Фильтр публикаций


How Children Succeed

In his book entitled "How Children Succeed," Tough explores the factors that contribute to children's success beyond traditional measures of intelligence and academic achievement. Through research and real-life examples, he argues that character traits such as perseverance, curiosity, and resilience play a crucial role in helping children thrive.

Dear parents:

Today, for our weekly message, we have chosen the following ten key lessons and insights from the book, "How Children Succeed,"  Enjoy reading the ten points and try your best to help your child succeed. 

1. The Importance of Character:

The author, Tough emphasizes that character traits, often referred to as "non-cognitive skills," are critical for success in life. Qualities such as determination, resilience, and emotional intelligence are just as important, if not more so, than IQ in determining a child's long-term outcomes.

2. Understanding Determination and Resilience:

The author highlights the concepts of determination and resilience as key components of success. Determination refers to the passion and perseverance needed to achieve long-term goals, while resilience is the ability to bounce back from setbacks. Both traits are essential for navigating challenges.

3. The Role of Adversity:

Tough discusses how experiencing adversity can actually foster resilience in children. He notes that overcoming obstacles can teach valuable life lessons and develop coping strategies, ultimately leading to greater success in the future.

4. The Impact of Environment:

The book explores how a child's environment influences their development of character traits. Supportive environments, whether at home or in school, encourage the growth of resilience and determination, while toxic environments can hinder these qualities.

5. The Importance of Relationships:

Tough emphasizes the significance of strong relationships in a child's life, particularly with adults. Positive mentorship and supportive adult interactions can help children develop the skills and confidence needed to succeed.

6. Teaching Self-Regulation:

The author discusses the concept of self-regulation, which involves managing emotions, thoughts, and behaviors. Teaching children how to self-regulate can improve their academic performance and social interactions, contributing to their overall success.

7. The Role of Failure:

Tough argues that experiencing failure is an essential part of personal growth. Allowing children to face challenges and learn from their mistakes fosters resilience and helps them understand the value of perseverance.

8. Educational Approaches:

The book examines various educational models that prioritize character development alongside academic achievement. Schools that focus on social and emotional learning create environments where children can develop the necessary skills for success.

9. Mindset Matters:

Tough explores the concept of a growth mindset, popularized by psychologist Carol Dweck. Encouraging children to view challenges as opportunities for growth rather than as threats can significantly impact their motivation and willingness to take risks.

10. Long-Term Strategies for Success:

Finally, the author advocates for long-term strategies that prioritize character development from an early age. Programs that focus on social-emotional learning, mentorship, and building resilience can set children on a path toward lifelong success.

In his book "How Children Succeed," Paul Tough presents a compelling argument for the importance of character and resilience in children's success. By highlighting these ten key lessons, he encourages parents, educators, and policymakers to prioritize the development of non-cognitive skills alongside traditional academic measures, ultimately fostering a generation of capable, resilient individuals.


ለአል-ዓፊያ ማኀበረሰብ በሙሉ
እንኳን ደስ አላችሁ!

በኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ በወረዳ 06 ት/ጽ/ቤት አዘጋጅነት በተካሄደው የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ትምህርታዊ ውድድር የአል-ዓፊያ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ቤተል ቅርንጫፍ ተማሪዎች በ8ኛ ክፍል 1ኛ፣ በ6ኛ ክፍል ደግሞ 2ኛ በመሆን አስደናቂ ውጤት ማስመዝገባቸው በጣም ያስደስታል!
እንኳን ደስ አላችሁ‼️‼️


Репост из: ስለ እውነት
ክፍል 2

5. የልጆችዎን የትምህርት አቀባበል የሚመዝኑባቸው ቀላል ዘዴዎች ይኑርዎት

ወላጆች ልጆቻቸውን በትምህርታቸው ለመርዳት በየዕለቱ ምን ተምረው እንደመጡ መፈተሸና መከታተል እንዲሁም ቀለል ባለ ዘዴ የምዘና ጥያቄ አዘጋጅተው መመዘን ይችላሉ፡፡ በተወሰነ የጊዜ ርቀት ይህን ተግባር በማከናወን ልጆችዎን ከተማሩት ምን ይህል በሚገባ እንደተረዱት መገንዘብ ይቻላል፡፡ ይህ ግን ልጅዎን በሚያሳስብና በሚያስጨንቅ መልኩ መካሄድ የለበትም፡፡ ልጆችዎ እተዝናኑና እየተጫወቱ ሊሰሩ የሚችሉበትን ድባብ መፍጠር ይገባል፡፡ ልጆችን በዚህ መልኩ የተማሩትን በተለያየ ዘዴ እየገመገሙ ማነፅ በልጆቻችን ትምህርት በስፋት ተሳታፊ እንድንሆን፤ ልጆችንም የተማሩትን ትምህርት በጊዜ በሚገባ እንዲከልሱና በጥልቀት እንዲረዱ እንዲሁም በቀላሉ የተማሩትን አስታውሰው በምዘና መለኪያዎች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ እና በክፍል ውስጥም በንቃት እንዲሳተፉ ጭምር ያበረታታቸዋል፡፡

6. ልጆችዎን በትምህርታዊ ጉዞ ያዝናኑዋቸዋል

“ካሉበት ቦታ መቀየር ከድካም ዕረፍት የመውሰድ ያህል አስደሳች ነው” ይባላል፡፡ እንግዲያው እርስዎ ልጆችዎን ቀኑን ሙሉ ከሚውሉበት ት/ቤት እንዲሁም ከቤትዎ በተወሰነ ጊዜም ቢሆን በማላቀቅ ለምን በሽርሽር አያዝናኗቸውም? ከተለመደ ቦታ መቀየር ለሁሉም ቢሆን ያዝናናል፡፡ በተለይ ደግሞ ትምህርት በመማር ከፍተኛ ውጣ ውረድ በት/ቤትም ሆነ በቤት ለሚጋፈጡ ልጆችዎ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ እዚህ ጋር ግን አንዴ ቆም ብለን ማሰብ የሚገባን አለ እሱም ልጆቻችን በሽርሽር/በጉብኝት ለማዝናናት ከመነሳታችን በፊት የምናዝናናበት/የምናስጎበኝበት ቦታ ለልጆቻችን የአካልም ሆነ የአዕምሮ ጤና እንዲሁም የሥነ ልቦና ደህንነታቸው ብሎም ሞራልና ግብረ-ገብነታቸው ላይ ምንም አይነት ጉዳት የማያስከትል (ዋጋ የማያስከፍለን) ስለመሆኑ ቅድሚያ እርግጠኛ ልንሆን ይገባል፡፡ አለያ ግን አተርፍ ባይ . . . ነው የምንሆነው፡፡

7. ልጆችዎ የተሻለ ውጤት ሲያስመዘግቡ ዕውቅና ሰጥተው ያበረታቱ፤ ይሸልሙ

ልጆችዎን ለሚያስመዘግቧቸው የትምህርት ስኬቶች ዕውቅና ሰጥቶ ማበረታታትና መሸለም የተሻለ እንዲሰሩ በጣም ያግዛቸዋል፡፡ እርስዎ ታዲያ ልጆችዎ የላቀ ውጤት ይዘው ወደ ቤት ሲመጡ በማበረታታትና በሽልማት ሊቀበሏቸው ይገባል፡፡ ይህን ለማድረግ ግን የግድ ከፍተኛ የሆነ ወጪ ማውጣት አይጠበቅም፡፡ አቅም በፈቀደ ከወላጅ ለልጆች የሚደረግ ሽልማት ልጆች ደክመው ያመጡት ውጤት በወላጅ የላቀ ዋጋ እንደሚሰጠው መልዕክት ለማስተላለፍ መሆን ነው የሚገባው፡፡

8.ልጆችዎ እረፍት እንዲኖራቸው ያድርጉ! ለልጆችዎ ሰዓት ይኑርዎት! 

ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን ከጥናት ዕረፍት መውሰድ ለልጆች ጠቃሚ ነው፡፡ ይህም ልጆችዎን በትምህርት ለማገዝ የሚረዳ ቀላል መንገድ ነው፡፡ በቤት ውስጥም ቢሆን አንዳንዴ ልጆች ከትምህርት ተለይተው (አቋርጠው) ሊዝናኑ የሚችሉበት ጊዜ ያመቻቹላቸው፡፡ እርስዎም ካለዎት ሰዓት ምርጡን ከልጅዎ ጋር በመሆን ያሳልፉ፡፡ ግን ግን ስንቶቻችን ነን ካለን ሰዓት ምርጡን ነገ እኛን ይተኩናል ብለን ብዙ ከምንደክምላቸው ውድ ልጆቻችን ጋር የምናሳልፈው? ምን ያህል እርስዎ ለልጆችዎ ቅርብ ነዎት? ለልጅዎት ምርጡን ሰዓት ሰጥተው ያገኟቸዋል ወይስ . . . ? እኛ ለልጆቻችን ቅርብ ልንሆን ይገባል፡፡ ይህን የማናደርግ ከሆነ ግን ልጆቻችንን እኛ ሳንሆን የሚያንፃቸው ሌላ ይሆናል፡፡ ለምሳሌ ኢንተርኔት፣ ፌስቡክ፣ ቲቪ፣ እና የመሳሰሉት፡፡ ይህ ከሆነ ደግሞ ነገ የምንመኘውን አይነት ትውልድ ማፍራት ባዶ ተስፋ ሆኖ ይቀራልና ለልጆቻችን ሰዓት መስጠታችን በሚገባ መፈተሽ ለነገ የማይባል ነው፡፡

9.ልጆችዎ በአግባቡ መመገባቸውንና በተገቢው ሰዓት ወደ መኝታቸው መሄዳቸውን ያረጋግጡ!

ት/ቤት እንደ ስያሜው እውቀት የሚቀሰምበት ቦታ ነው፡፡  ትምህርት ለመማር ደግሞ ተማሪ በአካልም ሆነ በአዕምሮ ዝግጁ መሆን አለበት፡፡ ይህ እንዲሆን ደግሞ የምግብ ስርዓትና የመኝታ ሰዓት የተስተካከለ ሊሆን ይገባል፡፡ እንደ ወላጅ ለልጆች አሸክመን ለምንልከው ምግብ ምን ያህል ተገቢውን ጥንቃቄ እናደርጋለን? አንዳንዴ ልጆች እንደማይመቻቸው እየታወቀ የሚታሰርላቸውን ምግብ እንዲጨርሱ በት/ቤት የሚፈጠረው ግብ ግብ  ለጉድ ነው፡፡ ወላጆች የልጆቻቸውን ምግብ በዕርግጥ እየተመለከቱት ነውን? የሚል ጥያቄም ያስነሳል፡፡ በተመሳሳይ የልጆች የእንቅልፍ ሰዓትም ከፍተኛ ክትትል ያሻዋል፡፡ ልጆች መተኛት በሚገባቸው ሰዓት ስለመተኛታቸው እንደ ወላጅ ማረጋገጥ ይገባል፡፡ ልጆች ማረፍ በሚገባቸው የመኝታ ሰዓት ተገቢ ባልሆኑ ተግባራት የሚጠመዱ ከሆነ በአካልም ሆነ በአዕምሯቸው ላይ የሚፈጠረው ጫና በትምህርታቸው ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ ነው፡፡

ውድ ወላጅ እንግዲህ ልጆቻችንን በትምህርታቸው ሥኬታማ ማድረግ ከሚቻልባቸው ቀላል ዘዴዎች 9ኙን የጠቆምንበት  መልዕክት በዚሁ ተጠናቋል፡፡

እንደ ወላጅ ከጽሑፉ ልጅዎን በትምህርቱ/ቷ ለመርዳት የሚያስችሉ ጠቃሚ ነጥቦች እንዳገኙ ተስፋ እናደርጋለን፡፡ እባክዎ ልጆችዎን በትምህርታቸው ስኬታማ ይሆኑ ዘንድ ለመርዳት እንደወላጅ ሃላፊነትዎን በአግባቡ ይወጡ የዛሬው መልዕክታችን ነው፡፡ ሰላም!


