Posts filter


የሰው ልጅ የልምምድ ውጤት ነው፡ በልምምድ እንጂ በመወለድ ብቻ ሰው መሆን አይቻልም።

በነገራችን ላይ ከወዳጆች ጋር በመሆን ይወ ወይም Yw shopping የተሰኘ "ኦርጂናል" ምርቶችን የምታገኙበትን የቴሌግራም መገበያያ ከፍተናል።

የሚፈልጉት አይተው እንዲሸምቱ አሁንም እጋብዝዎታለሁ። የቴሌግራም አድራሻው ይህ ነው ➡️ @ywshopping


እንኳን ለማዕዶት አደረሳችሁ። ማዕዶት ማለት መሻገር ሲሆን ከሲኦል ወደ ገነት የተሻገርንበት ቀን ነው። ከሲኦል የወጣንበት ቀን ፀአተ ሲኦል ነው-ሰኞ። ከምድራዊው ሲኦልም እንድትወጡ ከዚሁ ጋር አያይዤ ለመናገር እፈልጋለሁ። በሌላ እንዳትረዱት። የራሳችሁን ሀገር ሲኦልም ገነትም ማድረግ በእናንተ እጅ ላይ ነው። ሀገራችሁን ከሲኦል ወደ ገነት አምጧት። እኔ የቆምኩበት ግድብ ሰው ሰራሽ ሀይቅ ነው። ወንዝ አቧራ እያጠበ እንዲሄድ አይፈቅዱለትም።

በጀርመን ሀገር ወንዞች ፏፏቴ እንዲያሰሙ እንኳን አይፈቅዱላቸውም። በጀርመን ያሉ ወንዞች በትብብር እንዲሰፉ ተደርገዋል። የኢትዮጵያ ወንዞች ግን እንደመነጩ አፈሩን እያጠቡ ነው ሳይሰናበቱ የሚፈሱት። እናንተ በትብብር ብታሰፏቸው ኖሮ ግን እንደዛ አይዘሉም ነበር።

ሰዎችን እያፈናቀለ የኮሪደር ልማት ከሚል አስሬ እርከን ከመስራት 130 ሚሊዮን ህዝብ ካለ ወንዞች እንዲሰፉ ቢደረግ በሁለት አመት ውስጥ ቢያንስ ከኢትዮጵያ የሚታጠበው አፈር ብዙ ይቀንስ ነበር። የጀርመን ወንዞች እንደዛ ነበሩ ድሮ። ሀገራችሁን ሲኦልም ገነትም የምታደርጓት በእናንተ የትብብር እጅ ነው። ውሸት የለመደ ማህበረሰብ እውነት ሲነግሩት ውሸት ይመስለዋል።

ግፉዓን (Afrikaans Edition) https://amzn.eu/d/ecDfNKF


ፎቶ ገጭ 😎

እንኳን አደረሳችሁ ወዳጆች ፤ ለበዓል የፈለጋችሁት ምርቶች ከወዳጆች ጋር በጀመርነውና "ይወ ወይም Y.W Shpping" ብለን በሰየምነው የመገበያያ መድረክ ለራሳችሁ እና ለወዳጆች ማዘዝ ትችላላችሁ።

የቻናሉ አድራሻ ይሄ ነው 👉🏿 @Ywshopping


መሆን ከተመኘህ ፣ ዛፍነትን ምረጥ
ቆርጠዉህ ሲሄዱ ፣ ሺ ሆነህ አቆጥቁጥ

(ይስማዕከ ወርቁ)
@yismakeworku


... የተበደለ ሰው፣ ችግር ላላት ነፍሱ
ኑሮ እንዴት ነው ቢሉት፣ ፈገግታ ነው መልሱ።

@yismakeworku


"መንገድ ብዙዎችን ያገናኛል። ጉንዳኖች ተያይዘው በሚሠሩት መንገድ ታላቅ ወንዝ ይሻገራሉ። ጉንዳኖች ተያይዘው ዓባይን ሲሻገሩ ዓይቻለሁ። እኛም ተያይዘን በምንሠራው መንገድ ወደስልጣኔ እንሸጋገራለን። የኢትዮጵያን እውናዊ አንድነት ከቃል የምናሸጋግረው ህዝቡን በኢኮኖሚና በብዙ ማህበራዊ መስተጋብሮች ስናስተሳስረው ነው። መንገድ የኢትዮጲያ አንድነት ደም ሥር ይሆናል። ..."

ዴርቶጋዳ
ገጽ 196

መንገዳችንን አትዝጉብን። ለማስተላለፍ የተሞከረው ሐሳብ ይህ ነው።


"እያንዳንዱ ሰከንድ የዘላለምን ያህል ረዝምብናል። ከአስጨናቂው ትንፋሻችን በቀር የሚሰማን ነገር የለም።ጭንቅላታንችን ቁሟል። ባዶ ...። እንደ ባዶ ጭንቅላት የሚከብድ ነገር የለም ።"

የኦጋዴን ድመቶች

@yismakeworku


ከዚህ ቀደም ቃል በገባችሁልኝና "አዎ በአንተ የማህበራዊ ሚዲያዎች ማስታወቂያ ብታስነግርን ማስታወቂያውን "Like, Share and Comment" በማድረግ እናግዝሃለን" ባላችሁኝ መሰረት እነሆ ጥሪ አቀረብኩ!

በዚህ የቴሌግራም ገፅ ወይም ከ240 ,000 በላይ ወዳጆች ባፈራሁበት የፌስቡክ ገፅ ማስታወቂያ ማሰራት የምትፈልጉ ቤተሰቦች @YWPromo በተሰኘው መድረክ ስለ ድርጅታችሁ፣ ማስተዋወቅ ስለፈለጋችሁበት ሁናቴ ብታሳውቁኝ የሶሻል ሚዲያ ተቆጣጣሪው ሁሉንም ያሳውቃችኋል።

መልዕክት / ማስታወቂያ ለማስነገር ምን ያስፈልጋል ?

✅ ሀቀኝነት፣ ተዓማኒነት (ወዳጆቼ ላይ ጥርጣሬ የማይጭር)

✅ ክፍያ በተመለከተ በመነጋገር መፈፀም ይቻላል።
(በቴሌግራም ገፄ ብቻ ማስተዋወቅ የምትፈልጉ ለብቻው የዋጋ ደረጃ ስላለው እሱን ግልፅ ማድረግ)

✅ ረጅም ጊዜ ማስታወቂያ ከሆነ ውል ማዘጋጀት።

Contact : @YWPromo


የሆሳዕና በዓል በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ቀኖ መሰረት ከዘጠኙ አብይ በዓላት ውስጥ አንዱ በዓል ሲሆን የሚከበረውም ከትንሳኤ አንድ ሳምንት ቀድሞ በሚውለው እሁድ ነው። ሆሳዕና ማለት መድሃኒት ማለት ነው።በዚያቺ እለት ወደ ቤተ መቅደስ ሲገባ ሆሳዕና እያለ ስላመስገኑት እለቱ በጌታ ስም ተጠርቷል ።አንዳንዶች ክርስቲያኖች ደግሞ ሆሳዕናም እያሉ ይጠሩታል:አንዳንዶቹም የፀበርት እሁድ እያሉ ይጠሩታል ።

ፀበርት እየተባርክ ለህዝብ ይታደላል ህዝቡም ፀበርቱን እየተቀበለ እንደ መስቀል አድርጉ እየሰራ እራሱ ላይ ያስራል በቤቱም ይስቅለዋል አንዳንዴም እንደ ጣት ቀለበት አደርጉ እየሰራ በጣቱ ይስክዋል በቤተክርስቲያን በእለቱ ከቅዳሴ በኃላ በአራቱ ማዕዘናት ወንጌላት ይነበባሉ።ከስርክ ሆሳዕና ጀምሮ እስክ ትንሳኤ ያሉት እለታት የአመተ ፍዳ መታሰቢያ (ስሞነ-ሕመማት) ሰለሆኑ ፀሎተ ፈትሐት አስተርእዮ አይፈጸምም።

በአንዳንድ አከባቢዎች ታሪኩን እንዳለ ለመግለጥ አህያ ጭነው በዚያ ላይ ስው እያስቀመጡ ስራዐተ -ዑደት ይፍፀማሉ።

እንኳን አደረሳችሁ፣ እንኳን አብሮ አደረሰን!

