የብዙዎች ዋና ሃሳብ አርሰናል አጥቂ ያስፈልገዋል የሚል ብቻ ነው አዎ አጥቂ ያስፈልገናል ጥያቄው አጥቂ ብቻ በቂ ነው ወይ የሚለው ነው።
ያገኛቸውን እድሎች ወደ ግብ የመቀየር እድሉ ሰፊ የሆነ አጥቂ ማግኘት ለአንድ ክለብ እጅግ ወሳኝ ነው ምክንያቱም ትናንሽ ቡድኖች እንኳን ሳይቀር ትልቅ ፈተና እየሆኑ በመጡበት ሰዓትና ታክቲካዊ ግብግቡ እየጨመረ በመጣበት ቢዘህ ወሳኝ ጊዜ ከ20 በላይ ግቦችን ማስቆጠር የሚችል አጥቂ ማግኘት የግድ ነው።
ለአርሰናል ግን እንደዚህ አይነት አጥቂ ብቻ ማግኘት በቂ አይደለም ፈጣንና ማንም በቀላሉ ሊያስቆመው የማይችል የክንፍ ተጫዋች በጥብቅ ያስፈልገዋል ይህ ቡድን ክንፍ ላይ የተለየ ነገር የሚፈጥር ተጫዋች የለንም ከሳካ ውጪ በተለይ በግራ በኩል ያሉን ተጫዋቾች የተለየ የድሪብሊንግ ብቃት የሌላቸውና አርሰናልን የሚያክል ቡድን ውስጥ ቋሚ ሆኖ የመጫወት ብቃቱ የሌላቸው ተጫዋቾች ናቸው።
ፍጥነቱን ተጠቅሞ በፈጣን መልሶ ማጥቃት ቡድኖች ላይ አደጋ እንድንፈጥር የሚያስችለን፣ጥሩ ኳስ የመምታት ብቃት ያለው፣ወደ ሳጥን ከባባድ ኳሶችን በአየርም በመሬትም ማሻማት የሚችል የክንፍ ተጫዋች የግድ ያስፈልገናል።
ሌላኛው የአስር ቁጥር ተጫዋች ነው ሁላችንም እያስመሰልን ያለ ይመስለኛል በዚህ ጉዳይ ላይ ነገርግን ከሳካ ጉዳት በኋላ ምን ተመለከትን? መልሱ እኮ ግልፅ ነው ያለቀላቸውን እድሎች መፍጠር የሚችል ተጫዋች የለንም መጥፎው ነገር ግን ይህ ችግራችን ሳካ ከመጎዳቱ በፊትም ነበር።
እውነት ከምንም ተነስቶ የግብ እድል መፍጠር የሚችል 10 ቁጥር ተጫዋች አለን፣ኳስን በሚገርም ሃይል የሚመታ፣ተከላካዮች ሊቆጣጠሩት የማይችሉት ፓሶችን ማድረግ የሚችል የአጥቂ አማካይ አለን?
ይህ በእውነቱ ከሆነ ትልቅ ጥያቄ ነው ምክንያቱም እንደዚህ አይነት ተጫዋቾች ምን ያህል ወሳኝ እንደሆኑ ለማየት እዚህ ቦታ ላይ ሌሎች ትላልቅ ክለቦች ያሏቸውን የአጥቂ አማካዮች ማየት በቂ ስለሆነ።
መልካም ቀን!
SHARE
@ETHIO_ARSENAL