አዲስ የተዋሕዶ መዝሙር


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ አሜን።
#አዲስ_የተዋሕዶ_መዝሙር
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ አስተምህሮና ስርዓትን የጠበቁ ያሬዳዊ መዝሙሮችን እና ወረባትን ከነዜማቸው ለማግኘት ቻናላችንን ይጎብኙ።
እንዲሁም አዳዲስ የሚወጡ የኦርቶዶክስ መዝሙሮችን በትንሽ ሜጋባይት በዚህ ቻናል ያገኛሉ
#ሼር በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ🙏

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций


#ወረት_የሌለው

ወረት የሌለው መውደድ
ወረት የሌለው ፍቅር
አንተ ጋር ብቻ ነው
ያለው እግዚአብሔር /2/
#አዝ

ዘመን የማይዘው ጊዜ የማይገድበው
ያንተ ፍቅር ብቻ ቀን በቀን አዲስ ነው
ከዴማስ ጋር ስሄድ ትቼው የአንተን መንገድ
ከቶ መች ቀነሰ ለእኔ ያለህ መውደድ
#አዝ

በአመጽ ብጠፋም ከመንጋህ መካከል
ይመሻል ይነጋል እኔን ስትከተል
እንደወጣ ይቅር ብለህ መቼ ተውከኝ
ሴኬም ድረስ ወርደህ ልጅህን ፈለከኝ
#አዝ

በዝናዬም ዘመን ባለጸጋ እያለሁ
ቤቴ በወዳጆች ቀን በቀን ሙሉ ነው
እንደ ጤዛ ሲረግፍ ሃብትና ንብረቴ
ያላንተ ማን ነበር በፈርሰው ቤቴ
#አዝ

የታመንኩባቸው ወዳጆች ሲከዱኝ
ሕመሜ ስር ሆነው ደጋግመው ሲወጉኝ
ላንተ ጊዜ ባጣም ለኔ ጊዜ አለህ
ገፋህ ክፉ ቀኔን ከኔ ጋራ አብረህ

📥ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች📥
            •ሼር // SHARE
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#ልቤ_ያውቀዋል

ልቤ ያውቀዋል ያደረክልኝን ነገር
የሰራህልኝን ስራ
መድኃኔዓለም አወጣኝ ከመከራ
በቃል ጉልበት አይወራ

መስቀል ተሸክመህ በደም ርሰህ
እኔን በመከራ ዳግም ወልደህ
በክብር ተሻገርኩ ክሰህልኝ
በሕይወት አቆምከኝ ወድቀህልኝ /2/

አዝ=====



የበደሌን ጋራ አቀበቱን
የባርነት ሰነድ እዳ ክሱን
አጥፍተኸው ጌታ መዳን ሆነ
እርቃኔ በእርቃንህ ተሸፈነ /2/

አዝ=====



በፍቅርህ መዓዛ ረክቷል ልቤ
በማይቆም መውደድህ ተከብቤ
የሕይወቴ ወደብ መስቀልህ ነው
ወጀብ እና ነፋስ የማይነቅለው /2/

አዝ=====


የእሾህ አክሊል ደፍተህ ኤልሻዳይ
እፎይ አለ ልቤ ከስቃይ
ሆኖልኛል መዳን አንተ ታመህ
ነጻ ወጣው ሸክሜን ተሸክመህ /2/

   
አዝ=====


ዙፋንህን አስተወህ የእኔ ፍቅር
ከሰማይ ሀገርህ መጣህ ከምድር
ታየ ስትፈልገኝ ልጄ ብለህ
ፈራጅ እና አጽዳቂ አምላክ ሆነህ
  ..................................................
📥ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች📥
            •ሼር // SHARE
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


#በልዕልና

በልዕልና ያለ በልዕልና
ዓለቴ የነፍሴ ዋስትና
አንተ ነህ ጉልበቴ መታመኛዬ
እግዚአብሔር ኃይሌ መከታዬ

#አዝ

በለመለመ መስክ የምታሰማራኝ
ከእረፍቱ ውኃ የምታጠጣኝ
እርካታዬ መኖርያ አገሬ
ታመሰግናለች ነፍሴ በዝማሬ
#አዝ

የምታመንብህ መደገፈያዬ
ከጠላቴ ቀስት መሸሸጊያዬ
ያለኸልኝ የማላጣህ ዕድሌ
ልዘምር ልቀኝ ላመስግንህ ሁሌ
#አዝ

ሰማይ ነው ዙፋንህ መረገጫህ ምድር
የደስታዬ ምንጭ ምስጉን ክብር
ዝም አልልም ዘወትር አዜማለሁ
ባንተ ተማምኜ መች አፍሬ አውቃለሁ
#አዝ

በለመለመ መስክ የምታሰማራኝ
ከእረፍቱ ውኃ የምታጠጣኝ
እርካታዬ መኖርያ አገሬ
ታመሰግናለች ነፍሴ በዝማሬ

📥ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች📥
            •ሼር // SHARE
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


እንኳን ለአስተርእዮ ማርያም መታሰቢያ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን

✍️"ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ"

❖ ሞት ለሚሞት ሁሉ የተገባ ነው፤ የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል።

📚ነግስ ዘቅዱስ ያሬድ ማህሌታይ)

🕯@Addis_Mezmure 🕯
   🕯@Addis_Mezmure 🕯


#እንግዲህ_ምን_ልበል

እንግዲህ ምን ልበል
እንግዲህ ምን ላውራ
እጄን በአፌ አስጫነኝ
የአማኑኤል ስራ
#አዝ

በሞት ጥላ ምድር ያሳለፈኝ መርቶ
ደግሞም ዛሬ አነሣኝ በልጁ ሞት ጠርቶ
ክብሬን ለማይረባ ነገር አልለውጥም
ከአመድ ስላነሳኝ ክብሩ ለዘለዓለም
#አዝ

የሺሖርን ውኃ ለምን እጠጣለሁ
ፊቴን የማዞረው ምን አግኝቼበት ነው
ሁልጊዜ እየራራ ሳይዘነጋኝ ላፍታ
እኔ የዓይኑ ስስት እርሱ የኔ ርካታ
#አዝ

ስለምን ሆምጣጣ ፍሬ አፈራ ብለህ
እኔ አልተነቀልኩም ስለፍጹም ፍቅርህ
ቢቀላ እንዳለላ ነጣ እንደባዘቶ
የተከፋው ልቤ ሄደ ተደስቶ
#አዝ

ከወዜ ላይ ቀለብ ምናልባት ቢሰፍሩ
ወራቶቼ እንባን መከራን ቢያዘሩ
ልቤን ያስነከሰው ያ ቀን አለፈና
የበፍታዬን ኤፋድ ለበስኩ እንደገና

📥ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች📥
            •ሼር // SHARE
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️
    ❤️ @Addis_Mezmure ❤️


📥ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች ሼር በማድረግ እንተባበር 📥
            •SHARE
https://t.me/Addis_Mezmure/5576
https://t.me/Addis_Mezmure/5576





























Показано 20 последних публикаций.