@yismakeworku


ሰይፉ ፋንታሁን ፈጣሪ ያን መጥፎ ጊዜዬን እንዳሳለፈልኝ ሁሉ ላንተም ጤናህን እንዲመልስልህ እፀልያለሁ አንተ መልካም ሰው!

@yismakeworku


አፍሪካንስ ቋንቋ (Afrikaans language)
(ይስማዕከ ወርቁ)

ብዙ ጊዜ ለአማዞን የመጻህፍት ቲም (Amazon team) የአማርኛ ቋንቋ የብቻው የፊደል ገበታ እንዲሰጠው ጽፌአለሁ። ቀደምት ከሆኑት የአፍሪካ ቋንቋዎች አንዱ የሆነው የግዕዝ ቋንቋ ቢሆንም የአማርኛ ቋንቋ ብዙ እድገት ያሳዬ ነው። ብዙ መጻህፍትም ተተርጉመውበታል። አሁን ግን የግሌ ብቻ ሳይሆን እንደ ቋንቋ የብዙሃኑ ድምጽ ጭምር ያስፈልጋል። በአማዞን ላይ የአማርኛ ወይም የግዕዝ መጽሀፍ ለማንበብ ስትገቡ አንድ የሚያስቸግር ነገር አለ። ይኸውም ከአማዞን የፊደል ገበታ ላይ የአማርኛ ወይም የግዕዝ የፊደል ገበታ የለም። ለምሳሌ የሌሎች ሀገራት የእንግሊዝኛ፣ የጀርመንኛ፣ የፈረንሳይኛ፣ የአረብኛ፣ የቻይንኛ ወዘተ ቋንቋ ሲኖር፣ አማርኛ ወይም ግዕዝ ፊደል ግን የለም። በጥቅሉ Afrikaans language በሚባል ውታፍ ሥር ታገኙታላችሁ። ማንም አማዞን ላይ መጽሐፉን ለመጫን የተሰናዳ ሰው የሚገጥመው ፈተና ይሄ ነው።

ይህ Afrikaans language የሚባለው ቋንቋ ምን አይነት ቋንቋ ነው ብዬ ማንበቤን ቀጠልኩ። የሚያስገርም ነገር ጫፍ ላይ ደረስኩ። ቅኝ ገዥዎች ለካ ለአፍሪካ ሀገር ብቻ አልፈጠሩም። ቋንቋም ጭምር ፈጥረውለታል። Afrikaans language የሚባለው ቋንቋ በአፍሪካ ጫፍ የሚነገር ቋንቋ ነው። "በኬፕ ኦፍ ጉድ ሆፕ" የሚነገር መላ ቅጡ የጠፋበት ቋንቋ። የብዙ ቋንቋዎች ክልስ። የኔዘርላንድ፣ የጀርመን እና የፈረንሳይ ቋንቋ ክልስ ነው።

አፍሪካንስ ቋንቋ (Afrikaans language) የቅኝ ገዢዎች ቋንቋ ብቻ አይደለም፤ ከ17ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በኮይሳን ተወላጆች (በደቡብ አፍሪካ፣ በናሚቢያ፣ በዚምባቡዌ፣ በሞዛቢክ) እና የእስያ ባሪያዎች ቋንቋ አድርገውታል። እንዴውም መጽሀፍ ቅዱስን ሁሉ ተርጉመውበታል። በውስጡም የባህል ቅርስ ለማልበስ ሞክረዋል። እንደ ኔዘርላንድስ ደች፣ ቤልጂየም ደች፣ የኢንዶኔዥያ ደች እና የሱሪናም ደች በተለየ ከብሔራዊ ዝርያ ይልቅ የተለየ መደበኛ ቋንቋ አድርገውታል። በደቡባዊ አፍሪካ የሚገኙትን የአፍሪካ ህዝቦች፣ የአፓርታይድ አገዛዝ ህዝቦቹን ሲጨቁንበት የኖረ ቋንቋ ነው።

