በብራዚል የ65 ዓመቱ ከንቲባ የ16 ዓመቷን ልጅ በማግባት ለወላጅ እናቷ ከፍተኛ ሹመት ሰጡ
በብራዚል አንድ ከተማ ከንቲባ በተያዘው ወር መጀመሪያ ላይ የ16 ዓመቷን ልጅ በህጋዊ መንገድ ካገቡ በኃላ የሚስታቸውን እናት የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ዋና ኃላፊ አድርገው መሾማቸው ከፍተኛ ውዝግብ አስነስቷል።የ65 አመቱ ዴሃይኒ በደቡብ ብራዚል የምትገኘው የአራካሪያ ከተማ ከንቲባ የሰጡትን ሹመት በፓራና ግዛት የሚገኘው አቃቤ ህግ ፅህፈት ቤት ተቃውሞታል።
ከንቲባው ከሠርጋቸው ከአንድ ቀን በኋላ የሚስታቸውን እናት ሾመዋል።በብራዚል ህግ መሰረት እድሜያቸው ከ16 ዓመት በላይ የሆኑ ታዳጊዎች በወላጆቻቸው ፍቃድ ብቻ በህጋዊ መንገድ ጋብቻ መመስረት ይችላሉ። የሙሽሪትን እናት በማዘጋጃ ቤቱ አስተዳደር ውስጥ ጥሩ ክፍያ በሚያስገኝ የስራ መደብ ላይ ከንቲባው መሾማቸው ግን በብዙዎች ዘንድ እንደ ጉቦ ተወስዷል።
ለቀረበው ክስ ምላሽ የሰጠው የከንቲባው ጽሕፈት ቤት "ሹመቱ አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎችን አሟልቷል በማለት በሕዝብ አገልግሎት የ26 ዓመት ልምድ ስላላት ተሹማለች" ብሏል።ጥንዶቹ አጭርን ቢሆን ወደ ጫጉላ ሽርሽር መሄድ እንደሚኖርባቸው ይጠበቃል።
በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል