《山ㄒ丂》♤ Ҝ丨几ᎶƊㄖ爪 😵


Channel's geo and language: Ethiopia, English


Different 1080p serious movie pictures for you 😲😯😯
Used for profile 😁💯
.
.
If You Want High Quality😉 Movie ☠️🗡 Wallpaper🤳 And Best wallpapers for gamers🎮🃏
Click the link👇 and join the channel
.
https://t.me/+eroSuqSQh49kYzJk

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, English
Statistics
Posts filter










♦️✨️ሽማግሌው✨️♦️

        🎗አስተማሪ አጭር ታሪክ🎗

🥇በግሩም ተበጀ የተፃፈ

🥈በ《山ㄒ丂》♤ Ҝ丨几ᎶƊㄖ爪 😵 Telegram Channel የቀረበ
       __

    ገና በጠዋቱ...2፡30 ላይ....ክሊኒካችን በህመምተኛ በተጨናነቀበት ወቅት ነበር 
አንድ አረጋዊ ወደ ክሊኒካችን የገቡት። በግራ ክንዳቸው ላይ የቁስል እሽግ 
ይታያል። በግምት 70 ዓመት የሚሆናቸው አዛውንት ናቸው። በቀስታ አግዳሚው 
ወንበር ላይ ተቀምጠው ሰዓታቸውን ማየት ጀመሩ። 
የቸኮሉ ይመስላሉ፡፡ 
“ምን ልርዳዎት” አልኳቸው፡፡ 
የቁስሉ እሽግ እንዲቀየርላቸው ነው የመጡት። ከ30 ደቂቃ በኋላ ግን ቀጠሮ 
ስላላቸው ቸኩለዋል፡፡ 
ህክምና ሊያገኙ የሚችሉት ገና ከ1 ሰዓት በኋላ እንደሆነ ይገባኛል፡፡ ምን ማድረግ 
እችላለሁ! ግን እስቲ ቢያንስ ቁስሉን ፈትቼ ልየው ብዬ እሽጉን ስፈታው ቁስሉ 
ደርቋል፡፡ 
በጣም ጥሩ!
ከአንዱ ዶክተርጋ ተነጋገርኩ። አስፈላጊውን መድሃኒቶችና የህክምና ቁሳቁሶች 
ወስጄ ህክምናውን አከናወንኩላቸው፡፡ አረጋዊው ወደ ቀጠሯቸው በጣም 
በመቸኮላቸው ምክንያት ትዕግስት አጥተዋል። አሁንም አሁንም የሚያዩት የእጅ 
ሰዓታቸው ቁስሉ ያለበት ግራ ክንዳቸው ላይ ነው ያለው፡፡ ስለዚህ እንዴት 
ሰዓታቸውን ይዩ...፡፡ ቁስሉን እየፈታሁላቸው እሳቸው አስግገው ሰዓታቸውን 
ለማየት ይጣጣራሉ፡፡
“ለመሆኑ ይሄን ያህል የቸኮሉበት ቀጠሮዎት የት ነው...” አልኳቸው እንደ 
ጨዋታ ያህል። 
“3፡00 ሰዓት ላይ ከባለቤቴ ጋር ቁርስ ለመብላት ቀጠሮ አለኝ” አሉኝ። 
“አሀ...”
ቁስላቸውን መልሼ እያሸግኩላቸው አረጋዊው ታሪካቸውን አጫወቱኝ፡፡ 
እንዳሉኝም እንዲህ የቸኮሉት ከሚስታቸው ጋር 3፡00 ሰዓት ላይ ቁርስ የመብላት 
ቀጠሮ ስላላቸው ነው፡፡ ሚስታቸው ግን ቤት አይደለም ያሉት፡፡ ህመምተኛ 
ናቸው፡፡ ሆስፒታል ነው ያሉት፡፡
“ባለቤትዎ ሀይለኛ ሴት ናቸው ማለት ነው...ለዚህ ነው ላለማርፈድ ይሄን ያህል 
የቸኮሉት” አልኳቸው። 
“አይ...እሷ እንኳ ምንም አትለኝም” አሉኝ አረጋዊው፤ “እኔው ነኝ ...፡፡”
“እንዴት...” አልኳቸው እንዲጫወቱ ፈልጌ። 
“አዬ ልጄ፣ ባለቤቴማ ላለፉት አምስት ዓመታት አልዛሜር በተባለ የመርሳት 
በሽታ ተይዛ ባለቤቷ እንደሆንኩ እንኳ አታውቅም” አሉኝ ትክዝ ብለው፡፡
ገረመኝ። አረጋዊው ላለፉት አምስት አመታት አንድም ቀን ሳያስተጓጉሉ 
ሆስፒታል እየሄዱ ከባለቤታቸው ጋር ቁርስ ቆርሰዋል፡፡ ባለቤታቸው ግን 
እያንዳንዱን ቀን ከተለያየ ሰው ጋር ቁርስ እንደበሉ ነው የሚያውቁት፡፡
ግማሽ ምዕተ ዓመት በዘለቀው ትዳራቸው...የትዳር አጋራቸው የሆኑትን 
ባለቤታቸውን ፈጽሞ ረስተዋል። ምስኪኑ አረጋዊ ግን ሁልቀን ሳያረፍዱ 
ሆስፒታል እየተገኙ ጨርሶ ከማያስታውሷቸው ባለቤታቸው ጋር ፍቅርን 
ይቆርሳሉ፡፡