ወላጆች ልጆቻቸውን በትምህርታቸው ስኬታማ ማድረግ የሚችሉባቸው 9 ቀላል ዘዴዎች

Easy ways for parents to support their children's studies


ክፍል 1

ባለንበት ዘመን ልጆች ማሳደግ እጅግ ፈታኝ ከሆኑት ሃላፊነቶች አንዱ ነው፡፡ “ልጄ ምርጥ ትምህርት አግኝቶ ስኬታማ መሆን እንዲችል እኔ ምን ማድረግ አለብኝ?” የሚለውም እንደወላጅ በጣም አሳሳቢና ዕረፍት የማይሰጥ ርዕሰ ጉዳይ ነው፡፡ አፋጣኝና ተገቢ ምላሽ የሚሻ:: የልጅዎትን የትምህርት ሁኔታ ሲያስቡም ልጆችን በትምህርታቸው ለመርዳት ይህ ነው የሚባል አስተዋፅኦ ማበርከት የማይችሉ ሊመስልዎት ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ጥናቶች እንደሚነግሩን ወላጆች ልጆቻቸውን በትምህርታቸው መርዳት ወይም ሥኬታማ ማድረግ የሚችሉባቸው በርካታ ዘዴዎች መኖራቸውን እንገነዘባለን፡፡

እኛም ወላጆች ልጆቻቸውን በትምህርታቸው ሥኬታማ ማድረግ ከሚችሉባቸው ቀላል ዘዴዎች መካከል 9ኙን ለዛሬው ሳምንታዊ የግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክት በርዕሰ ጉዳይነት መርጠናል፡፡ በጽሑፉ ልጆችዎትን በትምህርታቸው ለመርዳት የሚያስችሉ ጠቃሚ ዕውቀቶችን እንደሚቀስሙበት እምነታችን ነው፡፡ መልካም ንባብ

1. ልጆችዎ ሲማሩ የሚቸገሩበት ስለመኖሩ ጊዜ ሰጥተው ይጠይቋቸው፡፡ ቀረብ ብለው ያወያዩዋቸው፤ የሚችሉትን ዕገዛም ያድርጉላቸው!!

ልጆችዎን በትምህርታቸው ከሚረዱበት ዘዴዎች እጅግ ቀላል የሚባለው የልጆችዎን የትምህርት እንቅስቃሴ እርስዎም ጉዳዬ ብለው እንደሚከታተሉዋቸው ማሳየት፤ የሚከብዳቸው ትምህርት ካለም እነርሱን መጠየቅ ነው፡፡ “ትምህርት እንዴት ነው? ምን ችግር ገጠመህ/ሽ? የምረዳህ/ሽ ነገር አለ?” እና መሰል ጥያቄዎችን ልጆችን ቀርቦ መጠየቅ ቀላል ግን የላቀ ፋይዳ የሚገኝበት ነው፡፡ ግን ስንቶቻችን ነን ሥራዬ ብለን ይህን የምናደርገው? ስንቶቻችን ነን ልጆቻችንን ት/ቤት ከመላክ በዘለለ እንዲህ በትምህርታቸው ተጨንቀን የምንጠይቅ? እራሳችንን እንጠይቅ! ልጆችዎ የርስዎን ዕርዳታ ሲፈልጉ ለዚህ ዝግጁ መሆንዎን ማወቃቸው በራሱ እርስዎ ለእነርሱ ትምህርት ዋጋ እንደሚሰጡ ብሎም ከጎናቸው መሆንዎን ለማሳየት ጭምር ይጠቅማል፡፡ ልጀችዎ የሚቸገሩበትን የትምህርት ርዕስ (topic) ለእርስዎ መጥተው ካሰረዱዎት በቻሉት መጠን ሳይዘገዩ ተገቢውን ምላሽ መስጠት ይገባዎታል፡፡ ልጅዎን የገጠመው/ማት የትምህርት ችግር ከአቅም በላይ ከሆነም በጉዳዩ ዙሪያ የተሻለ መርዳት የሚችሉ ባለሙያዎችን በማማከር አለያም በትምህርቱ ዙሪያ የተዘጋጁ መጽሐፍትን ገዝተው ማቅረብን እንደ መፍትሔ መጠቀም አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ይህ ብቻም ሳይሆን ልጆችዎ ላይ የሚያስተውሉት የትምህርት ችግር እየከፋ ከሄደና ለመስተካከል ረጅም ጊዜ የሚፈልግ አይነት ከሆነ ልጅዎን በትምህርት አይነቱ (subject) ዙሪያ የግል አስጠኚ መቅጠርዎ ሌላው አማራጭ ሊሆን ይችላል፡፡ በተለይ ልጅዎ ከትምህርት ገበታ የቀረ ወይም ታሞ ከነበረ አለያም ሌላ የጤና ችግር ገጥሞት የትምህርት አቀባበሉ ላይ ጉልህ ችግር ከተፈጠረ ከት/ቤት ባሻገር ቤት መጥቶ በግል የሚረዳው የትምህርት ባለሙያ (አስጠኚ) ቀጥሮ ልጅዎ እንዲረዳ ማድረግ ተገቢ ነው የሚሆነው፡፡

