🎤 የሙስሊሞች ድምፅ 🎙️


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


🍁ወደ መልካም ነገር ያመላከተ ሰው የሰራ ሰውን አጅር ያህል ያገኛል"(አመላካች የሰሪውን ምንዳ ያገኛል) (ﷺ)🍁
🍁ሸሪዓዊ ስርዓቶችን ባማከለ መንገድ መማማርና መተራረም በሙስሊሞች መካከል ሊሰፍን የሚገባ የወንድማማችነት መገለጫ ነው::!!!🍁
🍁(በእውቀትህ ተናገር፤ አሊያም ችለህ ዝም በል::!!)🍁

ሀሳብ አስተያየት ካለዎት
@Nesiha_Academicbot

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


በዛሬው እለት ደሴ ከተማ በመከላከያ ሰራዊታችን ክፍተት በትግራይ ወራሪ ሀይሎች እጅ ስር ወድቃለች😭😭😭


በደሴ ከተማ የትግራ ወራሪ ሀይል ገብቱዋል ጦርነት አለ እያለ የውሸት ወሬ የሚያወራ ካለ እውሸት ነው እንዳትሰሙ ሰውን ለማሸበር የፈለገ ነው ደዛ የሚለው !!!

ደሴ ውስጥ መቸም አይገባም ኢንሻአላህ ሲያምረው ይቀራል ላም አለኝ በሰማይ ወተቷንም አላይ እያለ ነው የተመለሰው

በደሴ በኩል ለመግባት ሞክሮ ነበር በጀግናዊ ሰራዊታችን ከፍተኛ ምት ደርሶበት ወደመጣበት ተመልሷል!!!

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube


ደሴ
ቦሩ ስላሴ

በዛሬው የግንባር ውሏችን ደግሞ የትግራይ ወራሪ እና ዘራፊ ሀይል የጥፋት እና የዘረፋ ተልእኮን በትንሱ ተመልክተናል

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube


ደሴ
ቦሩ ስላሴ

በዛሬው የግንባር ውሏችን በጀግናው ፋኖ ፣ በጀግናው መከላከያ ሰራዊት እና በጀግናው የሚሊሻ ሀይላችን ትብብር በዛሬው እለት ደሴ ቦሩ ስላሴ ከወራሪው የትግራይ ሀይል ሙሉ ለሙሉ ነፃ ወጥቱዋል!!!

የትግራይ ወራሪ ሀይል 2 ሲኖ አስክሬኖችን እና የቆሰሉ ወራሪወችን ይዞ መሄዱን መስማታችን እና ከ70 በላይ የሚሆኑ የወራሪው አስክሬኖች ደግሞ በየቦታው ወድቀው ለመመልከት ችለናል

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube


ደሴ
ቦሩ ስላሴ

ዛሬ ጀግናው ፋኖ ፣ የአማራ ልዩ ሀይይ ፣ መከላከያ ሰራሚታችን እና የሚሊሻ ሀይላችን፣ ቦሩ ስላሴ ሰዴጅ በምትባል ቦታ ላይ በሚያደርገው ፍልሚያ ጀግናው ሀይላችን ወራሪውን የትግራይ ሀይል በማሳደድ ላይ ነው....

የደሴ ከተማ ወጣቶች ከጥዋት እስከማታ ድረስ ከሰራዊታችን ጎን በመቆም ለሰራዊታችን ምግብ መጠጥ እና አልባሳት ግንባር ድረስ በመሄድ እያደረሳችው እና ከጎኑ አብራችው ደጀን በመሆን ለሰራዊታችን ብርታትና ጥንካሬ የበኩላችሁን አስተዋጾ በማድረግ ሰራዊታችንን ማስደሰታችን አይዘነጋም...

በመሆኑም አሁንም የደሴ ከተማ ወጣቶች ልክ እንደስከዛሬያችን ነገም ከነገም ቡሀላ ለሰራዊታችን ደጀን በመሆን እስከ ትግሉ መጨረሻ ድረስ ከስከዛሬው በበለጠ መልኩ የበኩላችንን አስተዋጽኦ በማድረግ ለሰራዊታችንን ደጀን መሆናችነንን አጠናክረን መቀጠል አለብን

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube


ደሴ!!!!

ደሴ የትግራይ ወራሪ ሀይ ገብቷል የሚል ወሬ ከሰማችው እውሸት ነው!!!!!!!

በደሴ ከተማ ጦርነትም ሆነ ምን አይነት የፀትታ ችግር የለም ወደፊትም አይኖርም ኢንሻ አላህ እኛን ብቻ እመኑ የማንኔም ወሬ አትስሙ አዳድስ ነገር ሲኖር እናሳውቃችዋለን!!

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube


#ደሴ
ቦሩ ስላሴ !!

ቦሩ ስላሴ ላይ ወራሪወቹ ደሴ ከተማን ለመያዝ ከወገን ጦር ጋር ተኩስ የከፈቱ ቢሆንም የወገን ጦር እየወሰደ ባለው እርምጃ ወራሪወቹ እየተማረኩና እጅ እየሰጡ ነው።

የወገን ጦር በከባድ መሳሪያ ሳይቀር ብትንትናቸውን እያወጣው ነው!!

ወደፊት ጉዞው ይቀጥላል !!!

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube


"ታሊባን ፀጉር አስተካካዮች ጺም እንዳይቆርጡ ወይም እንዳይላጩ አገደ

ታሊባን ከሥልጣን ከተወገደ በኋላ የወንዶች የውበት ሳሎኖች በአፍጋን ወንዶች በስፋት ሲዘወተሩ ቆይተዋል

ታሊባን የእስልምና ሕግን ይጻረራል በሚል በአፍጋኒስታን ሄልማድን ግዛት ውስጥ የሚገኙ ፀጉር አስተካካዮች የደንበኞቻቸውን ጺም እንዳይላጩ ወይም እንዳይቆርጡ አገደ።

ታዲያ ይህንን እገዳ የሚጥስ ማንኛውም የፀጉር አስተካካይ ቅጣት እንደሚጠብቀው የታሊባን የሐይማኖት ፖሊስ አስጠንቅቋል።

በመዲናይቱ ካቡል የሚገኙ አንዳንድ ፀጉር አስተካካዮችም ተመሳሳይ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ተናግረዋል።

አሁን እየወጡ ያሉ መመሪያዎች ታሊባን ከሳምንታት በፊት ስልጣን ሲጨብጥ ከገባው ቃል በተቃራኒ ቡድኑ ቀደም ሲል በነበረው የሥልጣን ዘመኑ ሲያስፈጽማቸው የነበሩትን ጥብቅ ውሳኔዎች እየመለሰ እንደሆነ ጠቋሚ ነው ተብሏል።

ታሊባን ነሐሴ ወር ላይ ስልጣኑን መልሶ ከያዘ በኋላ በተቃዋሚዎቹ ላይ ከባድ ቅጣት እየፈጸመ ይገኛል።

ቅዳሜ የቡድኑ ተዋጊዎች አራት ጠላፊዎች ናቸው የተባሉ ሰዎችን በጥይት ገድለው አስከሬናቸው በሄራት ግዛት ጎዳናዎች ላይ እንዲሰቀል አድርገዋል።

የታሊባን መኮንኖች በደቡባዊ ሄልማንድ ግዛት ውስጥ በፀጉር ማስተካከያ ቤቶች ላይ በለጠፉት ማስታወቂያ የፀጉር አስተካካዮች ለፀጉር እና ጢም የሸሪዓ ሕግን መከተል እንዳለባቸው አስጠንቅቀዋል።

በቢቢሲ የተመለከተው ማስታወቂያ "ማንም ቅሬታ የማሰማት መብት የለውም" ሲል ይነበባል።

በካቡል አንድ ፀጉር አስተካካይ "ተዋጊዎቹ መጥተው ጺም እንዳናሳጥር አዘውናል። ከመካከላቸው አንዱ በስውር የሚቆጣጠሩንን እንደሚልኩ ነገሮኛል" ሲል ገልጿል።

በከተማዋ ካሉ ስመ ጥር የወንዶች የውበት ሳሎኖች ውስጥ አንዱን የሚያስተዳድረው ሌላ የፀጉር ሥራ ባለሙያ ፣ የመንግሥት ባለሥልጣን ነኝ ከሚል ሰው ተደውሎለት እንደነበር ተናግሯል።

"የአሜሪካን ስታይል መከተል አቁም" ብሎኛል ያለ ሲሆን የማንንም ጺም መላጨት ወይም ማሳጠር እንደሌለበት እንደተነገረውም ተናግሯል።

እንደ አውሮፓውያኑ ከ1996 እስከ 2001 ታሊባን በስልጣን በነበረበት ጊዜ የተለያዩ የፀጉር አቆራረጦችን ከልክለው የነበረ ሲሆን ወንዶች ጺም እንዲያሳድጉ አጥብቀው ያዙ ነበር።

ሆኖም ጺምን ሙለጭ አድርጎ መላጨት በአብዛኛው አፍጋኒስታኒዊ ወንዶች ዘንድ የተለመደ ተግባር ነው።

ለደኅንነታቸው የሰጉና ስማቸውን ያልጠቀሱ ፀጉር አስተካካዮች "አዲሶቹ ሕጎች ኑሮን ለመቀጠል አስቸጋሪ አድርጎብናል" ይላሉ።

"ለብዙ ዓመታት ወደ ፀጉር ማስተካካያ ቤቴ ወጣቶች እየመጡ እንደፍላጎታቸው እና ወቅቱን መስለው መታየት የሚችሉበት ቦታ ነበር። ከዚህ በኋላ እዚህ ሥራ ላይ መቆየት ምንም ፋይዳ የለውም" ሲል ለቢቢሲ ተንግሯል።

ሌላኛው የፀጉር ባለሙያ ደግሞ "የፋሽን ሳሎኖች እና የፀጉር አስተካካዮች የሚከለከሉ ሥራዎች እየሆኑ ነው። ይህ ለ15 ዓመታት የቆየሁበት ሥራዬ ነበር፤ ከዚህ በኋላ መቀጠል የምችል አይመስለኝም" በማለት ገልጿል።

በምዕራባዊው ሄራት ከተማ የሚገኝ አንድ ፀጉር አስተካካይ ደግሞ ጺም እዳይቆርጥ በግልጽ ትዕዛዝ ባይደርሰውም ይህንን አገልግሎት መስጠት ማቆሙን ተናሯል።

"ደንበኞች ጺማቸውን አይላጩም [ምክንያቱም] በጎዳና ላይ በታሊባን ተዋጊዎች እንዲነኩ አይፈልጉም። መቀላቀል እና መምሰል ይፈልጋሉ። የፀጉር ማስተካከያ ዋጋ ቢቀንስም ለፋሽን ማንም ግድ የለውም" ብሏል።"

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube


"ምሥራቅ ወለጋ ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች 29 ሰዎች መገደላቸው ተነገረ

ኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ ኪራሙ ወረዳ ውስጥ በተፈጸሙ ጥቃቶች 29 ሰዎች መገደላቸውንና ከ40 ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ገለጸ።

በኪራሙ ወረዳ ቦቃ ቀበሌ መስከረም 7 እና 8 ቀን 2014 ዓ.ም በተፈጸሙ ሦስት ተያያዥ ጥቃቶች 18 ሲቪል ሰዎች ሲገደሉ በተመሳሳይ መስከረም 8 ቀን 2014 ዓ.ም ውልማይ በተባለው ቀበሌ በተፈጸመ ሌላ ጥቃት 11 ሰዎች መገደላቸውን ሪፖርት እንደደረሰው ኮሚሽኑ አስታውቋል።

በርካታ ሰዎችን ህይወት የቀጠፉትን ጥቃቶች በመሸሽም ከ40 ሺህ በላይ የሚሆኑ በኪራሙ ወረዳ ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ሰዎች አካባቢያቸውን ጥለው ወደ አጎራባች ቀበሌዎች ተሰደዋል።

በተከታታይ በሚፈጸሙት በእነዚህ ጥቃቶች ሳቢያም በወረዳው የሚገኙ ሰላማዊ ነዋሪዎች ለደኅንነታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ የሚገኙ መሆናቸው እንደሚያሳስበው ኢሰመኮ ጨምሮ ገልጿል።

ባለው አሳሳቢ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት ከተለያዩ የወረዳው አካባቢዎች የተፈናቀሉት ሰዎች በአሁኑ ጊዜ በኖሌ ቀበሌ፣በሀሮ እና ኪራሙ ከተሞች ተጠልለው እንደሚገኙ ኮሚሽኑ አመልክቷል።

ተፈናቃዮቹ ለወራት ከቀያቸው ርቀው በመጠለያዎች ውስጥ ቢገኙም አስቸኳይ ሰብአዊ እርዳታና ሌሎች ድጋፎችን ባለማግኘታቸው አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ ነዋሪዎች ለኢሰመኮ መግለጻቸውን አስታውቋል።

በአካባቢው ባለው የፀጥታ ስጋት ምክንያትም በአሁኑ ወቅት ኪራሙ ወረዳን ከቡሬና ነቀምቴ ከተሞች ጋር የሚያገናኙ ዋና ዋና መንገዶች ለተሸከርካሪ እንቅስቃሴ ተዘግተው እንደሚገኙ ኮሚሽኑ ማረጋገጡን ገልጿል።

ኢሰመኮ ባወጣው መግለጫ ላይ ለበርካታ ሰዎች ሞትና መፈናቀል ምክንያት የሆነው ጥቃት በማን እንደተፈጸመ ያለው ነገር ባይኖርም በአካባቢው ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ጥቃት ሲፈጸም መቆየቱ ይታወቃል።

ለእነዚህ ጥቃቶች መንግሥት በሽብርተኝነት የፈረጀው ሸኔ የሚባለውና እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ተጠያቂ እንደሆነ በተደጋጋሚ ይከሰሳል።

ኢሰመኮ ጥቃቶቹን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ የፌዴራል መንግሥትና የክልሉ መስተዳደር የፀጥታ ኃይሎች በኪራሙ ወረዳ የሚፈጸመውን ጥቃት ለማስቆም አስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርቧል።

የሚመለከታቸው አካላት በወረዳው ላለው የፀጥታ ስጋት "ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት እና በነዋሪዎች ላይ በተደጋጋሚ ጥቃት የሚያደርሱ ኃይሎችን ከሕግ ፊት ለማቅረብ ተጨባጭ እርምጃዎችን እንዲወስዱ" አሳስቧል።

ኢሰመኮ ጨምሮ እንዳለው በግጭቱ ሳቢያ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ፣ የተዘጉት ወረዳውን ከሌሎች አካባቢዎች ጋር የሚያገናኙት መንገዶች እንዲከፈቱና አስፈላጊው ሰብአዊ እርዳታ እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።"

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube


"የህወሓት ኃይሎች ከአፋር ክልል ተሸንፈው መውጣታቸው ተነገረ

ከትግራይ ክልል ጋር ወደ ሚዋሰነው የአፋር ክልል ገብተው የነበሩት የህወሓት አማጺያን ተሸንፈው ከክልሉ መውጣታቸው ተነገረ።

የፌደራሉ መንግሥትና የአፋር ክልል እንዳሉት ከሐምሌ ወር ወዲህ ወደ አፋር ክልል የገባው የአማጺው ቡድን ኃይል በአገሪቱ መከላከያ ሠራዊትና በክልሉ ልዩ ኃይል በተወሰደበት እርምጃ ሽንፈት ገጥሞት ከአፋር ክልል እንዲወጣ ተደርጓል።

የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው ተዋጊዎቻቸው ከአፋር የወጡት ተሸንፈው ሳይሆን ወደሌላ ስፍራ እንዲሰማሩ ተፈልጎ እንደሆነ ለሮይተርስ የዜና ወኪል ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አማባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ ሐሙስ ረፋድ ላይ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት በተወሰደ እርምጃ አማጺው ኃይል ከክልሉ መውጣቱን አመልክተዋል።

አምባሳደር ዲና የህወሓት አማጺያን ከአፋር ክልል "ባለን ወታደራዊ መረጃ መሠረት በተወሰደ ወታደራዊ እርምጃ ተሸንፎ ወጥቷል" ሲሉ ተናግረዋል።

በተመሳሳይ ህወሓት ከአፋር ክልል በራሱ ለቆ የወጣው በመከላከያ ሠራዊት እና በክልሉ ልዩ ኃይል በተወሰደ እርምጃ ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበት እንደሆነ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት ቢልለኔ ስዩም ሐሙስ ከሰዓት በኋላ በሰጡት መግለጫ ላይ ተናግረዋል።

የአፋር ክልልም እንዲሁ አማጺው ይዟቸው ከነበሩ የክልሉ አካባቢዎች በተከታታይ የተደረጉ ውጊያዎችን ተከትሎ እንዲወጡ መደረጋቸውን በተመለከተ ከሰኞ ዕለት ጀምሮ ይፋ ሲያደርግ ቆይቷል።

የአፋር ክልል ኮምዩኒኬሽን ቢሮ እንዳለው የህወሓት ኃይሎች ተቆጣጥረውት ነበሩ ካለው ፈንቲ ረሱ ከሚባለው የክልሉ አካባቢ ሙሉ በሙሉ እንዲወጡ መደረጋቸውን አመልክቷል።

ሮይተርስ የዜና ወኪል ያነጋገራቸው የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በበኩላቸው ተዋጊዎቻቸው ከክልሉ መውጣታቸውን አረጋግጠው ነገር ግን የወጡት ሽንፈት ግጥሟቸው እንዳልሆነ መናገራቸውን ዘግቧል።

አቶ ጌታቸው ረዳ ካልተጠቀሰ ቦታ በሳተላይት ስልክ ለሮይተርስ "አልተሸነፍንም። በአፋር ክልል ግጭት አልነበረም ስለዚህ የወታደሮች እንቅስቃሴ ከዚያ ወደ አማራ ክልል ተራራማ ስፍራዎች አንቀሳቅሰናል" ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ህወሓት ተዋጊዎቹን ከአማራ እና አፋር አካባቢዎች ማስወጣቱን በትግራይ ቴሌቪዥን አስነግሯል።

ትግራይ ቴሌቪዥን ላይ በተላለፈው መግለጫ ህወሓት ወታደሮች አካባቢዎቹን ለቀው የወጡት የፌደራሉ መንግሥት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሲቪሎችን በጦርነቱ እንዲሳተፉ በማሰማራቱ ነው ብሏል።


የፌደራሉ መንግሥት ባለፈው ሰኔ ወር ማብቂያ ላይ የተናጠል የተኩስ አቁም አውጆ ሠራዊቱን ከትግራይ ማስወጣቱን ተከትሎ የህወሓት ኃይሎች ጥቃት በመሰንዘር በአፋር እና በአማራ ክልል ውስጥ ያሉ አካባቢዎችን መያዛቸው ይታወሳል።

ባለፉት ጥቂት ሳምንታት የፌደራሉ መከላከያ ሠራዊት፣ የክልሎች ልዩ ኃይሎች እንዲሁም ሚሊሻዎች የህወሓት ኃይሎች ይዘው ከቁባቸው አካባቢዎች ለማስወጣት ከፍተኛ ጦርነት ሲካሄዱ እንደነበር ሲዘገብ ቆይቷል።

በዚህም የፌደራሉ መንግሥት የተለያዩ ድሎችን እያስመዘገበ እና ቦታዎችን እየተቆጣጠረ መሆኑን እንዲሁም የህወሓት ኃይሎች ይዘዋቸው ከነበሩ ቦታዎች ሲለቁ በንጹሃን ላይ ጥቃት መፈጸማቸውንና ንብረት መውደም መዝረፋቸውን ገልጿል።

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በዳባት ወረዳ ጭና በሚባል አካባቢ የህወሓት ታጣቂዎች ከ120 በላይ ንፁሃን ሰዎችን ስለመግደላቸውን ነዋሪዎችና የወረዳው ለቢቢሲ ተናግረው ነበር።

ህወሓት በበኩሉ በወታደሮቹ ተፈጸመ የተባለውን የጅምላ ግድያ ክስን "ሐሰት" ሲል አስተባብሏል።

የትግራይ ጦርነት ያስከተለው ሰብዓዊ ቀውስ

በህወሓት እና በፌደራሉ መንግሥት መካከል የተነሳው ጦርነት አስረኛ ወሩን ያስቆጠረ ሲሆን ወደ አጎራባቾቹ የአፋርና የአማራ ክልሎች ተዛምቶ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ለረሃብ አደጋ አጋልጦ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑትን ደግሞ አፈናቅሏል።

የተባበሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም በትግራይ፣ አፋር እና አማራ ክልሎች በአጠቃላይ እስከ 7 ሚሊዮን ሕዝብ ለረሃብ ቀውስ ሊጋለጡ ይችላሉ ብሎ ነበር።

ድርጅቱ በሰሜን ኢትዮጵያ የተቀሰቀሰው ግጭት በአማራ እና አፋር ክልሎች ወደ 1.7 ሚሊዮን ሰዎችን ለረሃብ አደጋ ሲያጋልጥ ወደ 300ሺህ የሚጠጋ ሕዝብን ደግሞ ከመኖሪያ ቀዬው አፈናቅሏል ይላል።

በትግራይ ደግሞ ወደ 5.2 ሚሊዮን ሕዝብ አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ሲል ድርጅቱ አስታውሷል።

የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ ባደረጉት ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችና ቁጥራቸው የማይታወቅ ተዋጊዎች ተገድለዋል።"

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube


"የዓለም መሪዎች ገለልተኛ ቡድን አባላት በኢትዮጵያ የተኩስ አቁምና ድርድር እንዲደረግ ጠየቁ

የዓለም መሪዎች ገለልተኛ ቡድን አባላት፣ 'ዘ ኤልደርስ' (ታላላቅ ሰዎች) በትግራዩ ጦርነት እየተሳተፉ ያሉ ወገኖች የተኩስ አቁም እንዲያደርጉና እንዲደራደሩ ለማበረታታት እርምጃ እንዲወስድ የተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤትን ጠየቁ።

ቡድኑ ይህንን ያቀረበው ዓለም አቀፍ ደኅንነትና ሰላም ለማስፈንና የፀጥታው ምክር ቤት ሊኖረው ስለሚገባው ሚና ጳጉሜ 2፣ 2013ዓ.ም በተደረገ ጉባኤ ላይ ነው።

ምክር ቤቱ በአንድነት እርምጃ እንዲወስድና በብቃትም ቀውሶችን የመፍታት ሚና እንዲጫወት ተጠይቋል።

በዓለም ላይ እየተከሰቱ ካሉ ዋነኛ ቀውሶች ተብለው ከቀረቡት ጉዳዮች መካከል የትግራይን ጦርነት ጨምሮ አፍጋኒስታን፣ ምያንማር እንዲሁም በፍልስጥኤም እየተከሰቱ ያሉ ጉዳዮች ተነስተዋል።

"ጦርነቱን ማስቆም እየተከሰተ ያለውን ስቃይ ማክተሚያ ብቸኛው መንገድ ነው" በማለትም በዚህ ወቅት የቡድኑ ሰብሳቢ፣ የቀድሞ የአየርላንድ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚዳንት እና የቀድሞው የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር ሜሪ ሮቢንሰን ተናግረዋል።

ከጦርነቱም መባባስ ጋር ተያይዞ የሴቶችና የታዳጊዎች ጥበቃ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ ሰብሳቢዋ አፅንኦት ሰጥተዋል።

"ምክር ቤቱ በጦርነቱ ምክንያት እየተከሰተ ስላለው አስከፊ የሰብዓዊ ቀውስ ሁኔታና የምግብ ዋስትና አደጋ ውስጥ መውደቅ ከዚህ ቀደም ገለጻ ተደርጎለታል። በተጨማሪም በትግራዩ ጦርነት ረሃብና ወሲባዊ ጥቃት እንደ ጦር መሳሪያ መዋላቸውን ጨምሮ መጠነ ሰፊ የሰብዓዊ ጥሰቶች እየተፈፀሙ ነው" ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ምክርቤቱ መሬት ላይ ያለውን እውነታ ለመረዳት ትግራይን ጨምሮ በኢትዮጵያ ጉብኝት እንዲያደርግና አስቸኳይ የፖለቲካዊ መፍትሄም ሊበጀለት እንደሚገባም ተጠቁሟል። ሰብሳቢዋ "ወታደራዊ መፍትሄ አይበጅም" ብለዋል።

በዚህም ወቅት በተባበሩት መንግሥታት የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ "ቡድኑ በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያሉትን ምክክር እንደግፋለን" ከማለት በተጨማሪ የቀድሞው የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሉሴጎን ኦባሳንጆ የአፍሪካ ሕብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ሆነው በቅርቡ መሾማቸውንም ጥሩ እመርታ ነው ብለዋል።

በትግራይ ኃይሎችና በፌደራሉ መንግሥት መካከል የተነሳው ጦርነት አስረኛ ወሩን ያስቆጠረ ሲሆን ወደ አጎራባቾቹ አፋርና አማራ ክልሎች ተዛምቶ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎችን አፈናቅሏል።

በአፋር ክልል ካለው ጦርነት ጋር ተያይዞ የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር ከ112 ሺህ በላይ መድረሱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ አስታውቋል።

በትግራይ ወደ 900 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በረሃብ አፋፍ ላይ የሚገኙ ሲሆን ሌሎች 5 ሚሊየን የሚሆኑት የክልሉ ነዋሪዎች ደግሞ አስቸኳይ የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት ገልጿል። ።

የኢትዮጵያ መንግሥትና ህወሓት ከጥቅምት 24/2013 ዓ.ም ጀምሮ ባደረጉት ጦርነት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰላማዊ ዜጎችና ቁጥራቸው የማይታወቅ ተዋጊዎች ተገድለዋል።"

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube


"የህወሓት አማጺያን በሰሜን ጎንደር 119 ሰዎችን መግደላቸውን ነዋሪዎችና ባለስልጣን ተናገሩ

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን በዳባት ወረዳ ጭና በሚባል አካባቢ የህወሓት ታጣቂዎች 119 ንፁሃን ሰዎችን መግደላቸውን ነዋሪዎችና የወረዳው አስተዳዳሪ ለቢቢሲ ተናገሩ።

ግድያው የተፈጸመው አካባቢው በህወሓት ኃይሎች ቁጥጥር ስር በቆዩባቸው ቀናት ውስጥ መሆኑንና ሽማግሌዎች፣ ሴቶችና ህጻናት በተፈጸመባቸው ጥቃት መገደላቸውን ተናግረዋል።

የጭና አጎራባች ቀበሌ አብጥራ፣ ነዋሪ የሆኑት አቶ አስማረ ታፈረ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ነሐሴ 12/2013 ከቀኑ 9፡00 ጀምሮ በአካባቢው የህወሓት ኃይሎች በመግባት ተኩስ መክፈታቸውንና ውጊያ መካሄዱን አመልክተዋል።

ጦርነቱ እስከ ነሐሴ 29/2013 ዓ.ም ድረስ መካሄዱን የሚገልፁት አቶ አስማረ፣ እስካሁን ድረስ ተገድለው የተገኙ 119 ሰዎች በጦርነቱ ያልተሳተፉ የአካባቢው ነዋሪዎች መሆናቸውን ያስረዳሉ።

"ይህ ቁጥር መሞታቸው ታውቆ ለቅሶ እየተለቀሰ ያለ ነው" በማለት ይህ ቁጥር ከዚህም በላይ ሊጨምር እንደሚችል ነዋሪው ይናገራሉ።

አማጺያኑ በወሰዱት እርምጃ በወረዳው ነዋሪ የሆኑ አዛውንት፣ ህጻናት ቀሳውስት እና ሴቶች መገደላቸውንም አክለው ተናግረዋል።

አቶ አስማረ ከአንድ ቤተሰብ አምስት እና ስድስት ሰዎች የሞቱ መኖራቸውንም ለቢቢሲ ገልጸዋል።

ሌላው የአካባቢው ነዋሪ የሆኑት አቶ ሞላ ውቤ የተፈጠረውን ለቢቢሲ፣ በስፍራው ከነሐሴ 12/2013 ጀምሮ ግጭት ሲካሄድ እንደነበረ አመልክተዋል።

ነገር ግን የህወሓት ታጣቂዎች ወደ ጭና ሲገቡ ምንም ዓይነት ጥቃት እንዳልደረሰባቸው ገልፀው፣ "ጦርነቱ ሲፋፋም እና አማጺያኑ መሸነፋቸውን ሲያውቁ አዛውንት፣ ሕጻናት፣ ሴቶች እንዲሁም እንስሳትን እየገደሉ ሄደዋል" ብለዋል።

አቶ ሞላ ከአንድ ቤተሰብ አራት ሰዎች፣ ቀሳውስትን እንዲሁም ወንድማማቾችን እና ነፍሰ ጡር ሴትን ጨምሮ መገደላቸውን በስም እየጠቀሱ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

እነዚህ ሰዎች በአጠቃላይ በውጊያ የተሳተፉ አለመሆናቸውን በመግለጽም፣ አማጺያኑን በየቤታቸው ሠንጋ አርደው ሲያበሏቸው የነበሩ ሰዎች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጸዋል።

በጭና ቀበሌ ከአማጺያኑ ጋር ለአስራ አንድ ተከታታይ ቀናት ውጊያ ሲካሄድ እንደነበር የሚናገሩት የዳባት ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሰውነት ውባለም፣ የህወሓት ኃይሎች "እንስሳትን እና የአርሶ አደር ንብረቶችን መዝረፍ . . . እንዲሁም ማበላሸት" መፈጸማቸውን አመልክተዋል።

አስተዳዳሪው አክለውም በወረዳው ለተከታታይ አስራ አንድ ቀናት እስከ ነሐሴ 29/2013 ዓ.ም ድረስ የዘለቀ ውጊያ እንደነበርም አረጋግጠዋል።

እንደ አቶ ሰውነት ከሆነ በዚህ ሳምንት በአካባቢው ላይ በተደረገ ቅኝት የበርካታ ንፁሃን የአካባቢው ነዋሪዎች የጅምላ መቃብር ተገኝቷል።

አቶ ሰውነት ከአካባቢው ማኅበረሰብ እንዲሁም ከተገኙ የጅምላ መቃብር አረጋገጥን ባሉት መሰረት እስካሁን ድረስ 119 ሰዎች መገደላቸውን እንዳወቁ ገልጸዋል።

የወረዳ አስተዳዳሪው እስካሁን ድረስ ባለው መረጃ፣ ዛፍ ጋር ታስረው የተረሸኑ ሴቶች፣ አዛውንቶች፣ ህጻናት እና ከቅዳሴ እየተመለሱ የነበሩ ቀሳውስት ጭምር መኖራቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ጥቃቱ ለምን እንደተፈፀመ ሲያብራሩም "በቀላሉ ሊያሳልፋቸው ያልቻለ ሕዝብ በመሆኑ፤ ከተስፋ መቁረጥ የተነሳ ነው" በማለት፤ አማጺያኑ አባሎቻቸው ሲማረኩ እንዲሁም ከፍተኛ ጉዳት ሲደርስባቸው "በብስጭት" ጭና ቀበሌ ላይ በንጹሃንና በጦርነቱ ተሳታፊ ባልሆኑ ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ አካሂደዋል ብለዋል።

የህወሓት ኃይሎች በአካባቢው ለቀናት መቆየታቸውን የተናገሩት ነዋሪዎችና አስተዳዳሪው "በአካባቢው በተደረገው ከባድ ውጊያ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው እየተሸነፉ ወደ ኋላ ሲመለሱ ነው ሲቀልቧቸው የከረሙ ንጹሃንን በበቀል ገደሉ" በማለት አቶ አስማረ አስረድተዋል።

አካባቢውን እንደተቆጣጠሩ "እኛ ችግር ያለብን ከመንግሥት ጋር ነው፤ ከእናንተ ጋር አይደለም" በማለት ለነዋሪው ይናገሩ እነደነበር የገለጹት አቶ አስማረ፣ በኋላ ግን ጦርነቱ እየተጧጧፈ ሲመጣ ንፁሃንን ገድለዋል ብለዋል።

በአማጺያኑ ተገድለዋል ከተባሉት ከአንድ መቶ በላይ ሰዎች ባሻገር፣ አሁንም በአካባቢው ያልተገኙ እና የጠፉ ሰዎች መኖራቸውን ነዋሪዎች ገልጸው "ተይዘው ተወስደው ይሆናል" ሲሉ ይናገራሉ።

ጦርነቱን በመሸሽ ወደ ሌላ ቀበሌ የተሻገረ፣ በዋሻ ውስጥ የተደበቀ እንዲሁም ተጨማሪ የተገደለ ሰው እንደሚኖር ያላቸውን ግምት ነዋሪዎቹ አክለው ለቢቢሲ ገልፀዋል።

አቶ ሞላ ውቤ እስካሁን ድረስ 119 ሰዎች መገደላቸው በነዋሪው ቢቆጠርም ቁጥሩ ግን ከዚህ በላይ ከፍ ሊል እንደሚችል ያላቸውን ስጋት አስረድተዋል።

ባለፉት ሁለት ወራት ኃይሎቹን ወደ አማራ ክልልና አፋር ክልል ያሰማራው ህወሓት በሰሜን ጎንደር ጭና ውስጥ በታጣቂዎቹ ተፈጸመ ስለተባለው የንጹሃን ጅምላ ግድያ እስካሁን ያለው ነገር የለም።

ጭና ቀበሌ የገጠር ቀበሌ መሆኗን እና በእርሻ የሚትዳደሩ ገበሬዎች የሚኖሩባት፣ ከከተማ ርቃ የምትገኝ ስፍራ እንደሆነች የወረዳው አስተዳዳሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የህወሓት ታጣቂዎች ወደ ዳባት ጭና ከመድረሳቸው በፊት፣ አዳርቃይ እንዲሁም ደባርቅ ወረዳ ላይ ከፍተኛ ጥቃት መፈፀማቸውን አስተዳዳሪው ጨምረው ገልፀዋል።

በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ከህወሓት ኃይሎች ነጻ ከወጣ ከቀናት በኋላ የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ንጹሃን የተቀበሩበት የጅምላ መቃብር እንዳገኘ ያስታወቀው የዞኑ አስተዳደር ነው።

በዚህም የህወሓት ኃይሎች በወረዳው ውስጥ "ጭና ተክለ ሐይማኖት በተባለ ቀበሌ ቀሳውስትን ጨምሮ በንጹሃን ሰዎች ላይ ነሐሴ 26 እና 27 የጅምላ ግድያ ፈጽመዋል" በማለት በአንድ መቃብር ብቻ 47 አስከሬኖች እንደተገኙ ገልጿል።"

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube


"የመን ያሉ ወደ 5 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን አገር ቤት ለመመለስ እየተጠባበቁ መሆኑ ተገለጸ

በየመን ካለው አለመረጋጋትና የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ወደ 5 ሺህ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ወደ አገራቸው ለመመለስ እየተጠባበቁ መሆናቸውን ሪሊፍዌብ ዘግቧል።

በያዝነው ሳምንት 300 የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በገዛ ፈቃዳቸው ዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) በሚያዘጋጃቸው በረራዎች ወደ አገራቸው ለመመለስ ተዘጋጅተዋል።

ድርጅቱ እአአ እስከ 2021 መጠናቀቂያ ድረስ በሳምንት ሁለት በረራዎችን በማድረግ በገዛ ፈቃዳቸው የሚመለሱ ስደተኞች ወደ አገራቸው ለማስገባት እየሠራ እንደሆነ አስታውቋል።

"የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ከተከሰተ ወዲህ የመን የሚገኙ ስደተኞች በእጅጉ እየተረሱ ነው" ብለዋል በየመን የአይኦኤም ምክትል የሚሽን ኃላፊው ጆን ማኪው።

በ2021 እስካሁን ድረስ ወደ 600 የሚጠጉ ፈቃደኛ ስደተኞች ከየመን፣ ኤደን ወደ አዲስ አበባ የተመለሱ ሲሆን፤ ሌሎች 79 ስደተኞች ደግሞ ከሰነዓ ተነስተው አዲስ አበባ ገብተዋል።

ዛሬ ከኤደን የተነሳ ስደተኞችን የጫነ አውሮፕላን አዲስ አበባ እንደሚገባ ይጠበቃል።

ይህ ስደተኞችን በገዛ ፈቃዳቸው ወደ አገራቸው የመመለስ ተግባር ቀላል እንዳልሆነና አይኦኤም ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ 3 ሚሊየን ዶላር እንደሚያስፈልገው የተገለጸ ሲሆን፤ ይህ ገንዘብ ከበረራዎች በተጨማሪ በየመን እና በኢትዮጵያ የሚገኙ የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማትን ለመርዳትም ይውላል።

"እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ተጨማሪ ድጋፎችን እንዲያደርጉልን ጥሪያችንን እናስተላልፋለን። በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በየመን መሄጃ አጥተው ይገኛሉ። ያላቸው ብቸኛ አማራጭ ይህንን አስቸጋሪ ሁኔታ በማምለጥ ወደ አገራቸው መግባት ነው" ብለዋል ምክትል የሚሽን ኃላፊው።

በየመን እስከ 32 ሺህ የሚደርሱ ስደተኞቹ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፤ አብዛኛዎቹ በኮቪድ-19 ስርጭት ምክንያት ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሊያደርጉት የነበረው ጉዞ የተደናቀፈባቸው ናቸው።

በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ከፍተኛ ፈተና ውስጥ መግባታቸውን ተከትሎ ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ስደተኞቹን ለሌሎች አላማዎች እያዋሏቸው እንደሚገኝ ተገልጿል።

አንዳንድ ስደተኞች እዳቸውን ለመክፈል የእርሻ ማሳዎች ላይ የጉልበት ሥራ እንዲሠሩ የሚገደዱ ሲሆን፤ ሌሎች ደግሞ ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ይፈጸምባቸዋል።

በተጨማሪም ስደተኞቹ እየታገቱ ከቤተሰቦቻቸው ገንዘብ ካላስላኩ እንደሚገደሉ ይነገራቸዋል።

በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ እነዚህን ሁሉ መከራዎች አልፈው በሕይወት መቆየት የቻሉት ደግሞ በቂ የሆነ ንጹህ ውሃ፣ ምግብ እና የጤና አገልግሎትን ማግኘት አይችሉም።

