ቤተ ሊባኖስ ₃


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


የኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አስተምሮ ና ስርዓት የጠበቁ
👉 መንፈሳዊ መዝሙሮች
👉 መንፈሳዊ ትምህርቶች
👉 መንፈሳዊ ግጥሞች
👉 መንፈሳዊ ታሪኮች
👉 ምንፈሳዊ ምክር ነክ ፁፎች
👉 ንግሶች ስኖሩ እናሳዊቃለን
👉ለመናፍቃለ የተለያዩ መልሶችን እንሰጣለን
ግሩፕን ለመቀላቀል @zemariwochu3
ለተለያየ ጥያቄ ና @DA121922 ካላቹ አናግሩኝ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций




የአእላፋት መዝሙር ጥናት ተጀመረ!!!

እንዳልዘምር የሚከለክለኝ ምንድን ነው?

አዲስ የአእላፋት መርሙራት ተለቀዋል!

መዝሙሮቹን በቴለግራም ለማጥናት JOIN በሉ!

@yeaelafat_zmare


በቅርቡ ተከፍቶ የስንቱን ቀልብ 😱የሳበው የምንጊዜም ምርጡ  የኦርቶዶክስ ቻናል ❤️

እኔ ተቀላቅዬ ወድጄዋለው እናንተም ተቀላቀሉ ትወዱታላቹ❤️

https://t.me/+05s9XgAljNBiNDRk




'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>📌ሰው ሲወለድ ሙስሊም ነበር ይላሉ ሙስሊሞች በተጨማሪ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ«እኔ ጌታ ነኝ አምልኩኝ አላለም ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ተበርዞዋል ይላሉ» 'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>እንግዲህ ለእያንዳንዱ ከሙስሊም ለሚመጣ ጥያቄ አጥጋቢ መልስ ለማግኘት ከፈለጉ ይህን ቻናል ይቀላቀሉ።
የተበረዘው መፅሐፍ ቅዱስ ነው ወይ  ቁርአን ? አንድ ቅጂ ብቻ አለው ፍፁም ከፈጣሪ ነው ተብሎ በሙስሊሞች የሚታመነው በዚ በኛ ዘመን 4 ዓይነት ቅጂዎች አሉት'https://t.me/addlist/2CQ3e4ZJYT9hZGNk' rel='nofollow'>.....READ MORE


Репост из: ኦርቶዶክሳዊ ንድፍ ትዩብ
ገብርኤል ፲፱  👑

ኦርቶዶክሳዊ ንድፍ 🌟
@orthodox_graphics_tub
ሪያክት ማድረግ አይርሱ 👇


  📱 📱 📱


የመዳን ትምህርት
(ነገረ ድኅነት) ክፍል ~ 1
መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ነገረ ድኅነት ትምህርት እንዲህ ይላል ...

♦️ "የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥቷልና »፡፡ ሉቃ. 19፡10

♦️" . . . ከአብ ዘንድ የነበረውንም ለእኛም የተገለጠውን የዘላለምን ሕይወት እናወራላችኋለን፤ እርሱም የሰጠን ተስፋ ይህ የዘላለም ሕይወት ነው።" 1 ዮሐ. 1፡1-2 ፤ 2፡25

♦️"በዚህ የእግዚአብሔር ፍቅር በእኛ ዘንድ ተገለጠ፥ በእርሱ በኩል በሕይወት እንኖር ዘንድ እግዚአብሔር አንድ ልጁን ወደ ዓለም ልኮታልና።" 1 ዮሐ. 4፡9

♦️“ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” ዮሐ. 3፡16

♦️“ለእናንተም ስለሚሰጠው ጸጋ ትንቢት የተናገሩት ነቢያት ስለዚህ መዳን ተግተው እየፈለጉ መረመሩት፤ በእነርሱም የነበረ የክርስቶስ መንፈስ፥ ስለ ክርስቶስ መከራ ከእርሱም በኋላ ስለሚመጣው ክብር አስቀድሞ እየመሰከረ፥ በምን ወይም እንዴት ባለ ዘመን እንዳመለከተ ይመረምሩ ነበር።”1 ጴጥ. 1፡10-11

♦️"ኢየሱስም በዚህ መጽሐፍ ያልተጻፈ ሌላ ብዙ ምልክት በደቀ መዛሙርቱ ፊት አደረገ፤ ነገር ግን ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደ ሆነ ታምኑ ዘንድ፥ አምናችሁም በስሙ ሕይወት ይሆንላችሁ ዘንድ ይህ ተጽፏል።" ዮሐ. 20፡30-31

♦️"ከሕፃንነትህም ጀምረህ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን፥ መዳን የሚገኝበትን ጥበብ ሊሰጡህ የሚችሉ ቅዱሳን መጻሕፍትን አውቀሃል፡፡ » 1 ጢሞ. 3፡15

♦️“ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ፣ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።” ማር. 16፡15-16

♦️« . . . ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ » 1 ጴጥ. 1፡2-3

♦️"አንተ ግን ሕይወት ለሚገኝበት ትምህርት የሚገባውን ተናገር" ብሎታል። ቲቶ 2፡21

♦️“ጌታ ሆይ፣ ማን ነህ? አለው። እርሱም፦ አንተ የምታሳድደኝ እኔ ኢየሱስ ነኝ . . . አለው። እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀ ጌታ ሆይ፥ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ? አለው። ጌታም፦ ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሃል አለው።” የሐዋ. 9፡5-“አሁንም ወደ ኢዮጴ ሰዎችን ልከህ ጴጥሮስ የሚባለውን ስምዖንን አስመጣ። … ልታደርገው የሚገባህን እርሱ ይነግርሃል።” የሐዋ. 10፡5

