በምስራቅ ሀረርጌ ፍቅረኛሽን ለምን ቤት ይዘሽ ገባሽ በማለት ልጇን በገጀራ ቆርጣ እና አቃጥላ የገደለችው ተጠርጣሪ እናት በቁጥጥር ስር ዋለች
በምስራቅ ሀረርሄ ዞን መደወላቡ ወረዳ አጋቤሎ ቀበሌ ልዩ ስሙ ሀወዳይ ተብሎ በሚጠራው አካበቢ ከዲቻ አብዲ የተባለችው ተጠርጣሪ ሳሪቱ ኢብራሂም የተባለችዋን ሴት ልጇን ሳትጋቡ የፍቅር ጓደኛሽን እንዴት ወደ ቤት ይዘሽ ትገቢያለሽ በማለት በገጀራ ቆርጣ እና በእሳት አቃጥ መግደሏ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ፖሊስ ኮሙኒኬሽን ዲቪዥን ሃላፊ የሆኑት ዋና ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
ሳሪቱ ባለትዳር እና የሶስት ልጆች እናት ስትሆን የቀድሞ ባለቤቷ ትቷት ሲሄድ እናቷ ቤት በድጋሚ ተመልሳ መኖር መጀመሯ ተገልጿል፡፡ ይሁን እና በህዝብ አገልግሎት ስራ ላይ ተቀጥራ በምትሰራበት ወቅት ከተዋወቀችው ሌላ ግለሰብ ጋር የፍቅር ግንኙነት በመጀመር እናቷ ቤት ይዛው መግባቷ ወላጅ እናቷን ደስተኛ አላደረጋቸውም፡፡ሳሪቱ ከአዲሱ ፍቅረኛዋ የሰባት ወር ነፍሰጡር በነበረችበት ወቅት የጠፋው ባለቤቷ መደወሉን እና እንዴት ሌላ ሰው ታገቢያለሽ በማለት ሲጨቃጨቁ የሰሙ እናት የልጃቸውን አዲሱን ፍቅረኛ የቀድሞ ባሏ ሊመጣ ነው በማለት ከመኖሪያ ቤታቸዉ ያባርራሉ፡፡በዚህ ከልጃቸው ጋር ግጭት ዉስጥ የገቡ ሲሆን ፍቅረኛዬን ለምን አባረርሽ በሚል ልጅ እናቷን በእርግጫ ገፍትራ መጣሏን ፖሊስ በምርመራ ወቅት ማረጋገጥ ችሏል፡፡
ይሁን እና ቂም የያዙት እናት ልጅ ስራ ውላ ደክማ በተኛችበት ወቅት በገጀራ አንገቷን ቆርጠው በመግደል ኩሽና ወስደው አስክሬኗን በማቃጠል ቀሪዉን የአስክሬን ክፍል ጎሮ ይቀብራሉ ፡፡
ከሶስት ወራት በኃሏ ቤተሰቧን ለመጠየቅ የመጣችው የሟች እህት እህቷ የት እንደሄደች ብትጠይቅም የተሰጣት መልስ አጥጋቢ አለመሆንና የወላጅ እናቷ ሁኔታ ትጠራጠራለች ፡፡በዚህ ጊዜ ወደ ጎሮ ስትሄድ ደም የነካው የእህቷን ፒጃማ ተቀብሮ ማግኘቷን ለአካባቢው ነዋሪ እና ለፖሊስ ታመለክታለች፡፡
በመሆኑም ፖሊስ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ምርመራው አጣርቶ ተጠርጣሪ የሆኑትን እናት ከዲቻ አብዲ በቁጥጥር ስር ማዋሏን ዋና ኢንስፔክተር ቶሎሳ ጎሹ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡
በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል