Addis Admass


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


የአዲስ አድማስ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
=====
አዲስ አድማስ https://bit.ly/2V1zyZQ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2V0I6jx
ትዊተር↠ https://bit.ly/33fDhaP
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/2JgeCvG
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3q2hXiv
የእርስዎና የቤተሰብዎ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ይህ ቤተመንግስተ በሚገባው መንገድ ታድሶ ለህዝብ እይታ ክፍት እንዲሆን ሲወስኑ የቤተ መንግስቱን ታሪካዊና ህያው ፋይዳ እንዲሁም ቅብብሎሽ ከፍ አድርገው መገንዘባቸውን ያሳያል ብለዋል፡፡

ታሪክ በቤተ መንግስት ካዝና ውስጥ ተቆልፎ የሚቀመጥ ሳይሆን ክፍት ሆኖ የምናየው የምናነበው የምንማርበት የምናደንቀው፣ ከዛሬ ፍላጎታችን ጋር አስማምተን ዛሬ በምንና እንዴት መገንባት እንዳለብን የምንረዳበት ነው ሲሉም አመላክተዋል፡፡

ዛሬ ዳግመኛ የተወለደው ይህ ቤተ መንግስት ለታሪካችን ድንቅ ምስክር ብቻ ሳይሆን ከፍ ያለ የቱሪስት መህስብ ፣ የዲፕሎማቲክ ተግባራት መከወኛ፣ የባህል ልውውጥ ማዕከል፣ የውይይትና ትብብር መድረክ ሆኖ እንደሚያገለግል እምነት አለኝ ብለዋል፡፡

መጪው ትውልድ ከቀደሙት ሰዎች ውርስ ጋር የሚገናኝበት የታሪክ ሀብልና ሰንሰለት ነው ያሉት ፕሬዚዳንት ታዬ፤ ይህንን እውን ለማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ላደረጉት አስተዋጽኦ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በቤተ መንግስቱ ዕድሳት መንግስታቸው ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።

(ፋና ዲጂታል)


”ብሔራዊ ቤተ መንግሥት የድላችንና የውጣ
ውረዶቻችን ድርሳን የሚነበብበት መጽሐፍ ነው”



ብሔራዊ ቤተ መንግሥት ከፍ ያለ ኪናዊ ጥበብ የተላበሰ ህንጻ ብቻ ሳይሆን የታሪካችን መድበል፤ የተጋድሏችን የፈተናዎቻችን፣ የድላችንና የውጣ ውረዶቻችን ድርሳን የሚነበብበት መጽሐፍ ነው ሲሉ የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቱ በብሔራዊ ቤተ መንግስት የምረቃ መርሀ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር፤ በዚሁ ቤተ መንግሥት የዲፕሎማሲና የውጭ ግንኙነት መስተጋብር ጎላ ብሎ ይታያል ብለዋል።

የቆምንበት ስፍራ ከንጉሰ ነገስታዊ ስብሰባዎች እስከ ውስብስብ የዲፕሎማሲ ድርድሮች ድረስ ያረፈበት አሻራ ዛሬም ይታያል ሲሉ ገልጸዋል።

የቤተ መንግሥቱ አዳራሽ በርካታ የአፍሪካ መሪዎችንና ተጽእኖ ፈጣዎችን አስተናግዷል ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ አፍሪካ የመጀመሪያው አህጉራዊ ተቋም እንዲኖራት ያስቻለው በዚህ አዳራሽ የተደረገ ውይይት ነው ሲሉም አስታውሰዋል፡፡

ይህ ለትውልድ የሚተርፍ ቅርስ ተጠብቆ ሲቆይ በኢትዮጵያ ታሪክ መዝገብ ውስጥ ዘመን ተሻጋሪ የረጅም ጊዜ ቅርስ የመጠበቅ ባህል እንዳለን ማሳያ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡


በመክፈቻው ላይ በተደረገው የፓናል ውይይት፣ የኢንዱስትሪው ባለድርሻ አካላት፣ ለሪል ስቴት ዘርፉ እድገት እንቅፋት የሆኑ በርካታ ተግዳሮቶችን ያነሱ ሲሆን፤ ከእነዚህም መካከል የረጅም ጊዜ የብድር አገልግሎት ህግ አለመኖርን ጨምሮ ውስን የፋይናንስ አማራጮችን በተግዳሮትነት ጠቅሰዋል፡፡

ኤክስፖው በመላ ኢትዮጵያ የቤትና የከተማ ልማትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ትብብር ያለውን ጠቀሜታ አፅንዖት ሰጥቶ ተወያይቶበታል፡፡


በፓናል ውይይቱ ላይ ከተሳተፉት የዘርፉ ባለድርሻ አካላት መካከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግሥትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ሃላፊ አቶ ዘሪሁን አምደማርያም፣ የካፒታል ገበያ ከፍተኛ አማካሪ አቶ አሰፋ ሱምሮና የኢኮኖሚ ባለሙያው አቶ ዘመድነህ ንጋቱ ይገኙበታል፡፡