ክፍል 2 ይቀጥላል


አጭር ተከታታይ ኮሪስ #ነገረ ድኀነት በምል በአንድ ሳምንት እንጨርሰዋልን በዚህ


. ቅዱሳን ማንን ይመስላሉ
#ቅዱሳኑ የሚመስሉት ክርስቶስን ነው ።
ቅዱሳኑን ልንቀበል : ልንመለከት : ልንሰማ : ልናይ : ልንመስላቸው ይገባል ።
#ቅዱሳን ነብያቱ የሚመስሉት ክርስቶስን ነው ።
#ቅዱሳን ሀዋርያቱ የሚመስሉት ክርስቶስን ነው ።
#ቅዱሳን ሰማእታቱ የሚመስሉት ክርስቶስን ነው ።
#ቅዱሳን መነኮሳቱ የሚመስሉት ክርስቶስን ነው ።
#ቅዱስ ጳውሎስ የሚመስለው ክርስቶስን ነው ።
#ቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት የሚመስሉት ክርስቶስን ነው::
#ቅዱስ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ የሚመስሉት ክርስቶስን ነው::
ስለኾነም እነርሱን መከተል ክርስቶስን መከተል ነው።
እነርሱን ማየት ክርስቶስን ማየት ነው
እነርሱን መስማት ክርስቶስን መስማት ነው ።
እነርሱን መምሰል ክርስቶስን መምሰል ነው ።
እኔ ጳውሎስ (ሳውል) ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ ይላል...
እኛም ይሄንን ያለማመንታት እና ያለማወላወል እንቀበለዋለን በዚህ ደግሞ መናፍቃኑ ይከሱናል
"ቅዱሳኑን አትመልከቱ ይላሉ"
"ቅዱሳኑን አትምሰሉ ይላሉ"
"ቅዱሳኑን አትከተሉ ይላሉ"
ይከሱናል ። ይወነጅሉናል ።
እውነት ክርስቶስ ስለሆነ
ቅዱሳን ነብያቱ ተነበዩለት
ቅዱሳን ሃዋርያቱ ሰበኩት
ቅዱሳን ሰማእታት ተሰውለት
ቅዱሳን መነኮሳት በፍቅሩ ተማርከው መነኑለት እነዚህ ሁሉ ህይወታቸው ክርስቶስ ነው። ታሪካቸው ክርስቶስ ነው ።
መጽሀፋቸው የክርስቶስ መጽሐፍ ነው ። ቃላቸው የክርስቶስ ቃል ነው።እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ሰርቷል በመሆኑም እነርሱን ማየት እነርሱን መከተል እነርሱን መስማት
ክርስቶስን ማየት መስማት መከተል ማለት ነው ።
ቅዱስ ጳውሎስ እኔ ክርስቶስን እንደምመስል [ እኔን ምሰሉ ]፡፡
1ኛ ቆሮ 11፥1 ያለው እኮ ለዚህ ነው
እንዲሁም በ ፊልጵስዩስ ሰዎች። 3:17
ወንድሞች ሆይ፥ [ እኔን የምትመስሉ ሁኑ ]፥ እኛም እንደ ምሳሌ እንደምንሆንላችሁ፥ እንዲሁ
የሚመላለሱትን ተመልከቱ በማለት ይገልጠዋል:: ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ይሄንኑ
በራሱ ቃል ሲያጸናው
"እናንተን [ ቅዱሳኑን] የሚቀበል እኔን ይቀበላል፤እኔንም የሚቀበል የላከኝን ይቀበላል።ነብይን በነብይ ስም የሚቀበል የነብይን ዋጋ ይወስዳል፥ፃድቅንም በፃድቅ ስም የሚቀበል የፃድቁን
ዋጋ ይወስዳል።ማንም ከእነዚህ ከታናናሾቹ ለአንዱ ጽዋ ቀዝቃዛ ውኃ ብቻ በደቀ መዝሙር ስም የሚያጠጣ እውነት እላችኃለሁ ዋጋው አይጠፋበትም።"(ማቴ.10:40-42) አለን
ስለዚህ
[ ቅዱሳንን ስንቀበል ]የምንቀበለው ክርስቶስን ነው ።
ለቅዱሳኑ የተሰጣቸው ክብር እጅግ ከፍ ያለ ነው ። ቤተ ክርስትያን ማነጽ እነርሱን ማሰብ መከተል እና መስማት ብቻም አይደለም የማቴዎስ የምሥራች ምእራፍ 19 ቁ 28 እንዲህ አለ ራሱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለተከተሉት ቅዱሳኑ ሲናገር
“እውነት እላችኋለሁ፤ በሚመጣው አዲስ ዓለም የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን ላይ
በሚቀመጥበት ጊዜ፣ እናንተም የተከተላችሁኝ በዐሥራ ሁለት ዙፋን ላይ ተቀምጣችሁ
በዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ላይ [ትፈርዳላችሁ]።በማለት ቅዱሳኑ ምን ያህል የላቀ እና የመጠቀ ክብር በአሁኑ ብቻ ሳይሆን በሚመጣውም ዓለም ጭምር እንዳላቸው አስረግጦ
ነው የተናገረው ።
ስለኾነም ክብር ለሚገባው ክብርን መስጠት ያስፈልጋል መፈራትም ለሚገባው እንዲሁ የሚገባውን መፈራት ማስረከብ ተገቢ ነው..
ለኹሉ የሚገባውን አስረክቡ ፣ ግብር ለሚገባው ግብርን ፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን ፤
መፈራት ለሚገባው መፈራትን ፤ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ፡፡(ሮሜ 13÷7)
ተብለናልና..
ይሄም ለቅዱሳን የሚሰጣቸው ክብር እና መታሰቢያ ለዘለዓለም የሚኖር ነው :: በመጪውም
ዓለም የሚቀጥል ነው የቅዱሳን እና የቅዱሳት ኑሯቸው ሕይወታቸው ፤ ክርስቶስ ነው እና በፍርድ ጊዜም አብረውት ይመጣሉ ።
የጻድቅ መታሰቢያ ለዘላለም ይኖራል:: (መዝ 111÷6)
አሜን አሜን አሜን ።


ከላይ እንደተገለጸው ተቃዋሚዎች "ውኃ" የተባለው ምሳሌያዊ እንጂ በቀጥታ አካላዊውን ውኃ አይደለም በማለት ተቃውሞን ያቀርባሉ። ውኃ ለመንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ሆኖ "በእኔ የሚያምን መጽሐፍ እንዳለ የሕይወት ውኃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል ብሎ ጮኸ። ይህ ግን በርሱ የሚያምኑት ሊቀበሉት ስላላቸው ስለ መንፈስ ተናገረ" ዮሐ. 7:38-39 ቀርቧል። ዳግመኛም "ውሃ አጠጪኝ የሚልሽ ማን መሆኑንስ ብታውቂ አንቺ ትለምኚው ነበርሽ የሕይወትም ውኃ ይሰጥሽ ነበር አላት..." ዮሐ. 4:10-14 ውሃ በምሳሌያዊ መልኩ ተገልጿልና "ከውሃና ከመንፈስ ያልተወለደ..." ሲልም ውኃ" የተባለው ቀጥታ ውኃ ለማለት  ሳይሆን ምሳሌያዊ ነው መንፈስ ቅዱስን ወይም ጌታን ነው የሚያመለክተው ይላሉ

ማስረጃ 2:-  በዮሐ. 3:5 ላይ "ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም።" የተባለው በውኃ ስለሚፈፀመው ጥምቀት እንጅ በምሳሌነት መንፈስ ቅዱስን ለማለት የተጠቀሰ አይደለም።

ይህን ለመረዳት ጌታችን ይህን ለኒቆዲሞስ ሲነግረው "ውኃ" የተባለው በውኃ ስለሚፈጸመው ጥምቀት  ውጪ  ሌላ ትርጉም ቢኖረው ኖሮ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ  አብራርቶ በጻፈልን ነበር። ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌሉን ሲጽፍ የተሳሳቱ ወይም ግራ የሚያጋቡ ሃሳቦች ሲኖሩ አስተካክሎ አርሞ ያልፋል እንጂ እንዲሁ አይተወውም። "...እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር" ዮሐ. 2:19-21፤ "...ስለ አብ እንደ ነገራቸው አላስተዋሉም።" ዮሐ.8:25-27 "እንቅልፍ ስለመተኛት የተናገረ መስሏቸው ነበር" ዮሐ. 11፡13:: "የአትክልት ጠባቂ መስሏት ነበር" (ዮሐ. 21፡33)  በማለት አብራርቶ ስሕተትም ካለ አርሞ የሚጽፍ ሐዋርያ ነው።

ስለዚህም ከላይ 'ውኃ' የተባለው "መንፈስ ቅዱስ" ቢሆን ኖሮ በዮሐ. 7:37-39 ላይ እንደሰፈረው አብራርቶ ይጽፍልን ነበር።
በዮሐ. 7:38 ላይ "የሕይወት ውሃ"  የተባለው መንፈስ ቅዱስ መሆኑን አብራርቶ ገልጾ ነበርና።

ማስረጃ 3:-
በዮሐ. 3:5 ላይም የተጻፈው በቀጥታ በውኃ ስለሚፈጸመው ጥምቀት ባይሆን ኖር አብራርቶ ይገልጸው ነበር። "በውኃና በመንፈስ"  የተባለው በቀጥታ በውኃ ስለመጠመቅ እንጂ ስለ መንፈስ ቅዱስ ምሳሌ ሆኖ አለመቅረቡን ለመረዳት:-

1ኛ.  በዮሐ. 4:10-14 እና በዮሐ. 7:38-39 ላይ የሕይወት ውኃ (living water) እያለ ሲናገር በዮሐ. 3:5 ላይ ግን "ውኃ" በማለት ብቻ ነው የተባለው። ስለ መንፈስ ቅዱስ ሲናገር የሕይወት ውሃ እያለ ሲገልጸው በዮሐ.3:5 ላይ ደግሞ "ውኃ" ብቻ በማለት ምሳሌያዊ እንዳልሆነ ያስረዳናል።

2ኛ. በዮሐ. 4:10-14 እና በዮሐ. 7:37-39 ላይ በውኃና በሕይወት ውኃ (living water) መካከል በማነጻጸር ሲያስቀምጥ በዮሐ. 3:5 ግን እያነጻጸረ አልገለጸም ምክንያቱም "በውኃና በመንፈስ" በማለት የተገለጸው ምሳሌያዊ ሳይሆን በቀጥታ በውኃ ጥምቀት የሚፈጸመውን የሚያመለክት ነውና።

3ኛ. "በውኃና በመንፈስ" የተባለው ላይ "ውኃ" የተባለው ዮሐ. 7:38-39 ላይ "የሕይወት ውኃ" ተብሎ እንደተገለጸው መንፈስ ቅዱስን ለማመልከት ቢሆን ኖሮ "እና" በሚል አያያዥ ቃል ባልተጠቀመ ነበር። ምክንያቱም ውኃ የተባለው መንፈስ ቅዱስ ቢሆን ኖሮ "በውኃና በመንፈስ" በማለት አይገልጽም ነበር። ድግግምሽ ይሆናልና። ይልቁኑ በውሃና በመንፈስ የተባለው በጥምቀት የመንፈስ ቅዱስ ልጅነትን የምናገኝበትን የሚያመለክት ቃል ነው።


✍ ተክለ ማርያም

https://t.me/zemariwochu3


ጥያቄ :- ጌታችን በወንጌል "ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር የእግዚአብሔርን መንግስት ሊያይ አይችልም።" ዮሐ. 3:5 ያለው ምሳሌያዊ እንጂ  ጥምቀትን አይደለም የሚሉ አሉ፦

መልስ

👉 ውሃና ከመንፈስ መወለድ የተባለው በጥምቀት የእግዚአብሔር ልጅ መሆንንና ለመዳን የሚያስፈልግ መሆኑን የሚያመለክት ነው። እግዚአብሔር የሰጠንን ጸጋ ለመቀበል በጥምቀት የእግዚአብሔር ልጆች ሆነን ካልተወለድን በስተቀር  ከእናት ከአባት በተወለድነው ተፈጥሮአዊና ሥጋዊ ልደት መንፈሳዊና ሰማያዊ የሆነውን የእግዚአብሔርን መንግስት ለመውረስ አንችልም።

ሐዋርያትና ከሐዋርያት የተማሩ ቅዱሳን ሊቃውንት ያስተማሩት በጥምቀት ዳግም ልደት መንግስቱን መወረስ የሚያስችል ምስጢር እንደሆነ ነው።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ጥምቀት መንግስተ ሰማያት የሚያስወርስ ምስጢር እንደሆነ ሲገልጽ "ለማያምኑት አልቅሱላቸው የጥምቀትን ማሕተም ሳያገኙ ለሞቱት አልቅሱላቸው። እነርሱ ከመንግስተ ሰማያት ውጪ ናቸውና ልናለቅስላቸው ይገባናል። ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ  በስተቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም" ተብሏልና።" [ትርጓሜ ፊልጵስዩስ
ክፍለ ትምሕርት 3]

ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌምም "ማንም ሰው ካልተጠመቀ በቀር መዳንን አያገኝም፣ በውኃ ሳይሆን በደማቸው ከተጠመቁ ከሰማዕታት በስተቀር። ጌታችን ዓለምን በመስቀሉ ባዳነ ጊዜ ጎኑን ተወጋ ያን ጊዜም ደምና ውኃ ከጎኑ አፈለቀልን። ይህም በሰላም ጊዜ የሚኖሩ ሰዎች በውኃ ይጠመቁ ዘንድ በስደትና በመከራ ጊዜ የሚኖሩ ሰዎች ደግሞ በደማቸው ይጠመቁ ዘንድ ነው።..."።[ በእንተ ጥምቀት ትምሕርት 3 ቁ.10] ብሏል።"

