TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
English
Site language
Russian
English
Uzbek
Sign In
Catalog
Channels and groups catalog
Search for channels
Add a channel/group
Ratings
Rating of channels
Rating of groups
Posts rating
Ratings of brands and people
Analytics
Search by posts
Telegram monitoring
Telegram Analytics
Subscribe to stay informed about TGStat news.
Read channel
ad
TGStat Bot
Bot to get channel statistics without leaving Telegram
Start bot
ad
TGAlertsBot
Monitoring of keywords in channels and chats
Subscribe
ad
SearcheeBot
Your guide in the world of telegram channels
Start bot
ad
Statistics
Favorites
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
@zemarian
Channel's geo and language:
Ethiopia, Amharic
Category:
not specified
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ቤት የሚከናወኑ ተግባራቶች አስመልክቶ ቆየት ያሉ ያሬዳዊ ዝማሬ በሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ፣የሰንበት ት/ቤታችን ወቅታዊ ትምህርቶና የቤተክርስቲያን ወቅተዊ ጉዳዮችን ለማግኘትና ለመማማር
@zemariann
ይቀላቀሉን፡፡
ለማንኛውም አስተያየት
@mzbot_bot
Related channels
|
Similar channels
Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Favorites
Is this your channel?
Confirm
Канал в реестре блогеров РКН?
Confirm
Channel history
Posts filter
Select month
December 2024
November 2024
October 2024
September 2024
August 2024
July 2024
June 2024
May 2024
April 2024
March 2024
February 2024
January 2024
December 2023
November 2023
October 2023
September 2023
August 2023
July 2023
June 2023
May 2023
April 2023
March 2023
February 2023
January 2023
December 2022
November 2022
October 2022
September 2022
August 2022
July 2022
June 2022
May 2022
April 2022
March 2022
February 2022
January 2022
December 2021
November 2021
October 2021
September 2021
August 2021
July 2021
June 2021
May 2021
April 2021
March 2021
February 2021
January 2021
December 2020
November 2020
October 2020
September 2020
August 2020
July 2020
June 2020
May 2020
April 2020
March 2020
February 2020
January 2020
December 2019
Hide deleted
Hide forwards
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
1 Dec, 20:31
Open in Telegram
Share
Report
1.5k
0
1
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
1 Dec, 20:31
Open in Telegram
Share
Report
ኅዳር ጽዮን
"ጽዮን" ማለት "ጸወን አምባ፣ መጠጊያ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል፡፡
ኅዳር ፳፩ ቀን በታቦተ ጽዮን የተፈጸሙ ታላላቅ ተአምራት የሚታሰቡበት ቀን ነው፡፡ በዚህ ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የታቦተ ጽዮንን ተአምራት እግዚአብሔር ቃል ቅድስት ድንግል ማርያምን ታቦቱ አድርጎ ከፈጸማቸው ታላላቅ የድኅነት ሥራዎች ጋር በማነጻጸር እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በነገረ ድኅነት ውስጥ ያላትን ድርሻ በስፋት ታስተምራለች፡፡
