ዘመን ባንክ መቄዶንያን ጨምሮ ለበርካታ የበጎ አደራጎት ድርጅቶች በህምጻ ምርቃት ስነስርዓቱ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ
ዘመን ባንክ ያስገነባውን የዋና መስሪያቤት ህንጻ ምርቃት ስነስርዓት በማስመልከት ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።
ባንኩ ለመቄዶንያ የ 3 ሚሊዮን ብር ፣ በቀድሞ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ እና ቀዳማዊት እመቤት ሮማን ስም ለተመሰረተዉ ሀይለማርያም እና ሮማን ፋዉንፌሽን የ 2 ሚሊዮን ብር፣ ለልብ ህሙማን ህጻናትል ማዕከል 2 ሚሊዮን ብር ፣ ቀይመስቀል ማህበር 2 ሚሊዮን ብር ፣ ጌርጌሴኖን የአእምሮ ህሙማን ማዕከል 2 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ለሀይሌ ማናስ አካዳሚ የ2 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።
በተጨማሪም ፕሮጀክት ሀረር ለተሰኘ የግብረ ሰናይ ተቋም 1 ሚሊዮን ብር ፣ የፓርኪንሰን ህሙማን ማዕከል 500 ሺህ ብር ፣ነኸሚያ ኦቲዝም ማዕከል 500 ሺህ ብር ፣ ጎጆ ህሙማን ማረፊያ 500 ሺህ ብር ፣ ፍሬገነት ኪዳን ለህጻናት ማዕከል 250 ሺህ ብር ፣ የወደቁትን አንሱ የነዳያን መርጃ ማህበር 125 ሺህ ብር እና ሰሊሆም የአምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል 125 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል።
በነገዉ እለት ረፋድ ለአቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት በዋና መስሪያቤቱ እንደሚኖር የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ደረጄ መናገራቸውን ብስራት ራዲዮ ሰምቷል።
በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል