስቶስ በኋላ የተነሱት ሐሰተኛ ነቢያት ተልእኳቸውን ከእርሱ ጋር በማያያዝ የእርሱን አጽዳቂነት (Validation) ሲፈልጉ የምንመለከተው፡፡ እንደ እውነቱ ከሆነ ግን ሐሰተኛ ነቢያትም ሆኑ የእነርሱ ተከታዮች የክርስቶስ ሕይወትና ትምህርት በኃጢአት የተነከረውን ስብእናቸውን ስለሚኮንን ከክርስቶስ በላይ የሚጠሉት ምንም ነገር የለም፡፡ ለቅቡልነት ሲሉ በአንደበታቸው እንደሚያከብሩት ቢናገሩም በተግባራቸውና በተጠኑ ንግግሮቻቸው እርሱን ዝቅ ለማድረግና የእርሱን ሥልጣን ለማጣጣል ጥረት ሲያደርጉ ይታያሉ፡፡ ሙሐመድ ይህንን ሲያደርግ ነበር፡፡ የእርሱም ተከታዮች ዛሬ ይህንኑ ሲያደርጉ እንታዘባለን፡፡ ለአብነት ያህል በምስሉ ላይ እንደሚታየው አሕመዲን ጀበል የተሰኙ ግለሰብ የጻፉትን ተመልከቱ፡፡ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሐሰተኛ ነቢያትም ሆነ ከተከታዮቻቸው ጋር ሕብረት የለውም፡፡ እነርሱ ዝቅ ሊያደርጉት ቢሞክሩም እርሱ ግን በአባቱ ዘንድ ከዘላለም እስከ ለዘላለም ከብሮ የሚኖር በቅዱሳኑ የሚመለክ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው!

እውነት ለሁሉ


ከህንፃ ቤተ ክርስትያን በላይ የሰዎች ነብስ ሊያሳስበን ይገባል


ሰላም ውድ የዚ ቻናል አባላት እንዴት ናችሁልኝ እንዴት እንደሆነ ባይገባኝም accounte እምቢ ብሎኝ ነበር።

ምንምም መፖሰት አልቻልኩም ነበር።እና የቻናሉ promoter የ prommotion ፖስት ከመፖሰት ውጪ ጠፍቼባችዋለው እና አሁን ተመልሻለው መርሀባ እውነትን እንመሰክራለን ❤!


እኔ ፖለቲካ አልወድም ስለ ብሄርም ስለ ፖለቲካም ስለ ቦታም ፅፌላችው አላውቅም።

ሁሌም ከብሄራችሁም ሆነ ከኢትዮጵያ ቤተክርስትያንን እና ክርስትናችሁን እንድታስቀድሙ ግን እመኛለው።

መቻቻል የሚባል ነገር አይገባኝም ስለመቻቻል እፅፋለው ጠብቁኝ ግን ግን መቻቻል በሚል ካባ ውሸት ለእውነት ስትመሰክር ማየት ያሳዝናል።

እኔ ኢትዮጵያዊ ለመባል መሰተር አለብኝ እንዴ ? እኔ ኢትዮጵያዊ ለመባል በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ያልተባረከ ምግብ መጎራረስ አለብኝ እንዴ?

እኔ ኢትዮጵያዊ ለመባል እስልምናን መሰበክ አለብኝ እንዴ?

ለማንኛውም ከኢትዮጵያዊነት ክርስትናን አስቀድማለው ኢትዮጵያዬም ከፍ ትበል ሰፋ አድርጌ እመለስበታለው በዚ ጉዳይ በደንብ እፅፋለው
@yenebsetiyakewoch
@yenebsetiyakewoch

20 last posts shown.

3 004

subscribers
Channel statistics