ነቢዩ ሙሴ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ጸልዮና ጹሞ ዐሥርቱ ቃላት የተጻፈበትን ጽላት ከእግዚአብሔር የቃል ኪዳኑን ታቦት ‹ታቦተ ጽዮንን› እንደተቀበለ መጽሐፍ ቅዱስ ይገልጻል፡፡
ታቦተ ጽዮን ከማይነቅዝ እንጨት የተቀረጸችበት ምክንያት የእመቤታችን ድንግል ማርያምን ንጽሕና ለማመልከት ነው፡፡ በውስጥም በውጪም በጥሩ ወርቅ የተለበጠች መሆኗ ደግሞ የእመቤታችን ድንግል ማርያም ቅድስናዋንና በሁለት ወገን ድንግል የመሆኗ ምሳሌ ነው፡፡
ንጉሥ ዳዊት የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ጽዮን ከተማ ባስመጣበት ወቅት በታቦቷ ፊት በሙሉ ኃይሉ በደስታ እየዘለለ ለእግዚአብሔር በዝማሬ ምስጋና አቅርቧል፡፡ ‹‹ለንጉሥ ዳዊትም “እግዚአብሔር የአቢዳራ ቤት የነበረውን ሁሉ ስለ እግዚአብሔር ታቦት ባረከ” ብለው ነገሩት፡፡
ዳዊትም ሄዶ የእግዚአብሔርን ታቦት ከአቢዳራ ቤት ወደ ራሱ ከተማ በደስታ አመጣት፡፡ ከእርሱም ጋር የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ሰባት መሰንቆ የሚመቱ መዘምራን ነበሩ፤ በሬዎችንና በጎችን ይሠዉ ነበር፡፡ ዳዊትም በእግዚአብሔር ፊት በገና ይደረድር ነበር›› እንዲል፤ ነቢዩ ዳዊት በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት የተቀኘው ለሰው ልጆች ሁሉ የመዳናችን ምክንያት የሆነችውን ቅድስት ድንግል ማርያምንና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ሲያመስገን ነው፡፡ (፪ሳሙ.፮፥፲፪-፲፬)
ታቦተ ጽዮን እስራኤል የዮርዳኖስን ባሕር ለመሻገር በተቸገሩ ጊዜ ነቢዩ ኢያሱ እግዚአብሔር አምላክ በነገረው መሠረት ካህናቱ የቃል ኪዳኑን ታቦት ይዘው በሕዝቡ ፊት ወደ ዮርዳኖስ እንዲሄዱ ነገራቸው፤ እነርሱም እንደታዘዙት አደረጉ፤ ታቦቱን የተሸከሙት የካህናቱ እግሮች በውኃው ዳር ሲጠልቁ ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል በደረቅ መሬት ጸንተው ቆመው ነበር፤ ሕዝቡም ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው እስኪሻገሩ ድረስ እስራኤል ሁሉ በደረቅ መሬት ተሻገሩ፡፡ (ኢያ. ፫፥፩-፲፯)
እስራኤላውያን በመካከላቸው የቃል ኪዳኑ ታቦት በያዙ ቁጥር በጦርነታቸው ሁል ጊዜ ያሸንፉ ነበሩ፡፡ ነገር ግን ልዑል እግዚአብሔር ሕዝበ እስራኤል ስለበደሉት እንዲሁም የኤሊ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ በደላቸውና ክፋታቸው ስለበዛ ታቦተ ጽዮን ተማርካ ወደ ፍልስጥኤም ሄደች፡፡ በዚያ በአሕዛብ ምድርም ልዩ ልዩ ተአምራትን እያደረገች ፍልስጥኤማውያንን ስለአስጨነቀቻቸው የፍልስጥኤማውያን አለቆች የቃልኪዳኑን ታቦት ልዩ ልዩ ገጸ በረከቶችን አስይዘው ወደመጣችበት በሠረገላ አድርገው በክብር ሸኝተዋታል፡፡ (፩ኛ.ሳሙ. ፭፥፩-፲፭)
ሀገራችን ኢትዮጵያም በንግሥተ ሳባ አማካኝነት ለታቦተ ጽዮን መቀመጫ እንድትሆን የእግዚአብሔር ፈቃዱ ሆኗል፡፡ ይህም እንዲህ ነበር፤ ንግሥተ ሳባ የንጉሥ ሰሎሞንን ጥበብ ለማድነቅ ምድረ እስራኤል ድረስ መጓዟን ተከትሎ ከንጉሡ ቀዳማዊ ምኒልክን ፀነሰች፡፡
ቀዳማዊ ምኒልክ ከአደገ በኋላ አባቱን ሊጠይቅ ሂዶ ወደ ኢትዮጵያ ሲመለስ አብረውት አንድ ሺህ ሁለት መቶ እስራኤላውያን የበኩር ልጆች፣ ሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት በአዛርያስ የሚመሩ ሌዋውያን ካህናትም አብረውት ለጉዞ ተነሡ፡፡ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍትንና ሌሎች በርካታ ቁሳቁሶችን ይዘውም ነበር።
ነገር ግን ታቦተ ጽዮንን አዛርያስና ካህናቱ ተማክረው ቀዳማዊ ምኒልክ እንኳን ሳይሰማ በምሥጢር ይዘዋት ሊመጡ ተስማሙ፡፡ ዕቅዳቸውን ለማሳካት በታቦተ ጽዮን አምሳያ ሌላ ታቦት አዘጋጅተው ለመሄድ በሚነሡበት ዕለት ሌሊትም ወደ ቤተ መቅደስ ይዘውት ሄዱ፡፡
ከቤተ መቅደስ ሲደርሱም የእግዚአብሔር ፈቃድ ነበርና የቤተ መቅደሱ በር ተከፍቶ እና ውስጡም በብርሃን ተሞልቶ ታቦተ ጽዮንም ከመንበሯ በመነሣት ከፍ ብላ አገኟት። በዚህም የአምላክን ፈቃድ ተረድተውና እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በፍጥነት ይዘዋት ወጡ፡፡ በአምሳያዋ የሠሩትንም ቅርፅ በመንበሩ ላይ አስቀምጠው ሄዱ።
የንጉሡ ወታደሮች በፍጥነት ቢጓዙም ቀዳማዊ ምኒልክ እና አዛርያስ ታቦተ ጽዮንን ይዘው ሲጓዙ እጅግ ፍጣን ስለበር ሊደርሱባቸው አልቻሉም። መጽሐፈ ክብረ ነገሥት ይህንን ሲጠቅስ ‹‹ከመሬት አንድ ክንድ ያህል ከፍ ብለው ይሄዱ ነበር›› በማለት ይገልጸዋል። ባሕረ ኤርትራን ከተሻገሩና ግብፅ ከደረሱ በኋላ ዕረፍትን ባደረጉ ጊዜ አዛርያስ ለቀዳማዊ ምኒልክ ታቦተ ጽዮንን ይዘዋት እንደመጡ ነገረው፡፡