ከስደት ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ አንዷ የሆነችው የ24 ዓመቷ ትዕግስት "ከባድ ድብደባ ደርሶብኛል፣ ታስሬያለሁ፣ እንዲሁም ያለአግባብ መብቴ ተጥሷል" ትላለች።

"አብዛኛውን ጊዜ እየራበኝ ነው የምተኛው። ይሄ ሁሉ ነገር ከደረሰብኝ በኋላ ወደ አገሬ እና ወደ ቤተሰቦቼ መመለስ መቻሌ በጣም አስደስቶኛል" ስትልም ታክላለች።

በፈቃዳቸው ወደ አገራቸው የሚመለሱ ስደተኞች ኢትዮጵያ ውስጥ በሚገኘው የአይኦኤም ማዕከል በኩል ድጋፍ የሚደረግላቸው ሲሆን፤ ወደ ቤተሰቦቻቸው እንዲመለሱ የመጓጓዣ ወጪያቸው ይሸፈንላቸዋል።

በተጨማሪም ወደ ማኅበረሰቡ ከመቀላቀላቸው በፊት የሥነ ልቦና ድጋፍ ይደረግላቸዋል።

"በየመን የሚገኙ ፈቃደኛ ስደተኞችን የመመለስ ሥራ በጣም ወሳኝ ነው። ሥራውም ዘላቂ መፍትሔ ሊያመጡ በሚችሉ ሂደቶች መደገፍ አለበት" ብለዋል በኢትዮጵያ በአይኦኤም በኃላፊነት የሚሠሩት ማላምቦ ሙንጋ።

የአይኦኤም መረጃ እንደሚያመላክተው እአአ በ2019 ብቻ በአጠቃላይ 138 ሺህ ስደተኞች ወደ የመን የገቡ ሲሆን፤ በ2021 ደግሞ 37 ሺህ 500 ስደተኞች የመን ገብተዋል።"

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube


"የፀጥታው ምክር ቤት አባላት በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ ምን አሉ?

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭት በተመለከተ ሐሙስ ነሐሴ 20/2013 ዓ.ም ውይይት አድርጓል።

ምክር ቤቱ የትግራይ ግጭት ከተቀሰቀሰ በኋላ ለበርካታ ጊዜ በኢትዮጵያ ጉዳይ በዝግና በይፋ ውይይት ማድረጉ ይታወሳል። የአሁኑ ስብሰባም በከፊል ክፍት የነበረ ሲሆን ከመጀመሪያው ዙር ውይይት በኋላ ውይይቱ በዝግ ተደርጓል።

በዚህ ስብሰባ ላይ የምክር ቤቱ አባላት በሰሜን ኢትዮጵያ ስላለው ቀውስ አስተያየት ሰጥተዋል። ማን ምን አለ?

የተባበሩት መንግሥታት

የተባበሩት መንግሥታት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ከትግራይ ተነስቶ ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች የተስፋፋው ጦርነት ቆሞ ሁሉም ወገኖች ወደ ድርድር መምጣት አለባቸው ሲሉ ለፀጥታው ምክር ቤት ተናግረዋል።

ሁሉም አካሎች ተኩስ አቁመው ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲፈልጉ በተደጋጋሚ የጠየቁት ዋና ጸሐፊው በትላንቱ የመንግሥታቱ ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ጉባኤም ይህንኑ አቋም አንጸባርቀዋል።

"ሁሉም ወገን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ አቁሞ ወደ ድርድር መምጣት አለበት። ስለ ኢትዮጵያ ሲሉ ሰላማዊ መንገድን አማራጭ ማድረግ አለባቸው። ሁሉን አካታች የፖለቲካ ውይይት ያስፈልጋል። የውጭ ኃይሎችም ከአገሪቱ መውጣት አለባቸው" ብለዋል።

ከአንድ ሳምንት በፊትም ያለ ቅድመ ሁኔታ የተኩስ አቁም ላይ እንዲደረስ የጠየቁት ጉቴሬዝ፤ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር እንደተነጋገሩና ራሱን የትግራይ ክልል ሕጋዊ አስተዳዳሪ እያለ የሚጠራው አካል የሆኑት ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ደብዳቤ እንደላኩላቸው ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ከአፍሪካ ሕብረት እና ሌሎችም አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ሁሉን አቀፍ ውይይት እንዲካሄድ ድጋፍ እንደሚሰጥ ጨምረው ገልጸዋል።

"ወታደራዊ ግጭት መፍትሔ እንደማያመጣ ሁሉም ወገኖች መገንዘብ አለባቸው" ሲሉም ዋና ጸሐፊው ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊ መብት ኮሚሸን ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ጋር በመጣመር እያካሄደ ያለው ምርመራ እየተጠናቀቀ እንደሆነ ጉቴሬዝ ጠቁመዋል።

ጉቴሬዝ ያነሷቸው ሦስት ቁልፍ ነጥቦች ሁሉም ወገኖች በአፋጣኝ ተኩስ እንዲያቆሙ፣ ያልተገደበ የሰብአዊ እርዳታ እንዲዳረስ መንገድ አመቻችተው ለሕዝብ አገልግሎት የሚሰጡ መሠረተ ልማቶች መልሰው እንዲከፈቱና በኢትዮጵያ የሚመራ ፖለቲካዊ ውይይት እንዲጀመር ነው።

"የኢትዮጵያ አንድነት እና የቀጠናው ሰላም አደጋ ውስጥ ወድቀዋል" ያሉት ዋና ጸሐፊው ጦርነቱ ከትግራይ ክልል ወደ አማራ እና አፋር ክልሎች ከመስፋፋቱ ባሻገር ሌሎች ቀጠናዊ ኃይሎች እንደገቡበትም አክለዋል።

"ነገሮችን የሚያቀጣጥል ትርክት እና ብሔርን ተመርኩዞ ሰዎችን ኢላማ ማድረግ ተባብሷል። ሴቶች እና ሕፃናትም ወሲባዊ ጥቃት እየደረሰባቸው ነው። ይህን እጅግ በጣም አወግዛለሁ" ሲሉ ለምክር ቤቱ ተናግረዋል።

ከሰብአዊ ቀውሱ ባሻገር የኢትዮጵያ ምጣኔ ሀብት እየተሽመደመደ መምጣቱንም ተናግረዋል። የአገሪቱ እዳ እየጨመረ፣ ብድር የማግኘት እድል እየቀነሰ፣ የዋጋ ንረት እየተባባሰ፣ መሠረታዊ ምግብ አቅርበት እያለቀ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ

በተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ለፀጥታው ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር "የኢትዮጵያ መንግሥት ሰላም ለማስፈን የወሰነውን የተናጠል ተኩስ አቁም ህወሓት እንዲቀበል ጫና መረደግ አለበት" ብለዋል።

ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት አክብሮ በገንቢ መንገድ ብቻ አገሪቱን ማገዝ እንደሚገባው ተናግረዋል።

"የእኛ ግብ ሰላም ነው። ህወሓት ግን በሰላምና በኢትዮጵያ መካከለ ቆሟል። ህወሓት ተጎጂ ሳይሆን አጥቂ ነው" ያሉት አምባሳደር ታዬ፤ በኢትዮጵያ ሰላም እንዲወርድ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በህወሓት ላይ ጫና እንዲያደርግ አሳስበዋል።

ሰብአዊ እርዳታ በሚተላለፍባቸው ቦታዎች ያለን ፍተሻ ለመቀነስ እና ፍተሻውን በዘመናዊ መሣሪያ ለማድረግ ኢትዮጵያ እንደምትፈልግ ተናግረዋል። በተጨማሪም ሰብአዊ በረራ እንደተፈቀደም አክለዋል።

አምባሳደሩ ይህንን ያሉት የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝና የአሜሪካው ተወካይ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መስተጓጎል ከተቹ በኋላ ነው።

እንደ መብራት እና ስልክ ያሉ መሠረተ ልማቶችን መተመለከተ "አገልግሎቱ የሚጀመረው ሰላም እና ሕግ ሲሲፍን ነው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

መንግሥት የተናጠል ተኩስ አቁም ያወጀው ሰብአዊ እርዳታ ወደ ትግራይ እንዲደርስ እና ለክልሉ ሕዝብ ሰላም ለመስጠት ቢሆንም፤ ህወሓት ጦርነቱን ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች አስፋፍቶ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው እንደተፈናቀሉ ለምክር ቤቱ ተናግረዋል።

ህወሓት የሰብአዊ እርዳታ እንዳይደርስ አድርጓል ብለው የተናገሩት አምባሳደር ታዬ፤ ቡድኑ በአገሪቱ አለመራጋጋት እንደፈጠረና መንግሥትም ሰላም ለማስፈን ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሆነ አስረድተዋል።

ብሔርን መሠረት ያደረገ ጥቃት እየተሰነዘረ እንደሆነ በኢትዮጵያ ላይ የሚሰነዘረውን ክስ በተመለከተ "ብሔርን መሠረት ያደረገ አድልዎ የለም። መርህ አለን። ለዓመታት ማኅበረሰባዊ መስታገብራችን የቀጠለው ልዩነትን መሠረት ያድርጎ ነው" ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

የምክር ቤቱን ውይይት አስመልክተውም "ጉዳዩን ማግነን እና ፖለቲካዊ ቅርጽ መስጠት የኢትዮጵያን መንግሥት ውሳኔ እንደማይለውጥ" አስታውቀዋል።"

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube


""ህወሓት በደቡብ ጎንደር ሆስፒታሎችን ሳይቀር ዘርፏል" የዞኑ የብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ

በአማራ ክልል በደቡብ ጎንደር ዞን ውስጥ የተለያዩ አካባቢዎችን ተቆጣጥሮ የነበረው የህወሓት ኃይል መጠነ ሰፊ ዘረፋ፣ የመሠረተ ልማት ውድመትና ጥቃት መፈጸሙ ተነገረ።

