✞ የመዝሙር ግጥሞች ✞


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


መዝሙር 147:7
ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፤ ለአምላካችንም
በመሰንቆ ምስጋና አቅርቡ።

📢 ለ ማስታወቂያ ስራዎች @Abaly_bot

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


✞ ይለይብኛል ሚካኤል ✞


ጠብቆ አሳድጎ ከልጅነቴ
አባት እየሆነኝ ሚካኤል አባቴ
ይለይብኛል ሚካኤል ይለይብኛል(2)
በክንፉ ሸፍኖ በቤቱ አሳድጎኛል (2)

አያምርብኝ ብዘነጋው ታሪኬን
ሚካኤል ነው ያስጌጠልኝ ህይወቴን
አረሳብኝ እርሱ አትርሳብኝ ያልኩትን
ለካስ ሰምቶኝ ኖሯል የልጅነት ጸሎቴን

ሚካኤል ያን ሁሉ ዘመን የታገሰኝ
ሚካኤል===ፍሬ ጠብቆ ያልቆረጠኝ
ሚካኤል===የከፍታዬ መሰላል
ሚካኤል===መነሻዬ ሆነሀል

አዝ===
=
እንዳይከፋኝ እንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳለፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ካጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል

ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ
ሚካኤል===ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤል===እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል===አሳምረው ፍፃሜዬን

አዝ====

ውድቅ አረገው የጠላቴ ክፉ እቅድ
አራመደኝ በከፍታዬ መንገድ
ሊያስቀረኝ አልቻለም ሊጎትተኝ ባላጋራ
ተጥሎ ስላለ በእግዚአብሔር ድንቅ ስራ

ሚካኤል===እሳታዊ ነው ነበልባል
ሚካኤል===ጠላቴ ፊትህ ይቀልጣል
ሚካኤል===ለኔ አይኔ ነው መከታዬ
ሚካኤል===የዘለዓለም ጠባቂዬ

አዝ===
እንዳይከፋኝ እንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳለፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ካጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል

ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ 
ሚካኤል===ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤል===እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል===አሳምረው ፍፃሜዬን

መዝሙር
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ


♡ አሳዳጊዬ ♡


አሳዳጊዬ ማይልህ አንተ ያላሳደግከው
ማን አለ ሚካኤል ከፍ ያላደረግከው
የሕይወቱ ነህ ከፍታ ክብርና ማዕረጌ
አልረሳም ሥራህን በቤትህ አድጌ


ከልጆቹ መሐል አንዷ ምስክር ነኝ
ሚካኤል አባቴ እርሱ እየጠበቀኝ
መጠበቅን ያውቃል መሰወር ከክፉ
አለው እየረዳኝ ከልሎኝ በክንፉ
መልካምን ያደርጋል ወዳጅ ለወዳጁ
ድንቅ አድርጎልኛል ሚካኤል ለልጁ

አዝ= = = = =
ይሰምራል የልቤ ጠይቄው አላፍርም
እርሱ ከእኔ ጋር ነው ብቻዬን አልቆምኩም
የትላንት ታሪኬ መዝገቡ ቢከፈት
በነገሬ ሁሉ ሚካኤል አለበት
መልካምን ይደርጋል ወዳጅ ለወዳጅ
ድንቅ አድርጎልኛል ሚካኤል ለልጁ

አዝ= = = = =
መገኛዬ ደጁ ሌላ አድራሻ የለኝ
የሚካኤል ልጅ ነኝ በፍቅሩ ያደኩኝ
በመላኩ ምልጃ አጊጧል ሕይወቴ
ለኔ ያላረገው ምን አለ አባቴ
መልካምን ያደርጋል ወዳጁ ለወዳጁ
ድንቅ አድርጎልኛል ሚካኤል ለሌጁ

አዝ= = = = =
ከኔ አልተለየም ዛሬም በሕይወት
አየዋለሁ ቀድሞ ሁልጊዜ ከፊቴ
ይሄ ነው ምስጢሬ ወጥቶ የመግባቴ
ሚካኤል ይመስገኔን ኃያሉ አባቴ
መልካም ያደርል ወዳጅ ለወዳጁ
ድንቅ አድርጎልኛል ሚካኤል ለልጁ

አዝ= = = = =
መገኛዬ ደጁ ሌላ አድራሻ የለኝ
የሚካኤል ልጅ ነኝ በፍቅሩ ያደኩኝ
በመላኩ ምልጃ አጊጧል ሕይወትቴ
ለኔ ያላደረገው ምን አለ አባቴ
መልካምን ያደርጋል ወዳጅ ለወዳጁ
ድንቅ አድርጎልኛል ሚካኤል ለልጁ