አያይዞም ‹‹አንተም ብትሻ ታቦቷንም ወደ ሀገሯ ልመልሳት ብትል አትችልም፤ አባትህ ሰሎሞንም ሊወስዳት ቢመጣ አይሆንለትም›› አለው። ከቦታ ቦታ ይዣት እንቀሳቀሳለው ቢልም ያለ ፈቃዷ ምንም እንደማያደርግና ሁሉ ነገር በአምላክ መልካም ፈቃድ እንደሚፈጸም ነገረው። ቀዳማዊው ምኒልክም ይህን ሲሰማ ተደሰተ፤ ሕዝቡና ሠራዊቱ በሙሉ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ ከግብፅ ምድር ወጥተው እስከ ኢትዮጵያ በታላቅ እልልታና ሆታ እግዚአብሔርን እያመሰገኑ መጡ።
ኅዳር ፳፩ ቀን አክሱም በደረሱ ጊዜም እናቱ ንግሥተ ሳባ ተቀበለችው፤ ደስታና እልልታውን ተመልክታ ያገኙት ነገር እንዳለ ብትጠይቀው ታቦተ ጽዮንን እንዳመጧት ነገራት፡፡ የእርሷም ደስታ እጥፍ ድርብ ሆነ። ታቦቷንም በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ማርያም ቤተ ክርስቲያን አስቀመጡአት፡፡
ከዚያም ዘመን ጀምሮ በየዓመቱ ኅዳር ፳፩ ቀን ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም በታቦተ ጽዮን የተፈጸሙ ታላላቅ ተአምራትን በማሰብ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ታከብራለች፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!!!
ምንጭ፤
ክብረ ነገሥት ተርጓሚ ሥርግው ገላው (1994 ዓ.ም)
መዝገበ ታሪክ ቊጥር 1 (መምህር ኅሩይ ኤርምያስ)
1.4k
0
4
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
24 Nov, 20:39
Open in Telegram
Share
Report
2.3k
0
2
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
24 Nov, 20:39
Open in Telegram
Share
Report
#ማር_ሚና (#ቅዱስ_ሚናስ_ገዳም)
ከራሱ አልፎ ለሀገርና ለወገኖቹ የተረፈ ፣በተባበረ ክንድ በረሃን ለምለም ያደረገ ተፈጥሮን በጥረት ያሸነፈ፣ የቅዱሳን አጽም ማረፊያ የሆነ ታላቅ ገዳም።
በታችኛው ግብጽ ይገኛል። ከፍተኛ የሆነ በረሃማነት ያለው ገዳም ነው። ይህ ገዳም ጥብቅ የሆነ ገዳማዊ ሥርዓትና የመነኮሳት አቀባበል ያለውና ከ120 በላይ መነኮሳትን የያዘ ነው። ገዳሙ 34 የተለያዩ ፋብሪካዎች ያሉት ሲሆን ከ1500 በላይ ሠራተኞችን ቀጥሮ የሚያሠራና ከግብጽ ገዳማት 1ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ገዳም ነው። ገዳሙ በጣም በረሃማ ቢሆንም የሚያመርተውን ምርት ወደ ተለያዩ ሀገራት export በማድረግ ለሀገሪቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚያበረክት ገዳም ነው። በሀገሪቷ መንግሥትም ልዩ ትኩረትና ጥበቃም ይደረግለታል። ገዳሙ ከሚያገኘው ገቢም በቀን ከ600 በላይ ለተቸገሩ ወገኖቹ በቋሚነት ርዳታ ያደርጋል።
በተጨማሪም ከንጉስ አፄ ኃይለ ሥላሴ ጋር የቅርብ ወዳጅነት እንደነበራቸው የሚነገርላቸውና የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የሆኑትን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስልዮስን የሾሙትን የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ቅዱስ አጽም ፣የቅዱስ ሚናስና የቅዱስ ማርቆስ ሐዋርያዊ ተረፈ አጽም በገዳሙ ይገኛል።
ዲ.ን አንድነት ተ
Facebook 👉 የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔዓለምና ደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሕይወት ሰንበት ትምህርት ቤት
1.9k
0
1
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
23 Nov, 15:38
Open in Telegram
Share
Report
"ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ"
ልዩ የአባላት የቃል ኪዳን ማጽኛ መርሐ ግብር
በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በሙሉ የተዘጋጀ ልዩ የአገልግሎት ቃል ኪዳን ማጽኛ መርሐ ግብር
በዕለቱም፦
👉 የአባላት ተቋማዊ ለውጥ ትግበራ ማስጀመሪያ ልዩ መርሐ ግብር ይካሄዳል
👉 የማኅበሩ የአገልግሎት ሂደት በታላላቅ ወንድሞችና እኅቶች ይቀርባል
👉 በተቋማዊ ለውጡ ለአባላት የተዘጋጁ የአገልግሎት አማራጮች ጥናት ይቀርባል
👉 እንዲሁም ሌሎች ከአባላት ጋር የተያያዙ መርሐ ግብራት ይከናወናሉ።
እርስዎም በማኅበሩ ምሥረታ ጀምሮ በየትኛውም ወቅት በአባልነት ሲሳተፉ ከነበሩ በዚህ መርሐ ግብር ላይ እንዲገኙ ተጋብዘዋል።
መረጃውን ለሌሎች አባላት በማጋራት የአገልግሎት ግዴታዎን ይወጡ!
