በትግራይ እና በአማራ ክልሎች 16•8 ሚሊዮን ሰዎች እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ተነገረ
በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በአማራ ክልል 11•6 ሚሊዮን ህዝብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገው ተጠቁሟል።ይህንኑ ተከትሎ የአለም ምግብ ፕሮግራም፣ ሲ አር ኤስ እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ህብረት እና በኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በኩል ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን እርዳታ እንዲደርስ እየተደረገ ይገኛል።
እስከ ግንቦት ወር ድረስ 241 ሺህ 697 ሜትሪክ ቶን እህል መላኩን በኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ደበበ ዘውዴ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።እንዲሁም በትግራይ ክልል 5•2 ሚሊዮን ህዝብ ድጋፍ የሚፈልግ ሲሆን የተለያዩ አጋር አካላት ድጋፍ እያደርጉ ይገኛሉ። ለዚህ የኢትዮጵያ መንግስት ድጋፉ ተደራሽ ለማድረግ በአየር ሆነ በየብስ እንዲጓጓዝ ማድረጉን ገልፀዋል።
በገንዘብ ዝውውር ረገድም 1•76 ቢሊዮን ብር ጥሬ ገንዘብ ለሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦት እንዲውል በ92 አጋር ድርጅቶች በኩል ወደ ትግራይ ክልል እንዲገባ ተደርጓል።20,279 ኪሎግራም መድኃኒት ፣ 406 ሺህ 403 ኪሎግራም የተመጣጠነ ምግብ፣ 91ሺህ 558 ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎችን ጨምሮ ውሃ ፣ ንጽህና መጠበቂያ ፣የመጠለያ ቁሳቁሶች በእነዚህ አጋር ድርጅቶች በኩል በአየር ትራንስፖርት መላኩን አስረድተዋል።4,029 ሊትር ነዳጅ ወደ ትግራይ ክልል ተልኳል እስካሁን ድረስ 1626 የጭነት ተሽከርካሪ ወደ ትግራይ ሲሄድ 596ቱ ሲመለሱ 1,030 ያህል እንዳልተመለሱ ተነግሯል።
በሰብአዊ አገልግሎት ድርጅቶች በኩል 221 በረራዎች ተደርገዋል ሲሉ አቶ ደበበ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
በቤተልሄም እሸቱ
#ዳጉ_ጆርናል