ኢትዮጵያ በቤት ልማት ዘርፍ እያሳየች ያለውን ዕድገት ተከትሎ የግሉ ዘርፍ የሚኖረውን ሚና ለማሳደግ እንዲረዳ ታስቦ በ251 ኮሚዩኒኬሽንና ማርኬቲንግ ኃ.የተ.የግ.ማህበር መዘጋጀት የጀመረው ኢቲ ሪል እስቴትና ሆም ኤክስፖ፤ የሪል እስቴት አልሚዎችን ከቤት ባለቤቶች፣ ከገዢዎች፣ ከሻጮችና ከንግዱ ማሕበረሰብ ጋር የሚያገናኝ ኤግዚቢሽን ነው ተብሏል፡፡


7ኛው የሪል እስቴትና የቤት ኤክስፖ ለ3 ቀናት ተካሄደ


• ለሪል እስቴት ዘርፉ ዕድገት ውስን የፋይናንስ አማራጮች በተግዳሮትነት ተነስተዋል


7ኛው ዓመታዊ የሪል እስቴትና የቤት ኤክስፖ ባለፈው አርብ ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል “የሪል እስቴት የወደፊቱ እጣፈንታ” በሚል መርህ የተከፈተ ሲሆን፤ በኤክስፖው ላይ በተደረገ ውይይት ለሪል እስቴት ዘርፉ ዕድገት ውስን የፋይናንስ አማራጮች በተግዳሮትነት ተጠቅሰዋል፡፡

ለሦስት ቀናት በተካሄደውና ትላንት እሁድ በተጠናቀቀው በዚህ ኤክስፖ ላይ ሴንቸሪ ሪል እስቴት፣ ፊሶን ሪል እስቴት፣ ዲኤምሲ ሪል እስቴትና አሚባራ ፕሮፐርቲስን ጨምሮ በርካታ የሪል እስቴት አልሚዎች ተሳትፈውበታል፡፡

የሪል እስቴትና የቤት ኤክስፖው ከፍተኛ አልሚዎችን፣ ባለሃብቶችን፣ የፋይናንስ ተቋማትን፣ የቤት ገንቢዎችንና የቤተ- ውበት ባለሙያዎችን ጨምሮ የሪል እስቴትና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ከፍተኛ ባለድርሻ አካላት በአንድ ላይ ያሰባሰበና ያገናኘ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡




አርቲስት ጌትነት እንየው
አምነው የወደዱ፣
ወደው የተካዱ፣
ተክደው የራዱ፣
ፍርሃት አንሸራቶ ቁልቁል የጣላቸው፣
የብቸኛ ልቦች የትነው መውደቂያቸው?
የትነው መድረካቸው?
ማነው አጃቢያቸው?
እንዴት ነው ምታቸው?
የተካዱ ልቦች አጋር የራቃቸው፣
የሚያቀነቅኑት ምንድን ነው ዜማቸው?
የተመረኮዙት እምነት ታጥፎባቸው፣
ድንገት የወደቁ ፍቅር ያዳጣቸው፣
ሚስጥር የሚያጋሩት ሰው የበረዳቸው፣
ብቸኝነት ሰርጎ ብቻ ያስቀራቸው፣
ዝምተኛ ልቦች ምን ይሆን ቋንቋቸው?
ከየት ነው ጥሪያቸው?
በየት ነው ጉዟቸው?
የት ነው መድረሻቸው?
እንደ ሰብአሰገል ጠቅሶ የሚመራቸው፣
የቃተቱ ልቦች የታል ኮከባቸው?
መቼም ከአምላክ ትንፋሽ ከውሃ ከአፈሩ፣
ከእምንት እና እውነት ከፍቅር ሲሰሩ፣
ዝምተኛ ልቦች ጥንቱን ሲፈጥሩ፣
ተገፍትረው ወድቀው፣
ደቀው እንዳይቀሩ፣
በተስፋ ጸንተው ነው ዘላለም ሊኖሩ።


በሲዳማ ክልል በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ71 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በሲዳማ ክልል ምስራቃዊ ዞን ቦና ዙሪያ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ71 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሽመልስ ቶማስ ለፋና ዲጂታል እንዳሉት ፣ አደጋው አይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ሰርገኞችን ጭኖ ሲጓዝ በቦና ዙሪያ ወረዳ ጋላና ወንዝ ድልድዩን ስቶ ወደ ወንዝ በመግባቱ ነው የተከሰተው።

በዚህም እስካሁን የ71 ሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልጸው ፥ጉዳት የደረሰባቸው ዜጎች በቦና አጠቃላይ ሆስፒታል ሕክምና እየተከታተሉ ነው ብለዋል ።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም ኮሚሽነሩ አመልክተዋል።




በደቡብ ኮሪያ በተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ የሟቾች ቁጥር 179 ደረሰ
****************

በደቡብ ኮሪያ 181 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ በነበረ አውሮፕላን ላይ በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር 179 መድረሱ ተገልጿል።

አውሮፕላኑ 175 መንገደኞችን እና 6 የሚሆኑ የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ ከታይላንድ ባንኮክ ወደ ደቡብ ኮሪያ ሙአን ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ሲሞክር መከስከሱ ተጠቅሷል።

ከተከሰከሰው አውሮፕላን ውስጥ የአደጋ ሠራተኞች ሁለት ሰዎችን በሕይወት ማግኘታቸው ተመላክቷል፡፡

ደቡብ ኮሪያ በተከሰተው የአውሮፕላን አደጋ ህይወታቸውን ላጡ ሰዎች የሰባት ቀናት ብሔራዊ ሀዘን ማወጇም ተጠቅሷል።

የአውሮፕላኑ የበረራ መረጃ መመዝገቢያ ሳጥን (ብላክ ቦክስ) መገኙቱና የአደጋ መንስኤውን ለማጣራት ምርመራ መቀጠሉም ተነግሯል።

የሟች ቤተሰቦች በአውሮፕላን ማረፊያው አዳራሽ ውስጥ ተሰብስበው አስከሬን እስኪታወቅ እየጠበቁ ሲሆን፤ ህይወታቸው ካለፉ ሰዎች መካከል የተወሰኑት በጣት አሻራቸው ብቻ መለየታቸው ተጠቁሟል።

እንደ ቢቢሲ ዘገባ አደጋ የደረሰበት ይህ አውሮፕላን ጀጁ የተባለ አየር መንገድ ንብረት የሆነ ቦይንግ 737-800 መሆኑ ተጠቅሷል፡፡


የግጥም መድበል እየተሸጠ ነው - ይዘዙን!

በዘውዴ አለልኝ የተጻፈው ‹‹ጊዜን መሸከም›› የተሰኘ የግጥም መድበል ለንባብ በቃ። መድበሉ 54 ግጥሞችን የያዘ ሲሆን በ162 ገጾች የተቀነበበ ነው፡፡

የመጽሐፉ ቅርጽ በዋሽንት አውታረ ቅኝት የተሠራ ሆኖ በጥቁር፣ ሰማያዊ፣ ሐምራዊና ነጭ ቀለማት የተከፋፈለ ነው። ቀለማቱ ከኢትዮጵያ ባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያዎች ዋሽንት፣ ክራር፣ ነጋሪትና ሞረሽ ከምትባል ወፍ ጋር የተቀነባበረ ነው። እያንዳንዱ ክፍል ቀለማዊና ሙዚቃዊ ፍካሬ መግቢያ አለው።

የግጥም መድበሉ ታትሞ ለሽያጭ ተዘጋጅቷል፡፡ መጽሐፉን ለመግዛት የምትፈልጉ በኦንላይን ይዘዙን፡፡ ዋጋው ለአገር ውስጥ 350 ብር ሲሆን፣ ለውጭ ሀገር በ20 ዶላር ተተምኗል።


የባንክ ሂሳብ ቁጥር...
አቢሲኒያ ባንክ ( bank of abyssinia) 200869327 ዘውዱ አለልኝ አራገው ( zewdu alelgn aragaw)

ዳሽን ባንክ (Dashen bank) 5472769396011 ዘውዱ አለልኝ አራጋው ( zewdu alelgn aragaw)

ንግድ ባንክ (CBE ) 1000298476936 (Daniel abreha) ዳንኤል አብርሃ

ቴሌ ብር / tellebirr፦ 0913240885 zewdu alelgn

እባክዎ ክፍያ የፈጸሙበትን የባንክ ደረሰኝ Screenshot አድርገው፣ ወይም ፎቶ አንስተው በዚህ የቴሌግራም ሊንክ @Gizienmeshekem2424 ይላኩልን፡፡


አሚጎስ ከ101 ሚሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

• የማህበሩ ጠቅላላ ሃብት ከ1 ቢ.ብር በላይ ደርሷል


አሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የህብረት ሥራ ማህበር፣ በ2016 በጀት ዓመት በአጠቃላይ 145 ሚሊዮን ብር ማትረፉንና ከ101 ሚሊዮን ብር በላይ የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

የማህበሩ አባላት የትርፍ ክፍፍል ድርሻ 53 በመቶ ነው ተብሏል፡፡

የህብረት ሥራ ማህበሩ ይህን ያስታወቀው ዛሬ ታሕሳስ 19 ቀን 2017 ዓ.ም፣ 11ኛ የባለአክስዮኖች ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በኢንተር ላግዠሪ ሆቴል ባካሄደበት ወቅት ነው፡፡

የማህበሩ አባላት በተገኙበት ለግማሽ ቀን በተካሄደው በዚህ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የ2016 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻፀም ሪፖርት የቀረበ ሲሆን፤ በዚህ ወቅትም የአሚጎስ ጠቅላላ ሃብት ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱ ተነግሯል፡፡

