ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


The best fiction is far more true than any journalism
📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ
👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56
👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


ሁለት ልጆችን ከቤተሰቦቻቸዉ እዉቅና ዉጪ ሰርቆ በመዉሰድ በጉልበት ስራ ላይ ሲያሰማራ የነበረዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመዉ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ጂዳ ወረዳ ዉስጥ ሲሆን ገዜ ታምሩ በተባለ ግለሰብ አማካይነት ነዉ ። ህፃናቱን በተለያየ ጊዜ እና ቀን ከቤተሰቦቻቸው እዉቅና ዉጪ ሰርቆ በመዉሰዱ በእስራት መቀጣቱን የሰሜን ሸዋ ዞን አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት ገልጿል ።

የሰሜን ሸዋ ዞን አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት የተለያዩ ወንጀሎችና የነፍስ ግድያ ምርመራ ክፍል ኃላፊ አቃቤ ህግ አብዮት አስፋዉ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ግለሰቡ ሀምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም በጂዳ ወረዳ ስርጤ ከተማ ዉስጥ ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ ከትምህርት ቤት በመመለስ ላይ የነበረዉን የ14 አመት ልጅ በወር 25ሺህ ብር ክፍያ ታገኛለህ አዲስአበባ ስራ ላስቀጥርህ በማለት አታሎ በመዉሰድ ለጉልበት ስራ እንዳሰማራዉ ገልጸዋል ።

ይህዉ ተከሳሽ ከ3 ቀናት በኋላ ከአዲስአበባ በመመለስ የ13 አመት ልጅን በወር 20ሺህ ብር የሚያገኝበት ስራ እንዳገኘለት በመንገር ከቤተሰቦቹ ሰርቆ በመዉሰድ ወደ አዲስአበባ በመጓዝ ላይ ሳሉ ሙቀጥሬ ከተማ ኬላ ላይ በቁጥጥር ስር ዉሏል ። ተከሳሹ ህፃናቱን አታሎ በመዉሰድ ለጉልበት ስራና ብዝበዛ እንዲገላጡ አድርጓ። ፖሊስ ተከሳሹን በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ የምርመራ መዝገቡን በበቂ ማስረጃ በማደራጀት ለአቃቤ ህግ ልኳል ።

አቃቤ ህግም ህገወጥ የሰዎች ዝዉዉርን ለመቆጣጠር የወጣዉን አዋጅ ቁጥር 1178/2012 እና በወንጀል ህግ ቁጥር 32 ንዑስ አንቀጽ 3 መሠረት ክስ መስርቷል ። ክሱን ሲከታተል የቆየዉ የሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተካሳሹን ጥፋተኛ በማለት በ10 ዓመት እስራትና በ10 ሺህ ብር መቀጮ እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን አቶ አብዮት አስፋዉ ገልጸዋል ።

በመባ ወርቅነህ
#ዳጉ_ጆርናል


በ2017 ዓመት በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ ካጋጠሙት 144 የእሳት አደጋዎች ውስጥ 57ቱ  የቤት ቃጠሎ ነው

በአዲስ አበባ የሚደርሱት አብዛኛው ድንገተኛ አደጋዎች የሚከሰቱት ከጥንቃቄ ጉድለት መሆኑንም የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

በየዓመቱ በአዲስ አበባ እና ዙሪያዋ በርካታ ከፍተኛ እና መለስተኛ አደጋዎች የሚከሰቱ ሲሆን ባለፈው ስድስት ወራት ብቻ 244 አደጋዎች ያጋጠሙ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 144 የሚሆኑት የእሳት አደጋ ፤ ቀሪው 100 አደጋ ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች መሆናቸው ተነግሯል።

ካጋጠሙት 144 የእሳት አደጋዎች ውስጥ 57  የቤት ቃጠሎ በመሆን ቅድሚያ የሚይዝ ሲሆን ይህም ባለፉት ሰባት ዓመታት ውስጥ 737 የሚሆኑት አደጋዎች በመኖሪያ ቤት ያጋጠሙ ናቸው።

የንግድ ሱቆች በሁለተኛ እና ፋብሪካዎች እና ሌሎች ተቋማት ተከታዩን ደረጃ ይይዛሉ።በተመሳሳይም በበጀት ዓመቱ ካጋጠሙት 100 ድንገተኛ አደጋዎች ውስጥ የመጀመሪያ ደረጃ  የሚይዘው የጎርፍ አደጋ መሆኑን ተገልፃል።

በከተማዋ በተደጋጋሚ ስለሚከሰቱ የእሳት እና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች አስቀድሞ በመከላከል እና ሲከሰትም የከፍ ጉዳት ሳያደርሱ መከላከል በሚቻልበት መንገዶች ዙሪያ ኮሚሽኑ ዛሬ ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር  ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ መሃመድ ለብስራት ሬድዮ እና ቴለቪዥን እንደተናገሩት እነዚህ አደጋዎች መንስኤቸው ሲጣራ አብዛኛው ከጥንቃቄ ጉድለት የሚከሰቱ ናቸው ብለዋል።

ይህንን ከጥንቃቄ ጉድለት የሚከሰቱ ድንገተኛ አደጋዎችን ለመከላከል ሁሉም በጋራ መስራት አለበት የተባለ ሲሆን ለህብረተሰቡም የግንዛቤ ማስጨበጫ መስራት እንደሚጠበቅ ኮሚሽነር ኮማንደር አህመድ ማሀመድ ጨምረው ተናግረዋል።

በትግስት ላቀው
#ዳጉ_ጆርናል


ቅዳሜን ከእኛ ጋር" ፕሮግራም በተወዳጁ ብስራት ኤፍ.ኤም 101.1 ዛሬ ይመለሳል፤ ስንመለስ...

[ ] በልዩ ፕሮግራም ቅዳሜን ከእኛ ጋር ዛሬ የሬዲዮ ሞገዳችሁን 101.1 ላይ ካደረጋችሁ አብረን እንቆያለን። 

[ ]  ለትወና ከተፈጠሩ ሰዎች ውስጥ አንዷ ናት፤ ከተሰጣት ገፀ ባህሪ በላይ መሆን የምትችል እና በኮሜዲ ትወና ውስጥ ከጥቂት ሴት ተዋንያኖች መካከል አንዷ የነበረችውን አርቲስት ሰብለ ተፈራን እንዘክራታለን።

[ ] ሀማስ በማያስተዳድረው የፍልስጥኤም ግዛት ዌስት ባንክ የእስራኤል ጥቃት ለምን ቀጠለ?

[ ] የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ26ኛ ሳምንት የመክፈቻ ጨዋታ እሮብ ሲመለስ ቪላ ፓርክ ላይ ሉቨርፑል በሽርፍራፊ ሰከንዶች ነጥብ ጥሏል። ዛሬ በምሳ ሰዓት ጨዋታ ኤቨርተን ከማንችስተር ዩናይትድ ይገናኛሉ። ምሽት ላይ ኤምሬትስ ላይ ደጋግመው በማሸነፍ የሚታወቁት ዴቩድ ሞይስ ዘንድሮ ደካም የሆነውን ዌስትሃም ይዘው አርሰናልን ይገጥማለ። የሳምንቱ ሌላኛው ተጠባቂ ጨዋታ ቪላ ፓርክ ላይ አስቶንቪላ ከቼልሲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል። ነገ በእለተ እሁው ኢትሃድ ላይ ማንችስተር ሲቲ ከሊቨርፑል የሚያደርጉት የሳምንትቱ ትልቁ ጨዋታ ይሆናል። ግምታችሁን ላኩልን

[ ] የቅዳሜ ወሬዎችን እያነሳሳን እንቆያለን ምርጥ ምርጥ ሙዚቃ ትጋበዛላችሁ፤ ተረክም አለ ፣ ስፖርታዊ ጥንቅር ከወቅታዊ መረጃዎች ጋር ተዘጋጅቷል።

ስፖንሰሮቻችን ፦
👉 ዘመን ባንክ
👉 ቨርጂኒያ ፋርማሲውቲካልስ
👉 ጣዕም ዳቦና ኬክ ቤት-ሻወርማን ይቅመሱ
👉 ማር ህይወት ሆስፒታል
👉 ጃፋር የመፅሃፍት መደብር
👉ዲያፕላንትስ - ፍቱን የባህል ህክምና
👉 አውት ዲተርጀንት -የፅዳት መላ