2. ልጆችዎ ማንበብን የደስታ ምንጫቸው እንዲያደርጉ ያበረታቱ

ማንበብ የብዙ ስኬታማ የሆኑ ተማሪዎች አይነተኛ ባህሪ ነው፡፡ ወላጆች ይህን ተግባር ልጆች ይተገብሩት ዘንድ ማበረታታት አለባቸው፡ ይህን ማድረግ ምን ይከብዳል? ወደ ቤተ-መጻሕፍት ሲሄዱ ልጆችዎንም ይጋብዟቸው ፣ በቤትዎ በቂ መጽሐፍ እንዲኖር ያድርጉ ከተቻለም የቤት ውስጥ ቤተ-መጻሕፍት (ላይብረሪ) ይኑርዎት፤ ልጆችዎ የተሻለ የትምህርት ውጤት ካመጡም መጽሐፍ ይሸልሟቸው፤ ስጦታም ያበርክቱላቸው፡፡ እነዚህ ተግባራት በየትኛውም የዕድሜ ክልል ለሚገኙ ልጆች የንባብ ፍቅርን ለማስረፅ የሚያስችሉ ቀላል ዘዴዎች ሆነው ማገልገል ይችላሉ፡፡

3. በቤት ውስጥ የፀጥታ ጊዜ እንዲኖር ያድርጉ

በቤት ውስጥ ያሉ ህጻናትም ሆኑ ዐዋቂዎች እየተንጫጩና እየረበሹ ሌሎች ልጆች ሀሳባቸውን ሰብሰብ አድርገው በአንድ ልብ ማንበብ፣የቤት ስራቸውንም ሆነ ሌሎች በትምርት ቤት የታዘዙትን መስራት ይቸግራቸዋል፤ ሀሳባቸው ይበታተንባቸዋል፡፡ የተሰበሰበ ትኩረት ማድረግ ይሳናቸዋል፡፡ ይህን ችግር ለመቅረፍ ታዲያ በቀን ውስጥ በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ ምንም አይነት የልጅዎትን ትኩረት የሚነሳ ጫጫታና ረብሻ የማይኖርበት የጸጥታ ጊዜ ስርዓት በቤትዎ ውስጥ ሊኖር ይገባል፡፡ ይህም ልጆች በቤት ውስጥ የሚያስፈልጋቸውን የትምህርት ተግባራት በተረጋጋና ፀጥታ የሰፈነበት (distraction-free) በሆነ ሁኔታ እንዲሰሩ ያመቻቻል፡፡