አሚጎስ በዛሬው ጉባኤው የኅብረት ስራ ማህበሩን ጠቅላላ ጉባኤ ተወካዮች የመረጠ ሲሆን፤ በቀጣይ ያቀዳቸው ሰፋፊ ስራዎችም ቀርበዋል።


የዛሬ 12 ዓመት በሦስት ዓይን ገላጭ መሥራቾች ተጀምሮ ዛሬ ወደ 10ሺ የሚጠጉ አባላትን ያፈራው የህብረት ሥራ ማህበሩ፤ ወደ 3 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ አጠቃላይ ካፒታል ያለው ሲሆን፤ ከ120 በላይ ሰራተኞች ይዞ በተለያዩ የክልል ከተሞች ቅርንጫፎቹን በማብዛት ተደራሽነቱን እያሰፋ እንደሚገኝ ከማህበሩ የተገኘ መረጃ ይጠቁማል፡፡


ኤልያስ መልካ የቅንብር አሻራውን ያሳረፈበት አልበም ሊወጣ ነው

አንጋፋው የሙዚቃ ባለሙያ ኤልያስ መልካ የቅንብር አሻራውን ያሳረፈበት የድምጻዊ አብርሃም በላይነህ (አብርሃም ሻላዬ) “ቀን በቀን” የተሰኘ አልበም ሊወጣ መሆኑ ተነግሯል። በአልበሙ ወጣትና አንጋፋ ባለሞያዎች እንደተጣመሩበት ተጠቅሷል።

የፊታችን ታኅሳስ 22 ቀን 2017 ዓ.ም. በድምፃዊው የዩቱዩብ ቻናል ለአድማጭ በሚደርሰው በዚሁ አልበም ላይ፣ የዚህ ትውልድ ቀለም የሆኑት ኤልያስ መልካና ሚካኤል ሃይሉ (ሚኪ ጃኖ) በላቀ ደረጃ በሙዚቃ ቅንብር የተጣመሩበት ሲሆን፤ ወንደወሰን ይሁብ፣ መሰለ ጌታሁን፣ ናትናኤል ግርማቸውና አንተነህ ወራሽን የመሳሰሉ የግጥምና ዜማ ሞያተኞች በአልበሙ ላይ ተሳትፈዋል።

“ቀን በቀን” አልበምን ሰርቶ ለማጠናቀቅ 9 ዓመታትን እንደፈጀ ተነግሯል።

ከአስራ ሦስት ዓመታት በፊት ለሙዚቃ አድማጮች ባደረሰው “ሻላዬ” የተሰኘ ባሕላዊ ነጠላ ዜማው ከፍተኛ ተወዳጅነትና ዕውቅናን ያተረፈው አብርሃም በላይነህ (አብርሃም ሻላዬ)፤ ለዓመታት በለቀቃቸው ነጠላ ዜማዎቹ በሙዚቃ አፍቃሪያን ዘንድ ከፍ ያለ ዝናን ከማትረፉም በላይ፣ “እቴ ዓባይ” በተሰኘ ስራውም በ“All African Music Award" አሸናፊ መሆኑ ይታወሳል፡፡


አርቲስት መስከረም አበራ የኢቭ የሕጻናት
ዳይፐር የብራንድ አምባሳደር ሆነች

በተለያዩ የፊልምና የመድረክ ተውኔቶች የምትታወቀው አርቲስት መስከረም አበራ፤ የኢቭ የሕጻናት ዳይፐር የብራንድ አምባሳደር ሆና ተመርጣለች። አርቲስት መስከረም ለብራንድ አምባሳደርነቱ የተከፈላትን ክፍያ በይፋ ከመግለጽ ተቆጥባለች።

ዛሬ ታህሳስ 19 ቀን 2017 ዓ.ም. በስካይላይት ሆቴል በተካሄደ መርሃግብር፣ ስለ አርቲስት መስከረም አበራ ሞያዊ አበርክቶና ስነ ምግባር፣ በደራሲና ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ ተ/አረጋይና በተውኔት ደራሲና አዘጋጅ ዳግማዊ “አመለወርቅ” ፈይሳ አማካይነት የቀረበ ሲሆን፤ ኢቭ ሞዴስ እና የሕጻናት ዳይፐር፣ አርቲስት መስከረምን ለብራንድ አምባሳደርነት መምረጡ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።
አርቲስት መስከረም በበኩሏ፤ ከኢቭ ሞዴስ ጋር የነበራትን ቀደም ያለ መስተጋብር በማውሳት፣ “ከራሴ ሴትነት ጋር በተገናኘ የ’ኢቭ’ን ምርት አውቀዋለሁ” ብላለች። አያይዛም፣ “ልጅ የለኝም፤ ነገር ግን ልጅ ለወለዱ ወዳጆቼ በመስጠት ምርቱን እንዲጠቀሙ አደርጋለሁ” ስትል ቃል ገብታለች።

የብራንድ አምባሳደርነቱ ለአንድ ዓመት የሚቆይ ሲሆን፣ የቢልቦርድ፤ የቴሌቪዥንና የራዲዮ ማስታወቂያዎችን መስራት የሚያስችላት መሆኑ ተነግሯል። አርቲስቷ ከአምራች ድርጅቱ ስለተከፈላት የገንዘብ መጠን በይፋ ከመግለጽ ተቆጥባለች።

“የእኔ ደስታ በሞያዬ መቆየት ነው፤ ፍላጎቴም የሕዝቡን ስሜት መረዳት ነው። የኢቭ ዳይፐር የብራንድ አምባሳደርነት የመጀመሪያ ስራዬ ይሆናል። ወደፊት ሌሎች ስራዎች ይኖራሉ” ብላለች፤ አርቲስት መስከረም አበራ፡፡

ኢቭ ሞዴስ እና ዳይፐርን የሚያመርተው ጊዮፒዮን የንጽህና መጠበቂያ ግብዓቶች አቅራቢ ድርጅት፣ በኢትዮጵያ ስራውን ከጀመረ 16 ዓመታት ያስቆጠረ ሲሆን፤ የተለያዩ የጥራት ሽልማቶችን እንዳሸነፈ ለማወቅ ተችሏል።


ዳሸን ባንክ የሴቶችን የመሪነት ሚና
ለማሳደግ የሚያስችል መርሃ ግብር አስጀመረ



ዳሸን ባንክ የሴቶችን የመሪነት ሚና ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል መርሃ ግብር አስጀምሯል፡፡ መርሃ ግብሩ የሴት ሰራተኞቹን አቅም ይበልጥ ለማጎልበት ያስችላል ተብሏል።


በመርሃ-ግብሩ ማስጀመሪያ ላይ ንግግር ያደረጉት የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አፋው ዓለሙ፤ “ዛሬ የምንኮራባቸው የአገራችን ታሪካዊ ድሎችን እንድንጎናፀፍ ሴቶች ከፍተኛ አስተዋፅዎ አበርክተዋል” ብለዋል፡፡


ከታላላቅ አገራዊና ተቋማዊ ስኬቶች ጀርባ የሴቶች ሚና የጎላ መሆኑን የገለጹት አቶ አስፋው፤ ሴቶች ተገቢው ዕውቅና ሊሰጣቸው እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡


ዳሸን ባንክ ይህን ክፍተት በአግባቡ ተገንዝቦ የሚሰራ በመሆኑ ከምስረታው ጀምሮ ሴቶችን በከፍተኛ የአመራር እርከኖች ላይ በመሾም ወደፊት በማምጣት ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡


ባንኩ ሴቶችን በአግባቡ ያካተተ አሰራር በመፍጠር አዳዲስ ፈጠራዎችንና ውጤታማነትን እንደሚያጎለብት ተመላክቷል፡፡


መርሃ-ግብሩ ባንኩ ሁሉም ሰራተኞች ዕኩል ዕድል የማግኘትና የማደግ አጋጣሚ እንዲያገኙ ለማድረግ ካለው ራዕይ ጋር አብሮ የሚሄድ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡


በዳሸን ባንክ የሰው ሐብት ዋና መኮንን ወ/ሮ ህይወቴ ከፈለኝ በበኩላቸው፤ “ፕሮግራሙ በባንካችን ወደፊት ከፍተኛ አመራር መሆን የሚችሉ ሴቶችን ከወዲሁ ለመለየትና ለማብቃት የተነደፈ ነው” ብለዋል፡፡


⬇️


በተጨማሪም፣ የተሻለ ልምድ ያላቸውን ሴቶች ድጋፍ ከሚሹ ሴቶች ጋር በማገናኘት ጠቃሚ የሙያ ዕድገት እንዲያገኙ የሚያስችሉ ድጋፎችን ለመስጠት ያለመ እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

በመድረኩ ላይ ሐሳባቸውን ያጋሩት የ'ሴታዊት ንቅናቄ' መስራች ዶ/ር ስህን ተፈራ፤ ዳሸን ባንክ ሴቶችን በሁሉም መስክ ብቁ ለማድረግ እየሰራ ያለው ሥራ ለሌሎች ተቋማት ምሳሌ የሚሆን ነው ብለዋል።


አዲሱ “ማይክሽን መከለሻ” ቅመም በይፋ ተዋወቀ


ባለፈው መስከረም ወር ላይ ገበያውን እንደተቀላቀለ የተነገረለት አዲሱ “ማይክሽን መከለሻ” ቅመም በዛሬው ዕለት በሸራተን አዲስ ሆቴል በይፋ ተዋወቀ፡፡

“ማይክሽን መከለሻ” የተለያዩ ሃገራዊ ቅመሞችን እንዲሁም በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነት ያተረፈውን የሸኖ ለጋ ቃናን በውስጡ የያዘ ነው ተብሏል፡፡

ዛሬ ታህሳስ 19 ቀን 2017 ዓ.ም፣ ረፋዱ ላይ አዲሱን ምርት በይፋ የማስተዋወቅ መርህ ግብር በሸራተን አዲስ የተከናወነ ሲሆን፤የአምራች ድርጅቱ ሎንግሪቨር አግሮ ኢንዱስትሪ መሥራችና ባለቤት ከአጋሮቻቸው ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ለተለያዩ የምግብ ዓይነቶች ከተፈጥሮአዊ ግብአቶች ተቀምሞ የተሰናዳው “ማይክሽን መከለሻ”፤ ሃገራዊ ቅመሞችን ያካተተ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ ቅርንፉድ፣ ከሙን፣ ቀረፋ፣ የካርዌል ዘርና ሌሎች የተለያዩ ቅመሞችን በአንድ ላይ የያዘ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ሎንግሪቨር አግሮ ኢንዱስትሪ ባወጣው መግለጫ፤ ”ለዘመናዊም ሆነ ለባህላዊ ምግቦች እንዲሁም በፍስክ ወቅት ጭምር ተስማሚ ነው ነው” ብሏል፡፡

በማናቸውም ሱቆችና ሱፐርማርኬቶች ለገበያ እንደቀረበ የተነገረለት “ማይክሽን መከለሻ”፤ አንዱ በ25 ብር እንደሚሸጥ ተጠቁሟል፡፡

የ“ማይክሽን መከለሻ” አምራች የሆነው ሎንግሪቨር አግሮ ኢንዱስትሪ እ.ኤ.አ በ2022 ዓ.ም በኢትዮጵያ የተቋቋመ ድርጅት ሲሆን፤ የተለያዩ የምግብ ምርቶችን ለማምረት የተቋቋመ የውጭ ኢንቨስትመንት ኩባንያ ነው፡፡ ድርጅቱ በዱባይ በዓለማቀፍ ደረጃ ዕውቅናን ያተረፈው የዩኒግሎካል ኢንተርትሬድ አካል ነው፡፡


ለዓመት በዓል የገንዘብ ስጦታው የታጩት የ600 መፃሕፍት መደብር ሠራተኞች አንድም ራሳቸው ያመለከቱ አሊያም በመደብር ባለቤቶች፣ በደራሲያን ወይም በደንበኞች የተጠቆሙ ናቸው ተብሏል- በትጋትና ታታሪነታቸው።
"የሚስተር ፓተርሰንን የገንዘብ ልግስናና የልብ ቸርነት እናደንቃለን። ሁላችንም ሚስተር ፓተርሰን ለግል መፃሕፍት ሻጮች ለሚያደርጉት የማያቋርጥ ድጋፍ ምስጋናችን ወደርየለሽ ነው፡፡" ብለዋል፤ የአሜሪካ መፃህፍት ሻጮች ማህበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ አሊሰን ሂል በመግለጫቸው፡፡
"መፃሕፍት ሻጮች በኢንዱስትሪው ውስጥ የሚጫወቱትን ወደር-የለሽ ሚና መገንዘባቸውና መሸለማቸው ከምንም ነገር የላቀ ነው" ሲሉም አክለዋል፤ ዋና ሥራ አስፈፃሚው።
ደራሲው ለመፃሕፍት ሻጮች የ500 ዶላር የበዓል ቦነስ ሲያበረክት ያሁኑ የመጀመሪያው አይደለም። ላለፉት አስርት ዓመታት ሲያደርገው የቆየው የልግስና ተግባር ነው፡፡ ሥነ-ፅሁፍን በማሳደግና ንቁ ማህበረሰቦችን በመገንባት ረገድ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ በማመን፣ የግል የመፃሕፍት መደብሮችንም ያለማቋረጥ በመደገፍ ይታወቃል፤ በአገረ አሜሪካ፡፡
በመጋቢት ወር ላይ ፓተርሰን ለመፃሕፍት ሻጮች የሚከፋፈል 600ሺ ዶላር እንደሚያበረክት የአሜሪካ መፃሕፍት ሻጮች ማህበር አስታውቆ ነበር፡፡ ቀደም ብሎ እ.ኤ.አ በ2020 ደግሞ በመላው አሜሪካ ለሚገኙ የግል መፃሕፍት መደብሮች 500ሺ ዶላር ለግሷል- ሥራቸውን እንዲያሳድጉና እንዲነቃቁ።
"ዋይት ሐውስ የአየር መንገድ ኢንዱስትሪንና ትላልቅ ቢዝነሶችን ከውድቀት መታደግ ያሳስበዋል - ያንን እረዳለሁ። እኔ ግን በመላ አገሪቱ ዋና ጎዳናዎች እምብርት ላይ የሚገኙ የግል የመፃሕፍት መደብሮች ህልውና ያሳስበኛል።" ብሏል ፓተርሰን በሰጠው መግለጫ።
"የምናሰባስበው ገንዘብ የመፃሕፍት መደብሮችን በጣም በምንፈልግበት በዚህ ወቅት ህያው እንደሚያደርጋቸው ተስፋ አደርጋለሁ።" ሲልም አክሏል፤ ደራሲው።
ጄምስ ፓተርሰን እ.ኤ.አ በ2014 ዓ.ም ለአሜሪካ የግል የመፃሕፍት መደብሮች 1 ሚሊዮን ዶላር ለግሶ ነበር- ለእያንዳንዳቸው 15ሺ ዶላር የሚከፋፈል። ባለፉት ዓመታት ደራሲው ለመፃሕፍት መደብሮችና መጻሕፍት ሻጮች ብቻ ሳይሆን ለቤተመጻህፍት ባለሙያዎችና ለመምህራንም የበዓል ቦነስ ሲያበረክት ቆይቷል።
የመፃሕፍት መደብሮችንና መፃሕፍት ሻጮችን በገንዘብ ከመደገፍና ከማገዝም በተጨማሪ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ መፃሕፍትን ለት/ቤቶች ቤተ-መፃሕፍት ለግሷል። የህፃናት መፃሕፍትንም በመፃፍ የሚታወቀው ደራሲው፤ ህፃናት የንባብ ባህል እንዲያዳብሩም በትጋት ይሰራል። "ህፃናት በለጋ ዕድሜያቸው የማንበብ ልማድ ካላዳበሩ ለውጭው ዓለም ባዕድ ከመሆናቸውም ባሻገር በራስ መተማመን ይጎድላቸዋል፤ ስለዚህ የግድ ማንበብ አለባቸው፤ ይህን ማድረግ ደግሞ የኛ የወላጆች ሃላፊነትና ግዴታ ነው፡፡" ይላል- ፓተርሰን።
ጄምስ ፓተርሰን የበኩር ስራውን ለንባብ ያበቃው እ.ኤ.አ በ1976 ዓ.ም ሲሆን፤ ርዕሱም "The Thomas Berryman Number" ይሰኛል። ከሌሎች በርካታ የሥነጽሁፍ ሥራዎቹ መካከልም፡- Alex Cross, Michael Bennet, Women's Murder Club እና Maximum Ride የተሰኙት ልብወለዶች ይጠቀሳሉ። ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ልብወለዶቹም ወደ ፊልም ተቀይረውለታል፡፡


