መንግሥት ጦርነትን እንደ መግዣ ሥልቱ ከመጠቀም ወደ መንግሥታዊ ኃላፊነት በመመለስ አገርና ህዝብን በጋራ ከጥፋት መታደግ ጊዜ የማይሰጠው አገራዊ ጥሪ ነው//
ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ (ኮከስ) በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የተሰጠ መግለጫ
የብልጽግና መንግስት ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ የአገራችን ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተጨባጭ ሁኔታዎች ከዕለት-ወደ
ዕለት ‹‹ ከድጡ ወደ ማጡ›› በሚያስብል ደረጃ ለሁለንተናዊ ምስቅልቅሎሽ እየዳረጉን ነው፡፡
ፖለቲካችን የተለመደውን የአፈናና
አግላይነት፣ የአንድ ፓርቲ የበላይነትና ጠቅላይነት አጠናክሮ ቀጥሏል፤ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከአጃቢነት፣ ህዝብ ከአገልጋይነት ያለፈ የፖለቲካ መብታቸውን የማንሳት ህገመንግስታዊ መብት ተገፎ፣በወንጀል ተቆጥሮባቸው ሰጥ-ለጥ ብለው እንዲገዙ ተፈርዶባቸው በከፍተኛ ድብርት ውስጥ ናቸው፡፡
ኢኮኖሚያችን ወደ ጦርነት ኢኮኖሚ ተሸጋግሮ ለተለያዩ የልማት መሰረተ ልማት አውታሮች ሊውል የሚችል የዓመታዊ በጀታችን ከፍተኛው ድርሻ ለጦርነትና ጸጥታ ማስከበር ግብዓቶች እንዲውል፣ልማትና ዕድገት ከቀለም-ቅብ ያለፈ መሰረት እንዳይኖረው ተገደናል፣ የኑሮ ውድነቱ ከህዝብ አቅም በላይ ሆኖ ምሬትና ተስፋ መቁረጥ በአደገኛ ሁኔታ የመሰደድን ምርጫ እያጎላው መጥቷል፡፡ ማኅበራዊ ህይወታችን በሥራ አጥነት፣መፈናቀል፣የማኅበራዊ ተቋማት መዳከምና የአገልግሎት መቋረጥ ወይም
መቀንጨር፣ የሠራተኞች ብሶት መገለጫቸው ከሆነ ውሎ አድሯል፤
በየአቅጣጫው የሚነሱ ጥያቄዎችም የሚያረጋግጡት ይህንኑ ነው፡
ከትምህርትና ጤና አገልግሎት ተቋማትና ሠራተኞች የሚሰማው ጩሄት በእጅጉ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡
ይህንኑ ለህዝብ፣ ለመንግስትና ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የሚያቀርቡ የሲቪል ማኅበረሰብ ፣የመገናኛ ብዙሃን፣ የሰብዐዊና ምግባረ ሰናይ ተቋማት
ድምጻቸውን የማሰማትና ዓላማቸውን ለማስፈጸም በነጻነት መንቀሳቀስ መብታቸው ከጥያቄ ውስጥ ገብቷል፡፡
በአጠቃላይ የህዝቡን ኢኮኖሚ አቅም ማዳከም፣ የማኅበራዊ ግንኙነት መሥመሮችንና ተቋማትን በመበጠስ ማፈናቀልና በዘር/ቋንቋና
ሃይማኖት በመከፋፈል፣ በትብብር፣መከባበርና መተሳሰብ በተቃራኒ በጥርጣሬና ጥላቻ እንዲተያይ የማድረግ አካሄድ፣ እነዚህንና ሌሎች ተፈጥሮኣዊ ልዩነቶችን ለፖለቲካ በማዋል ህዝብን በመከፋፈል ለተገዢነት በማዘጋጀትና ማመቻቸት ላይ መሆኑ የገዢው ፓርቲ
ድንበር ተሻጋሪ የአደባባይ መታወቂያው ሆኗል፡፡ በዚህ ተጨባጭ ሁኔታ ውስጥ ብልጽግና ‹‹ከተጨፈኑ ላሞኛችሁ›› አካሄዱ አልተላቀቀም፤ይልቁንም ሽግግር በሌለበት ስለሽግግር ፍትህ፣ከመለያየትና መከፋፈል አጥፊ፣ አፍራሽና አጫራሽ ፕሮፖጋንዳ ባልተላቀቀበት ህዝብን ለግጭት እያነሳሳ ባለበት፣ለመወያየትና ድርድር ቁርጠኝነት በሌለበትና ከመገዳደል ወደ መደራደር ፖለቲካ
ለመሸጋገር ወገቤን ባለበት ስለ ምክክር ኮሚሽን አብዝቶ ይደሰኩራል፡፡
ይሁን እንጅ ከባዶ የፕሮፖጋንዳ ድስኩሩ ውጪ ያለውን እውነታ ስንመረምር የሚከተሉትን በግልጽ መረዳት የሚያስችል ተጨባጭ ሁኔቶችን እናገኛለን፡፡
@zena_ethiopia24@zena_ethiopia24