4. ከልጆችዎ ት/ቤትና መምህራን ጋር ቅርብ ይሁኑ

ት/ቤት የነገ የልጅዎ ማንነት የሚቀረፅበት ስፍራ ነውና እንደ ወላጅ የልጆችዎን ት/ቤት ጉዳዬ ብለው ሊከታተሉ ይገባል፡፡ አሁን እያነበቡ ያሉት ሳምንታዊ ግንዛቤ ማስጨበጫ መልዕክትን  ጨምሮ ሌሎች በት/ቤቱ የሚዘጋጁ መልዕክቶችን (ዕለታዊ፣ወርሃዊ … ) በሚገባ ማንበብና ቦታ ሰጥተው መረዳት እንዲሁም ከልጆችዎ መምህራን ጋር በቅርብ መነጋገር ይጠበቅቦታል፡፡ ከዚህ ባሻገር በየጊዜው ስለ ልጆችዎ የትምህርት ጉዳይ ሳይታክቱ ከመምህራን ጋር በመወያየት (በመጠየቅ) ልጅዎ ምን አይነት ድጋፍ ከእርስዎ እንደሚያስፈልገው መረዳት ይጠበቅብዎታል፡፡ ከልጅዎ መምህራን ጋር ቅርርብ በመፍጠር በሚኖርም ውይይት ልጆችዎ ተጨማሪ ድጋፍ የሚፈልጉባቸው ክፍተቶችንም ይገነዘባሉ፡፡

ክፍል 2 ይቀጥላል


በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለአቅም ማሻሸያ (Remedial) ትምህርት ወደ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ የምዝገባ ጊዜ እንደሚከተለው መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል፣

👉ለመደበኛ Remedial ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሄደው ታህሳስ 21 እና 22/2017 ዓ.ም ሲሆን ትምህርት የሚጀምረዉ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ይሆናል፤

⚡️በቅጣት ምዝገባ ታህሳስ 23/2017 ዓ.ም ይሆናል፤

👉በግል ለመማር ለተመዘገባችሁ ተማሪዎች ትምህርት የሚጀምረዉ ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም ይሆናል፤

💥ለምዝገባ ስትመጡ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና አንድ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ፣ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክርፕት ፣ 3*4 የሆነ ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ፣ የትራስ ጨርቅ፣ አንሶላ፣ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን፤

• የካምፓስ ምደባ በሚመለከት ከዚህ በታች በተገለጸዉ መሠረት ይሆናል።

Natural Science

ስማቹህ A to G የሆናቹህ ዱራሜ ካምፓስ
ስማቹህ H to Z የሆናቹህ ዋና ግቢ

Social Science

ስማቹህ A to J የሆናቹህ ዱራሜ ካምፓስ
ስማቹህ K to Z የሆናቹህ ዋና ግቢ

ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ

#WachamoUniversity #Remedial

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library




ልጆችን ማበረታታት

ትምህርት ለልጆቻችን የወደፊት ስኬት ዋንኛው መሰረት መሆኑን ሁላችንም እንገነዘባለን፡፡በመሆኑም ወላጆች ልጆቻችን  በትምህርታቸው ስኬታማ መሆን ይችሉ ዘንድ ተገቢውን ትኩረት አድርገን መስራት ይጠበቅብናል፡፡ ልጆችን ማበረታታት ደግሞ  የልጆቻችንን ስኬት ዕውን ማድረግ ከምንችልባቸው ቁልፍ ዘዴዎች  መካከል ነው፡፡

በወላጅዎች የሚበረታቱ ልጆች ከሌሎቹ የበለጠ ውጤታማ የመሆን ዕድል እንዳላቸው በዘርፉ ጥናት ያካሄዱ በርካታ ሙሁራን ይናገራሉ፡፡ በወላጆቻቸው ተገቢውን ማበረታታት የሚደረግላቸው ልጆች ለትምህርት የሚኖራቸው አመለካከትም እየተስተካከለ እንደሚሄድ ጭምር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

