በቢሾፍቱ ከተማ የኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል በርካታ ንብረቶች የሰረቁ 8 ግለስቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ
በቢሾፍቱ ከተማ መስተዳድር ወረዳ 01 የተለያዩ የኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የመስመር ሽቦዎች የሰረቁት ስምንት ግለቦች መያዛቸውን የቢሾፍቱ ከተማ መስተዳድር ወረዳ 1 ፖሊስ ጽ/ቤት ምክትል ዳይሬክተር ኮማንደር ተስፋዬ በክሬ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
ግለሰቦቹ በተለያየ መንገድ በመቀናጅት ለሁለት ቀናት የኢትዮ ቴሌኮም የመስመር ሽቦ በጣጥሰው ሲወስዱ እና ሲሸጡ ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር እንደተያዙ ፖሊስ አስታወቋል።
አራቱ ግለሰቦች ድርጊቱን ሲፈጽሙ እጅ ከፍንጅ የተያዙ ሲሆን በግለሰቦቹ እጅ ላይ በርካታ የኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል የመስመር ሽቦ በኤግዚቢትነት ተይዟል።
በመሰረተ ልማት ላይ የስርቆት ወንጀል በመፈጸም ተጠርጥረው የተያዙት ስምንቱ ግለሰቦች ላይ የምርመራ መዝገብ ተጣርቶ ለምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት መላኩን ኮማንደር ተስፋዬ በክሬ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል