የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ግዴታ እና የተከለከሉ ነገሮች1. ማንኛውም ተፈታኝ አጤሬራ፣ ስልክ፣ ሃርድ/ፍላሽ ድስክ፣ ስማርት ሰዓት፣ የጌጥ መነጽር፣ ጌጠኛ ቀለበት፣ ማጂክ ጃኬት፣ ቁልፍ ወይም ምንም ዓይነት ድምጽና ምስል
የሚቀዱ/የሚቀርጹ ኤሌክትሮኒክስ መሣሪያዎችን ይዞ ወደ መፈተኛ ክፍል ውስጥ መግባት የተከለከለ ነው፡፡
2. ፈተና በሚሰጥባቸው ኮምፕዩተሮች ላይ በሚመለከተው አካል ደህንነቱ ያልተረጋገጠ የትኛውንም ዓይነት መተግበሪያ መጫን ወይም ማህበራዊ ሚዲያዎችን መጠቀም የተከለከለ ነው፡፡ ሆኖ ሲገኝም የፈተና ውጤት ከመሰረዝ በተጨማሪ አግባብነት ባለው ህግ ተጠያቂ ያደርጋል፡፡
3. ፈተና እየተሰጠ ባለበት ወቅት በማንኛውም አማራጭ የመፈተኛ ኮምፕዩተሮችን በመጠቀም የኤሌክትሮኒክ መልዕክት ለማንኛውም ሶስተኛ ወገን መላክም ሆነ መቀበል በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡ ሆኖም ሲገኝ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ፈተናው የሚሰረዝ ይሆናል፡፡ አግባብነት ባለው ህግ ተጠያቂ ይሆናል፡፡
4. ማንኛውም ተፈታኝ ከመፈተኛ ክፍል ውጭ ሆኖና ለፈተና ሥራ ተለይቶ እውቅና ከተሰጠው ኮምፕዩተር ውጭ ለመፈተን መሞከር ወይም መፈተን በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን ሆኖ ከተገኘ የፈተና ውጤቱ ሙሉ በሙሉ ይሰረዛል፤ አግባብነት ባለው ህግ ተጠያቂ ይሆናል፡፡
5. ለፈተና ሥራ የሚያገለግሉ የይለፍ ቀሎችን (Password) በማንኛውም ሁኔታ ለሶስተኛ ወገን አሳልፎ መስጠት ወይም ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ መያዝ ወይም በቀላሉ ተገማች ማድረግ የተከለከለ ነው፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ዓይነ ስውራን ተፈታኞች ለአንባቢዎቻቸው ወይም የአካል ጉዳት ያለባቸው ተፈታኞች ለረዳቶቻቸው ሊሰጡ ይችላሉ፡፡
6. ማንኛውም ተፈታኝ ወደ መፈተኛ አዳራሽ መግቢያ ካርድ እና ማንነቱን በግልጽ ለመለየት የሚያስችል የትምህርት ቤት ወይም የቀበሌ መታወቂያ ወይም የወሳኝ ኩነት ምስክር ወረቀት ይዞ የመገኘትና ሲጠየቅም የማሳየት ግዴታ አለበት፡፡ ወደ መፈተኛ አዳራሽ መግቢያ ካርድ ሳይዙ መፈተን የተከለከለ ነው፡፡
7. ተፈታኞች በሐኪም ከታዘዘ መድኃኒት ውጭ ወደ መፈተኛ ክፍል ምንም ዓይነት መድኃኒትና መድኃኒት መውሰጃዎችን ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
8. ተፈታኞች ወደመፈተኛ አዳራሽ ምግብና ውሃ ይዘው መግባት የጠከለከለ ነው፡፡ ነገር ግን አስቀምጠው ለፈታኝ መምህር እያሳወቁ ሲፈቀድላቸው መጠቀም ይችላሉ፡፡
ውስጥ መግባት የተከለከለ ነው፡፡ በጤና ምክንያት የግዴታ መጠቀም ያለባቸው ሲሆኑ ከመፍተኛ ከፍል ውጪ (በር አካባቢ) አስቀምጠው ለፈታኝ መምህር እያሳወቁ ሲፈቀድላቸው መጠቀም ይችላሉ፡፡
9. ተፈታኞች የተሟላ አካላዊ ፍተሻ ተደርጎና ማንነታቸው በግልጽ ተለይቶ ወደ መፈተኛ አዳራሽ የሚገቡ ይሆናል፡፡ ለዚህም የመተባበር ግዴታ አለባቸው፡፡
10. አካላዊ ፍተሻ ሳይደረጉ ፈተና ወዳለበት ሰርቨር እና ኮምፕዩተሮች አካባቢ ወይም ክፍሎች ውስጥ መግባት የተከለከለ ነው፡፡
11. በግልጽ ያልተፈቀደለትን ማንኛውንም ሰው ወደ መፈተኛ ክፍሎች ይዞ መግባት እና ፈተና የሚሰራባቸውን ኮምፕዩተሮች እንዲነካካ ወይም እንዲጠቀምባቸው መፍቀድ በጥብቅ የተከለከለ ነው፡፡
SHARE❤️
https://t.me/+QcLpbg9EiMllODhkhttps://t.me/+QcLpbg9EiMllODhk