የዛሬው መልዕክታችን ርዕሰ-ጉዳይ  ልጆችን ማበረታታት ላይ እንዲያተኩር መርጠናል፡፡ ልጆች በምን መልኩ ብናበረታታቸው ስኬታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ የተወሰኑ መንገዶችን እንዲካተት አድርገን ከዚህ በሚከተለው መልኩ አሰናድተን ለማቅረብ ሞክረናል፤ መልካም ንባብ፡፡

1.ከልጅዎ ጋር በመከባበር ላይ የተመሰረተ ግልፅ እና አዎንታዊ ግንኙነት ተግባራዊ በማድረግ ልጅዎን ያበረታቱ

ይህን ማድረግ በልጅዎ ላይ እጅግ ተፅእኖ መፍጠር የሚችሉበት ታላቅ መሳሪያ ነው፡፡ ለልጅዎ  በዚህ ርቀት ቅርብ መሆን ከቻሉ በእርግጥም በሚገባ እያበረታቱት መሆኖን ልብ ይበሉ፡፡

2. በልጅ አስተዳደጎ ሩህሩህ በመሆን ልጅዎን ያበረታቱ

ከሀይልና ከልክ በላይ ቁጥጥር እንዲሁም ቁጣና ቅጣት ታቅበው ለልጅዎ  ሩህሩህ ፣ ተባባሪ አና ጽኑ  ወላጅ ለመሆን  የድርሻዎትን ይወጡ፡፡ከልጅዎ ጋር በሚኖርዎት ቅርርብ ለምትፈጠር እያንዳንዷ  አሉታዊ ግንኙነት ብዙ እጥፍ አዎንታዊ አብሮነት በመፍጠር በጊዜ ያብሱት፡፡ልጆችዎን በሆነ ባልሆነ  ከመጨቅጨቅና ከማስጨነቅ ይልቅ እነሱን ርህራሄ በተሞላበት ሁኔታ በማገዝና ማበረታታት ላይ ትኩረትዎ እንዲሆን ያድርጉ፡፡

3.ከልጅዎ ጋር የመነጋገር ባህል  በማዳበር ልጅዎን ያበረታቱ

ልጆች በትምህርታቸው ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ስለትምህርት ፈላጎታቸው እና ችሎታቸው ማውራት በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡ወላጆች ልጆቻቸውን ሊያደምጧቸው፣ ጠንካራ ጎኖቻቸውንም  እውቅና ሰጥተው ሊያበረታቷቸው ይገባል፡፡ ለምሳሌ  “በጣም የምትወደው የትምህርት አይነት ምንድን ነው?”  “ እንዴት ይሄ ሊሆን ቻለ?” እያሉ መጠየቅና መወያየት  ፋይዳው የላቀ ነው፡፡

 4.የልጅዎን የትምህርት ዝንባሌ ዝቅ አድርጎ ባለመመልከት ያበረታቱ

የልጅዎ የትምህርት ምርጫ(ፍላጎት)  እርሶ ከሚያስቡትና ከሚጠብቁት የሚቃረን ሊሆን ይችላል፡፡ ቢሆንም ግን  የልጅዎን ፍላጎት ማክበርና በመረጠው ፊልድ ስኬታማ ይሆን ዘንድ ማበረታታት የላቀ ውጤት ይኖረዋል፡፡ ለምሳሌ ልጅዎ የስነ ፅሁፍ ፍላጎት እና ዝንባሌ ያለው ሆኖ እርሶ ግን ንባብ  ላይ እምብዛም ስለሆኑ ብቻ ስነ ጽሁፍን ፋይዳቢሰ  የትምህርት ዘርፍ (ፊልድ) አድርገው የልጅዎን የአስተሳሰብ ነፃነት መጫን አይገባም፡፡ ባይሆን ልጆዎን በዝንባሌው መሰረት ውጤታማ ይሆን ዘንድ በተለያየ መልኩ ግብዓቶችን በማቅረብ እንዲሁም ወደ ቤተ-መጽሀፍት ይዘው መሄድ  ከሁሉም ወላጅ የሚጠበቅ ልጆችን በትምህርታቸው ስኬታማ ይሆኑ ዘንድ የማበረታታት አይነተኛ ዘዴ  ነው፡፡

