University Students


Channel's geo and language: Ethiopia, English
Category: Technologies


ይህ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተወዳጅነትን ያተረፈ ለሁሉም ተማሪዎች የተከፈተ ጠቃሚ ቻናል ነው፣
Buy ads: https://telega.io/c/+BmKx2NUG8Nc1ZTU0
አባል ለመሆን ከታች 👇👇
🔸መረጃ እና መልእክት ለመላክ 📧 @Ethiiostudents_bot

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, English
Statistics
Posts filter


#EntranceExam #2017

" ፈተናው ስታንዳርዱን ፣ ደህንነቱንና ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ሁሉም ተማሪዎች በተማሩበት ሥርዓተ ትምህርት ይዘት እየተዘጋጀ እንደሆነ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

አገልግሎቱ ፤ " የ2017 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎች ከ9ኛ - 10ኛ በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣ ከ11ኛ - 12ኛ ደግሞ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው " ብሏል።

" ነገር ግን በ2015 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በናሙናነት በተመረጡ ት/ቤቶች የስርዓተ ትምህርት የሙከራ ትግበራ ላይ የተሳተፉ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች 10ኛ ከፍልን በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ናቸው " ሲል ገልጿል።

በአማራ ክልል በ2016 የትምህርት ዘመን መፈተን ሲገባቸው በጸጥታ ችግር ምክንያት ሳይፈተኑ የቀሩና የ11ኛ ክፍልን በነባሩ ሥርዓተ ትምህርት የተማሩ ት/ቤቶች ላይ የነበሩ ተማሪዎች በ2017 ዓ.ም  የሚፈተኑ እንዳሉም ጠቁሟል።

በዚህም " የ2017 ዓ.ም የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከላይ የተገለጹትን ሶስቱንም ነባራዊ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ባስገባ እና ሁሉንም የዘመኑን ተፈታኝ ተማሪዎች በማከለ መንገድ ስታንዳርዱን ፣ ደህንነቱንና ሚስጢራዊነቱን ጠብቆ በመዘጋጀት ላይ ይገኛል " ሲል አሳውቋል።

የፈተና ዝግጅቱ፡-

1) ከ9ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከነባሩ ሥርዓተ ትምህርት፣

2) ከ10ኛ ክፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣

3) ከ11ኛ ከፍል በነባሩና በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት ላይ ተመሳሳይ ይዘቶች፣

4) ከ12ኛ ከፍል ሙሉ በሙሉ ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት የሚዘጋጅ እንደሆነ ተገልጿል።

ከላይ የተዘረዘረው የዝግጅት ሂደት በሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ላይ እንደተጠበቀ ሆኖ የኢኮኖሚክስ የትምህርት ዓይነት ግን በስርዓተ ትምህርቱ አዲስ የተጀመረ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በ12ኛ ክፍል ይዘት ላይ ብቻ ተመስርቶ የሚዘጋጅ እንደሆነ ተመላክቷል።

በአጠቃላይ ሁሉም ተማሪዎች ከ9ኛ -12ኛ ክፍል በየተማሩበት የሥርዓተ ትምህርት ይዘት ላይ መመስረት ፈተናው እንደሚዘጋጅ አውቀው ተገቢውን ዝግጅት እንዲያደርጉ አገልግሎት መ/ቤቱ አሳስቧል።

ተማሪዎች አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ወላጆች፣ መምህራንና መላው የትምህርት ማህበረሰብ ተገቢውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ተላልፏል።

የዘንድሮ ሀገር አቀፉ የ12ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና መቼ እንደሚሰጥ እስካሁን የተወሰነ ነገር የለም።


✅ University News ✅
✅ University News ✅


"የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ውጤት እስከ ነገ ይለቀቃል።" - ትምህርት ሚኒስቴር

በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የ2017 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተፈታኞች ውጤት እስካሁን አልተለቀቀም።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አቅርበዋል።

ውጤቱ ለምን ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እኩል አልተለቀቀም ስንል የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራርን ጠይቀናል።

ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና የሚወስዱ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞችን ክፍያ የሚፈፅሙት ተቋማቱ መሆናቸውን አመራሩ ገልፀዋል።

ይሁን እንጂ ተቋማቱ ክፍያውን ባለመፈፀማቸው ውጤት መለቀቅ ላይ መዘግየት እንዳጋጠመ ኃላፊው ተናግረዋል።

አሁን ላይ ብዙዎቹ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ክፍያውን እየፈፀሙ በመሆናቸው የተፈታኞቹ ውጤት እስከ ነገ ቅዳሜ የካቲት 8/2017 ዓ.ም እንደሚለቀቅ ኃላፊው ለቲክቫህ አረጋግጠዋል።