👉 ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም" የሚለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል ይዘው ውኃው የተባለው ጥምቀት ሳይሆን በተቃዋሚዎች ዘንድ አንዳንዶቹ ውኃው ምልክት (symbolic) ነው ሌሎቹ  የእምነት ማጽኛ ነው ሌሎቹም የእግዚአብሔር ቃል ነው  የእምነት መመስከሪያ [አንዳንዶቹም ውኃ የተባለው ምሳሌያዊ ሲሆን መንፈስ ቅዱስን ያመለክታል ይላሉ።] በማለት ይተረጉማሉ።

ማስረጃ 1:-ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ በመድሎተ ጽድቅ መጽሐፉ ይህን አስመልክቶ "በተቃዋሚዎች ዘንድ ርስ በርሳቸው እንኳ ይህ ሁሉ የአረዳድ ልዩነት የተፈጠረው ግን ሁሉም አንብቦ መተርጎም ይችላል በሚል የተሳሳተ ትምህርታቸው የተነሳ ነው። ይህን የጻፈልን የወንጌላዊው ቅዱስ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር የነበረው የቅዱስ ፖሊካርፕስ ደቀ መዝሙር ቅዱስ ሄሬኔዎስ "እኛ በኃጢአት ምክንያት አካላችን የተቆማመጠብን እንደመሆናችን የእግዚአብሔርን ስም በመጥራትና በተቀደሰው ውኃ በመጠመቅ ከክፉ በደሎቻችን ሁሉ እንነጻለን፤ አዲስ እንደተወለዱ ሕጻናትም በመንፈሳዊ ልደት ዳግመኛ እንወለዳለን ራሱ ጌታችንም እንዲህ ብሎ እንደተናገረ፦ "እውነት እውነት እልሃለሁ ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም።" ዮሐ 3:5 (ቅሬታት፣ 34)

ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ደቀ መዝሙሩን ቅዱስ ፖሊካርፕስን ያስተማረው እንደዚህ ነበር። ቅዱስ ሄሬኔዎስም ከመምህሩ ከቅዱስ  ፖሊካርፕስ እግር ሥር ቁጭ ብሎ የተማረው ይህንኑ ነበር፣ በተግባር ያየውም እንደዚህ ነበር። ስለዚህ ቅዱስ ሄሬኔዎስም ሆነ ሌሎቹ ክርስቲያኖች ሁሉ የተረዱት ጌታችን በውኃ መጠመቅ ለዳግመኛ ልደትና መንግሥተ ሰማያት አስፈላጊ ነው ያለ መሆኑን ነው።በኒቂያውና በቁስጥንጥንያው የእምነት መግለጫ አንቀጽ ላይም "ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀት እናምናለን።" ተብሎ የተገለጸው ከእነርሱ በፊት ከነበሩ አባቶችና እነዚያም ከሐዋርያት፣ ሐዋርያት ደግሞ ከጌታ የተቀበሉት አተረጓጎምና አረዳድ ነው። ከዚህ የቤተ ክርስቲያናዊ አረዳድ የወጡና መጽሐፍ ቅዱስን በራሳችን መንገድ እንተረጉመዋለን የሚሉ ፕሮቴስታንቶች ግን ከዚህ ተቃራኒ የሆነ ነገር ይዘው ብቅ በማለት አንዳቸው ትክክለኛው ይኸኛው ነው፣ ሌላቸው ደግሞ እርሱ ሳይሆን እንደዚህ ነው እያሉ ሁሉም የራሳቸውን ግምት በሰዎች ላይ ለመጫን ይደክማሉ። (መድሎተ ጽድቅ ቅጽ 2. ገጽ 99)


ይቀጥላል...

✍ ተክለ ማርያም


📌 ያሳደገን የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓል ደረሰ!
ዘክረን ለበረከት እንረባረብ። በዓይነት፣ በጉልበት በገንዘብ በማገዝ የአቅምዎን ያድርጉ።
ለበለጠ መረጃ :-0987166180
0953125078

Your account
አሑዱ ባንክ #0065068310101 DAGNE  LEMU AND AZEB GEBREMICHAEL
ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000438455632

ቴሌ ብር 0953125078 Emebet tekle


🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲🌲
ቅዱስ ኒቆላዎስ (የገና አባት)
🎉🎊🎉🎊🎉🎊🎉🎊🎊🎉🎊🎊

🌷የገና አባት (ቅዱስ ኒቆላዎስ) ለድኆች ሥጦታ ይለግስ የነበረ ቅዱስ አባት ነው። ታሪኩም በስንክሳር ታኅሣሥ 10 ላይ ተጽፎአል። "የገና ዛፍ ባሕላችን አይደለም እነርሱ ክረምታቸውን የሚያስታውሱበት ነው ከእኛ ጋር አይገጥምም" "የተወለደውን ክርስቶስ የበዓሉ ማዕከል እንዳናደርግ ያደርገናል" ማለት ትክክለኛ ነገር ነው። Pagan Origin (የባዕድ አምልኮ መነሻ) አለው ብሎ ጣዖት አምልኮ ነው ማለት ግን ከገደብ ያለፈ ድምዳሜ ነው።

☀️በከዋክብት ያመልኩ የነበሩት የጥበብ ሰዎች በሚያመልኩት ነገር ወደ ክርስቶስ ተጠርተዋል ፣ የዙሐል ጣዖት ይከበርበት የነበረውን ዕለት ከክርስትና በኋላ በእስክንድርያ የቅዱስ ሚካኤል በዓል ቀን ሆኗል።

🌿የራሳችንን የገና ባሕላዊ አከባበሮች የገና ጨዋታን ፣ ቀጤማ መጎዝጎዝ የመሳሰሉትን ማክበር ይገባናል። ከዚያ ውጪ በክርስትና መንፈስ እስከተቃኘና የጌታን በበረት መወለድ ፣ የሰብአ ሰገልን ጉዞ ፣ ከዋክብቱን ፣ የመላእክትን ዝማሬ ፣ የእረኞችን ደስታ ፣ የሰብአ ሰገልን እጅ መንሻ የሚያሳይ እስከሆነ ድረስ የኛ ባሕል ያልሆነውን ሁሉ ጣዖት ነው ብሎ ማንቋሸሽ ፣ የሚያምር ነገርን ሁሉ ማውገዝ ያስመስላል። ቅዱስ ኒቆላስም የኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የምትዘክረው ቅዱስ ስለሆነ አጋጣሚውን ጻድቁን ለማስተዋወቅም ልንጠቀምበት ይገባል።