በአማዞን (Amazon books) ላይ መጻህፍትን መጫን ለመላው አለም ንባባችን እንዲዳረስ ዘመኑ የደረሰበት መሠረት ነው። ሆኖም ግን በአፍሪካ ሰፊ ህዝብ የሚናገራቸው ቋንቋዎች አሉ። ለምሳሌ አማርኛ ቋንቋ ፊደሉን ከግዕዝ ከወረሰ ወዲህ፣ በአፍሪካ ደረጃ ብዙዎቹ እየተግባቡበት ያለ ቋንቋ ነው። ብዙ መጻህፍትም በአማርኛ ቋንቋ አማዞን ላይ አሉ። አማዞን ላይ ለመጫን ግን የአማርኛ ቋንቋ የለም። በአማርኛ መጽሀፉን አማዞን ላይ የሚጭን ሰው መጀመሪያ ቋንቋውን መምረጥ አለበት እርሱም Afrikaans language የሚለውን ነው። ስለዚህ ለአማዞኖች (Amazon teams) አማርኛ ቋንቋ ራሱን ችሎ እንዲገባ ብዙ ጊዜ ፅፌላቸዋለሁ። እናንተም ዘመቻውን ተቀላቀሉ። ይህ ለትውልድም የሚተርፍ ሥራ ነው። ከዚህ በታች እኔ የጫንኳቸው ምን ያህል ቋንቋዬ እንዳልገባ ለማሳዬት ያህል ነው።

ሜሎስ (Afrikaans Edition) https://a.co/d/4kPnhSH
ተልሚድ (Afrikaans Edition)
https://a.co/d/cp9VX4f
ግፉዓን (Afrikaans Edition)
https://a.co/d/hmg9lJT
ተልሚድ (Afrikaans Edition)
https://a.co/d/2TITJQ9
ዴርቶጋዳ (Afrikaans Edition)
https://a.co/d/hGhO25E


ከመጸለይህ በፊት ተመስገን በል። ስለሁሉም ነገር አመስግን...በረከቶችህን ቁጠር! ጠዋት ገና ከእንቅልፍህ ስትነቃ....አይኖችህን ስትገልጥ በል!!!...ሞተህ ልታድር ትችል ነበርና!!! ደግሞ ከአልጋህ ወርደህ መሬት ስትቆም……‹‹ተመስገን>> በል! በሆነ ምክንያት የአልጋ ቁራኛ ሆነህ ልትቀር ትችል ነበርና!!! በየትኛውም መንገድህ ላይ አመስግን። ምስጋና ቢስ አንደበቶች ልመናን ሲያሻግሩ ለዛቸውን ያጣሉ!

እጅግ የምወደው የሙያ አባቴ ደራሲ ስብአት ገብረ እግዚአብሔር

@yismakeworku


እንዲህ ከባድ ድብደባ ተፈፅሞብኝ ከተዘረፍኩ 4 ዓመታት ተቆጠሩ። ጊዜው ይከንፋል።

እነሆ አሁን በሙሉ ጤንነት ላይ በጀርመን ሀገር እየኖርኩ እገኛለሁ

ከዛ በኋላም መፅሀፍ ፅፌ ወደ እናንተ አድርሻለሁ። እንዲሁም ከወዳጆች ጋር በመሆን ይወ ወይም Yw shopping የተሰኘ "ኦርጂናል" ምርቶችን የምታገኙበትን የቴሌግራም መገበያያ ከፍተናል።

የሚፈልጉት አይተው እንዲሸምቱ አሁንም እጋብዝዎታለሁ። የቴሌግራም አድራሻው ይህ ነው ➡️ @ywshopping


ከብዙ ትክክል ከሆኑ ሰዎች ቀድመው (በፍጥነት) ጨዋታውን በትክክል ገምታችሁ የመፅሀፍ ሽልማት ያሸነፋችሁ ሰዎች ስም ዝርዝር፡
(ቴሌግራም ላይ ባሰፈራችሁት ስማችሁ መሰረት)

1. Fishoooo Wegderes
2. ቃል ነፍስ ህይወት
3. typing....

በነዚህ የቴሌግራም ስያሜ የምትጠሩ አሸናፊዎች በውስጥ መስመር ቢያዋሩን ምንም እንኳ እኔ በጀርመን ሀገር ብገኝም ወዳጆቼ ያሉበት ድረስ እንዲያቃብሏችሁ አደርጋለሁ።


"እልፍ አእላፍ ቅማል...
የወረሰው ሱሪ - ተናዞልኝ ሞቶ
ይኸው እቀምላለሁ - ያ'ባቴን ድሪቶ።"

ይስማዕከ ወርቁ (ኑዛዜ)