የመፃሕፍት ሻጮች አለኝታ - ሚሊየነሩ አሜሪካዊ ደራሲ
“መጻሕፍት ሻጮች ህይወትን ይታደጋሉ”
ጄምስ ፓተርሰን በዓለም ዝናው የናኘ እጅግ ታዋቂና ትጉህ አሜሪካዊ ደራሲ ነው። የ77 ዓመቱ ፓተርሰን እ.ኤ.አ ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ 200 ገደማ ረዥም ልብ ወለዶችን ጽፎ ለህትመት ያበቃ ሲሆን፤ መፃህፍቱ በዓለም ዙሪያ ከ425 ሚሊዮን ቅጂዎች በላይ ተሸጠውለታል። 1 ሚሊዮን ያህል ኤሌክትሮኒክስ መፃሕፍት (e-books) በመሸጥም የመጀመሪያው ደራሲ ነበር፡፡
ፓተርሰን እ.ኤ.አ በ2016 ዓ.ም በፎርብስ የከፍተኛ ተከፋይ ደራሲያን ሰንጠረዥን በመቆጣጠር ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ዘልቋል- በ95 ሚሊዮን ዶላር ገቢ። አጠቃላይ ገቢው ደግሞ ከአሰርት ዓመታት በላይ ለሚሆን ጊዜ 700 ሚሊዮን ዶላር ይገመት ነበር፡፡
ሚሊየነሩ አሜሪካዊ ደራሲ ከተወዳጅ የሥነጽሁፍ ሥራዎቹ ባሻገር የመጻሕፍት ሻጮች አለኝታም ነው፡፡ የመፅሐፍ ኢንዱስትሪውን የጀርባ አጥንት በመደገፍ ይታወቃል - የግል የመፃሕፍት መደብሮችን።
በዚህ የፈረንጆች በዓል ሰሞን በመላው አሜሪካ በሚገኙ 600 የግል መፃህፍት መደብሮች ውስጥ ለሚሰሩ ሰራተኞች በአጠቃላይ የ300ሺ ዶላር የበዓል ቦነስ አበርክቷል - በነፍስ ወከፍ 500 ዶላር!
"መፃህፍት ሻጮች ህይወትን ይታደጋሉ- አራት ነጥብ!" በማለት ለABC ኒውስ የተናገረው ደራሲው፤ "በዚህ የበዓል ወቅት ለእነሱም ሆነ ለትጋታቸው ዕውቅና መስጠት በመቻሌ ደስተኛ ነኝ።" ብሏል።


ሲኖማ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ አዲስ ኮሌጅ ከፈተ

• በኢትዮጵያና ቻይና መካከል የቴክኖሎጂ ልውውጥና ትብብር ይፈጥራል

ሲኖማ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ አዲስ ኮሌጅ መክፈቱን ገልጿል። የኮሌጁ መከፈት በኢትዮጵያና ቻይና መካከል የቴክኖሎጂ ልውውጥና ትብብር የሚፈጥር ነው ተብሏል።