መዝሙር
ዘማሪት ሊዲያ ታደሰ

┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
   @maedot_ze_orthodox
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


♡ ብዙ ልጆች አሉት ♡

ብዙ ልጆች አሉት ለሥሙ ምሥክር
በዙሪያው ያሉትን አብቅቷል ለክብር
ስለ ፍጹም ምልጃው ለእኔ ግን ይለያል
መልዓኩ ሚካኤል ስለው ደስ ይለኛል

ከመላዕክት ክብሩ ከፍ ከፍ ብሎ
በአምላኬ ተሾመ ዘንዶውንም ጥሎ
አሳዳጊዬነው ሆኖ እናት አባቴ
ሚካኤል በአለበት ይሸሻል ጠላቴ

ከሚታየው ሁሉ ልቤ ከሚፈራው
ካላየሁት ነገር ጠላት ከሰወረው
ያድነኛል ፈጥኖ በመንገዴ ወቶ
ሚካኤል ሀያሉ ክንፎቹን ዘርግቶ

በባሕራን ታሪክ በነተላፊኖስ
በአፎምያ መትረፍ በነ ዱራታኦስ
በነብዩ ዳንኤል መች ይፈጸምና
የሚካኤል ስራ ይቀጥላል ገና

በጉዞ የረዳችሁ በባሕር በየብሱ
ፈጥኖ ደርሶላችሁ ዕንባን ስታፈሱ
ስለታችሁ ሰምሯል ቁሙ ለዝማሬ
በሚካኤል ምልጃ የቆማችሁ ዛሬ


ክብር ለሚገባው ክብርን እንሰጣለን
ንጉሥ ለወደደው አንሰግድለታለን
እንኳን ለሚካኤል ለሚቆም ጌታ ፊት
ክብርን እንሰጥ የለ ለምድር ሹማምንት

መዝሙር
በሊቀ መዘምራን ቴዎድድሮስ


እህቶች ይቅርታ ግን😁😁

“የወርቅ ቀለበት በእርያ አፍንጫ እንደ ሆነ፥
ከጥበብ የተለየች ቆንጆ ሴትም እንዲሁ ናት።”
[ምሳሌ 11: 22]

ቆንጆ መሆኗ እኮ ምርጥ ነው.. ግን ወፍ ጥበብ😭😭 ሎል..

የወርቅ ቀለበት በአሣማ አፍንጫ ላይ ቢገባ ወርቁ እርያውን ከፍ ሚያደርገው አይደለም.. እንደውም ወርቁ በእርያው ይሸፈናል ወይም ይረክሳል እንጂ.. ልክ እንዲሁ ቆንጂት የምርም ቆንጆ ሆና ግን ከጥበብ ከተለየችና በኃጢአት ምትመላለስ ከሆነ የሷ ቁንጅና በእርያ አፍንጫ ላይ እንዳለ ወርቅ ይሆናል..

እውነተኛው ጥበብ ኢየሱስ ነው.. ስለዚህ ቆነጃጅት ከኢየሱስ አትለዩ.. ትልቁ ውበት እርሱ ነው.. ለዘላለም የማይረግፍ ውበት ኢየሱስ..