የመውጫ ፈተናውን በግል የወሰዱ ድጋሜ ተፈታኞች ውጤትም ወደየተፈተኑበት ተቋማት ይላካል ብለዋል።

✅ University News ✅
✅ University News ✅


2017 midyear exit exam result Feb 13, 2025.pdf
1.3Mb
የ2017 ዓ/ም የዓመቱ አጋማሽ የመውጫ ፈተና ለተቋማት በተላከው መሰረት አንዳንድ ተቋማት ውጤቱን ለተማሪ እያጋሩ ናቸው።

ይህ ከላይ የተያያዘው የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ውጤት ነው።

የፋይሉ ባለቤት የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ህብረት ነው።

✅ University News ✅
✅ University News ✅


#Exit_Exam_Result

ሀገር አቀፍ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት ተለቋል።

https//:result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ExitExam የሚለውን በመምረጥና የራስዎን User Name በማስገባት ውጤትዎን መመልከት ይችላሉ።

በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም መሠጠቱ ይታወቃል።


✅ University News ✅
✅ University News ✅


የመውጫ ፈተና ውጤት ከሁለት ቀናት በኋላ ይፋ ይደረጋል፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር
ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም በመላ ሀገሪቱ በ87 የፈተና ማዕከላት መሰጠቱ ይታወቃል፡፡

ከፈተናው ጋር በተያያዘ በርካታ ቅሬታዎች ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ደርሰዋል፡፡ በተለይ የComprehensive Nursing ተፈታኝ ተማሪዎች፥ ፈተናው ከBlue Print ውጪ የተዘጋጀ እንደነበር በመግለፅ ትምህርት ሚኒስትር ለቅሬታቸው አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል፡፡

የመውጫ ፈተና ውጤት ከሁለት ቀናት በኋላ ይፋ እንደሚደረግ ከትምህርት ሚኒስቴር መስማቱን የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ህብረት ለቲክቫህ ገልጿል፡፡

ሚኒስቴሩ ከComprehensive Nursing የመውጫ ፈተና ጋር ተያይዞ የቀረበ ቅሬታን እያጣራ እንደሚገኝ ለህብረቱ አስረድቷል፡፡

በዚህም ከሁለት ቀናት በኋላ (ረቡዕ/ሐሙስ) አጠቃላይ የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ አሳውቋል፡፡

✅ University News ✅
✅ University News ✅


#MoE

አርብ ጥር 30/2017 ዓ.ም ጠዋት 5፡30 የሚጀመረው የመውጫ ፈተና ወደ 7፡30 እንዲሁም ከሰዓት 8፡30 የሚጀመረው ፈተና ወደ 10፡30 የተቀየረ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አረጋግጧል።

የመፈተኛ ማዕከላት በነበሩበት የሚቀጥሉ መሆኑ ተገልጿል።

✅ University News ✅
✅ University News ✅


ዛሬ መሠጠት የተጀመረውን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና #በጥብቅ የፈተና ዲሲፕሊን እንዲሰጥ እያደረጉ መሆኑን ዩኒቨርሲቲዎች ገለፁ።

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ተፈታኞች ወደፈተና ማዕከላት ይዘው እንዳይገቡ የተከለከሉ ነገሮችን ፍተሻ በማድረግ መያዙን ገልጿል።

በዚህም ዩኒቨርሲቲው ኩረጃ እና ስርቆት የሚያግዙ ክልክል የቴክኖሎጂ ውጤቶችን ይዘው የተገኙ ተማሪዎችን ወደ መፈተኛ ክፍሎች እንዳይገቡ አድርጓል።

✅ University News ✅
✅ University News ✅


#EXITEXAM #NOTE

ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመራቸው ስራዎች አንዱ የሆነ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከጥር 26 ቀን 2017 ዓ/ም ጀምሮ ይሰጣል።

⚡️በፈተና ወቅት ከተፈታኝ ተማሪዎች ምን ይጠበቃል ?


👉🏾 ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍል ሲመጡ ማንኛውም አይነት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት ፣ ላፕቶፕና ... ወዘተ ተመሳሳይ ኤክትሮኒክ ቁሳቁስ መያዝ በፍፁም የተከለከለ ነው።  (ይዞ የተገኘ ፈተናው /ውጤቱ ተሰርዞበት በቀጣይ ጊዜ እንዲቀመጥ ይደርጋል)

👉🏾 ፈተና ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት መፈተኛ ክፍል መገኘት አለባቸው ይህም ማለት ከጥዋቱ 2፡00 በፊት ፤ ከሰዓት ደግሞ ከ8፡00 በፊት ተፈታኞች መገኘት አለባቸው።

👉🏾 ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ID መያዝ ያለባቸው ሲሆን User Name እና Password lower-case and upper-case ፊደላትን ለይተው በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው።

👉🏾 ተፈታኞች ፈተና ከተጀመረ በኃላ ከ30 ደቂቃ በፊት ከፈተናው ክፍል መውጣት የለባቸውም።

👉🏾 ተፈታኞች ፤ ፈተናውን የሚያስፈትኑ መምህራን በሚያሳዩት ቦታ ብቻ መቀመጥ አለባቸው።

👉🏾 ሁሉም ተፈታኝ እንዲቀመጥ የተመደበበት የራሱ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ተቀምጦ መክፈትና መጠቀም አለበት።

👉🏾 በፈተና ክፍል ውስጥ መነጋገር እና ከቦታ ቦታ መዘዋወር በፍፁም የተከለከለ ነው። እንዲሁም ማንኛውም ተፈታኝ ከጎኑ ያለውን ተማሪ ኮምፒውተር በፍፁም ማየት የለበትም።

👉🏾 ምንም ዓይነት ወረቀት ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መምጣት አይቻልም።

👉🏾 ተፈታኞች በምንም ሁኔታ መኮርጅም ሆነ ማስኮርጅ ተግባር ላይ ቢሳተፉ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

👉🏾 ሁሉም ተፈታኞሽ ለፈታኝ መምህራንና ለአስተባባሪዎች  መታዘዝ ያለባቸው ሲሆን የፈተናው ደንብ እና ስርዓት ተገዢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 በድጋሚ ተፈታኞች የፈተና መግቢያ ትኬት (Exit Exam Entry Ticket) መያዝ ይጠበቅባቸዋል።

NB.  ሁሉም ተፈታኞች ወደ መፈኛ ክፍል ተፈትሸው እንዲገቡ የሚደረግ ሲሆን ማንኛውም ተፈታኝ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በፍተሻ ወቅት ይሁን ሥርዓት ለማስያዝ በሚደረግ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆኖ ከተገኘ ከመፈተኛ አከባቢ እንዲገለል ተደርጎ በቀጣዩ የመውጫ ፈተና መስጫ ወቅት እንዲቀመጥ ይፈቀድለታል።

⚡️ከፈታኝ መምህራን የሚጠበቅ

👉🏾 የተፈታኝ ተማሪዎችን ID በአግባቡ በማረጋገጥ ወደ ክፍል እንዲገቡ ማደረግ ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 ተፈታኝ ተማሪዎችን በሥም ዝርዝራቸው መሠረት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

👉🏾 ፈታኝ መምራህን የተማሪዎችን አቴንዳንሰ ይወስዳሉ ፤ ተማሪዎችን ፊርማ ያስፈርማሉ።

👉🏾 በፈተና ክፍል ውስጥ ደምጽ እንዳይሰማ፣ ተማሪዎች ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወሩ ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው።

👉🏾 የፈተናው አጠቃለይ ሂደት በትኩረት መከታተል አለባቸው።

👉🏾 በህመም ምክንያት ተማሪዎች ከክፍል መውጣት ቢፈልጉ ከሱፐርቨዘር ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እርዳታ ያደርጋሉ።

👉🏾 ተማሪዎች በጎናቸው ያለውን ሌላ ኮምፒውተር እንዳይመለከቱ መቆጣጠር አለባቸው።

👉🏾 ተማሪዎች ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በፊት እንዳይወጡ መቆጣጠር ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 ሲኮርጂ ወይንም ሲያስኮርጅ የተገኘ ተማሪ ከመፈተኛ ክፍል እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 ፈተናው ከጀመረ 15 ደቂቃ በኃላ የሚመጣ ተማሪ እንዲገባ ማድረግ የላባቸውም።

👉🏾 የፈተና አፈጻጸም ሪፖርት ለሱፐርቨዘር ማቅረብ

🍀 መልካም ፈተና 🍀

✅ University News ✅
✅ University News ✅




#ExitExam

176 ሺሕ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናን ለመውሰድ መመዝገባቸው ተገለጸ

👉ፈተናው ከጥር 26 እስከ 30 ድረስ ይሰጣል

ጥር 23/2017 (አሐዱ ሬዲዮ) በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ላይ የሚሰጠውን የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ለመውሰድ 176 ሺሕ ተማሪዎች መመዝገባቸውን ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ፈተናውን በድጋሚ የሚወስዱትን ጨምሮ በጠቅላላው 176 ሺሕ ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ በትምህርት ሚኒስቴር የአካዳሚክ ጉዳዬች መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ኤባ ሚጀና #ለአሐዱ ገልጸዋል።

በዚህም መሰረት በኢትዮጵያ የሚገኙ በሁሉም የኒቨርሲቲዎች ፈተናው የሚሰጥ ሲሆን፤ ተጠሪነቱ ለትምህርት ሚኒስቴር ያልሆነው የመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ጭምር በዚህ ፕሮግራም ተካታች መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

የግል ኮሌጆችን በሚመለከት አሐዱ ላቀረበላቸው ጥያቄ ትምህርት ሚኒስቴር የግል ኮሌጆች ላይ ገብቶ ለመፈተን የሚያስችል መዋቅር እንደሌለው በማንሳት፤ ነገር ግን ተማሪዎች በአቅራቢያቸው በሚገኝ የመንግስት ተቋም በኩል መፈተን እንደሚችሉ ገልፀዋል።

የፈተና ቀኑ በተለያዩ ምክንያቶች ዘግይተው ትምህርት የጀመሩትን ዩኒቨርሲቲዎች ታሳቢ ያደረገና በቂ ዝግጅት ማድረጋቸው ከተረጋገጠ በኋላ መወሰኑን ተናግረዋል።

ፈተናውን ለመስጠት ታቅዶ የነበረው ጥር 14 እና 15 የነበረ ቢሆንም፤ ሁሉም ዩኒቨርስቲዎች እኩል ትምህርት ባለመጀመራቸው ወደ ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም. እንዲሸጋገር መደረጉን ገልጸዋል፡፡

በዚህ የፈተና ፕሮግራም ተንቀሻቃሽ ስልክና የወረቀት ፅሁፍ ይዞ መገኘት ፈፅሞ #የተከለከለ መሆኑን የገለጹት የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ሥራ አስፈፃሚው፤ "ተፈታኞች መታወቂያ መያዝና ከፈተና ፕሮግራሙ 30 ደቂቃ ቀድሞ ቦታው ላይ መድረስ ይጠበቅባቸዋል" ብለዋል፡፡ የወጣው ፈተናም ከተማሩት በመሆኑ ሳይጨነቁ በተረጋጋ መንፈስ መስራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል።

የዘንድሮው የዩኒቨርስቲዎች የመውጫ ፈተና ከዚህ በፊት ይሰጥ እንደነበረው ሙሉ ለሙሉ በኦንላይን የሚካሄድ ሲሆን፤ ከጥር 26 እስከ 30 ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።

የተማሪዎች ፈተና እንደተጠናቀቀ ቅዳሜ ማለትም የካቲት 1 ቀን የመምህራንን ስልጠና ሲወስዱ የነበሩ መምህራን ፈተና ይወስዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

✅ University News ✅
✅ University News ✅


#Exit_Exam

የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር በድጋሜ አሳውቋል፡፡

የመውጫ ፈተናው ለአዲስ እና በድጋሜ ለመፈተን ላመለከቱ በሙሉ እንደሚሰጥ ተገልጿል፡፡

✅ University News ✅
✅ University News ✅


#ይመዝገቡ

የመውጫ ፈተና (Exit Exam) በድጋሜ ለመውሰድ ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች ምዝገባ ነገ ረቡዕ ጥር 14/2017 ዓ.ም ያበቃል፡፡

ለመመዝገብ 👉 https://exam.ethernet.edu.et

➫ የመፈተኛ User Name እና Password በመመዝገቢያ ፖርታል በኩል የሚላክ ይሆናል።
➫ የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 500 በቴሌብር በኩል ብቻ መፈፀም ይኖርባችኋል፡፡
➫ ምዝገባ ማድረግ የሚቻለው በተጠቀሱት የምዝገባ ቀናት ብቻ ነው፡፡

✅ University News ✅
✅ University News ✅


በ2017 ዓ.ም ለሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና የተፈታኞችን ምዝገባ ለማካሄድ ይረዳን ዘንድ ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ ተማሪዎችን መረጃ ለመሰብሰብ የሚያስችል የሶፍት ዌር ቴምፕሌት በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በመሆኑም በታህሳስ 30 /2017ዓ.ም በቁጥር 11/77/1201/17 ባለስልጣን መስሪያቤቱ ባወጣው ማስታወቂያ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተፈታኞቻቸውን መረጃ በሶፍት ዌር ቴምፕሌት ማስገባታችሁ ይታወቃል:: ነገር ግን በተሰጠው ጊዜ ቀን ገደብ ያላስገባቹ ተቋማት እና ማስተካከያ እንድታደረጉ እድል የተሰጣቹ ተቋማት በድጋሜ በሶፍት ዌር ቴምፕሌት ከ09/05/2017 ዓ.ም እስከ 14/05/2017 ዓ.ም ድረስ እንድታስገቡ እያልን ጥንቃቄ በተሞላበት አግባብ እንዲሆን እናሳስባለን፡፡

