ነባር መንደሮችን በማፍረስ የሚከናወኑ የልማት ስራዎች የተጠኑ እና የከተሜነት መርህን የተከተሉ አይደለም ተባለ
መንግስት በኮንዶሚኒየም ግንባታ እና በሌሎች የልማት ፕሮጀክቶች በተለይም በአዲስአበባ እና በዙሪያዋ ነባር መንደሮችን በማፍረስ የሚከናወኑ ስራዎች የከተማ ልማት መርህን የተከተሉ አለመሆናቸውን የፍሊንት ስቶን ሪልስቴት ም/ል ስራ አስኪያጅ አቶ ብሩክ ሽመልስ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።
ፍሊንት ስቶን ፤ ከአመታት በፊት በተለይም በአዲስአበባ የሚገኙ ነባር መንደሮችን በዘመናዊና የከተማዉን ደረጃ በሚጠብቅ መልኩ አፍርሶ ነዋሪዉ ከቀዬዉ ሳይፈናቀልና ወፈ ሌላ ቦታ ሳይዘዋወር ግንባታ ለማድረግ እቅድ ይዞ የነበረ ቢሆንም በአዲስአበባ ከተማ መስተዳድር በኩል ትብብር ባለማግኘቱ ተግባራዊ ሳይደረግ መቆየቱን ገልጸዋል።
ከተማዋን ማስተዳድሩ ከስርዓት ስርዓት ቢለዋዋጥም አሁንም በአዲስአበባ የሚሰሩ ፕሮጀክቶች ነዋሪዉን ወደ ሌላ አካባቢ እንዲፈናቀል የሚያስገድዱ ሆነዉ ዘልቀዋል። በተለይም በመኖሪያ ቤት ግንባታ ላይ ይህ ችግር በስፋት ይስተዋላል። ይህንንም እቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ከግንባታ ፈቃድ ጋር በተያያዘ በአንድ ካርታ ላይ ብቻ ግንባታ መፈቀዱ እና ተጨማሪ መመሪያዎች በማስፈለጋቸዉ ፣ የቀበሌ ቤቶች ባለቤትነት ፣ በግል የመሬት ይዞታ ላይ የቀበሌ ቤቶች መገኘታቸዉ ዉስብስብ እንዳደረገዉና እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ መቸገሩን አንስተዋል።
እንደ አቶ ብሩክ ገለጻ ፤ ከተማ ፈርሶ ነዋሪዉም አንዲበተን ሲደረግ የማህበረሰቡ ማንነትን የሚያጠፋ እና የከተማዉን መገለጫ የሚያሳጣ መሆኑን ጠቅሰዋል። ለዚህም ምክኒያቱ የከተማ አመሰራረትና ግንባታ ላይ መሰረታዊ ግንዛቤ የጎደለዉ አካሄድ ነዉ ብለዋል።
ፍሊንት ስቶን ፤ በአዲስአበባ ተግባራዊ ለማድረግ ያልቻለዉን እቅድ ወደ በኦሮሚያ ፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች ከተማና ከተሜነትን ተግባራዊ ለማድረግ የራሱን እቅድ አሰናድቶ በተለይም በገጠሩ ክፍል የሚገኘዉን ሰፊ የገበሬ ማህበረሰብ በማዘመንና የግብርና ስራዉን ጎን ለጎን እንዲያስኬድ የሚያስችል መንገድ ቢቀይስም ብቻዉን ግን ተግባራዊ ሊያደርገዉ አልቻለም ሲሉ ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል።
በበረከት ሞገስ
#ዳጉ_ጆርናል