በትናንትናው እለት ምሽት 4፡48 ላይ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ህንፃ ላይ የደረሰውን አደጋ ተከትሎ የፖሊስ ምርመራ እንደሚጀመር የከንቲባ ጽ/ቤት አስታወቀ፡፡
ጽ/ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመንና ሌብነትን ለመከላከል የዲጂታይዜሽን ስርዓትን ለመተግበር በርካታ ስራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውሷል::
በተለይም በለሚ ኩራ ክ/ከተማ የነበረውን ብልሹ አሰራር ሌብነትን ለማስተካከልና መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ይረዳ ዘንድ የዘመናዊ የቢሮ ግንባታና የተቋማዊ ሪፎርምና የዲጂታል ቴክኖሎጂ በመተግባር በከንቲባዋ አስተባባሪነት የኢትዮ ቴሌኮም ፤ የአርቴፊሻል ኢንተልጀንስ ፤የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ተቋማት የተሳተፉበት የዲጂታል አገልግት መስጠት የሚያስችል ስራ የፊታችን ቅዳሜ ለምረቃ የሚያበቃ ስራ በትጋት ተሰርቶ እንደነበር ጠቁሟል፡፡
ነገር ግን በትናንትናው እለት ምሽት 4፡48 ላይ የተዘጋጀው ከፍተኛ ቴክኖሎጂና ግብዓት የፈሰሰበት የክ/ከተማው አስተዳደር ህንፃ የእሳት አደጋ ደርሶበት መሰረተ ልማቱ ወድሟል ብሏል፡፡
የአደጋው ምክንያት እና መንስኤ በፖሊስ ምርመራ እየተካሄደበት ሲሆን ምርመራው እንዳለቀ ለህዝብ ይፋ የሚደረግ ይሆናል ሲልም በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል፡፡የአካባቢው ማህበረሰብም መንግስት የጀመረውን ጥረት ለመደገፍ ከዚህ አደጋ ጋር ተያይዞ ማንኛውንም መረጃዎች በመስጠት የተለመደ ትብብሩን እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል፡፡
#ዳጉ_ጆርናል