..... 😎😎






ነይ ድንግል ነይ ነይ ነይ ነይ ነይ ነይ ነይ አናቴ ነይ ነይ ድንግሌ ነይ



💚 @maedot_ze_orthodox
💛 @maedot_ze_orthodox
❤️ @maedot_ze_orthodox




💚 ኢትዮጵያ ሰላምሽ ይብዛ 💛
*።።።።።።።።❣️።።።።።።።።።።።*


ኢትዮጵያ ሠላምሽ ይብዛ
ተጠለይ በእግዚአብሔር ታዛ
ኢትዮጵያ ሠላምሽ ይብዛ
ተጠለይ በእግዚአብሔር ታዛ/፪/

ከሚራራልን ፍቅር ከሆነው
ዘላቂ ሠላም ከእግዚአብሔር ነው
ይኽን እወቂ ይኽን ተረጂ
በልብሽ ጉልበት ለእርሱ ሥገጂ

በሠይፍ ያልቃሉ ሠይፍ የሚያነሱ
የሚራራልን ሲፈርድ ንጉሡ
በቀል የእርሱ ነው አይደለም የአንቺ
በጸጋው ታጥረሽ በጸሎት በርቺ

የውጣ ውረድ የጉስቁልናው
በእግዚአብሔር ነው መከራ ማብቂያው
ሠላም ይሁን ሲል ይሆናል ሠላም
የአሳየሽውን ፍቅር አይረሳም

ማራት ኢትዮጵያን ማራት ሐገሬን
በእየሄድሁበት መጠሪያ ሥሜን
ይብቃት ሌሊቱ ይውጣላት ጸሐይ
አሁን ይዘርጋ እጅኽ ከሠማይ

እድትፈራርስ ጠላት ሸምቋል
ብርቱውን ጉልበት ከአፈር ደባልቋል
ይኽን ግፍ አስብ ዘንበል በልላት
ከአንተ በስተቀር መሄጃ የላት

ማራት ኢትዮጵያን ማራት ሐገሬን
በእየሄዱሁበት መጠሪያ ሥሜን
ይብቃት ሌሊቱ ይውጣላት ጸሐይ
አሁን ይዘርጋ እጅኽ ከሠማይ


🌸 ነይ አርሴማ ቅድስት ሰማዕት 🌸

ነይ አርሴማ ቅድስት ነይ አርሴማ
ነይ አርሴማ ቅድስት ሰማዕት



አርሴማ አርሴማ ነይ አርሴማ
አርሴማ ስልሽ ነይ አርሴማ
እንድታማልጅኝ ነይ አርሴማ
ከአምላክ ፈጣሪሽ ነይ አርሴማ
በደሌን ጭንቀቴን ነይ አርሴማ
ልናዘዝልሽ ነይ አርሴማ
ምሪኝ አርሴማ ሆይ ነይ አርሴማ
እጆቼን ይዘሽ ነይ አርሴማ
ወልድያ ሲሪንቃ ነይ አርሴማ
ልምጣ ከደጅሽ ነይ አርሴማ
አዝ

እንድታማልጅኝ ነይ አርሴማ
ከንጉስ ራማ ነይ አርሴማ
ትለምንሻለች ነይ አርሴማ
ነፍሴ ደጅሽ ቆማ ነይ አርሴማ
ወልድያ ሲሪንቃ ነይ አርሴማ
ሄዶ ያየሽማ ነይ አርሴማ
ቅዱሱን ዝናሽን ነይ አርሴማ
ገድልሽን የሰማ ነይ አርሴማ
ጸበልሽ ፈውስ ነው ነይ አርሴማ
እናቴ አርሴማ ነይ አርሴማ
አዝ

በጉብዝና ወራት ነይ አርሴማ
ፈጣሪህን አስብ ነይ አርሴማ
ብሎ እንዳስተማረን ነይ አርሴማ
በመጽሐፈ መክብብ ነይ አርሴማ
ስለ ጌታ ኢየሱስ ነይ አርሴማ
ስለ ዓለም መድኃኒት ነይ አርሴማ
ስለ ተዋህዶ ነይ አርሴማ
ስለ ፀናች እምነት ነይ አርሴማ
መከራን ተቀበልሽ ነይ አርሴማ
በጉብዝናሽ ወራት ነይ አርሴማ

ዘማሪት ፀዳለ ጎበዜ
💚 @maedot_ze_orthodox
💛 @maedot_ze_orthodox
❤️ @maedot_ze_orthodox




✞ አርሴማ ቅድስት ወሰማዕት ✞

አርሴማ ቅድስት ፪ ወሰማዕት
ወሰማዕት ፭ አርሴማ ቅድስት ኧኸ ፫


ከምድር ሙሽርነት ይበልጣል የሰማይ
በማለት ወሰነች ሰይፍ ስለቱን ሳታይ
የሰማዕትነቷ ፅኑ መከራዋ
ተቀበለችበት የክብርን ፅዋ
አዝ=======
የዚህችን ዓለም ጣዕም ፍፁም ያልበገራት
የንጉስ ግልምጫ ከእግዚአብሔር ያልለያት
አምላኯን መረጠች መክሊቷን አትርፋ
አክሊል ተቀዳጀች ለእምነት ተሰልፋ
አዝ=======

የማይታየውን ለመውረስ ተብሎ
በሚታየው ዓለም ይበዛል ተጋድሎ
የሰማዕታት ዋጋ  ይኸው ነው ውጤቱ
በዚህ ምድር ሳይሆን በሰማይ ነው ቤቱ
            አዝ=======
ውበት ከንቱ ነው ደም ግባት ሀሰት
እንዲህ ብላ ፀናች አርሴማ ቅድስት
ያመነችው ጌታ በሰጣት ቃልኪዳን
ልዩ እናት ሆናለች ትውልዱን በማዳን


➝ ​​ ​​​​⛪️ የመዝሙር ግጥሞች ⛪️


​​☦️ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አስተምሮና ስርአትን የጠበቁ የመዝሙር ግጥሞችን ከነዜማቸው በየቀኑ ወደናንተ ያቀርባል፡፡ ይቀላቀሉ👇👇


✥┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈✥
http://T.me/Yemezmurgtm
http://T.me/Yemezmurgtm ✢ ✥┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈✥




'ማርያም ደስ ይበልሽ'


መዝሙር ተለቀቀ ሙሉ መዝሙሩን በ ጃን ያሬድ jan | yared የቴሌግራም channel ላይ ያግኙ


https://t.me/+1rCQMEj6K2kzM2E8




በድንግል አማረ ህይወቴ

በድንግል አማረ ህይወቴ
በማርያም አማረ ህይወቴ
ስጠራት ገብታልኝ ከቤቴ

በድንግል አማረ ከሞት መሀል ነጥቀሽ
በድንግል አማረ ነፍስን ዘራሽብኝ
በድንግል አማረ ሀጥያተኛ ሳለው
በድንግል አማረ ሰው አርገሽ አቆምሺኝ
በድንግል አማረ ሀዘን መከራዬ
በድንግል አማረ ታሪክ ሆኖ ቀረ
በድንግል አማረ ህይወቴም ባንቺ
በድንግል አማረ
በድንግል አማረ በማርያም አማረ

አዝ....

በድንግል አማረ ሀጥያትን አብዝቼ
በድንግል አማረ ለምፅ ቢያጠቃኝም
በድንግል አማረ አንቺ እያነፃሺኝ
በድንግል አማረ ዳግም ብጨቀይም
በድንግል አማረ እሩሩህ ነሽ እና
በድንግል አማረ ምልጃሽ አይዘገይም
በድንግል አማረ ስምሽን ስጠራ
በድንግል አማረ
አታሳፍሪኝም /2/

አዝ....

በድንግል አማረ ሐዘኔ በርትቶ
በድንግል አማረ እንባዬ ሲቀድም
በድንግል አማረ ወዳጅ ያልኩት ሁሉ
በድንግል አማረ ፊቱን ሲያዞርብኝ
በድንግል አማረ አንቺ ደርሰሽልኝ
በድንግል አማረ ስሜ ተከየረ
በድንግል አማረ ኑሮዬ በሙሉ
በድንግል አማረ
በድንግል አማረ በማርያም አማረ

አዘ....

በድንግል አማረ ሐዘኔ በርትቶ
በድንግል አማረ እንባዬ ሲቀድም
በድንግል አማረ ወዳጅ ያልኩት ሁሉ
በድንግል አማረ ፊቱን ሲያዞርብኝ
በድንግል አማረ አንቺ ደርሰሽልኝ
በድንግል አማረ ስሜ ተቀየረ
በድንግል አማረ ኑሮዬ በሙሉ
በድንግል አማረ
በቃጥላ አማረ በግሸን አማረ

🔴 አዲስ ዝማሬ " በድንግል አማረ ሂወቴ " - ዘማሪ ያብስራ ሲሳይ


♡ ዮም ፍስሐ ኮነ ♡

ዮም /ፍስሐ ኮነ/(፪)
በእንተ ልደታ ለማርያም

በባርነት ሳለን - - -  ፍስሐ ኮነ
ኃጢአት በአለም ነግሳ - - - ፍስሐ ኮነ
በድንግል መወለድ - - - ፍስሐ ኮነ
ቀረልን አበሳ - - - ፍስሐ ኮነ
እግዚአብሔር መረጠሸ - - - ፍስሐ ኮነ
ልትሆኚው እናቱ - - -  ፍስሐ ኮነ
ይኸው ተፈፀመ - - - ፍስሐ ኮነ
የዳዊት ትንቢቱ - - - ፍስሐ ኮነ
        