🌲ሥጦታም የምንሠጣጠው የሰብአ ሰገልን ሥጦታ መነሻ አድርገን ሲሆን ልግስናውን ለነዳያን ብናደርገው የበለጠ በረከት እንቀበልበታለን።

ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ


👉 አስተማሪ

ዶክተሩ በድንገት ተደውሎለት ለአስቸኳይ የቀዶ ህክምና በጥድፊያ ወደ ሆስፒታሉ እየገባ ነው።

በተቻለው አቅም የስልክ ጥሪውን በአግባቡ አስተናግዷል። የህክምና ልብሱን በአስቸኳይ ቀይሮ ወደ ቀዶ ጥገና ክፍል እያመራ ሳለ ኮሪደሩ ላይ የዶክተሩን መምጣት እየተንጎራደደ ይጠብቀው የነበረውን ሰው አገኘው።

"እንዴት ለመምጣት ይህን ያህል ግዜ ይፈጅብሀል? የልጄ ህይወት ልትጠፋ አደጋ ላይ እንዳለች አይታይህም? ህሊና የለህም?" ብሎ ዶክተሩ ላይ ጮኸበት።

ዶክተሩም በትንሹ ፈገግ አለና ,,,,
"አዝናለሁ ሆስፒታል ውስጥ አልነበርኩም። የስልኩን ጥሪ ከተቀበልኩ በሗላ በቻልኩት ፍጥነት እዚህ ለመድረስ ጥሬያለሁ አሁን አንተም ብትረጋጋ እኔም ስራዬን ብሰራ መልካም ነው" ብሎ ሊያረጋጋው ሞከረ።

ሰውየው ግን ,,,
"ተረጋጋ ነው ያልከው? ያንተ ልጅ ቢሆንስ አሁን እዚህ ክፍል ውስጥ ሆኖ ትረጋጋ ነበር? ልጅህ ቢሞት ምን ታደርግ ነበር?" አለ አባት በቁጣ።

ዶክተሩ አሁንም በትንሹ ፈገግ አለና እንዲህ መለሰለት
"የአምላክ ፈቃድ ይሁን። ዶክተር ህይወት ሊያራዝም ሊያጠፋም ሊተካም አይችልም ግን የቻልነውን ያህል እንጥራለን። እንደ አምላክ ፍቃድ ልጅህም ይድንልሀል አንተ ብቻ ተረጋጋ" አለው አሁንም ፈገግ እያለ።

ሰውየውም ,,,
" ባልገቡበት ጭንቀት አስተያየትና ምክር መስጠት ቀላል ነው" እያለ አጉረመረመ። ቀዶ ጥገናውም የተወሰነ ሰዓታትን ወስዶ በሰላም ተጠናቀቀ ዶክተሩ በደስታ እየተጣደፈ ከቀዶ ጥገናው ክፍል ውስጥ ወጣ።

ለአባትየውም ,,,,
"ፈጣሪ ይመስገን ልጅህ ተርፏል።" ብሎት የአባትየውን መልስ ሳይጠብቅ "ማንኛውም ጥያቄ ካለህ ሌሎች ረዳት ዶክተሮችን መጠየቅ ትችላህ።" ብሎት ዶክተሩ መንገዱን በሩጫ ቀጠለ።

የልጁም አባት "ለምንድነው ዶክተሩ እንደዚህ ስሜታዊና ችኩል የሆነው? ምናለ አሁን አንድ ደቂቃ ስለ ልጄ ሁኔታ ብጠይቀው?" ሲል ተናገረ።

ይህን የሰማችው ነርስ እንባ በጉንጮቿ እየጎረፈ ,,,,
"ትላንት ነበር የዶክተሩ ልጅ በመኪና አደጋ የሞተው። ለልጅህ ህክምና ስንደውልለት የልጁ ቀብር ላይ ነበር አሁን ያንተን ልጅ ህይወት ታደገ የራሱን ልጅ ደግሞ የቀብር ስርዓት ሊጨርስ በሩጫ ሄደ።" አለችው።

አባት ከሰዓታት በፊት ዶክተሩ ያሳየውን ፈገግታ እያሰበ ተንሰቀሰቀ። የፀፀት ለቅሶ

አንድ ሰው ምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንዳለ ሳታውቅ
ለመፍረድ አትቸኩል

"ቀድሞ መፍረድ ለህሊና ፀፀት ይዳርጋል"
https://t.me/Abalibanos333


#ለምንድነው_መኖር_የደከመህ??
.
ለምን መኖር ደከመህ? ለምን ህይወት ድግግሞሽ ሆነብህ? ለምን ራስህን ለማጥፋት ወሰንክ? በስደት ስላለህ? በህመም ስለሆንክ? ያሰብከው ስላልተሳካ? ያመንከው ስለከዳህ? አሞታለሁ ብለህ ለምን ታስባለህ? አበቦች ሲፈኩ እንደሚደርቁ ያውቃሉ፡፡ ግን እደርቃለሁ ብለው ሳይፈኩ አይቀሩም፡፡ ሰውም ሟች ነው ግን ሟች ነኝ ብሎ መተው የለበትም፡፡ ሁሉም ሰው በየመስኩ ያብብ፡፡ ወዳጄ እፅፍልሀለው አንተ አላስፈልግም ትላለህ እንጂ ያላንተ የማይሆኑ ብዙ ነገር አለ

☞ያላንተ የማይሞቅ ቤት አለ፡፡
☞ያላንተ የማይሳካ ህልም አለ፡፡
☞ያላንተ የማያምር ጨዋታ አለ፡፡
☞ያላንተ የማይደምቅ ቤት አለ፡፡
☞ያላንተ የማይነበብ ፅሁፍ አለ ይኸው ስላለህ ይህንን አነበብክ ታስፈልገናለህ፡፡

ይህቺ አለም ትልቅ ዳመራ ናት አንተ በዳመራው ስር ያለህ አንድ ችቦ ነህ አንተ ስትጠፋ የዳመራው ብርሀን ይቀንሳል፡፡ የቻልከውን ያህል ብራ አንተ ከነገሮች በላይ ነህ፡፡ በነገሮች አትረበሽ፡፡ እደግመዋለሁ ህይወት ልክ እንደ ክራር ጨዋታ ነው፡፡ አጨዋወቱን ያወቀ ጥሩ ሙዚቃ ይሰማል ያላወቀ ደግሞ ዝብርቅርቅ ጩኸቷን ለመስማት ይገደዳል፡፡ አሁንም እልሀለው ህይወት በደመነፍስ አትሄድም ስልቷን እወቀው፡

፡ በህይወትህ ትላንት ያለፈውን መጥፎ ህይወትህን መቀየር ማስተካከል መሰረዝ አትችልም፡፡ የምትችለው አምኖ መቀበልና ለተሻለ ነገ መስራት ነው፡፡ "መቀየር የማንችለውን ነገር መቀበል ማለት ተስፋ መቁረጥ ወይም መሸነፍ ማለት ሳይሆን አቅማችንን የምንችለው ነገር ላይ ማዋል ማለት ነው::"
በፍፁም ተስፋ አትቁረጥ ግን አቅምህን የምትችለው ነገር ላይ አውለው፡፡ ሳትኖር ለመሞት አትቸኩል ይሄ ማለት ሳትፅፍ ለማጥፋት መሞክር ማለት ነው፡፡

ለኔ ና ለእናተ

https://t.me/Abalibanos333


ከሰይጣን በቀር ምንም ጠላት አይኑርህ፡፡የሰዎችን ስህተት አትመራመር፤ የባልንጀራህ ኃጢአት አትግለጥ፡፡ የባልጀራህ ውድቀት ደጋግመህ አታውራ፡፡ በራስህ ኃጢአት ላይ ፍረድ እንጂ በሌሎች ላይ አትፍረድ ገዢያቸው አይደለህምና፡፡ኃጢአትን በፈጸመ ሰው ላይ ወቀሳ አታብዛ አንተም ትበድላለህና፡፡ ነገር ግን ከኃጢአቱ ይመለስ ዘንድ ረዳትና መካሪ ሁነው፡፡ ከወደቀበትም የስህተት ሥራ እንዲወጣ አበርታው፡፡ ተስፋውን በእግዚአብሔር ላይ ቢያደርግ ኃጢአቱን ልክ በእሳት ፊት እንደወደቀ ገለባ ፈጥኖ እንደሚወገድለት ንገረው፡፡

ቅዱስ፣ ጥንቁቅ፣ ግልጽና ብልህ ሁን፡፡ እርጋታን የተላበሰ ሰብእና ይኑርህ፡፡ ደስተኛ ሁን፤ ሰላምታህ በፈገግታ የታጀበ ንጹህ ይሁን፡፡ ንግግርህ የታረመ አጭርና በጨው እንደተቀመመ ጣፋጭ ይሁን፡፡ ቃላቶችህ የተመጠኑ እና ጤናሞች ሁሉም የሚረዳቸው ይሁኑ፡፡የጓደኛህን ምስጢር አትግለጥ፤ ለሚወዱህ ሁሉ የታመንክ ሁን፡፡ ወደ ጭቅጭቅ እና ንትርክ ከመግባት ራህን ጠብቅ፡፡ የሚሰሙህ ሁሉ እንዳይጠሉህ ወደ ጠብ አትግባ፡፡

(የምክር ቃል ለኔ ና ለእናተ)


✞በሦስተኛ ዓመቷ✞

በሦስተኛ ዓመቷ ታኅሣሥ ሦስት ዕለት(፪)
የገባችው ድንግል መቅደሰ ኦሪት(፪)

ዓለም ሳይፈጠር በአምላክ ልቦና
በሥላሴ ዙፋን በክብር ተሥላ
ድንግል ማርያም በቅድመ ሕሊና
ለእኛ ለአዳም ልጆች ታስባለችና
አዝ= = = = =
ሐናና ኢያቄም አምላክን ለምነው
በጾምና ጸሎት ብዙ ተፈትነው
ልጅ እንዲሰጣቸው ዘወትር ሲመኙ
በመልአከ ብሥራት ድንግልን አገኙ
አዝ= = = = =
መልአኩ ፋኑኤል ከአምላክ ተልኮ
ሰማያዊ መና ለድንግል አቅርቦ
የጸጥታ መጠት እንድትጠጣ ብሎ
ያገለግላታል ውዳሴን አቅዶ
አዝ= = = = =
ሐርና ወርቅን ተፈትላ አስጊጣ
በቤተ መቅደሱ መጽሐፉን ገልጣ
ስታገለግል በትህትና ሆና
ቃል ሥጋ ሆነ በእርሷ አደረና

መዝሙር
ቴዎድሮስ አለማየሁ

"ልጄ ሆይ ስሚ እዪ ጆሮሽንም አዘንብዪ ወገንሽን የአባትሽን ቤት እርሺ"
መዝ ፵፭፥፲
https://t.me/zemariwochu3

👉✍ @DA121922


✞ #ታህሳስ_ወር_የንግስ_በዓላት ✞

ማክሰኞ ታህሳስ 1 - የነብዩ ኤልያስ ልደቱ - በእንጦጦ እና በጎፋ ገብርኤል

ሐሙስ ታህሳስ 3 - ባዕታ ማርያም ወደ ቤተ መቅደስ የገባችበት ቀን
                      -ቅዱስ ፋኑኤል - በዓለም ባንክ
      _በአያት መሪ ቅዱስ ፋኑኤል
                      -ዜና ማርቆስ - በጣፎ

እሁድ ታህሳስ 6 - ቅድስት አርሴማ ቅዳሴ ቤቷ - የቅድስት አርሴማ ታቦት ባለበት

ማክሰኞ ታህሳስ 8 - አባ ኪሮስ ልደታቸው - አለምባንክ ጀሞ ተራራ መድኃኔዓለም ቤ/ክ - በጣፎ

ረቡዕ 9 - እስትንፋሰ ክርስቶስ ልደታቸው - በቦሌ ቡልቡላ ዋሻ ተክለሃይማኖት

አርብ 11 - ቅዱስ ያሬድ - ጎተራ አጎና ሲኒማ ፊት ለፊት

ቅዳሜ ታህሳስ 12 - አባ ሳሙኤል እረፍታቸው - በአቃቂ አባ ሳሙኤል ቤተ ደናግል ገዳም ፣ በቦሌ ቡልቡላ አባ ሳሙኤል እና በሲኤሚሲ ሚካኤል