✅ University News ✅
✅ University News ✅


ለ6ኛ ፣ ለ8ኛ እና ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሞዴል ፈተና መሠጠት ጀምራል።


የ6ኛ ፣ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በቀጣይ ለሚወስዱት የከተማና ሀገር አቀፍ ፈተናዎች በቂ ዝግጅት ለማድረግ እገዛ የሚያደርግ ሞዴል ፈተና በ11 ድም ክፍለ ከተማዎች በሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች መሠጠት ጀምራል።


የሞዴል ፈተናው ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 3ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።



✅ University News ✅
✅ University News ✅


ማሳሰቢያ - ሁለት ቀን ብቻ ቀረው!

የ2ዐ17 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ( የ12 ኛ ክፍል) ፈተና ምዝገባ ማክሰኞ ጥር 6/2017 ዓ/ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ላይ ይጠናቀቃል።

ስለሆነም በተለያየ ምክንያት ያልተመዘገባችሁ ካላችሁ በነዚህ ቀሪ ሁለት ቀናት ላይ ብቻ እንዲትመዘገቡ እናሳስባለን።
ያልተመዘገበ አይፈተንም❗️


የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
Via_Atc


✅ University News ✅
✅ University News ✅


#Update

የሕዋ አካሉ ባለቤትነቱ የቻይና የሆነ ሺ ጂያን-19 (ShiJian-19) የተባለ ሳተላይት ቀሪ አካል ሊሆን እንደሚችል መረጃዎች ጠቁመዋል ሲል የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ አስታወቀ

በትናንቱ እንግዳ የሕዋ ክስተት ዙሪያ ከተለያዩ የሕዋ አካላት መከታተያ እና የመረጃ ቋቶች ያገኘናቸውን መረጃዎች በማጠናቀር ባደረግነው ጥልቅ የሆነ ትንተና መሰረት የሚከተለው ሳይንሳዊ መላምት ላይ ደርሰናል ብሏል የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ ሶሳይቲ ።

በመረጃው መሰረት የሕዋ አካሉ ባለቤትነቱ የቻይና የሆነ ሺ ጂያን-19 (ShiJian-19) የተባለ ሳተላይት ቀሪ አካል ሊሆን እንደሚችል ያመላክታል።

ከዚህም በተጨማሪ የሳተላይቱን ቀሪ አካል የምህዋር እና የይዘት መረጃ ጨምረን ጠቅላላ ትንታኔውን ከዚህ ልጥፍ ጋር አጋርተናል። ሳተላይቱ በ መስከረም 17 2017 ዓ.ም ወደ ምህዋር የተወነጨፈ ሲሆን ተልዕኮውን ጨርሶ በጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም  ወደ መሬት ተመልሷል።

ነገር ግን ሳተላይቱ በተልዕኮው ላይ ሲገለገልባቸው የነበሩ የተለያዩ ክፍሎቹ ከዋናው ሳተላይት ተነጥለው በምህዋር ላይ ሲዞሩ ቆይተዋል።

ለትንተናው የተጠቀምናቸው መረጃዎች ከሶስተኛ ወገን የመረጃ ቋቶች የተገኙ በመሆኑ የተረጋገጠ መረጃውን የሳተላይቱ ባለቤት ሃገር ቻይና እስክታረጋግጥ መጠበቅ ይኖርብናል ነው የተባለው።


✅ University News ✅
✅ University News ✅


Here's a highly reliable online part-time job platform that I would like to recommend to you: BTT.
BTT is one of the largest advertising networks globally and is currently recruiting online part-time employees in Ethiopia.
No academic qualifications or work experience are required, and you can easily start earning money with just a smartphone. By downloading the designated app and increasing the download rate of other companies, you can earn lucrative referral fees.
💸 Daily income up to 4,000 ETB
📱Simple operation, only 15-20 minutes per day
✅ Free without any investment
📈 Provides exclusive training to help you
If you are interested in this opportunity
please click the BTT official channel to contact customer service:
https://t.me/+fKeyX9Wh95wxMWNl



18 last posts shown.