ቀን፡
ኅዳር 22/2017 ዓ.ም
ሰዓት፡
ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ጀምሮ
ቦታ፡
በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም እና መጥምቁ ዮሐንስ ካቴድራል አዳራሽ
ለተጨማሪ መረጃ፡- 0911898990
"ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ"
1.8k
0
2
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
13 Nov, 21:52
Open in Telegram
Share
Report
በስደቱ ጊዜ እነ ኮቲባ ወደ ዝንጀሮና ጦጣ እንደተለወጡ ይነገራል ከሥነ ፍጥረት አንጻር ይስማማልን? የስደት ዐቢይ ምክንያቶችን እና ስደቱን ለምን በወርኀ ጥቅምት እናስባለን? ከወቅቱ ጋር የተሳሰረ ምሥጢር አለው የሚሉ ጉዳዮችን በሊቃውንት ምላሽ ይዛለች ።
ሐመር መጽሔት #፴፩ ኛ ዓመት ቁጥር ፲፩ በማሰራጨት ፡በማንበብና በማስነበብ የድርሻችን እንወጣ !
2.8k
0
3
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
13 Nov, 21:52
Open in Telegram
Share
Report
• ሐመር መጽሔት ፴፩ ኛ ዓመት ቁጥር -፲፩ ኀዳር ፳፻፲፯ ዓ.ም በመልዕክት ዐምድ “#እናንተ ግን የሌቦችና የቀማኞች ዋሻ አደረጋችሁት፤” በሚል ዐቢይ ርእስ በሁሉም መስክ ከወሬ ባለፈ ብልሹ አሠራርንና ዘረኝነትን በተግባር የሚፀየፍ አገልጋይ በታሰበው መጠንና ፍጥነት መፍጠር እንዳልተቻለ ፤በተቀደሰው ሥፍራ የጥፋት ርኵሰትን ማከናወን ሊቋቋሙት የማይችሉትን የእግዚአብሔር ቍጣ በራስ ላይ መጥራት ነው።
ሲገሠጹም ከመመለስ ይልቅ ለምን ታወቀብኝ ብሎ ሌላ በደል ለመጨመር መሯሯጣቸውና የእግዚአብሔርን ትዕግሥት መፈታተን መሆኑን አለመረዳታቸው ደግሞ ሌላው ጉዳይ እንደሆነ ፤ ችግር ዳር ሆኖ በማውራት፣ ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በማንሸራሸር፣ ከንፈር በመምጠጥና በተናጠልም እዚህም እዚያም በማለት የሚፈታ እንዳልሆነ ልንገነዘብና ሁላችንም ተገቢውን ሥራ ልንሠራ እንደሚገባ ፤ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ለአጥፊዎች መከታ፣ ሽፋንና ዋሻ የሆኑ አካላትም ከእነርሱ ጋር ከተሳሰሩበት ምድራዊ ማሰሪያ ይልቅ አባታቸው እግዚአብሔርና እናታቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደምትበልጥባቸው አስታውሰው አካሄዳቸውን በማስተካከል ከእውነት ጐን እንዲቆሙ ጥሪዋን ታስተላልፋለች።
. #ዐውደ ስብከት ሥር ‹‹ወዳጄ በእሾህ መካከል እንዳለ የሱፍ አበባ ነሽ››(መኃ.፪፥፪) በሚልርእስ ከመዝሙራት ሁሉ በሚበልጥ መዝሙሩ ጠቢቡ ሰሎሞን በመንፈሰ ትንቢት ስለ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስለ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ስለ ቅዱሳን ጻድቃን ስለ እውነተኞቹ ምእመናን (ክርስቲያኖች)፣ ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ክብር ወዘተ. የተናገረው ነው፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን ትንቢቱን ምሳሌያዊ በሆነ አነጋገር ተናግሮታል፡ መሆኑን ያሳያል።
#በትምህርተ ሃይማኖት ዐምድ ሥር “#ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ (ዕብ.፲፫፥፰)" በሚል ዐቢይ ርእስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን በኦሪት፣በነቢያት ፣በወንጌል፣ እንዴት እንደምስብከው ሰፊ ትምህርት ይሰጣል፡፡ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በሥርዓተ አምልኮቷ የክርስቶስን የባሕርይ አምላክነት በልዩ ልዩ መልኩ ታስረዳለች።
በሥርዓተ ቅዳሴዋ ውስጥ ቤተ ክርስቲያን ክርስቶስን እንደምትሰብከው ሁሉ ሥርዓተ ቅዳሴዋን እና ማኅሌት በምትፈጽምባቸው ንዋየ ቅድሳትም ትሰብከዋለች ።ቤተ ክርስቲያንን ሳያውቋት ሰዎች ስሟን እንዲሁ እናጠፋለን ብለው የሚያስቡበትን ልቡናቸውን ሽህ ጊዜ እንደገና መልሰው መላልሰው ሊያስቡበት ይገባል ። ይህን ሁሉ ቤተክርስቲያን ስታስተምር እየታየች ቤተ ክርስቲያን ስለ ክርስቶስ አታስተምርም ማለት ባላዩት ምስክር መሆን፤ ለራሱ ሳያውቅ እኔ ላሳውቅህ ማለትና ከአንተ ይልቅ እኔ ስለ አንተ አዋቂ ነኝ እንደ ማለት ይቆጠራል፡፡
#ዐቢይ ጉዳይ ዐምድ ሥር ደግሞ “‹‹ወይሠረዉ መፍቀርያነ ወርቅ፤ ወርቅን የሚወዱ ይነቀሉ›› (ቅዳሴ እግዚእ ቁ.፭) በሚል ዐቢይ ርእስ የወቅቱ የቤተ ክህነታችን ፈተና በጥልቀት ትዳስሳለች ።በአሁኑ ዘመን አንዳንድ የቅድስት ቤተክርስቲያን ባለሥልጣናት እንደ መንፈሳዊ መሪነት ሚናቸውን መወጣት ተስኗቸው እንደሚታዩ በመረጃ ትሞግታለች፡፡አንዳንድ የቅድስት ቤተክርስቲያን መሪዎች ብዙውን ጊዜ ከእግዚአብሔር አገልጋይነት ይልቅ እንደ ምድራዊ ምንደኛ፣ እንደ ፖለቲከኛ፣ እንደ ቢዝነስ ሰው ያለ የአካሄድ ዝንባሌን የሚያሳዩም መኖራቸውን ትጠቁማለች፡፡
በተለይ ገንዘብን በመሰብሰብና በማከማቸት ጥማት የታወሩትን ዛሬ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ፈተና ሆነውብኛል ብላ እስከ ማወጅ ደርሳለች፡፡-አንዳንድ የቤተ ክህነቱ ባለሥልጣናት የቅድስት ቤተክርስቲያን የመንፈሳዊ ኃላፊነት ቦታዎችን፣ የአገልጋዮችን ቦታ ገንዘብ ለሚሹ ሰዎች በገንዘብ የሚሸጡ እየተበራከቱ እንደሆነ በመረጃ ትሞግታለች፡፡-በቅድስት ቤተ ክርስቲያን የአገልግሎት መደቦችንና የክህነትን ሥልጣን እንደ ቢዝነስ የሥራ መደቦችን የመሸጥ እና የመግዛት አካሄድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በእጅጉ እየፈተናት ነው፡፡
የካህናት ቅጥርና ዝውውር፣ ስእለትና የምጽዋት ገንዘብ አስተዳደር፣ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሰበሰበችው ገንዘብ የምታውልበት ዓላማ፣ የጥቂት አገልጋዮች ማካበት የብዙ አገልጋይ ካህናት መጎስቆል፣ የገንዘቡ አወጣጥና አገባብ፣ በግንባታ ሥራዎች ላይ ያለው የግዢና የገንዘብ አወጣጥ ሥርዓት የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የኪራይ ቤቶች አስተዳደር፣ምእመናን ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ማቀላጠፊያ ብለው የሚሰጡት ገንዘብ የሚተዳደርበት መንገድ፣ የቤተ ክህነቱ የአገልግሎት መደቦች ስያሜና ቁጥር፣ የንዋየ ቅድሳት አስተዳደር ጥያቄ፣ የሚነሣበት እየሆነ መምጣቱን ታሳያለች ፡፡ ሙሉውን #ከመጽሔቱ ይነበብ
#ክርስትና በማኀበራዊ ዐምድ ሥር ደግሞ "#ጭንቀት ክፍል_፪ "በሚል ርእስ መጋቤ ሐዲስ #አእምሮ ደምሴ #የኳታር ጸርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን የብሉያትና የሐዲሳት ትርጓሜ መ/ር ደግሞ መንፈሳዊ ጭንቀት ስለሰማያዊው እና ዘለዓለማዊው ሕይወት መጨነቅና ማሰብ እንደሆነ በጥልቀት ያስተምራሉ፡፡ከመንፈሳዊ ጭንቀቶች ስቀምጣሉ፡፡ ሙሉውን ከሐመር መጽሔት ታገኛላችሁ፡፡
• #በእናስተዋውቃችሁ ዐምድ ሥር “ከገነተ ልዑል እስከ መንበረ ልዑል”በሚል ዐቢይ ርእስ በሚል ርእስ የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያንን ለመመሥረቱ ምክንያቶችና የአመሠራረት ሁኔታውን የሰንበትትምህርት ቤቱ አመሠራረት፣ የሊቃውንት አሻራ በመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ ቤተ ክርስቲያን ሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም የምረቃ መጽሔትን በምንጭነት በመጠቀም ታስቃኛለች ።
• #በነገዋ ቤተ ክርስቲያን #ዐምድ ሥር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ኦርቶዶክሳውያን ምሩቃን ለቤተ ክርስቲያን ያላቸው አስተዋፅኦ" በሚል ላለፉት ሠላሳ ዓመታት በመላው ዓለም በሚገኙ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የግቢ ጉባኤያትን በመመሥረት ኦርቶዶክሳውያን ወጣቶች ስለ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ፣ ዶግማ እና ቀኖና እንዲሁም ሥርዓት እንዲያውቁ፣ ራሳቸውንም ከክፉ ነገር በመጠበቅ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን ማነጽ እንዲችሉ አገልገሎቱን በማጠናከር ከፍተኛ ሥራ ሲሠራ መቆየቱን ያሳያል ። የግቢ ጉባኤ ተመራቂዎች ከምረቃ በኋላ በቤተ ክርስቲያን ያላቸው ድርሻ ዘርፈ ብዙ ቢሆንም ዓበይት የሆኑትን ሐመር መጽሔት ታስቃኛለች፡:
#በኪነ ጥበብ ዐምድ "#በፍላጻ የተወጋ ልብ-ክፍል ፩ "በሚል እጅብ ባሉ ሀገር በቀል የተፈጥሮ ዛፎች በተከበበ ዐፀደ ቤተክርስቲያን ውስጥ መጸለይ እጅግ ይወዳል፡፡ ከዚያ ውጣ ውጣ አያሰኘውም፡፡ አንድ ቀን እንደልማዱ ሲጸልይ ቆይቶ ጸሎቱን ሲያበቃ ከአንድ ዛፍ ሥር አረፍ አለ፡፡ እጅግ የሚያስደስት መዐዛ ቢያውደው የትመጣውን ለማወቅ ከአንገቱ ተቃንቶ ዙሪያውን ሊቃኝ ጀመረ በማለት ግሩም የኪነጥበብ ጹሑፍ ታስነብባለች ።
• #በጥያቄዎቻችሁ መልስ ዐምዳችን “ወርኀ ጽጌን” ክፍል አንድን በተመለከተ የሚነሡ ጥያቄዎችን መሠረት አድርገን ምላሽ ይሰጡን ዘንድ መጋቤ ሐዲስ ተስፋ ሚካኤል ታከለን በወርኃ ጥቅምት ዝግጅታችን ማቅረባችን ይታወቃል፡፡ ቀጣይና የመጨረሻውን ክፍል ደግሞ ጌታ ወደ ግብፅ የተሰደደበት ምክንያት ለምንድ ነው?
2.6k
0
3
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
13 Nov, 21:52
Open in Telegram
Share
Report
" ..በዚህ ወቅት በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ላይ በስፋት የሚሰማውን ብልሹ አሠራር ማረምና ለቀጣዩ አገልግሎት መልክ ማስያዝ የካህናቱ ትልቅ ድርሻ ነው፡ ፡ ፡"#ሐመር መጽሔት
ሐመር መጽሔት #የኀዳር ወር ዕትም በሁሉም የማኅበሩ ሱቆች ትገኛለች
༺ ༻
#የኅትመት ዘመን ፦#ኀዳር ፳፻፲፯ ዓ.ም ቁ.፲ ፩
#አዘጋጅ ፦በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኀበረ ቅዱሳን በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል #በየወሩ የሚዘጋጅ ትምህርታዊ መጽሔት
• ገጽ ብዛት፦፳፰
ዋጋ ፦፵ ብር
• ሐመር መጽሔት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ሃይማኖት ሥርዓትና ትወፊት ጠብቃ በልማት ተቋማት አስተዳደር በመጽሔት ዝግጅት ክፍል በየወሩ የምትወጣ መንፈሳዊ መጽሔት ናት፡፡
1.7k
0
1
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
10 Nov, 20:26
Open in Telegram
Share
Report
Prev
Next
2k
0
1
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
10 Nov, 20:26
Open in Telegram
Share
Report
#ፎቶዎቹ ፤ እመቤታችን ከልጇ ጋር ያረፈችበት ገዳመ ቊስቋም ማርያም ገጽታ የሚያሳዩ
___
ደብ