ሁሌም ቅዳሜያችሁን ከ 5 እስከ 7 በተወዳጁ ጣቢያ ብስራት ኤፍ.ኤም 101.1 ላይ እንጠብቃችኃለን።

#ቅዳሜን ከእኛ ጋር
ለአዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎች ቴሌግራም ቻናላችንን #ዳጉ_ጆርናል ይቀላቀሉ
ሊንክ :- @zena24now




አዋጭ ሁለት ሚሊየን አምስት መቶ ሺህ ብር ለሜቄዶንያ ለገሰ

አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ህብረት ስራ ማህበር ለሜቄዶንያ 2,500,000 (ሁለት ሚሊየን አምስት መቶ ሺህ )ብር ለግሷል።

አንድ ሚሊየን ብር በቁጠባና ብድር አንድ ሚሊየን በፋውንዴሽኑ አምስት መቶ ሺህ ብር ከሰራተኞቹና ከአባላት በአጠቃላይ ሁለት ሚሊየን አምስት መቶ ሺህ ለመቅዶኒያ አስገብቷል።

በቀጣይም በየአመቱ አንድ ሚሊየን ብር ለመስጠት ቃል ገብተዋል።

#ዳጉ_ጆርናል


በኢትዮጵያ በአንድ ዓመት ዉስጥ 45 ሰዎች በፖሊዮ በሽታ መያዛቸው ተነገረ

በኢትዮጵያ ባለፋት አስራ ሁለት ወራት 45 ሰዎች በፖሊዮ በሽታ መያዛቸውን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት አስታውቋል።የኢንስቲትዮቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ሀይሉ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም ከፓሊዮ ቫይረስ ነፃ እንድትሆን የተለያዩ ስራዎችን ስትሰራ ቆይታለች።

በዚህም በ2009 ላይ ከዋይድ ፖሊዮ ነፃ መሆኗን የሚገልፅ ሰርቲፊኬት አግኝታለች ብለዋል።ይሁን እንጂ ከ2011 ጀምሮ የፖሊዮ በሽታ በአንዳንድ የኢትዮጵያ ቦታዎች ተከስቷል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ ባለፋት አስራ ሁለት ወራት አርባ አምስት የፖሊዮ ታማሚዎች ሪፓርት ተደርገዋል።

ከኦሮሚያ ክልል 23፣ ከአማራ 7፣ ከጋምቤላ ደግሞ 6 ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።ኢንስቲትዮቱ የተለያዮ በሽታዎችን አስመልክቶ በሚደረጉ ምላሾች ዙሪያ በሳይንሳዊ መረጃ ላይ የተደገፈ ምርምሮችን ሲያከናውን መቆየቱን ዋና ዳይሬክተሩ ገልፀው የፖሊዮ በሽታን በሚመለከት በቂ ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ ስራዎች እንደሚከናወኑ አስረድተዋል።

አያይዘውም በዛሬው እለት በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ ለፖሊዮ በሽታ ምላሽ መሆን የሚችል የሀገር አቀፍ የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት  ዘመቻ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሂዷል።የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት ከጤና ሚኒስቴር፣ከክልል ጤና ቢሮዎች፣ከአለምአቀፍ የፖሊዮ ማጥፋት ፕሮግራም እና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ከየካቲት 14  እስከ 17 2017  ድረስ በ9 ክልሎችና በአንድ ከተማ መስተዳድር የሚያከናውን ይሆናል።በዘመቻውም 18 ነጥብ 3 ሚሊዮን ህፃናትን ለመከተብ ታቅዷል።

ቅድስት ደጀኔ ከጅግጅጋ ከተማ
#ዳጉ_ጆርናል


የአረብ መሪዎች የትራምፕን የጋዛ እቅድ ለመቃወም በዛሬዉ እለት ይመክራሉ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዩናይትድ ስቴትስ የጋዛ ሰርጥ ለመቆጣጠር እና ህዝቦቿን ለማባረር ያቀዱትን እቅድ ለመቃወም ዛሬ አርብ በሳዑዲ አረቢያ የአረብ ሀገራት መሪዎች ተገናኝተዉ ሊመክሩ ነዉ ሲሉ የዲፕሎማቲክ እና የመንግስት ምንጮች አስታዉቀዋል።የሳውዲው አልጋ ወራሽ ልዑል መሀመድ ቢን ሳልማን የባህረ ሰላጤው አረብ ሀገራት፣ ግብፅ እና ዮርዳኖስን መሪዎች በመዲናይቱ ሪያድ ለስብሰባ መጋበዛቸውን የሳዑዲ አረቢያ መንግስት የዜና ወኪል ኤስፒኤ ዘግቧል።

ስብሰባው መደበኛ ያልሆነ እና "መሪዎቹን በሚያገናኝ የቅርብ ወንድማማችነት ግንኙነት ማዕቀፍ" ውስጥ ይካሄዳል ሲል ኤስፒኤ አክሏል፡፡የትራምፕ እቅድ የአረብ ሀገራትን አንድ አድርጎታል፣ ነገር ግን ክልሉን ማን ማስተዳደር እንዳለበት እና መልሶ ግንባታውን እንዴት መደገፍ እንዳለበት ላይ አለመግባባቶች አሉ።የሳዑዲ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ኤክስፐርት የሆኑት ኡመር ከሪም ጉባኤውን ባለፉት አሥርተ ዓመታት ለሰፊው አረብ ዓለም እና ለፍልስጤማዉያን “በጣም አስፈላጊ ነዉ” ብለውታል።

ትራምፕ ዩናይትድ ስቴትስ "የጋዛን ሰርጥ ትቆጣጠራለች" እንዲሁም 2.4 ሚሊዮን ህዝቦቿ ወደ ጎረቤት ግብፅ እና ዮርዳኖስ እንዲዛወሩ ባቀረቡት ጥሪ አለም አቀፋዊ ቁጣ ቀስቅሷል።"የአረብ የጋራ ዕርምጃን በተመለከተ እና በጉዳዩ ላይ የወጡትን ውሳኔዎች በግብፅ ሪፐብሊክ ውስጥ በሚካሄደው የመጪው የአረቦች አስቸኳይ ጉባኤ አጀንዳ ይሆናል" ሲል ኤስፒኤ በመጥቀስ በእስራኤል እና ፍልስጤም ላይ ለመወያየት በመጋቢት 4 ለሚደረገው አስቸኳይ ጉባኤ ዕቅዶች ይያዛሉ ብሏል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል


ወሊሶ በደረሠ የትራፊክ አደጋ የስድስት ሰዎች ሕይወት አለፈ

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ወሊሶ ወረዳ በደረሠ  የተሽከርካሪ አደጋ የስድስት ሰዎች ሕይወት አልፏል።

የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ ፣3-83143 ኢቲ የጭነት ተሽከርካሪ ሴኖትራክ ተሽከርካሪ ከጐሮ ወደወሊሶ ሲጓዝ ከወሊሶ ወደ ወልቂጤ አስራ ሰባት ሰው አሣፍሮ  ሲጓዝ ከነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ጋር በመጋጨቱ  የሚኒባሱ ሹፌሩን ጨምሮ ወዲያው አራት ሠዎች ህይወት አልፏል።

በሆስፒታል ደግሞ ሑለት ሰው በአጠቃላይ ስድስት ሠው ሲሞት አስራ አንድ ሰው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል። አደጋው ዛሬ ንጋት ላይ የደረሠ ሲሆ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ወሊሶ ቅዱስ ሉቃስ ሆስፒታል በህክምና ድጋፍ ላይ እንደሚገኙ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ የኮሙኒኬሽን ኃላፊ ኢንስፔክተር ትግሉ ለገሠ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል


ኢትኮፍ ያስገነባውን የቡና ማዕከል አስመረቀ

ኢትኮፍ ያስገነባውን ባለ አምስት ወለል የቡና ማዕከል በትናንት  እለት የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው የመንግስት አካላትና እንግዶች በተገኙበት የምርቃት ስነስርእት ተካሂዷል::

ይህ የቡና ማዕከል በውስጡ የመዝናኛ ማዕከልን የያዘ ሲሆን የቡና ቅምሻ ስርዓትን፣ የባህላዊ ቡና አቅርቦትን፣ ሰርቶ ማሳያ፣ የቡና ትርኢት፣ የአርት ጋለሪና ቢዝነስ ሴንተርን ማካተቱም ተገልጿል::

ኢትኮፍ ለመጠጣት የተዘጋጁ የቡና ምርቶችን በራሱ ፋብሪካ ውስጥ እያመረተ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን እነዚህን ምርቶችንም ሃገር ውስጥ ለሚገኘው የውጪ ማህበረሰብ፣ ለኤምባሲዎች፣ ለዲፕሎማቶች፣ ለተለያዩ አየር መንገዶች፣ ደረጃቸውን ለጠበቁ ባለ ኮከብ ሆቴሎች ያቀርባል፡፡

በተጨማሪም ከሃገር ውጪም ኤክስፖርት የሚያደርግ ሲሆን ለተለያዩ የግል ተቋማት፣ ለመንግስት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች፣ መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች እስከ ቡና ማፍያ ማሽን እንደሚያቀርብ ተነግሯል፡፡

ኢትኮፍ ቡናን ከተለመደው በጥሬና ቆልቶ ወደውጪ በመላክ በርካሽ የሚሸጥበትን ልማድ በመቀየር አዲስ አሰራርን ይዞ የመጣና ለሃገራችን በተለይም ለከተማችን ቱሪዝም ዕድገት የበኩሉን ድርሻ የሚያበረክት ነው ተብሏል::


በሰብል አበበ
#ዳጉ_ጆርናል


በሱዳን ነጭ ናይል ግዛት የኮሌራ ተጠቂዎች ቁጥር ከ400 በላይ መድረሱን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች ተዘጉ

ከፍተኛ የሆነውን የኮሌራ ወረርሽኝ ለመግታት በኮስቲና ዋይት ናይል ግዛት ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸው የተገለፀ ሲሆን እስካሁን ድረስ ከ400 በላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች እና 13 ሰዎች መሞታቸውን የክልሉ ባለስልጣናት ሪፖርት አድርገዋል። የኮሌራ በሽታ መስፋፋት በደቡባዊ ሱዳን በምትገኘው የነጭ ናይል ግዛት ነዋሪዎች ላይ ስጋት ደቅኗል። አክቲቪስቶች ሰዎች በበሽተኞች የተጨናነቀውን ኮስቲ ሆስፒታልን እንዲደግፉ አስቸኳይ ጥሪ አቅርበዋል።

የዋይት ናይል ግዛት የትምህርት ሚኒስቴር ተጠባባቂ ሚኒስትር አል-ታይብ አሊ ኢሳ በሰጡት መግለጫ “በኮስቲ የሚገኙትን ሁሉንም ትምህርት ቤቶች እና መዋለ ህፃናት ለአንድ ሳምንት ለመዝጋት ተወስኗል” ብለዋል። ውሳኔው ባለፉት ሰአታት ውስጥ “አጣዳፊ ተቅማጥ” መከሰቱን ተከትሎ የነጭ ናይል ጤ ሚኒስቴር ግምገማ የህብረተሰቡን እና የተማሪዎችን ደህንነት ስጋት ላይ ይጥላል የሚል ነው ሲሉ ተደምጠዋል።የትምህርት ሚኒስቴር በኮስቲ እና በሌሎች የክልሉ አካባቢዎች ያለውን ሁኔታ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመቀናጀት ትምህርት ቤቶችን መዘጋት ወይም  መከፈትን ለመወሰን ይሰራል ተብሏል።

የነጭ ናይል ግዛት የጤና ሚኒስትር አል ዘይን አደም ሳድ የኮሌራ ተጠቂዎች ቁጥር ከ400 በላይ መድረሱንና 13 ሰዎች መሞታቸውን ገልጸዋል። ሚኒስቴሩ ከአርብ ጀምሮ በአስተማማኝ የአፍ ክትባት ህክምና ለመስጠት እና የኮሌራ ምላሽ ዘመቻዎችን ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉንም ቅድመ ጥንቃቄዎች መደረጋቸውን ተናግረዋል። ሚበኮሌራ ምክንያት በኮስቲ ሆስፒታል በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎች መሞታቸውን የሚያሳየው ሪፖርትን ያስተባበሉ ሲሆን የሟቾች ቁጥርም 13 ብቻ መሆኑን አረጋግጠዋል።

በሱዳን ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች እስከ 80 በመቶ የሚደርሱ የጤና ተቋማት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ ሲሆን 45 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ደህንነቱ በተጠበቀ አካባቢ ውስጥ ሆነውም አገልግሎት መስጠት ሳይችሉ ቀርተዋል። ከፍተኛ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ እጦት ፣የጦርነት ሰለባዎች እና መከላከል የሚቻሉ በሽታዎች ስርጭት እየተባባሰ ባለበት በተዳከመ ስርዓት ውስጥ የኮሌራ ስርጭት ለጤና ቀውሱ ተጨማሪ ፈተና መሆኑን ኮሚቴው አፅንዖት ሰጥቷል።ዓለም አቀፍ ድርጅቶች በተለይም የዓለም ጤና ድርጅት፣ ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን እና ቀይ መስቀል በአስቸኳይ ጣልቃ በመግባት ወረርሽኙን ለመቆጣጠር እና ወደ ሌሎች ክልሎች እንዳይዛመት ለመከላከል የጤና ሚኒስቴር እና የህብረተሰቡን ጥረት እንዲደግፉ ጠይቀዋል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል




የሆንግ ኮንግ ዋና ተቃዋሚ ፓርቲ ራሱን ሊያከስም ማቀዱን አስታወቀ

የፓርቲው ሊቀመንበር ሎ ኪንሃይ በሰጡት መግለጫ የሆንግ ኮንግ ዲሞክራቲክ ፓርቲ መሪዎች በአንድ ወቅት የከተማዋ ትልቁ ተቃዋሚ የነበረውን ቡድን ይበተን ወይስ ይቆይ በሚለው ጉዳይ ላይ ድምፅ ለመስጠት እንደሚሰበሰቡ ገልፆል።

2019 የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞና ቻይና በከተማው ውስጥ ያለውን ተቃውሞ ለመቆጣጠር የወሰደችውን እርምጃ ተከትሎ ከተመሰረተ 31 ዓመታት ያስቆጠረው ፓርቲው አሁን ላይ በህይወት ለመቆየት እየታገለ ነው። የቤጂንግ እና የሆንግ ኮንግ መንግስት ግን እንዲህ አይነት እርምጃዎች ለብሄራዊ ደህንነት አስፈላጊ ናቸው ሲሉ ይከራከራሉ።

በ2021 በሆንግ ኮንግ ውስጥ ለኮሚኒስት አገዛዝ ታማኝ የሆኑ ሰዎች እንደ ህግ አውጭ ወይም የአከባቢ ምክር ቤት አባል ሆነው ሊያገለግሉ እንደሚችሉ የሚያረጋግጥ “የአርበኞች ህግ” እየተባለ የሚጠራ ህግ ወጥቷል። ይህ ህግ ደግሞ አንድ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ በምርጫ እንዳይሳተፍ በትክክል ይከለክላል።

ሊቀመንበሩ ከፓርቲው ስብሰባ በኋላ ማምሻውን በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሚስተር ሎ የፓርቲው አመራሮች “በወቅቱ የፖለቲካ ሁኔታ” ላይ ተመስርተው ፓርቲውን ለማክሰም ወይም ለማቆየት እንዲወስኑ ጥሪ አቅርበዋል። "በሆንግ ኮንግ ዲሞክራሲን ማዳበር ሁሌም አስቸጋሪ ነው፣በተለይም ባለፉት ጥቂት አመታት በጣም ከባድ ሆኗል"ሲሉ ሚስተር ሎ ለጋዜጠኞች ተናግረዋል። የፓርቲው አመራሮች ውሳኔ የተደረገው በፖለቲካ ጫና ስለመሆኑ ሲጠየቁ ግን አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል።