ካላወቃችሁ ከወዳጆች ጋር በመሂን
ይ.ወ ወይም YW Shopping

የተሰኘ ሀቅ እና ፍቅር ያለበት እውነተኛ ምርቶች የሚገኙበት የቴሌግራም መገበያያ ሱቅ ከፍተናል።

የኔ ኑዛዜም የሚሆነው ቻናሉን ጆይን በማድረግ እቃ እንድትገዙ ነው 😁

ወረኛ ሁኛለሁ ልበል? 😁

ቻናሉ በዚህ ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ ፡ 🔜 @ywshopping


ይወ | YW Online Shop🇪🇹 በሚል ወደ እናንተ መጥተናል።

በሀቅ ልናገለግልዎ ተዘጋጅተናል።

✅ ትክክለኛ (Original) ምርቶችን ፤ ባሉበት ልናደርስልዎ እነሆ የእርስዎን ስልክ በመጠባበቅ ላይ እንገኛለን!

YW Shopping🇪🇹 ምቾትን ያስቀደሙ በእምነትና ፍቅር ወደ እርስዎ የሚደርሱ ምርቶች መገኛ!

📱 የቴሌግራም ቻናሉን Join ይበሉና ይዘዙ ➡️ @ywshopping


"የትርክት ኃይል"

ተፃፈ በ Gemechu Merera Fana
-
እዚህ ሰፈር ስንቱን አጤሪራ እያዘጋጀን በማስጠናት ሙድ ያሳየሁት Game of Thrones የተሰኘ ተከታታይ ፊልም ነበር። ( ጉራ intended)! የማይታመኑ ሱፐር ናቹራል ገቢሮች (የሞተ የሚነሳበትን፣ ድራጎን የሚበርበትን ወዘተ) የማይመቹኝን ሰውዬ ሰኞ ጠዋት 11:00 ላይ 'ፓይሬት ሳይቶች' ላይ ጠብቄ አዳዲስ ኢፒሶዶች እንዳይ ያደረገኝ ውስጡ የታጨቀው ገራሚ የቃላት ምልልስ ነው።
ሁለተኛው ሲዝን ላይ ሎርድ ቫርይስ እና ሎርድ ቲሪዮን ቁጭ ብለው ወይን እየጠጡ ይወያያሉ . . .
*
VARYS: Power is a curious thing, my lord. Are you fond of riddles?
TYRION: Why, am I about to hear one?
VARYS: Three great men sit in a room. A king, a priest and a rich man. Between them stands a common sellsword. Each great man bids the sellsword kill the other two. Who lives, who dies?
TYRION: Depends on the sellsword.
VARYS: Does it? He has neither crown nor gold nor favor with the gods.
TYRION: He has a sword, the power of life and death.
VARYS: But if it's swordsmen who rule, why do we pretend kings hold all the power? When Ned Stark lost his head, who was truly responsible? Joffrey? The executioner? Or something else?
TYRION: I've decided I don't like riddles.
VARYS: Power resides where men believe it resides. It's a trick, a shadow on the wall. And a very small man can cast a very large shadow.