ረ ቁስቋም በደቡብ ግብፅ የሚገኝ ተራራ ነው፡፡ ደብረ ቁስቋም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንዲሁም ቅዱስ ዮሴፍንና ቅድስት ሰሎሜን ይዛ ከስደት ሲመለሱ ያረፉበት ቦታ ነው፡፡
ይህም ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብፅ ሽሽ›› ባለው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ (ማቴ. ፪፥፲፫-፲፭)
የክርስቶስ ስደቱ ቀድሞ በነቢዩ ኢሳይያስ ‹‹. . . እነሆ፥ እግዚአብሔር በፈጣን ደመና ተቀምጦ ወደ ግብፅ ይመጣል፡፡ የግብፅም ጣዖታት በፊቱ ይዋረዳሉ›› ተብሎ በተነገረው መሠረት የተፈጸመ ነው፡፡ ነቢዩ ፈጣን ደመና ያለው ጌታችን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ጀርባ ላይ ሆኖ ወደ ግብፅ መውረዱን ለመግለጽ ነው፡፡ ፈጣን ደመና የተባለችውም እመቤታችን ነች፡፡ (ኢሳ. ፲፱፥፩) በስደቱም ጣዖታተ ግብፅ እየተሰባበሩ ሲወድቁ፤ በእነርሱም አድረው ሰውን ሲያስቱ የነበሩ አጋንንትም ሲሸሹ ታይተዋል፡፡
ደግሞም ጌታችን ዳግማዊ አዳም ነውና በምክረ ከይሲ (ዲያብሎስ) ምክንያት ተሰዶ የነበረው ቀዳማዊ አዳምን ለመካስ ተሰደደ፤ በዚህም አጋንንትን ከሰው ልቦና አውጥቶ አሳደደ፡፡
እመቤታችንም ልጇን ይዛ ከስደት ስትመለስ ያረፈችበትን ተራራ ደብረ ቁስቋምን ባረከችው ቀደሰችውም፤ ይህ ተራራ የተቀደሰ ተራራ ስለመሆኑ የእስክንድርያው ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ታኦፊሎጎስ በድርሳነ ማርያም እንዲህ አለ፤ ‹‹ይህም ከሀገሮቹ ሁሉ ተራሮች የሚበልጥ (የተለየ) ከፍ ያለ ተራራ ነው፡፡ በውስጡ ቅዱስ አግዚአብሔር ያድራል፡፡ ይህንን ተራራ የእግዚአብሔር ልጅ ወዶታል፤ አክብሮታልምና፤ ከዓለም ሀገሮች ሁሉ ከተቀደሰች እናቱ ጋር አድሮባታልና፡፡ ከመላእክት ቤት ያድር ዘንድ አልወደደም፤ ቢታንያንም አልመረጠም፡፡ ከተራራው ላይ ባለች ገዳም ቤት ውስጥ አደረ እንጂ፤ ነቢዩ ዳዊት፤ የጽዮንን ተራራ ወደደ፤ በአርያምም መቅደሱን ሠራ እንዳለ፡፡››
‹‹አንተ ተራራ ሆይ የእግዚአብሔር ማደሪያ በሆንህ ጊዜ በኪሩቤልና በሱራፌል መካከል ፍጹም ደስታ ተደረገ፡፡ የመላእክት ሠራዊት ቅዱስ የሆነ ፈጣሪያቸውንና ጌታቸውን ይታዘዙ (ያገለግሉ) ነበር፡፡ አንተ ተራራ ሆይ ያደረብህ ጌታችን ስለሆነ ከተራሮች ሁሉ ከደብረ ሲናም ይልቅ ከፍ ከፍ አልህ፤ ጌታችን በደብረ ሲና ባረፈ ጊዜ ፍጹም ደስታ፣ ታላቅ ብርሃንም በሆነ ጊዜ መቅረብና መመልከት ከሙሴ በቀር የቻለ የለም፡፡ እርሱም ቢሆን ፊቱን ማየት አልቻለም፡፡ ሥጋ ለባሽ ሁሉ እርሱን ዐይቶ በሕይወት መኖር የሚቻለው የለምና፡፡ እኛ ግን አየን፤ ከዚህ ማደሩንም ተረዳን፤ ዳግመኛም ንጽሕት በሆነች በማርያም ዘንድ አየነው፡፡ ቅድስት ከሆነች ከእመቤታችን ማርያም ዘንድ በቤተልሔም ስለ እኛ በተዋሐደው ሥጋ በጨለማና በሞት ጥላ ሥር ያለን እኛን ከቸርነቱና ሰውን ከመውደዱ የተነሣ መጥቶ አዳነን፤ ከዓለም ሁሉ ይልቅ ጣዖትን በማምለክ ሲበድሉም ወደ ግብፅ ሀገር ወርዶ በእነርሱ ላይ የመለኮትነት ብርሃኑን በማብራት ታላቅ የሆነ ክብሩን ገለጠ››፡፡ (ድርሳነ ማርያም)
ኅዳር ፮ ቀን የሚነበበው የመጽሐፈ ስንክሳር ክፍል ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዳግመኛም በኋላ ዘመን ሐዋርያትን በደብረ ቁስቋም ሰብስቦ፤ ታቦትንና ቤተ ክርስቲያኑን አክብሮ የቊርባን መሥዋዕትንም ሠርቶ ቅዱስ ሥጋው ክቡር ደሙን እንደ ሰጣቸው፤ እኛንም ለዚህ ክብር የበቃን እንሆን ዘንድ የእግዚአብሔር አምላክ ቅዱስ ፈቃድ ይሁንልን፤ አሜን።
2.1k
0
7
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