ባለፈው ታህሳስ 6 ቀን 2017 ዓ.ም. በሲኖማ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ዋና ጽሕፈት ቤት በተካሄደ መርሃ ግብር፣ ሉባን-ሞዚ ኮሌጅ መመስረቱ የተበሰረ ሲሆን፤ በጂናን ሞያ ኮሌጅ፣ የሲኖ-ጀርመን ቴክኖሎጂ ዲፓትመንት የፓርቲ ቅርንጫፍ ዋና ጸሐፊ ዣንግ ያሩ እና በኢትዮጵያ የሲኖማ ኢንተርናሽናል ኢንጂነሪንግ ዋና ስራ አስኪያጅ ሚንግ ጂያንግቶ በመርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል።

ይኸው ኮሌጅ የተቋቋመው በኢትዮጵያ የሲኖማ ኢንተርናሽናል ቅርንጫፍና በጂናን ሞያ ኮሌጅ ቀጥተኛ አመራር በተሰጣቸው አምስት ያህል የሻንዶንግ ሞያ ኮሌጆች ጥምረት እንደሆነ ተገልጿል። የኮሌጁ ዓላማ በኢትዮጵያና ቻይና መካከል የቴክኖሎጂ ልውውጥና ትብብር መፍጠር፣ ብሎም ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ፈጠራን ማስተዋወቅ ነው ተብሏል።

ሚንግ ጂያንግቶ ወደፊት ኮሌጁ አመርቂ ስራዎችን እንደሚሰራ ያላቸውን ተስፋ አጋርተዋል። አክለውም፣ እርሳቸው የሚመሩት ኩባንያ በመማር ማስተማር ሂደት ላይ የኮሌጁ ትምሕርቶች ተግባራዊ እንደሚሆኑ፣ እንዲሁም የቻይንኛ ቋንቋን እንደሚያጎለብትና የሞያ ስልጠናዎችን ለማስፋት በትብብር ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል።

ዣንግ ያሩ በበኩላቸው፣ ሉባን-ሞዚ ኮሌጅ ተመርቆ መከፈቱን አብስረዋል። ወደፊትም የተለያዩ ስራዎችን ከኮሌጁና ከኩባንያው ጋር ለመስራት እንዳቀዱ ነው የገለጹት።

ሲኖማ ኢንተርናሽናል ከሌሎች የኢትዮጵያ ኮሌጆችና ዩኒቨርስቲዎች ጋር በመተባበር ለመስራት እንዳቀደም በመርሃ ግብሩ ላይ ተነግሯል።


የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ፣የመቄዶንያ አረጋውያንን ጎበኙ


• ፕሬዚዳንቱ የመቄዶንያ የበላይ ጠባቂ ለመሆን ተስማምተዋል



• ወጣቱ ባለሃብት በ2 ሚ. ብር ወጪ አረጋውያኑን ምሳ አብልቷል


የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታየ አጽቀ ሥላሴ፣ በአዲስ አበባ የሚገኘውን መቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል በዛሬው ዕለት ጎብኝተዋል።

በድርጅቱ የአረጋውያን ተወካይ በየዓመቱ ታህሳስ 18 በእሳቸው ስም እንዲሰየምና የድርጅቱ የበላይ ጠባቂ እንዲሆኑ የቀረበላቸውን ጥያቄ ተቀብለዋል።

“መቄዶንያ የአረጋውያንና አዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል የሚሰራው በጎ ስራ ነውና፤ ሁሉም በአቅሙ ሊደግፈው ይገባል” ብለዋል፤ ፕሬዚዳንቱ፡፡

በመቄዶንያ እየተሰራ ያለው በጎ ስራ ብርታትን የሚሰጥ ነው ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ማዕከሉ የበጎ አድራጎት ሥራውን ይበልጥ ተደራሽ እንዲያደርግ ሁሉም በሚችለው መደገፍ አለበት ብለዋል።

ከዚሁ ጋር ተያይዞ የመቄዶንያ የምንጊዜም አጋዡ ወጣቱ ባለጸጋ ምህረትአብ ሙሉጌታ፣ የፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀስላሴን ጉብኝት ምክንያት በማድረግ፣ ከ2 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በመመደብ በድርጅቱ ለሚገኙ 8 ሺ የሚደርሱ አረጋውያን የምሳ ወጪያቸውን ሸፍኗል።

የመቄዶንያ መሥራቹ ዶ/ር ቢኒያም በለጠ ባደረገው ንግግር፤ “ወጣት ምረትአብ ሙሉጌታ ለድርጅታችን እያደረገ ያለው ነገር ቀላል የሚባል አይደለም፤ ዛሬም ሙሉ የምሳ ወጪ ስለሸፈነልን ከልብ እናመሠግናለን” ብሏል፡፡

Показано 20 последних публикаций.