የባራክ ኦባማ ሴት ልጅ የኢትዮጲያ የዘር ግንድ ካለዉ አሜሪካዊዉ ዳዊት ኤክሉድ ጋር የፍቅር ግንኙነት ዉስጥ መሆናቸዉ ተነገረ
ማሊያ ኦባማ በሎስ አንጀለስ ከሙዚቃ ፕሮዲዩሰር ከሆነዉ ዳዊት ኤክሉድ ጋር አብረዉ ሲያሳልፉ የሚያሳይ ምስል በ ዴይሊ ሜል ፎቶ ግራፈሮች እይታ ስር ወድቀዋል፡፡ የ 24 ዓመቷ የቀድሞ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ ሴት ልጅ እና የ 33 ዓመቱ ዳዊት ኤክሉድ ጋር በሎስ አንጀለስ ካውንቲ የስነ ጥበብ ሙዚየምን ሲጎበኙ ዘ ዴይሊ ሜይል ባገኛቸው ፎቶዎች ላይ ታይተዋል።
ጥንዶቹ ከንፈራቸውን ሲሳሳሙ ባይታዩም ማሊያ ኦባማ እና ፕሮዲዩሰሩ ተቃቅፈው ነበር ይላል። ዘ ዴይሊ ሜይል የኤክሉንድ እጅ በማሊያ ሰዉነት ላይ ያረፈበት ሁኔታም የፍቅረኞች ይመስላል ሲል አክሏል፡፡
ኤክሉድ በዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ከጆይስ ሊም እና ሳሚ ዬኒጉን ጋር በመሆን 1432 አር የተሰኘ ሪከርድ መስርቷል፡፡ ጥንዶቹ በመገናኛ ብዙሃን እይታ ዉስጥ ሲወድቁ የአሁኑ ለሶስተኛ ጊዜ ነዉ፡፡የኤክሉድ አባት በአፍሪካ በርካታ ሀገራት ውስጥ ባሉ የአሜሪካ ኤምባሲዎች ውስጥ ጡረታ እስከወጡበት ጊዜ የሰሩ ሲሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዉስጥ እንደሰሩና ጆን ኤክሉንድ እንደሚባሉ ድረ-ገጹ ዘግቧል።ወላጅ እናቱ የሺ ኢክሉንድ ይባላሉ።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል