የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ ወንጀል ላይ ተሰማርተው ተገኙ በተባሉ ሰባት የኤጀንሲው ባለሙያዎች ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ
የአዲስ አበባ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና መረጃ ኤጀንሲ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ በህበረተሰቡ ዘንድ የሚነሱትን ቅሬታዎች ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጿል። በተቋሙ ውስጥ እና ከተቋሙ ውጭ በሚስተዋለው ህገ-ወጥነት እና ሌብነት ላይ ተሳታፊ የሆኑትን ተጠያቂ እያደረገ እንደሚገኝም ይፋ አድርጓል።
በዚህ መሰረት ባለፉት ሁለት ሳምንታት በተደረገው ክትትል 7 ባለሙያዎች ላይ እርምጃ ሲወሰድ አንድ ባለሙያ በፈፀመው የአሰራር ጥሰትና ወንጀል ክትትል እየተደረገበት ይገኛል።ከዚህ በተጨማሪ በሃሰተኛ ሰነድ ዝግጅት ላይ የተሰማሩ ተጠርጣሪዎች ላይ በሚደርሱ ጥቆማዎች እርምጃ ለመውሰድ እየሰራ መሆኑን የኤጀንሲው ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለሙ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ለአብነትም አዲስ የነዋሪነት መታወቂያ አገልግሎት ከመታገዱ በፊት በልደታ ክ/ክተማ ወረዳ ስምንት አሰራርን በመጣስ እና የዝውውር ማሰረጃ (መሸኛ) ሳይቀርብ የነዋሪነት መታወቂያ በመስጠት አሰራርን የተላለፈው የወረዳው ጽ/ቤት ባለሙያ ከክ/ከተማው የመዋቅሩ ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመሆን ከስራ እንዲታገድ ተደርጎ የወንጀል ምርመራ እየተደረገ ይገኛል። ከዚህ ባሻገር በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 14 ጽ/ቤት ሃሰተኛ መታወቂያ ይዘው በመቅረብ አገልግሎት የጠየቁ ሁለት ግለስቦች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ከጉዳዩ ጋር ተያያዥ የሆነ ተጠርጣሪም ተይዞ በፖሊስ ምርመራ ላይ ይገኛል።
ተቋሙ ሌሎች የቀረቡ ቅሬታዎችንና አቤቱታዎችን መነሻ በማድረግ በሰዓት አገልግሎት ተገኝተው የማይሰጡ፣ አላግባብ ባለጉዳይ ያመላለሱ እንዲሁም መረጃ ሳያጣሩ አገልግሎት የሰጡ ባለሙያዎችን ከማስጠንቀቂያ የዲሲፕሊን እርምጃ እስከ ከተቋሙ ማሰናበት የሚደርሱ ውሳኔዎች አሰራርን ተከትሎ እንዲተላለፉ አድርጓል ሲሉ አቶ ዮናስ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በቤተልሄም እሸቱ
#ዳጉ_ጆርናል