አዝ = = = =
የሔዋን ተስፋዋ - - - ፍስሐ ኮነ
የአዳም ዘር ህይወት - - - ፍስሐ ኮነ
የኢያቄም የሐና - - - ፍስሐ ኮነ
ፍሬ በረከት - - - ፍስሐ ኮነ
ምክንያተ ድኂን - - - ፍስሐ ኮነ
ኪዳነምህረት - - - ፍስሐ ኮነ
ድንግል ተወለደች - - - ፍስሐ ኮነ
የጌታዬ እናት - - - ፍስሐ ኮነ
       
አዝ = = = =
በሔዋን ምክንያት - - - ፍስሐ ኮነ
ያጣነውን ሰላም - - - ፍስሐ ኮነ
ዛሬ አገኘነው - - - ፍስሐ ኮነ
በድንግል ማርያም - - - ፍስሐ ኮነ
የምስራች እንበል - - - ፍስሐ ኮነ
ሀዘናችን ይጥፋ - - - ፍስሐ ኮነ
ተወልዳለችና - - - ፍስሐ ኮነ
የአለም ሁሉ ተስፋ - - - ፍስሐ ኮነ


              መዝሙር
          ዘማሪ ፍቃዱ አማረ


✞ ልደታ ለማርያም ✞

ልደታ ለማርያም ስምሽ ስንጠራ
መላ አካላታችን ለመለመ አፈራ/2/


ከገነት የፈለቅሽ ልዩ መአዛችን
የቃላችን ቃና ናርጎስ ወዛችን
በጉዛችን ሁሉ ስምሽን አስከትለን
እንቅፋት ሳይነካን/2/ ከእርስቱ እንገባለን



ቃልኪዳን እንዳለ ስምሽን ለጠራ
ዘወትር ይድናል ከክፋ መከራ
ልደታ ለማርያም ስምሽን ስንቅ አድርገን
ምን አለ ያጣነው/2/ አንቺን ተስፋ አድርገን


በወንጌል አጸዶች ዙርያሽን ተከበሽ
የዜማ አውአፍ ቀን ከሊት ሲቀኙሽ
የዘካርያስ እጣን ምድርን ያሻተተ
ነፍሳችን ተነጥቆ/2/ ካንቺ ሊኖር ሻተ


እንደምን ያለ ክብር እንዴት ያለ ግርማ
የጥበብ መገኛ የዜማ አውድማ
የሚዘራ ወንጌል ከደጊቱ መሬት
ሰላሳና ስልሳ/2/ የመቶ ፍሬው


በእናት ፊት ማደግ ሰቆቃ የለበት
ሳይጠይቁት ሰጪ የልብ አውቃ እመቤት
ስምሽን ለመጥራት ለዚህ ያበቃሽን
ድንግል ማርያም ሆይ/2/ ከቁጥር አታጉዲይን



     መዝሙር
ዘሩባቤል ሀብታሙ

┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


❤️ ማርያም ማርያም ብዬ ❤️


ማርያም ማርያም ብዬ ስምሽን ልጥራው
አይደክመኝም እኔ ብደጋግመው
አሁንም ጠራሁሽ አላስችልህ ቢለኝ
አውቀዋለሁ ስምሽን እናቴ ስትወለደኝ/2/


ገና በማህፀን በእናቴ የምጥ ቀን
ደጋግሜ ሰማሁ ሲጠሩት ስምሽን
በሰከንዳት እድሜ የማውቃት አንዲት ቃል
ልቤላይ ያለው ስም ማርያም ማርያም ይላል
ማርያም...ማርያም

አዝ= = = = =
ሔዋን ምጧ ቀሎ ልጆቿን ታቀፈች
በአመላጅነትሽ እናቴም ታመነች
በተወለድኩባት በመጀመሪያው ቀን
ስምሽን እየሰማሁ ወጣሁ ከማህፀን
ማርያም...ማርያም

አዝ= = = = =
ከቃልኪዳን ስም ጋር አደኩኝ አብሬ
ምልጃሽ ሳይለየኝ አለሁ እስከዛሬ
የሕይወቴን ፈደል ካንቺ ላይ ቆጠርኩኝ
በልጅሽ አምኜ ዳግም ተወለድኩኝ
ማርያም...ማርያም

አዝ= = = = =
የክፉ ቀን ስንቄ ያዘልኩሽ በልቤ
የሕይወቴ ምግብ እንጀራ መሶቤ
እንደትላንትናው ዛሬም እጠራሻለሁ
የመስቅል ስር ክብሬን እንዴት እረሳለሁ
የመስቅል ስር ክብሬን እንዴት እተዋለሁ

ማርያም...ማርያም
❤️❤️❤️

20 last posts shown.