                        🔸️ THE END 🔹️

https://t.me/+eroSuqSQh49kYzJk
@TheDarkJah
@Nahpac28






እንደዚህም ተብሎ ነበር 🤭

https://t.me/+eroSuqSQh49kYzJk
@TheDarkJah
@Nahpac28


◈👩‍🍼እናት_ለዘለአለም_ትኑር👩‍🍼◈
━━━━━━•°*✨*°•━━━━━━
°
°
አንድ እናት ወደ አንድ የሞባይል መጠገኛ ሱቅ ሄዱና
°
°
🧓እናት: "ስልኬ ተበላሽቷል ስራልኝ" ብለው ለጠጋኙ ሰጡት ።
°
°
👨‍🔧ጠጋኙ: ስልኩን አገላብጦ ከፈተሸው በሗላ "እማ' ስልክዎ ምንም አልሆነም
ይሰራል" አላቸው።
°
°
🧓እናት: አይናቸው እንባ አቀረረና ስልኩ ካልተበላሸ "ልጆቼ የማይደውሉልኝ
ለምንድን ነው " አሉ በደከመ ድምፅ።
°
°
እድለኛ ሆነን ወላጆቻችን በህይወት ካሉ እንከባከባቸው ፤ እርቀንም ከሆነ ።
ይህን ያክል አመት ሰጥተው እንዳሳደጉን ጊዜ አንንፈጋቸው።

https://t.me/+eroSuqSQh49kYzJk
@TheDarkJah
@Nahpac28




In the early 2000s, it was not your phone that took a picture of you, but you took a picture of your phone!🤔😁

https://t.me/+eroSuqSQh49kYzJk
@TheDarkJah
@Nahpac28


Legend Nipsey 🕊🖤

https://t.me/+eroSuqSQh49kYzJk
@TheDarkJah
@Nahpac28


ይሄ የመጨረሻህ እድል ነው።

👉የምንሠራው ለመስራት ቀጠሮ ለነገ መቅጠር እና ማስረዘም የብዙዎቻችን የህይወት ልማድ ነው። ምናልባት( The Count down ) የሚለውን ፊልም ላያችሁ ሰዎች የጊዜ ትርጉም በጣም ይገባችሁዋል ብዬ አስባለው።