በአሁኑ ሰዓት ፓርቲውን የመዝጋት ሂደት የሚከታተል የስራ ቡድን ተቋቁሟል። በመጪው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ከሚሳተፉት አባላቱ ቢያንስ 75 በመቶ የሚሆኑት እርምጃው ከመጠናቀቁ በፊት ማጽደቅ አለባቸውም ተብሏል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል


ከመንግስት ጋር እርቅ ፈጽመዉ የተመለሱ የቀድሞ የተገንጣዩ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አመራሮች በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ኃላፊነት ተሰጣቸዉ

የመንግሥትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ኅብረተሰቡ ለተቀላቀሉ የቀድሞ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አመራሮች በኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ኃላፊነት ተሰጥቷል።

በዚህም መሠረት፡-

1. አቶ ያደሳ ነጋሣ - በቢሮ ኃላፊ ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የደኅንነት አማካሪ፣

2. አቶ ኦሮሚያ ረቡማ ተሰማ - የኦሮሚያ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ምክትል ኃላፊ፣

3. አቶ ቶሌራ ረጋሣ - የኦሮሚያ አስተዳደር እና ፀጥታ ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሆነው ተሹመዋል።

#ዳጉ_ጆርናል


የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የ16ቱ ጥሎ ማለፍ ድልድል ይፋ ሆኗል ፦

ፒኤስቪ ከ አርሰናል
ሪያል ማድሪድ ከ አትሌቲኮ ማድሪድ
ቤንፊካ ከ ባርሴሎና
ባየር ሙኒክ ከ ባየር ሊቨርኩሰን
ፌይኖርድ ከ ኢንተር
ክለብ ብሩጅ ከ አስቶን ቪላ
ዶርቱመንድ ከ ሊል
ፒኤስጂ ከ ሊቨርፑል

- በቀጥታ 8ቱን የተቀላቀሉ ክለቦች የመጀመሪያውን ዙር ከሜዳቸው ውጪ የመልሱን በሜዳቸው የሚያደርጉ ይሆናል።

ሩብ ፍፃሜ ፦

የፒኤስቪ እና አርሰናል ከ ሪያል ማድሪድ እና አትሌቲኮ

የፒኤስጂ እና ሊቨርፑል ከ ክለብ ብሩጅ እና አስቶን ቪላ

የቤንፊካ እና ባርሴሎና ከ ዶርቱመንድ እና ሊል

የባየርን እና የባየር ሊቨርኩሰን ከ ፌይኖርድ እና ኢንተር የሚገጥሙ ይሆናል።

#UCLDRAW
#ዳጉ_ጆርናል


በአዲስ አበባ ከተማ አምስት ሊትር ዘይት ከ1400 እስከ 1600 ብር እየተሸጠ ይገኛል

በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ መጠን እየጨመረ እንደሚገኝ ብስራት ሬድዮ እና ቴሌቪዥን ባደረገው የገበያ ቅኝት ለማወቅ ችሏል።

በተደገው የገበያ ቅኝት ከዚህ ቀደም 1200 እስከ 1300 ብር ይሸጥ የነበረው አምስት ሊትር የምግብ ዘይት አሁን ላይ ከ200 መቶ እስከ 300 ብር ጭማሪ አሳይቷል።

እንዲሁም መሰረታዊ የምግብ ፍጆታ የሚባሉት ምስር ከ200 ወደ 270 ፣ እንቁላል ከ11 ብር ወደ 18 ብር ጭማሪ የታየበት ሲሆን ሌሎች ምርቶች ላይ በአንድ ሳምንት ውስጥ የተጋነነ የዋጋ ጭማሬ መኖሩን በቅኝታችን አረጋግጠናል።

በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል


የሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም የገጠመው ችግር  ለመቅረፍ የገቢ ማሰባሰብ ስራ ሊጀመር ነው