8 Nov, 22:49
Open in Telegram
Share
Report
Prev
Next
የማኅበረ ቅዱሳን ስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት ሦስት አብያተ ክርስቲያናትን አስገንብቶ አስመረቀ።
ማኀበረ ቅዱሳን በአሪና ደቡብ ኦሞ ዞኖች ሀገረ ስብከት ጥቅምት 23፣24 እና 25 ቀን 2017 ዓ.ም ሦስት አብያተ ክርስቲያናትን አስገንብቶ በማጠናቀቅ ለአገልግሎት ክፍት አድርጓል፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን ስብከተ ወንጌል እና ሐዋርያዊ አገልግሎት አብያተ ክርስቲያናቱን ያስገነባው ባለድርሻ እና ተባባሪ አካላትን በማስተባበር ሲሆን የሦስቱ አብያተ ክርስቲያናት ሙሉ የግንባታ ወጪ 15 ሚልዮን 4 መቶ ሺህ ብር መሆኑ እና ወጪውንም በአሜሪካን ሀገር የሚገኙ የስብከተ ወንጌል ቤተሰቦች መሸፈናቸው ተገልጿል።
አብያተ ክርስቲያናቱ የተገነቡት ቀደም ባሉት ጊዜያት የቅድመ ጥምቀት ትምህርት ተሰጥቷቸው አምነው ለተጠመቁ አዳዲስ አማንያን እና በቅርበት ቤተ ክርስቲያን ባለመኖሩ ከምስጢራተ ቤተ ክርስቲያን እና ሥርዓተ አምልኮ ለመካፈል ሲቸገሩ ለነበሩ ምእመናን ነው ።
የተመረቁት ሦስቱ አብያተ ክርስቲያናት የወልባክ ቅዱስ ገብርኤል ፣ የጉዶ አሸከር አቡነ ተክለ ሃይማኖት እና የተንቤል ቅዱስ መርቆርዮስ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።
የአብያተ ክርስቲያናቱ ቅዳሴ ቤት ተከብሮ አገልግሎት በጀመረበት ዕለት ቀደም ባሉት ጊዜያት የቅድመ ጥምቀት ትምህርት ሲሰጣቸው የነበሩ 784 አዳዲስ አማንያን ተጠምቀው የቅድስት ሥላሴ ልጅነትን አግኝተዋል ።
በምርቃት መርሐግብሩ የአሪ እና የደቡብ ኦሞ ዞኖች ሀገረ ስብከት ልዑካን ፣ የማኀበረ ቅዱሳን ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና ሌሎች ልዑካን እና የጂንካ ማእከል አባላት እንዲሁም የጽርሐ ጽዮን የሐዋርያት አንድነት የኑሮ ማኀበር ፣ የላፎቶ ደብረ ትጉኃን ሰ/ት/ቤት እና ጥሪ የተደረገላቸው የስብከተ ወንጌል ቤተሰቦች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
1.8k
0
0
መዝሙረ ማኅሌት ቁ፩ ¶ቻናል
6 Nov, 18:39
Open in Telegram
Share
Report
ወረብ ፩ኛ ኢየሀፍር የ፩ኛ ዓመት የ፮ኛ እሁድ ጽጌ — #መዝሙረ_ማኅሌት #
02:32
ወረብ ፪ኛ እዜምር ለኪ የ፩ኛ ዓመት የ፮ኛ እሁድ ጽጌ — #መዝሙረ_ማኅሌት #
03:16
ወረብ ፫ኛ እንዘ ተሐቅፊዮ የ፩ኛ ዓመት የ፮ኛ እሁድ ጽጌ — #መዝሙረ_ማኅሌት #
03:11
ወረብ ፬ኛ ክበበ ጌራ ወርቅ የ፩ኛ ዓመት የ፮ኛ እሁድ ጽጌ — #መዝሙረ_ማኅሌት #
03:49
ወረብ ፭ኛ ናሁ ተፈፀመ የ፩ኛ ዓመት የ፮ኛ እሁድ ጽጌ — #መዝሙረ_ማኅሌት #
02:35
ወረብ ፮ኛ ተመየጢ ተመየጢ የ፩ኛ ዓመት የ፮ኛ እሁድ ጽጌ — #መዝሙረ_ማኅሌት #
02:17
2.3k
0
17
12
last posts shown.
Show more
14 602
subscribers
Channel statistics
Popular in the channel
Post #16939: Photo
#ማር_ሚና (#ቅዱስ_ሚናስ_ገዳም) ከራሱ አልፎ ለሀገርና ለወገኖቹ የተረፈ ፣በተባበረ ክንድ በረሃን ለምለም ያደረገ ተፈጥሮን በጥረት ያሸነፈ፣ የቅዱሳ...
"ወደ ቀደመው ነገር እንመለስ" ልዩ የአባላት የቃል ኪዳን ማጽኛ መርሐ ግብር በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት በሙሉ የተዘጋጀ ልዩ...
Post #16941: Photo
ኅዳር ጽዮን "ጽዮን" ማለት "ጸወን አምባ፣ መጠጊያ" ማለት ነው:: ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ም...