#Update
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ በማህተም ተደግፎ ስለተለጠፈው " የምግብ በጀት እጥረት አጋጥሞናል ስለዚህ የሜኑ ማሻሻያ አድርገናል " የሚለውን ማስታወቂያ በተመለከተ መግለጫ አውጥቷል።
ተቋሙ በመግለጫው ምን አለ ?
- " ከዚህ ቀደምም ቢሆን በየወቅቱና እንዳስፈላጊነቱ ' የምግብ ሜኑ ማሻሻያ ' ሲደረግ ነበር። "
- " አንዳንድ ኃላፊነት የማይሰማቸው የማህበራዊ ትስስር ገጾች እንዲሁም የሚድያ ተቋማት ዩኒቨርሲቲው ያደረገውን የምግብ ማሻሻያ ሜኑ አስመልክቶ ተጨባጭነት የሌለውን መረጃ በማሰራጨት የተቋሙን በጎ ገጽታ ለማጠልሸት እና የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ ነው። "
🔴 የትኞቹ ማህበራዊ ትስስር ገጾችና ሚዲያዎች ተጨባጭነት የሌለው መረጃ እንዳሰራጩ በግልጽ ስም አልጠቀሰም።
- " ከወራት በፊት የተደረገ የሜኑ ማሻሻያ ለማሳወቅ ማስታወቂያ ወጥቷል። ይህም የቀን ስህተት የነበረበት መሆኑን እና ' አዲስ የተደረገ የምግብ ሜኑ ማሻሻያ ' እንደሌለ እንገልጻለን። "
- " ኃላፊነት በማይሰማቸው የማህበራዊ ትስስር ገጾች እንዲሁም የሚድያ ተቋማት ' ዩኒቨርሲቲው በምግብ እጥረት ምክንያት ተማሪዎችን ሊበትን ነው ' እየተባለ የሚሰራጨው ሀሰተኛ መረጃ በተቋሙ ዘንድ በፍጹም ተቀባይነት የለውም። "
🔴 የትኛው የማህበራዊ ትስስር ገጽ እና ሚዲያ ተማሪዎች ሊበተኑ ነው ብሎ እንዳሰራጨ ስም አልጠቀሰም።
- " ለተማሪዎቻችን ከምንጊዜውም በላይ የተቋሙ አቅም በሚፈቅደው መጠን ጥራት ያለውን ምግብ በበቂ ሁኔታ በማቅረብ የመማር ማስተማር ሥራው እንዳይስተጓጎል አበክረን እንሰራለን። "
- " ለተማሪዎቹ ወቅቱ በሚፈቅደው አግባብ ጥራቱን የጠበቀ ምግብ ለማቅረብ የሜኑ ማሻሻያ ከማድረግ ያለፈ በተማሪ ምገባ ላይ አንዳች ጉዳት አይፈጽምም። "
- " አንዳንድ ኃላፊነት የጎደላቸው የማህበራዊ ትስስር ገጾች እና መገናኛ ብዙሃን ተቋሙን የፖለቲካ መጠቀሚያ ለማድረግ በዩኒቨርሲቲው ላይ የከፈቱትና እየከፈቱ የሚገኙት የገጽታ ማጠልሸት ድርጊት በፍጹም ተቀባይነት የሌለውም፤ በህግ አግባብ ያስጠይቃል። "
🔴 እዚህም ጋር የትኞቹ እንደሆኑ በግልጽ ስም አልተጠቀሰም።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ፤ ከሰሞኑን በወላይታ ሶዶ እና በዲላ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የተለጠፉትን ማህተም ያረፈባቸውን ተመሳሳይ ይዘት ስላላቸው ማስታወቂያዎች በተመለከተ መረጃ ማጋራቱ ይታወሳል።
ተቋማቱ ውስጥ የተለጠፉ ማስታወቂያዎች ፥ " እንደ ሀገር የምግብ በጀት እጥረት አጋጥሞናል። የምግብ ጥሬ ዕቃ ዋጋም በየቀኑ ከመጨመሩ ጋር በተያያዘ የተማሪዎች የምግብ በጀታቸው ሙሉ በሙሉ ካለቀ ወራት ተቆጥሯል " ይላል።
ይቀጥልና ፥ " ተቋሟችን የሚያደርገው ድጎማ ተማሪዎቻችን ትምህርታቸውን አቋርጠው እንዳይወጡ ባሉን የምግብ ጥሬ እቃዎች አገልግሎት እየሰጠን ነው " ሲል ይገልጻል።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ማስታወቂያ ደግሞ " ባሉን የምግብ ጥሬ ዕቃዎች አገልግሎት እየሰጠን ቢሆንም በአሁን ሰዓት እጅግ በጣም #እየከበደ ስለሆነ የሜኑ ማሻሻያ ለማድረግ ተገደናል " ይላል።
ይህ በተመለከተ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና ቴክኖሎጂ ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር ሀብታሙ ተመስገን ፥ ማስታወቂያውን ሆነ ሀሳቡን #እንደማያዉቁት በመግለጽ " ማን ይህን ሀሳብ እንዳመጣ እንዲሁም ማስታወቂያ እስከ መለጠፍ ድረስ እንደደረሰ እናጣራለን " የሚል ምላሽ ነው የሰጡት።
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዝደንት ዶ/ር አክብር ጩፋ ደግሞ ፤ " ሶሻል ሚዲያ ላይ መረጃው ሲንሸራሸር እያየን ነው " ካሉ በኃላ ሁኔታዉን ለማጣራት #ማኔጅመንቱ ስብሰባ እንደሚቀመጥ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።
❤️
@temhert_bebete ✅
❤️
@temhert_bebete ✅