እንቁላል ጣይ ዶሮ የሰረቀው ታዳጊ የ1 አመት ከ8 ወር እስር ተቀጣ
በምእራብ ጉጂ ዞን ሀምባላ ወረዳ ቢምቱ ከተማ 02 ቀበሌ ውስጥ አንድ ዶሮ ሲሰርቅ የተያዘው ግለሰብ ላይ የእስራት ቅጣት መወሰኑን የሀምባላ ፖሊስ አስታወቀ።
የሀምባላ ወረዳ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል እንደገለፀው ተከሳሽ ሮቤል ሽብሩ የተባለው የ18 አመት ታዳጊ ወጣት ሰኔ 3 ቀን 2016አ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ የአንድ ግለሰብን እንቁላል የምትጥል ዶሮ ሰርቆ በመውሰድ ሲሮጥ እጅ ከፍንጅ መያዙ ተገልጿል።
ግለሰቡ በፖሊስ የምርመራ መዝገብ በአስቸኳይ የተጣራበት ሲሆን የምርመራዉም መዝገብ ለአቃቢ ህግ ተልኳል።
አቃቢ ህግም ወድያውኑ ክስ መስርቶበት በአስቸኳይ ችሎት ውሳኔ እንዲሰጠው በመጠየቁ እንቁላል ጣይ ዶሮ የሰረቀው ታዳጊ ሮቤል ሽብሩ ሙሉ ለሙሉ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ1 አመት ከ8 ወር እስራት እንዲቀጣ የሀምባላ ወረዳ ፍርድ ቤት ውሳኔ ማስተላለፉን የሀምባላ ወረዳ ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ክፍል ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን የላከው መረጃ ያመላክታል።
በማህደር ጌቱ
#ዳጉ_ጆርናል