ቢቢሲ ያናገራቸው የአካባቢው ነዋሪዎችና የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ እንዳሉት አካባቢዎቹን ለመቆጠጠር በተደረገ ውጊያና ከዚያ በኋላ በነበሩ ጊዜያት በህወሓት ኃይሎች ሰዎች መገደላቸውን ተናግረዋል።

በደቡብ ጎንደር ዞን የብልፅግና ፓርቲ ኃላፊ የሆኑት አቶ ይርጋ ሲሳይ ቅጣው ለቢቢሲ እንደተናገሩት አማጺያኑ ወደ ደቡብ ጎንደር ዞን በመግባት በተለይ ጋይንት፣ ንፋስ መውጫ፣ ጎብጎብ ሳሊህ፣ እንዲሁም ጉና በጌምድር እንዲሁም በከፊል የፋርጣን አካባቢዎችን ተቆጣጥረው ነበር ብለዋል።

በዚህ ወቅትም በአካባቢዎቹ የሚገኙ ሆስፒታሎች፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋም፣ የመብራት ሰብ ስቴሽን፣ ባንኮችና ሌሎችም ሕዝባዊ መሠረተ ልማቶች እንዲሁም የግል ንብረቶች ሳይቀሩ መዘረፋቸውን ሚናገሩት አቶ ይርጋ ሌሎች ንብረቶች ደግሞ መልሰው ጥቅም ላይ እንዳውሉ ሆነው ወድመዋል ብለዋል።

የመንግሥት ሠራተኛ የሆኑት የንፋስ መውጫ ነዋሪ አቶ አልማው ጥጋቡ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ለሦስትና ለአራት ቀናት አጎራባች በሆነው ደብረዘቢጥ በሚባለው ስፍራ ጦርነት እንደነበርና የከባድ መሳሪያ ድምጽ ሲሰማ እንደነበር ያስታውሳሉ።

አማጺያኑ "ወደ ከተማችን ከገቡ በኋላ በአካባቢው የሕዝብ መገልገያ የሆኑት እንደ ጤና ጣቢያ፣ ሆስፒታል፣ ትምህርት ቤቶችና ባንኮችን የመሳሰሉ ተቋማትን ዘርፈዋል። ከጥቅም ውጪ እንዲሆኑም አድርገዋል" ይላሉ።

ከባድ ውድመትና ዘረፋ ደርሶበታል የተባለው በንፋስ መውጫ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፊታውራሪ ገብርዬ ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዓለምነው ስዩም ለቢቢሲ እንዳረጋገጡት ባንኩ በሚሊዮኖች ብር የሚገመት ዘረፋና የንብረት ውድመት ደርሶበታል።

አማጺያኑ ወደ ዞኑ በገቡበት ወቅት ነዋሪዎች በግልም ሆነ በቡድን ለመከላከል ጥረት ሲያደርጉ ከሠራዊቱ ውጪ ከነዋሪው አስካሁን በደረሳቸው መረጃ ቢያንስ 21 ሰዎች መሞታቸውን የሚገልጹት አቶ ይርጋ ቁጥሩ ከዚህ በላይም ሊሆን እንደሚችል አስረድተዋል።

ሌላኛው የነፋስ መውጫ ከተማ ነዋሪ ያሬድ አለነ በበኩሉ ከተማዋ በህወሓት ኃይሎች ስትያዝ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ገልጾ፤ ጥቃቱን በመፍራት ወደ ሌሎች ቦታዎች የሸሹ ነዋሪዎች ስላሉ ሁሉም ሲመለስ የሞቱት ሰዎች ትክክለኛ ቁጥር እንደሚለይ ገልጿል።

"ንፋስ መውጫ ከተማ እንዳልነበረች ሆናለች" የሚለው ያሬድ ባንኮችና በከተማዋ የሚገኙ የተለያዩ የሕዝብ ተቋማት እንዲሁም የግል ንብረቶች ስለተዘረፉና እንዲወድሙ ስለተደረገ በአሁኑ ወቅት ከተማዋ ከእንቀስቃሴ ውጪ ሆና ቀዝቅዛለች ብሏል።

የዞኑ ዋና ከተማ ከሆነችው ከደብረ ታቦር በተጨማሪ በንፋስ መውጫ ላይ የህወሓት ኃይሎች በተኮሱት ከባድ መሳሪያ የአንድ ቤተሰብ አባላት መገደላቸውን አቶ ይርጋ ተናግረዋል።

የነፋስ መውጫ ከተማ ነዋሪው አቶ አልማው በበኩላቸው አማጺያኑ ወደ ከተማዋ ከገቡ በኋላ "እኔ የማውቃቸውና በዚሁ ቀበሌ የሚኖሩና በስም የማውቃቸው ጭምር ከሃያ በላይ ሰዎች ተገድለዋል" ሲሉ ተናግረው፤ ተገደሉ ካሏቸው ሰዎች መካከል የሚያወቋቸውን ሰዎች ስም ዘርዝረዋል።

በአካባቢዎቹ በሰውና በንብረት ላይ ከደረሰው ጉዳት ባሻገር "በርካታ የቤት እንስሳት በጠላት ተመተዋል። የአርሶ አደሩ ንብረት የሆኑ ብዙ ከብቶች፣ ፈረሶች፣ በጎች የጠፉበት ሁኔታ ነው ያለው" ያሉት ደግሞ አቶ ይርጋ ናቸው።"

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube


"አሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት የኤርትራ ጦር ዳግም ወደ ትግራይ እየተሰማራ ነው አሉ

አሜሪካ እና የአውሮፓ ሕብረት የኤርትራ ጦር በቅርብ ቀናት ውስጥ ዳግም ወደ ትግራይ እየገባ መሆኑ አሳስቦናል አሉ።

የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር አንቶኒ ብሊንከን ከትናንት በስቲያ፤ "[የኤርትራ ጦር] ሰኔ ወር ላይ ከወጣ በኋላ በበርካታ ቁጥር ዳግም ወደ ኢትዮጵያ ተመለሶ ገብቷል" ማለታቸውን ሮይተርስ የዜና ወኪል ዘግቧል።

የአውሮፓ ሕብረት ዲፕሎማቶች ደግሞ ነሐሴ 14 የጻፉት የውስጥ ማስታወሻ (ኢንተርናል ሜሞረንደም) ኤርትራ የትግራይ ድንበርን ተሻግረው የገቡ ተጨማሪ ኃይሎች አሰማርታለች ይላል።

ይህ የአንቶኒ ብሊንከን እና የአውሮፓ ሕብረት ማሳሰቢያ የተሰማው አሜሪካ በትግራይ ክልል ከተካሄደው ጦርነት ጋር በተያያዘ የኤርትራ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ላይ በሰብአዊ መብቶች ጥሰት ምክንያት ማዕቀብ መጣሏን ካስታወቀች በኋላ ነው።

ጄነራል ፊሊጶስ ወልደዮሐንስ፤ በጦርነቱ ውስጥ በከባድ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት የሚከሰሰው የኤርትራ ሠራዊት መሪ ወይም ከፍተኛ ባለሥልጣን በመሆናቸው ማዕቀቡ ተጥሎባቸዋል።

ሮይተር ተመልክቸዋለሁ ያለው የአውሮፓ ሕብረት የውስጥ ማስታወሻ፤ ኤርትራ የይገባኛል ጥያቄ በሚነሱባቸው ምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች ጦሯን አስፍራለች ይላል።

እንደ ሮይተርስ የዜና ወኪል ከሆነ የአውሮፓ ሕብረት የውስጥ ማስታወሻ፤ የኤርትራ ጦር አዲ ጎሹ እና ሑመራ ከተሞች አካባቢ "ታንክ እና ከባድ መሣሪያዎችን በመታጠቅ መከላከያ ቦታ ይዟል" ይላል።

ከዚህ በተጨማሪም ጠቅላይ ሚንሰትር ዐብይ አሕመድ ወደ ቱርክ ከማቅናታቸው ከአንድ ቀን በፊት ማለትም ነሐሴ 11 ወደ አስመራ ተጉዘው ነበር ይላል። ማስታወሻው ጠቅላይ ሚንሰትሩ ወደ አስመራ ስለማቅናታቸው ይፋ አለመደረጉን አስታውሷል።


በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተውበታል በሚባለው ጦርነት የኤርትራ ጦር ከፌደራሉ መንግሥት ጎን ተሰልፎ የህወሓት አማጺያንን ወግቷል።

የፌደራሉ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም አውጆ በርካታ የትግራይ ስፍራዎችን ለቅቆ ከወጣ በኋላ የህወሓት አማጺያን መቀለን ጨምሮ በርካታ የክልሉን ቦታ መቆጣጠራቸው ይታወሳል።

በመቀጠልም ህወሓት ያስቀመጠውን የተኩስ አቁም ቅድመ ሁኔታዎችን የፌደራሉ መንግሥት እንዲቀበል ለማስገደድ በሚል ምክንያት የህወሓት አማጺያን ወደ አፋር እና አማራ ክልሎች በመዝመት የተለያዩ ቦታዎችን መያዛቸው ይታወቃል።

የፌደራሉ መንግሥት ከክልል ኃይሎች ጋር በመሆን የህወሓት አማጺያንን ከያዟቸው ስፍራዎች ለማስለቀቅ ጥቃት እያደረገ እንደሆነ ተገልጿል።"

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube


"በምሥራቅ ወለጋ በተፈጸመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸው ተነገረ

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ ነሐሴ 12/2013 ዓ.ም ጀምሮ በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት እና ግጭት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ከጥቃቱ የተረፉ ነዋሪዎች እና የዞኑ አስተዳዳሪ ለቢቢሲ ተናገሩ።

ለደኅንነታቸው ሲባል ስማቸ እንዳይገለጽ የጠየቁ ነዋሪ ለቢቢሲ እንደገለጹት በአካባቢው መንግሥት ኦነግ ሸኔ እያለ የሚጠራቸው ታጣቂዎች ቀደም ብሎም እንደሚንቀሳቀሱ አስታውሰው፤ በነዋሪዎች ላይ ግድያውን የፈጸመው ይህ ታጣቂ ቡድን መሆኑን ይናገራሉ።

የአማራ ብሔር ተወላጅ የሆኑት ነዋሪው እንደሚሉት በስፍራው የነበረው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ከስፍራው መውጣቱን ተከትሎ ታጣቂዎች በነዋሪዎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ገልጸዋል።

"በነሐሴ 11 ልዩ ኃይሎቹ ከአካባቢው ወጥተው ኦነግ ሸኔ በ12 ወረራ ጀመረ። ከስፍራው የነበሩ በርካታ ሰዎች ተገድለዋል፤ ማንም የተረፈ የለም። ንጹሀን ተጨፍጭፈው ቀሩ። ንብረት ሁሉ ተቃጠሎ ወደመ" ይላሉ።

ነዋሪው በጥቃቱ የሞቱ ሰዎች በመቶዎች እንደሚቆጠሩ የተናገሩ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከ8 ሺህ በላይ ሰው ተፈናቅሎ በወረዳው ከተማ እንደሚገኝ አመልክተው "ለተፈናቃዩ ሕዝብ የደረሰ እርዳታ የለም" የለም በማለት በችግር ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል።

የምሥራቅ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ተስፋ ለቢቢሲ እንደገለጹት ከአምስት ቀናት በፊት በአካባቢው ግጭት እንደነበረ አረጋግጠው፤ ጉዳት የደረሰው "የጁንታው ተላላኪ በሆነው ሽፍታው ሸኔ እና በታጠቁ አማራዎች" ምክንያት ነው ብለዋል።

ጨምረውም "ጥቃቱን በዋናነት የሸኔ ሽፍታዎችና የጁንታው ተላላኪዎች ናቸው በኦሮሞና በአማራ ሕዝብ ላይ ተኩስ በመክፈት የፈጸሙት። ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የአማራ ታጣቂዎችም አሉ። አሁን ግጭቱ ቆሟል" ብለዋል።

"በዋናነት በኦሮሞ እና አማራ ሕዝብ ላይ ተኩስ የከፈተው ሽፍታው ሸኔ ነው። የታጠቁ የአማራ ታጣቂዎችም አሉ። ሁለቱ ሽፍታ ቡድኖች ናቸው በሁለቱ ብሔር ላይ ጉዳት ያደረሱት"

የአካባቢው አስተዳዳሪ አቶ አለማሁ እንዳሉት "በአሁኑ ወቅት የፀጥታ አካላት ገብተው እርምጃ እየወሰዱና ሕዝቡን እያረጋጉ ነው። እስካሁን ድረስ በግጭቱ የሞተውና የተጎዳው ሰው ቁጥር እየተጣራ ነው። ውጤቱ ሲደርስ እናሳውቃለን" ሲሉ ተናግረዋል።

በስፍራው ይንቀሳቀሳሉ ያሏቸው "ሽፍታው ሸኔ እና የአማራ ታጣቂዎች" የተኩስ ልውውጥ ማድረጋቸውን ተናግረው፤ "እነዚህ ሁለት ቡድኖች እርስ በእርሳቸው ተታኩሰዋል። ሕዝብም ላይ ተኩሰዋል" ብለዋል አስተዳዳሪው።

የሁለቱ ቡድን ዓላማ "ለብዙ ዓመታት አብሮ በሰላም የኖረን ብሔር ማጋጨት ነው" ያሉት አቶ አለማየሁ፤ በግጭቱ የሰዎች ሕይወት ማለፉን እና በርካታ ሰዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን አረጋግጠዋል።

በአሁኑ ወቅት በአካባቢው መረጋጋት መኖሩን እና ከቀያቸው የተፈናቀሉትን መልሶ ለማቋቋም የሚመለከታቸው ባለሥልጣናት ርብርብ እያደረጉ እንድሚገኙ አክለዋል።

ሌላኛው ያነጋገርናቸው ነዋሪ ደግሞ በአካባቢው በኦሮሞና በአማራ ተወላጆች መካከል ግጭት እንደነበር ተናግረው ጉዳት የደረሰውም በዚሁ ምክንያት ነው ብለዋል።

"በአማራ እና በኦሮሞ ማኅበረሰብ መካከል ግጭት ነበር። ከድሮ ጀምሮ የሚኖሩ የአማራ ማኅበረሰቦች ነበሩ። ከዚህ ቀደም በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ወደ ክልላቸው ከሄዱ በኋላ ሴቶች እና ሕጻናትን ትተው ወደ አካባቢው ተመልሰው በመምጣት እዚያ ከሚኖር የኦሮሞ ማኅበረሰብ ጋር ተጋጭተዋል" ይላሉ የኦሮሞ ብሔር ተወላጁ።

ነዋሪው ይህን ይበሉ እንጂ የዞኑ አስተዳዳሪ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ከአማራ ክልል ወደ አካባቢው የገባ ታጣቂ የለም።

"በማኅበራዊ ሚዲዎችያ ላይ ብዙ ነገር ይወራል። በተለያየ መንገድ ብሔሮች አንዲጣሉ ይደረጋል። ነገር ግን ከሌላ አካባቢ ገቡ ስለተባሉት ታጣቂዎች ምንም ማስረጃ የለም። ካለም ወደፊት እንናጣራለን" ብለዋል የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ አለማየሁ ተስፋ።

ቢቢሲ በጥቃቱ የደረሰውን ጉዳት ለማወቅ ባደረገው ሙከራ ከተለያዩ ወገኖች መጠኑ የተለያየ አሃዝ ያገኘ ሲሆን ነገር ግን በርካታ ቁጥር ያላቸው ሰዎች መገደላቸው ተገልጿል።

በንብረትም በኩል ቤቶች መቃጠላቸው የተነገረ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ደግሞ ከጥቃቱ ሽሽት ቤት ንብረታቸውን ትተው ወደ አቅራቢያ አካባቢዎች መሄዳቸው ተነግሯል።

መንግሥት ሸኔ የሚለውና በሽብርተኛነት የተፈረጀው እንዲሁም በቅርቡ ከህወሓት ጋር ጥምረት መፍጠሩን ያሳወቀው እራሱን የኦሮሞ ነጻነት ጦር አሁን ጥቃቱ በተፈጸመበት አካባቢ ታጣቂዎቹ ከዚህ በፊት ጥቃት መፈጸማቸው አይዘነጋም።"

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube


"ሳማንታ ፓወር ህወሓት ከአፋር እና አማራ እንዲወጣ ዳግም ጠየቁ

የአሜሪካ መንግሥት ዓለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤይድ አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓዎር ህወሓት ከያዛቸው የአማራ እና የአፋር ክልል አካባቢዎች እንዲወጣ ዳግም ጥሪ አቀረቡ።

ህወሓት ግጭቱን አቁሞ ከያዛቸው የአማራ እና የአፋር ክልል አካባቢዎች ወጥቶ ወደ ድርድር እንዲመጠ የመንግሥታቸው ፍላጎት መሆኑን ሳማንታ ፓወር በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።

"የህወሓት የሚፈጽመው ጥቃት ግጭቱን እንዲሁም የኢትዮጵያን ሕዝብ ስቃይ ያራዝማል" ብለዋል የተራድኦ ድርጅቱ ኃላፊ።

ከሁለት ወራት በፊት የፌደራሉ መንግሥት የተናጠል የተኩስ አቁም አውጆ ከትግራይ መዲና መውጣቱን ተከትሎ የህወሓት አማጺያን በርካታ የትግራይ ክልል ቦታዎችን ከተቆጣሩ በኋላ በመልሶ ማጥቃት ወደ አማራ እና አፋር ክልል ዘልቀው መግባታቸው ይታወሳል።

የህወሓት አማጺያን የፌደራሉ መንግሥት የተኩስ አቁም ጥያቄያቸውን እንዲቀበል ለማስገደድ እያደረጉ ያሉትን ጥቃት እንደማያቆሙ ገልጸው ነበር።

የአገር መከላከያ ሠራዊት ከክልል ኃይሎች ጋር በመሆኑ የህወሓት ኃይሎች በአማራ እና አፋር ክልል የያዟቸውን አካባቢዎችን ለማስለቀቅ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተጠናከረ ወታደራዊ እርምጃ እየወሰዱ መሆኑን የአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በተደጋጋሚ ተዘግቧል።

ሳማንታ ፓዎር በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሑፍ በህወሓት ጥቃት ከአፋር እና ከአማራ ክልሎች በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መኖሪያቸውን ለቀው እንዲወጡ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያም ዩኤስኤይድ በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸው 136ሺህ በላይ የክልሎቹ ነዋሪዎች የምግብ እርዳታ እያቀረበ መሆኑን ሳማንታ ፓዎር ገልጸዋል።


ይህ በእንዲህ እንዳለ ሳማንታ ባለፈው አርብ በትግራይ ክልል ጦርነት ከተቀሰቀሰ ከዘጠኝ ወራት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ የእርዳታ ድርጅቶች ለተረጂዎች የሚያቀርቡት ምግብ ሊያልቅባቸው እንደሆነ አስታውቀው ነበር።

ሳማንታ የየኤስኤይድ እና ሌሎች ድርጅቶች የእርዳታ ምግብ ማከማቻ መጋዘኖች ባዶ ናቸው በሚባል ደረጃ ላይ ይገኛሉ ብለው ነበር ባወጡት መግለጫ።

ይህ የእርዳታ ምግብ እጥረት የተከሰተው ምግብ ባለመኖሩ ምክንያት ሳይሆን "የአየርና የመንገድ እርዳታ አቅርቦት መስመሮችን ጨምሮ የእርዳታ አቅርቦትና የእርዳታ ሠራተኞችን ሥራ የኢትዮጵያ መንግሥት በማደናቀፉ ነው" ሲል ከሷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ውንጀላ ውድቅ አድረጎ ወደ ክልሉ አስፈላጊው እርዳታ እንዲደርስ አስፈላጊውን ሁሉ እያደረገ መሆኑን ነገር ግን በክልሉ ካለው የደኅንነት ስጋት አንጻር በተለያዩ ስፍራዎች የፍተሻ ጣቢያዎች በመኖራቸው ማንኛውም አካል በፌደራል መንግሥቱ የተቀመጠውን አሰራር መከተል እንዳለበት ገልጿል።"

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube


"በትግራይ ያለው የእርዳታ አቅርቦት ሊያልቅ መሆኑን ሳማንታ ፓወር ገለጹ

የአሜሪካ መንግሥት ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤይድ ኃላፊ ሳማንታ ፓወር በትግራይ ክልል ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ በነበሩት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የእርዳታ ድርጅቶች ለተረጂዎች የሚያቀርቡት ምግብ ሊያልቅባቸው እንደሆነ አሳወቁ።

በድርጅቱ ዋና ኃላፊ ሳማንታ ፓወር ስም በወጣው መግለጫ ላይ እንደተጠቀሰው በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ለረሃብ አደጋ በተጋለጡበት በትግራይ ክልል ውስጥ ያሉ የየኤስኤይድ እና ሌሎች ድርጅቶች የእርዳታ ምግብ ማከማቻ መጋዘኖች ባዶ ናቸው በሚባል ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ይህ የእርዳታ ምግብ እጥረት የተከሰተው ምግብ ባለመኖሩ ምክንያት ሳይሆን "የአየርና የመንገድ እርዳታ አቅርቦት መስመሮችን ጨምሮ የእርዳታ አቅርቦትና የእርዳታ ሠራተኞችን ሥራ የኢትዮጵያ መንግሥት በማደናቀፉ ነው" ሲል መግለጫው ከሷል።

ስለዚህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ለመታደግ የእርዳታ አቅርቦት በፍጥነት ወደ ትግራይ ክልል እንዲቀርብ የኢትዮጵያ መንግሥት በአስቸኳይ እንዲፈቅድ ጠይቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ዛሬ አርብ በሰጠው መግለጫ መንግሥት ሆን ብሎ እርዳታ እንዳይደርስ እያገደ ነው የሚለውን ውንጀላ ውድቅ አድርጎታል።

የጠቅላይ ሚኒስተሩ ፕሬስ ሴክሬታሪ በሰጡት ምላሽ በክልሉ ካለው የደኅንነት ስጋት አንጻር በተለያዩ ስፍራዎች የፍተሻ ጣቢያዎች መኖራቸውንና ማንኛውም ወደ ትግራይ ክልል ለመግባት የሚፈልግ አካል በፌደራል መንግሥቱ የተቀመጠውን አሰራር መከተል እንደሚኖበት ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት በአፋር ሰመራ ወደ ተግራይ የሚገቡ እና የሚወጡ የእርዳታ እህል የሚያጓጉዙ መኪኖችን በሚመለከት እየሰራ መሆኑን በመግለጽ የተፈጠሩ መስተጓጎሎች ካሉ በቀጣይ በሚኖር ውይይት እንደሚታዩ አመልክተዋል።

ባለፈው አንድ ወር ተኩል ውስጥ የተወሰነ መጠን ያለው እርዳታ ወደ ትግራይ እንዲገባ መፈቀዱን ያስታወሰው መግለጫው አሁንም የምግብ እርዳታ ጭነው ሰመራ አፋር ውስጥና በሌሎች የአገሪቱ ክፍሎች እየተጠባበቁ ያሉ ተሽከርካሪዎች እንዳሉም አመልክቷል።

በተጨማሪም በትግራይ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ እርዳታ ፍላጎት ለማሟላት በየቀኑ 100 ምግብና የነፍስ አድን አቅርቦቶችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ማቅረብ ቢቻል ኖሮ በሐምሌ ወር በአጠቃላይ እስከ አምስት ሺህ መኪኖች መግባት ይኖርባቸው እንደነበር ገልጾ እስከአሁን የቀረበው ግን በ320 መኪኖች የተጫነ እርዳታ ነው ብሏል።

መግለጫው ጨምሮ የኢትዮጵያ መንግሥት የተወሰነ መጠን ያለውን የምግብ አቅርቦት እንዲጓጓዝ በፍጥነት እንዲንቀሳቀስ ማድረጉን በአዎንታዊ መልኩ የጠቀሰው ቢሆንም አቅርቦቱ በጣም ትንሽና የዘገየ ነው ብሎታል።

የኢትዮጵያ መንግሥት የእርዳታ አቅርቦት ወደ ትግራይ ክልል እንዲገባ መፍቀዱን በተደጋጋሚ የገለጸ ሲሆን ቁጥጥር የሚያደርገው የጦር መሳሪያ ለአማጺያኑ እንዳይደርስ ለመከላከል ነው ብሏል።

በትግራይ ክልል በጥቅምት ወር ማብቂያ ላይ ጦርነት ተቀስቅሶ ለወራት ሲካሄድ ከቆየ በኋላ የፌደራል መንግሥቱ የተናጠል ተኩስ አውጆ ባለፈው ሰኔ ወር ሠራዊቱን ማስወጣቱ ይታወሳል።

ነገር ግን የህወሓት አማጺያን በአጎራባቾቹ የአፋርና የአማራ ክልሎች ውስጥ ጥቃት መሰንዘራቸውን ተከትሎ ጦርነቱ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ተስፋፍቷል።

በዚህም ሳቢያ በአማራና በአፋር ክልሎች ውስጥ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንዲፈናቀሉ በማድረግ ተጨማሪ ሰብአዊ ቀውስ ቀስቅሷል።

ሳምንታ ፓወር በመግለጫው ላይ የህወሓት ኃይሎች ጥቃት መፈጸማቸውን አቁመው ከገቡባቸው ክልሎች እንዲወጡ እንዲሁም የአማራ እና የኤርትራ ኃይሎችም ከትግራይ ክልል እንዲወጡ ጠይቀዋል።

የአሜሪካ መንግሥት ተራድኦ ድርጅት ዩኤስኤይድ ዋና ኃላፊ ሳማንታ ፓወር ከሁለት ሳምንት በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ ስላለው ጦርነትና የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ለመነጋገር ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸው ይታወሳል።"

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube


"በኢትዮጵያ አስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ ጠየቁ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ በሰሜን ኢትዮጵያ የሚካሄደውን ግጭት የሚያበቃ አስቸኳይ የተኩስ አቁም እንዲደረግ በድጋሚ ጥሪ አቀረቡ።

ኒው ዮርክ ውስጥ ለጋዜጠኞች የተናገሩት አንቶኒዮ ጉቴሬዝ እየተካሄደ ያለውና ወደ አጎራባች ክልሎች ለተስፋፋው ጦርነት ወታደራዊ መፍትሄ ሊገኝለት አይችልም ብለዋል።

ዋና ጸሐፊው "በአገሪቱ ውስጥ ለተከሰተው ቀውስ መፍትሄ ለመፈለግ በኢትዮጵያውያን የሚመራ ፖለቲካዊ ንግግር ለመጀመር የሚያስችል መላ መፈጠር አለበት" ብለዋል።

ጨምረውም "እንዲህ አይነቱ ንግግር ላጋጠመው ግጭት ምክንያት ለሆኑት ነገሮች መፍትሄ ለመፈለግ ከማስቻሉ በተጨማሪ ወደ ሰላም ለመሄድ የኢትዮጵያውያን ድምጽ እንዲሰማ ያስችላል" ሲሉ ተናገረዋል።

በትግራይ ክልል ውስጥ ከአስር ወራት በፊት ተቀስቅሶ አሁን ወደ አማራና አፋር ክልሎች የተዛመተው ጦርነት በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን ለመፈናቀል የዳረገ ሲሆን በርካቶች ደግሞ ችግር ላይ ጥሏል።

የመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሐፊ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ውስጥ ያለው ሁኔታ እጅግ በጣም አስከፊ የሆነ ደረጃ ላይ በመድረሱ የእርዳታ ድርጅቶች ድጋፍ እንዲያቀርቡ ያልተገደበ እንቅስቃሴ እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

ጉቴሬዝ ጨምረውም ከግጭቱ ጋር በተያያዘ በሴቶች ላይ የሚፈጸምን ወሲባዊ ጥቃት እንደ ጦር መሳሪያ ጥቅም ላይ መዋሉን አውግዘዋል።

በጥቅምት ወር መጨረሻ ላይ በተቀሰቀሰው ጦርነት ምን ያህል ሰዎች እንደሞቱ ባይታወቅም በርካቶች ህይወታቸው ሳያልፍ እንዳልቀረ ይታመናል።

የእርዳታ ድርጅቶች እንደሚሉት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውንና ሌሎች በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ደግሞ ለከፋ ረሃብ መጋለጣቸውን ሲገልጹ ቆይተዋል።

ከሰኔ ወር ማብቂያ ወዲህ ጦርነቱ ወደ አማራና አፋር ክልሎች ከተስፋፋ በኋላ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን ክልሎቹ አሳውቀዋል።"

┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈

𝐉𝐨𝐢𝐧👉 @Ummah_Tube

20 last posts shown.

4 309

subscribers
Channel statistics