እሁድ ታህሳስ 13 - ቅዱስ ሩፋኤል ቅዳሴ ቤቱ - በሸጎሌ

ረቡዕ ታህሳስ 16 - ፍቅርተ ክርስቶስ ቃልኪዳን የተቀበለችበት እለት - በአንቆርጫ መድኃኔዓለም ከፈርንሳይ ጉራራ ኪዳነምህረት ቤተክርስቲያን ጋር ባጃጅ እና ታክሲ አለ የአንቆርጫ

ቅዳሜ ታህሳስ 19 - ቅዱስ ገብርኤል - ሶስቱን ህፃናት ያዳነበት

ማክሰኞ ታህሳስ 22 - ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን አምላክን በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እደምትወልድ ያበሰረበት - በብስራተ ገብርኤል

ሐሙስ ታህሳስ 24 - አቡነ ተክለሃይማኖት - ልደታቸው

ሰኞ ታህሳስ 28 - ቅዱስ አማኑኤል - የልደቱ መታሰቢያ - በመሳለሚያ

ማክሰኞ ታህሳስ 29 - ባለወልድ - የኢየሱስ ክርስቶስ የልደቱ መታሰቢያ በዓል - በ4 ኪሎ ባለወልድ ቤተክርስቲያን - በለቡ መብራት አብርሃም ገዳም

✞ መምጣት የማትችሉ #Share በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ ✞

         https://t.me/zemariwochu3


✝ "የበቃሁ ነኝ" የሚባለው መቼ ነው?

በአንድ ገዳም ውስጥ የሚኖር መነኩሴ ነበር። ከገዳሙ አበምኔት ጋርም ስለመንፈሳዊ ሕይወታቸው እያነሱ ሲወያዩ " አባቴ እኔ ዛሬ የዓለምን ኋጢአት ግፍና በደል አየሁ፡፡ ስለዚህ የበቃሁ ሆኛለሁ።" ብሎ አጫወታቸው፡፡ አበምኔቱም " ወንድሜ ሆይ እስቲ በርትተህ ጸልይ ፥ገና ነህ።" ብለው መለሱለት።

እንዲሁም በሌላ ግዜ ወደ አበምኔቱ ቀርቦ " አባቴ አሁንስ በቅቻለሁ ቅዱሳን መላእክት ከሰማይ ሲወጡና ሲወርዱ የሕዝቡንም ኋጢአት ሲያስተርዩ አይቻለሁ።" አላቸው። " ልጄ ሆይ ገና ነህ፥ አሁንም በርታና ጸልይ።" ብለው ሸኙት፡፡ ይህም መነኩሴ ወደ ዋሻው ገብቶ ኣብዝቶ ይጾምና ይጸልይ ጀመር። ይህም መነኩሴ ወደ ዋሻው ገብቶ አብዝቶ ይጾምና ይጸልይ ጀመር። ለሶስተኛ ጊዜ ስላየውም ራእይ ለአበምኔቱ እንዲህ ሲል ገለጠላቸው፡፡ " አባቴ ሆይ ዛሬስ በዓለም ሳለሁ የሰራሁትን ኋጢአት ሁሉ አንድ በአንድ አሳየኝ።" አላቸው እርሳቸውም " ልጄ የበቃኸው አሁን ነው።" ብለው አሰናበቱት።

ክርስቲያናዊ ሕይወት ምድራዊ ፍላጎቶችንና የሰይጣን ሸንገላ በመቃወም ሰማያዊ መንግስት የሚወረስበት ምስጢር በመሆኑ ፈተናውን የዛኑ ያህል ከበድ ይላል። ብዙ ሰዎች ወደ ቤተ ክርስቲያን መመላለስ ቃለ #እግዚአብሔር መማር ሲጀምሩ የራሳቸው ኋጢአት እያሰቡ ከማልቀስ እና ንስሓ ከመግባት ይልቅ የሌላውን በደል መቁጠር ይጀምራሉ፡፡ " እነ እገሌ እንኳን እንዲህ አደረጉ ጉድ ነው!" ማለት ያበዛሉ። ሌላውን ሲመለከቱ ሊዱኑበት የሚችሉበትን ወርቃማ የንሰሓ ጊዜ በኮንቱ ያበላሹታል። መጽሓፍ ግን "ለዚህ ዓለም ከማይመችና የአረጊቶችን ሴቶች ጨዋታ ከሚመስለው ተረት ራቅ"(1ኛ ጢሞ 4 ፡ 7) ይላል። ይህ መነኩሴ የተገለጠለት ራእይ ለመዳኑ የጠቀመው የራሱን ኋጢአት ያየ ጊዜ መሆኑን ከታሪኩ መረዳት እንችላለን፡፡ እኛስ የሚታየን የማን ኋጢአት ነው? የራሳችን ወይስ የሌላው?


🍃🍃የአባቶች ምክር 🍃🍃
✅‼ ልጄ ሆይ ፤ ዋዘኛና ቀልደኛ አትሁን ፡፡ በመከራ ለሚኖሩ ሰዎች ሁሉ የምታዝንና የምትራራ ሁን ፤ በድኃ ላይ አትጨክን ፤ ርስቱንና ቤቱንም በምክንያት አትውሰድበት ፤ ለመጨረስም የማትችለውን ነገር አትጀምር ፡፡

✅‼ ልጄ ሆይ ፤ በልተህ ስትጠግብ ረኃብን ፤ ስትበለጥግ ድኅነትን ፤i ስትሾም ሽረትን ፤ ሌላውንም ይህን የመሰለውን ሁሉ አትርሳ ፡፡

✅‼ ልጄ ሆይ ፤ ለሞተው ወዳጅህ ከማልቀስ ይልቅ በሕይወቱ ሳለ የክፋት ሥራ ለሚሠራ ወዳጅህ አልቅስለት ፡፡

✅‼ ልጄ ሆይ ፤ ባለ ጠጋ ሰው ሁሉ ይደግፈዋል ፤ ድኃ ሲወድቅ ግን ሰው ሁሉ ወዲያው ይገፋዋል ፡፡ ባለ ጠጋ ሲከሰስ በሸንጎ የተቀመጠው ሁሉ ይሟገትለታል ፤ ድሀ ሲከሰስ ግን በሸንጎ የተቀመጠው ሁሉ ይፈርድበታል ፡፡ መልካም ዳኛ በመካከላቸው የተቀመጠ እንደ ሆነ ግን ፍርዱ እንደ ፀሐይ ያበራለታል ፡፡ ስለዚህ በምትኖርበት ሀገር መልካም ዳኛ አያጥፋብህ ፡፡

