የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኛ በስራ ላይ እያለ በኤሌክትሪክ አደጋ ህይወቱ አለፈ
በትላንናው እለት እሁድ ግንቦት 20 ቀን 2015 ዓ.ም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ዓለም ባንክ እየተባለ በሚጠራዉ አካባቢ በኤሌክትሪክ አደጋ የአንድ ሰዉ ህይወቱ ማለፉን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ።
አደጋዉ ያጋጠመዉ ወጣት እድሜዉ 28 ዓመት የሆነ የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኛ ሲሆን በስራ ላይ ሆኖ ባለገመድ የስልክ መስመር በመዘርጋት ላይ እያለ ከከፍተኛ የኤሌክትሪክ መስመር ጋር ተገናኝቶ የሞት አደጋ መድረሰን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የወጣቱን አስከሬን አዉርደዉ ለፖሊስ አስረክበዋል።
በተመሳሳይ ዓርብ ግንቦት 18 ቀን 2015 ዓ.ም በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፖርክ ሰራተኛ በስራ ላይ እንዳለ በኤሌክትሪክ አደጋ ህይወቱ ማለፉ ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል።
በሳምራዊት ስዩም
#ዳጉ_ጆርናል