Forward from: ስለ እውነት📢📢
ካለፈው #ስህተትህ ተማር ፥ የሚበጅህን #መዝን ያልተመዘነ ህይወት ትርጉም የለውምና ፥ አረማመድህን #መትር እግሮችህ በደመነነፍስ አይርገጡ። በዚኛው በአዲሱ በተሰጠህ ዘመን እንደ #ተርታው ሰው አታስብ ፥ አመለካከትህ ሳይለወጥ ዘመኑ ቢለወጥ በጳጉሜ 5 እና በመስከረም 1 መሀል ምንም ልዩነት አይኖረውም ከግርግር ፣ ከፌሽታ ፣ ከኪሳራ ውጪ። ከማሰብ መብላት መጠጣትን የህይወት ትርጉም ጣሪያ አድርገህ አትመልከት ፥ ቀን ቀን ነው ባይሆን በቀኑ #ታሪክ መስራት ነው ሲወርድ ሲዋረድ የመጣን ነገር በግርድፉ ከመቀበል ይልቅ። ከስሜት #አዋጅ ተላቀህ #ደስታን #ከአንዲት ቀን #ማዕቀፍ ውስጥ #አውጥተህ ለቀሪ #ዘመንህ ደስታ #መሥራት ፣ የበዓላት #ባሪያ ሳትሆን የአውዳመቶች #ገዢ ሁን ፣ #ከጊዜው ይልቅ #ጊዜውን አንተ #ግዛው ፡፡ #የድል ዘመኔ ነው ፥ #የከፍታ ዘመኔ ነው ፥ #የመሻገር ዘመኔ ነው ፥ #የመጠርመስ ዘመኔ ነው ከሚል #የምኞት አለም ውጣ። ነገርኩህ #አስተሳሰብህ ሳይለወጥ ምንም #ብታውጅ ህይወትህ #አይለወጥም ፣ ትርፉ ዕድሜ #መቁጠርና ኦክስጅን #ማጣበብ ብቻ ነው።
━━━━━⊱✿⊰━━━━━
♻️ @ewunetawu ♻️
🔱 @ewunetawu 🔱
━━━━━⊱✿⊰━━━━━
♻️ @ewunetawu ♻️
🔱 @ewunetawu 🔱