*
አራት ሰዎች አሉ። ንጉሥ፣ ካህን፣ ባለሀብት እና ቅጥር ነፍሰገዳይ። የመጀመሪያዎቹ ሦስቱ ነፍሰገዳዩን ተመሳሳይ ነገር ነው የሚያዝዙት። ወደሁለቱ ጠቁመው "ግደላቸው" ነው የሚሉት። ከሦስቱ ኃይለኛው ማናቸው ናቸው፣ ነፍሰገዳዩሰሰ የማንን ትዕዛዝ ይፈፅማል? ነው ጥያቄው። በቫርይስ ዕንቆቅልሽ/ተረት ውስጥ ነፍሰገዳዩ ሕዝብን ነው የወከለው።
ነፍሰገዳዩ ኃይማኖተኛ ከሆነ ንጉሡንና ባለሀብቱን ይገላል። መንግሥትን ማገልገልና መታዘዝ አለብኝ ካለ ካህኑንና ባለሀብቱን ይገላል። የሚሻለኝ ሀብት ነው ካለ ደግሞ ንጉሡንና ካህኑን ይገድላል። ከሦስቱ ሰዎች በobjective መለኪያ ኃይል ማናቸውም ጋር ቢኖር ዋጋ የለውም፣ ነፍሰገዳዩ ኃይል አለው ብሎ የሚያምንበት ሰው ብቻ ነው ከሞት የሚተርፈው። ኃይል subjective ነው። የሚመጣው ደግሞ በትርክትና በድርጊት ነው።
በቫርይስ እንቆቅልሽ/ተረት ነፍሰገዳዩ ሕዝብን ነው የሚወክለው። ሕዝቡ የሚያምንበትን ራሱ ይመርጣል። ሕዝብ ኃይል አለው ብሎ የሚያምንበት አካል ኃይል ይኖረዋል። የተለያዩ አካባቢዎች ላይ የተለያዩ ገዢ dominant ትርክቶች አሉ። ለአንዳንዱ የድል፣ ለሌላው የዕስር ትርክቶች (and the vice versa) ናቸው። በየአካባቢው ትርክቶቹን የሚጠቀሙባቸው እንዳሉ ሁሉ፣ የትርክቱ ታጋቾች (hostages of that narrative) አሉ። ለዚህ ነው ሁሉንም ወደመሀል የሚያመጣ ትርክት የሚያሻው። 'What's history but a fable [we] agreed upon እንዲሉ!
"Power resides where men believe it resides."
* * *
ከጥቂት ዓመታት በፊት ነው። ከሀገራችን ከተሞች ውስጥ በአንዷ ባርና ሬስቶራንት ያላት አንድ ጓደኛዬ ቤት የተፈጠረ ነው። ሁለት ሰራተኞቿ ተጣልተው ካለችበት ተደውሎ ተጠራች። ዘበኛውና ወጥ ቤቷ ናቸው የተጣሉትና ቤቱን ቀውጢ ያደረጉት።
ወጥ ቤቷ ታለቅሳለች። "በቃ አሰናብቺኝ!" ብላ ኡኡ ትላለች። ምክንያቷን በብዙ ልመና ተጠይቃ ተናገረች። ዘበኛው ሰድቧት ነው። ዘበኛውና ወጥ ቤቷ የሁለት የተለያዩ ብሔር አባላት ናቸው። (አልጠቅስም)። እና ዘበኛው "እናንተማ ጠገባችሁ! ልክ አስገባሻለሁ አንቺ ጥምብ *ብሔር*" ብሏታል። አበደች። እና ለጓደኛዬ እያለቀሰች ብሶቷን፣ ስድቧን ስትናገር እንዲህ አለቻት
"እኔን "ጥምብ *ብሔር*"ይለኛል እንዴ?! እሱ የትኛውን ትግሬ/አማራ/ኦሮሞ ሆኖ ነው?!"
*
"Power resides where men believe it resides." Varys


ማን ያሸንፋል?

ቀድመው ውጤቱን በትክክል ለገመቱ 3 ሰዎች የሚፈልጉትን አንድ መፅሀፌን በስጦታ መልክ የማበረክት ይሆናል።

ጨዋታው እስከሚጀመር ድረስ ግምትዎን በዚህ አድራሻ ይላኩልኝ @WhowinsBot


ማቸነፋችን አይቀርም😁💪🏿


ደራሲን እንደ ሰው ያለመመልከት አባዜ አለ፥ እናንተም ይሄን ያስተዋላችሁ ይመስለኛል። ከድርሰት በተጨማሪ እናንተን የሚጠቅሙ እና በርግጥም ቢተዋወቁ መልካም ናቸው የምላቸውን መልዕክቶች ባጋራ ምን ይመስላችኋል?
ተጨማሪ ገቢ መጨመር የድርሰት ነፃነትን ይሰጣል።

ሀሰተኛና ያልተረጋገጡ ማስታወቂያዎችን በጭራሽ አለጥፍም!

ስለሆነም እናንተ አንድ ነገር ልጠይቃችሁ! በዚህ ገፅ ከግጥም፣ ድርሰቶችና ቁምነገሮች በተጨማሪ ማስታወቂያዎችን ባጋራ የድርጅቶችን መልዕክቶችን በመከታተል እና ገንቢ አስተያየት በመስጠት ታግዙኛላችሁ?

🅰️ አዎ ፣ ማስታወቂያዎችን ብታጋራ እኛም እነሱን በመከተል እናግዝሃለን
🅱️ አይ፣ ላግዝህ አልፈልግም

ምረጡ ወዳጆች!

20 last posts shown.