✅‼ ልጄ ሆይ ፤ በማናቸውም ነገር ቢሆን ሞት አይቀርም ፡፡ ነገር ግን በሰው እጅ ከመውደቅ በእግዚአብሔር እጅ መውደቅ ይሻላል ፡፡

✅‼ ለአፍህ መሐላ አታልምደው ፤ እግዚአብሔር ስሙን ከንቱ ያደረገውን ሳይቀስፈው አይቀርምና ስሙን በከንቱ አትጥራ ፡፡ ልጄ ሆይ ፤ የምትሠራውን ሥራ ሁሉ ሰው ቢያየው ቢሰማውም አይጎዳኝም ብለህ እንደ ሆነ ነው እንጂ አይታይብኝም ፤ አይሰማብኝም ብለህ አትሥራው ፡፡ አንተ ምንም ተሰውረህ ብትሠራው ከተሠራ በኋላ መታየቱና መሰማቱ አይቀርም ፡፡

✅‼ ልጄ ሆይ ፤ አንተ አስቀድመህ በሰው ላይ አትነሣ ፤ ሰው በአንተ ላይ ቢነሣብህ ግን እንዳትሸነፍ ጠንክረህ መክት ፡፡ እምነትህንም በእግዚአብሔር ላይ አድርግ ፡፡

✅‼ ልጄ ሆይ ፤ ሰው ሳይኖር ብቻህን ከሴት ጋር አትነጋገር ፡፡ ባሏ አለመኖሩን በደጅ ጠይቀህ ከደጅ ተመለስ እንጂ ወደ ቤት አትግባ ፡፡ ሰው ሳይኖር ብቻህን ከሴት ጋር የተነጋገርህ እንደ
ሆነ ግን ፤ ምንም ሌላ ምስጢር ባይኖራችሁ በመነጋገራችሁ ብቻ መጠርጠር አይቀርም ።

✅‼ ልጄ ሆይ ፤ በጌታህም ቤት ቢሆን በሌላም ስፍራ ቢሆን ገንዘብ ወይም ሌላ እቃ ወድቆ ብታገኝ አታንሣ ፡፡ ብታነሣውም መልሰህ ለጌታህ ወይም ለዳኛ ስጥ እንጂ ሰውረህ አታስቀር ፡፡

✅‼ ልጄ ሆይ ፤ በፍፁም ልብህ ለማትወደው ሰው ቤትህንና የቤትህን ዕቃ አታሳይ ፡፡

✅‼ ልጄ ሆይ ፤ ንፁሕ አለመሆንህን እግዚአብሔር ያውቃልና በእርሱ ፊት ንፁሕ ነኝ አትበል ፡፡ በንጉሥ ፊትም ብልህ ነኝ አትበል ፤ የብልሃት ሥራ ሠርተህ አሳየኝ ያለህ እንደ ሆነ ታፍራለህና ፡፡

✅‼ ልጄ ሆይ ፤ ጠላት በዛብኝ ፤ ምቀኛ አሴረብኝ ብለህ እጅግ አትጨነቅ ፡፡ በዓለም የሚኖር ፍጥረት ሁሉ ጠላትና ምቀኛ አለበት እንጂ ባንተ ብቻ አይደለም ፡፡ ከዚሁም በጥቂቱ
እጽፍልሃለሁ ፡፡ በፍየል ነብር ፤ በበግ ተኩላ ፤ በአህያ ጅብ ፤ በላም አንበሳ ፤ በአይጥ ድመት ፤ በዶሮ ጭልፊት አለባቸው ፡፡

ይህንንም የመሰለ ብዙ አለ ፡፡ ሰውም እርስ በርሱ እንዲሁ ነው ፡፡ ስለዚህ የሚመጣብህን ነገር ሁሉ በትእግሥት ሆነህ ተቀበለው ፡፡ በመጨረሻው ግን ሁሉ አላፊ ነውና ጠላቶችህ ሁሉ ያልፋሉ ፡፡ ወይም አንተ አስቀድመህ ታልፍና ከዚህ ዓለም መከራና ጭንቀት ታርፋለህ ፡፡

✅‼ ልጄ ሆይ ፤ እስቲ ያለፉትን ሰዎች ሁሉ አስባቸው ፡፡ እነዚያ ሁሉ ጀግኖች ሁሉም መሬት ሆነዋል ፡፡ እነዚያ ሁሉ ዓለመኞች ፤ እነዚያ ሁሉ ቀልደኞችና ፌዘኞች ፤ እነዚያ ሁሉ ግፈኞች ፤ እነዚያ ሁሉ በድኃ ላይ የሚስቁና የሚሳለቁ ሁiሉም መሬት ሆነዋል ፡፡ እነዚያ ሁሉ ድሆች ሲበደሉ ፣ ሲያዝኑ ፣ ሲያለቅሱ ካንዱ ሀገር ወደ ሌላው ሀገር ሲሰደዱ ፣ ሲራቡ ፣ ሲጠሙ ፣ ሲታረዙ የነበሩ መሬት ሆነዋል ፡፡

✅‼ ስንት ሰዎች የነበሩ ይመስልሃል ? የድኃ እንባ ሲፈስ የወንዝ ውኃ የሚፈስ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ ፡፡ ድኃ ሲጮህ ውሻ የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ ፡፡ ድኃ ታስሮ ወይም በሌላ ጭንቅ ነገር ተይዞ ሲሞት የወፍ ግልገል የሚሞት የሚመስላቸው ስንት ሰዎች ነበሩ ፡፡ ጉልበት ካለን ብለው በደካሞች ላይ ያሰቡትን ሁሉ የሚሠሩ ስንት ሰዎች ነበሩ ፡፡

✅‼️ሰውን ለማጥፋት እጅግ የሚጥሩ ሰውን ካላጠፉ እንቅልፍ የማይወስዳቸው ስንት ሰዎች ነበሩ ፡፡ ነገር ግን ከዚህ ቀድሞ የነበሩት ሁሉም መሬት ሆነዋል ፡፡ ከመሬት የተገኘ ሁሉ መሬት ስለ ሆነ ወደ መሬትም የማይመለስ ስለሌለ እኛም ነገ እንደዚያው እንሆናለን ፡፡ ስለዚህ በማናቸውም ምክንያት & የሰው ደስታውና አዘኑ እጅግ አጭር መሆኑን



ለኔ ና ለእናተ

2k 0 40 1 12
Показано 20 последних публикаций.