👉 አካባቢው በረሃማ በመሆኑ ለከፍተኛ ድርቅ የሚጋለጥ ነው

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በማዕከላዊ ጎንደር ሃገር ስብከት በምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተክህነት ለሚገኘው  የሙት አንሣ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንደነት ገዳም የገቢ ማሰባሰቢ መርሃ ግብር ሊከናወን ነው።ለገዳሙ  እስካሁን 11 ሚሊዮን  ብር  የገንዘብ ድጋፍ የተደረገ ሲሆን ለእንቅስቃሴ አስቸጋሪ የነበረውን ቦታ የማስተካከል  እንዲሁም ሌሎች ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኝ እና ወደ ገዳሙ የሚደርስ 8 ኪ.ሜ የጠጠር  መንገድ ተከናውኗል ። 

እነዚህ አብያተ-ክርስቲያናት እና ገዳማት መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን እየሰጡ  እያገለገሉ እንዲቀጥሉ ገቢ የማሰባሰብ መርሃ የሚከናወን መሆኑ ተነግሯል በራሳቸው አቅም ገቢ የሚያስገኙ  ስራዎችን ማከናወን እንዲሁም ምዕመኑ በሚሰጠው መባ እና አስራት በኩራት ይጠቀሳሉ። ሙትአንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም በአሁኑ ወቅት የገጠመው ችግር  ለመቅረፍ የገቢ ማሰባሰብ ስራ አስፈላጊ ነው ተብሏል።

በማዕከላዊ ጎንደር ሐገረ ስብከት በምስራቅ በለሳ ወረዳ ቤተክህነት የሚገኘው ይህ ገዳም፣ ከዘጠና በላይ መነኮሳትና በመቶ የሚቆጠሩ ፀበልተኞች የሚገኙበት እጅግ ድንቅ ተዓምር ያለበት ታሪካዊ የአንድነት ገዳም  ነው ። ይሁን እና  መነኮሳቱ በአሁኑ ወቅት ትልቅ ችግር ውስጥ  ይገኛሉ። አካባቢው በርሃማ በመሆኑ በበጋ ወቅት ለከፍተኛ ድርቅ ይጋለጣል። በዚህም ምክንያት ምንም ዓይነት አዝዕርት አይበቅልበትም ይህን ተከትሎ ቀደም ሲል ድጋፍ ያደርጉ የነበሩት የአካባቢው ነዋሪዎች ሳይቀር ለገዳሙ ምንም አይነት ድጋፍ ለማድረግ ተቸግረዋል መባሉ ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን  ሰምቷል።

ገዳማዊያኑ የሚቀምሱት እህል፣ የሚለብሱት ልብስ በመጠኑ የተሟላላቸው ቢሆንም ከጾም፣ ጸሎት መልስ ስጋቸውን የሚያሳርፉበት  ቤት የላቸውም። በአንድ  ጎጆ  ውስጥ ለሶስት ለአራት የሚያድሩበት ሁኔታ መኖሩ ተነግሯል ።በዚህ ገዳም የሚገኙ ገዳማዊያን  ከጸሃይ፣ ከብርድ፣ከዝናብ የሚከላከል መጠለያ አጥተው በከፍተኛ ችግር እየተፈተኑ የሚገኙ በመሆኑ፣ ገዳማዊያኑን ከነዚህ ችግሮች እንዲወጡና በቀጣይም ገዳሙ ራሱን እንዲችል ለማድረግ፣ በጠቅላይ ቤተክህነት እውቅና እና በሐገረ ስብከቱ ፍቃድ ገዳሙ ብቻ የሚጠቀመው በገዳሙ ስም የተከፈቱ የባንክ አካውንቶች ይፋ ተደርገዋል ። በሕዝበ ክርስቲያኑ በሚደረገው ድጋፍ ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን፣ ገዳሙም የተለያዩ ፕሮጀክቶችን በወረዳ ቤተ-ክህነት፣በሐገረ ስብከትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት ጸድቆ በሊቃነ ጳጳሳት ቡራኬና የቅርብ ክትትል እየተደረገበት በመሰራት ላይ ይገኛል።

እነዚህን የታቀዱ ለገዳሙ አስፈላጊ እና መሰረታዊ የሆኑትን የልማት ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችል ገቢ ለማሰባሰብ የሚረዱ የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ መንገዶችን ለመጠቀም ጥረት  እየተደረገ እንደሚገኝ  ተገልጿል ።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል

16 last posts shown.