👉በዚህ ፊልም ላይ ሰዎች የስለክ አፕ አውርደው የሚሞቱበትን ጊዜ የሚቆጥሩበት ሲሆን በጣም አስፈሪ ዘውግ ያለው የጊዜን ትርጉም የሚያስረዳን ፊልም ነው።
    እናንተም የምትሞቱት በዚህ ጊዜ በዚህ ሰአት እና ደቂቃ ነው ተብሎ ቢነገራችሁ የምትኖሩትን ህይወት ሳስበው እገረማለው።

👉በነገራችን ላይ መች እንደምትሞቱ አልተነገራችሁም እንጂ ጊዜው ግን ተመድቦላችሁዋል። የዛሬዋ ጊዜያችሁ ታድያ ያልጨረሳችሁትን እንድትጨርሱ የተሰጣችሁ የመጨረሻ እድላችሁ ነው። ለነገ የሚባል ነገር አለ ማለት የነገ ስራችሁን ለተነገ ወዲያ አስተላልፋችሁዋል ማለት ነው።

👉ልክ ስንኖር እንደሚሞት ሰው እንኑር። ነገ የእኛ አይደለም። ለመለወጥ ፣ ለመዋደድ ፣ ከጠሉን ጋር ለመታረቅ ፣ አላማችንን ለመኖር ፣ ይቅርታ ለመጠየቅ ለነገ የምንይዘው ቀጠሮ የለም ምክንያቱም ነገ የኛ ስላልሆነ ማለት ነው። ምድር ላይ እስከመጨረሻው እንደሚኖር ሰው ለመለወጥ የነገ ቀጠሮ ስናስቀምጥ ትንሽ ይከብዳል ብዬ አስባለው። ከፈጣሪ ጋር ለመታረቅ ጊዜው ዛሬ ነው። የበደሉንን ለማቀፍ ጊዜው ዛሬ ነው። ልጆቻችንን ለመንከባከብ ጊዜው ዛሬ ነው። ፍቅረኞቻችንን ለማስደሰት ጊዜው ዛሬ ነው።

👉የሚገርማችሁ ይህንን እንድታደርጉ የተሰጣችሁ የመጨረሻው እድል የዛሬው ቀን ብቻ ነው። ስለዚህ በማለዳ ስትነሱ ጀምሩት። እወዳችሁዋለው መልካም ቀን

https://t.me/+eroSuqSQh49kYzJk
@TheDarkJah
@Nahpac28

https://t.me/kiya2313


☞*አንድ ተማሪ ወደ ሩሚ በመምጣት ፈጣሪ የሚደሰትበት
ቅዱስ ለመሆን ምን ማድረግ እንደሚገባው
ይጠይቃቸዋል፡፡**

ሩሚም፦ ቅድስናን ከፈለካት ልብህን ወደ ህፃናት ልብ
ቀይረው››ይሉታል
ተማሪውም፦ ለምን? ይጠይቃል

፩ ህፃናት አምስት መልካም ነገሮች በልባቸው እንዳሉ
አታውቅምን አሉና ሩሚ ዘረዘሩለት፡፡

፪ ህፃናት ስለእለት እንጀራቸው አይጨነቁም

፫ ህመም ሲሰማቸውም ቀንና ለሊት ስለመጥፎ እድላቸው
ፈጣሪያቸውን አያማርሩም

፬ በእጃቸው የያዙትን ምግብ ሁልግዜም ያካፍላሉ
ሲጣሉም ቂም በልባቸው አያሳድሩም

፭ እንዲሁም ጥቃቅኑ አደጋና ማስፈራራት ሁሉ
ያስፈራቸዋል እንባም በአይናቸው እንዲሞላ ያደርጋል
በማለት መለሱለት፡፡
እናም ቅድስናን ከፈለጋችኋት ልብህን ወደ ህፃናት ልብ ቀይሩት።

https://t.me/+eroSuqSQh49kYzJk
@TheDarkJah
@Nahpac28













20 last posts shown.

123

subscribers
Channel statistics