5. ለልጅዎችዎ ጥረት ተገቢውን ዕውቅና በመስጠት ያበረታቱ

ልጆች ከውጤታማነት በላይ ጥረቶቻቸው በወላጅዎቻቸው ተገቢውን እውቅና ተሰጥቷቸው መመልከት ደስተኛ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል፤  የበለጠም ያበረታታቸዋል፡፡ለልጆቻቸን ጥረቶች ተገቢውን ዕውቅና ሰጥተን የምናበረታታ ከሆነ ልጆች ከውጤት ባሻገር ትምህርትን ጠንክሮ መማር የበለጠ ዋጋ እንዳለው መረዳት ያስችላቸዋል፡፡ ለምሳሌ ልጅዎ ፈተና የተሻለ ውጤት ሲያስመዘግብ ከውጤቱ በላይ ጠንክሮ ማጥናቱ ላይ ትኩረት አድርገው አስተያየት ይስጡ፡፡ “አየህ ለፈተና ያደረጋቸው ጥረቶች ሁሉ ከንቱ አልቀሩም፤ በእርገጥም በውጤትህ ተንፀባርቋል፡፡ ” በማለት የልጅዎን ብርቱ የጥናት ሂደት ማበረታታት በልጅዎ የትምህርት ስኬት የላቀ ሚና ይጫወታል፡፡

6.ልጅዎችዎ ውጤት ባያስመዘግቡምኳ የበረታቷቸው

ልጅዎችዎ እንደጠበቁት ውጤታማ ሆነው ሳይገኙ ሲቀሩ ወደፊት እንዴት ውጤታማ ሊሆኑ እንደሚችሉ ገንቢ ምክሮትን በመለገስ ያበረታቷቸው፡፡ ውጤት ስላልተመዘገበ ብቻ የልጅዎን ጥረትና ድካም በፍጹም ዝቅ አድርገው አይመልከቱ፡፡እነዲህ የሚያደርጉ ከሆነ ልጅዎ ወደፊት ስህተቱን አርሞ፤ ክፍተቱንም ሞልቶ ወደ ውጤታማነት ከመገስገስ ይልቅ ጠንክሮ ማጥናትና ጥረት ማድረጉ ፋይዳ እንደሌለው በማሰብ ፊቱን ከትምህርት ይልቅ ወደ ሌላ በማዞር ቀጣይ የትምህርት ህይወቱ ላይ አደጋ ሊደቀን ፤ስኬታማነነታቸውንም ሊያጨናግፍ ይችላል፡፡ ልጆች ውጤታቸው ምንም ያህል ዝቅ ቢልኳ “   አንተ ሰነፍ፤የማይገባህ፣  ” እና  መሰል እጅግ ጸያፍ እና አፍራሽ የፍረጃ ቃላትና ውንጀላዎች  ወላጅዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል፡፡ ለልጅዎ ካስመዘገበው  ውጤት በላይ እነደሚጠብቁና ለዚህም ተባብሮ ለመስራት እስከመጨረሻው
ዝግጁነትን ከማንጸባረቅ  ውጭ ልጆችን በወቀሳ ናዳ ማስበርገግ ፤ በዛቻ ማዕበል ማጥለቅለቅ  የማበረታታት ተቃራኒ የስኬታማነትም ፀር ነው፡፡

7.በልጅዎችዎ ላይ የሚተገብሯቸው የቅጣት ዕርምጃዎች ሁሉ ልጆችዎ የተሻሉ ሆነው ይቀረጹ ዘንድ ለማበረታተት እንጂ ለሌላ አለመሆኑን በተግባሮትና በቃልዎ ይረጋግጡላቸው፡፡

ለምሳሌ “አበዛኛውን ሰዓት ለቲቪ ሰጥተህ ከጥናትህ በመዘናጋትህ ውጤትህ ምን ያህል መበላሸቱን ተመልከት?!” ብሎ መገሰጥም  ልጆችን ከአገጓጉል ተግባራት እንዲታቀቡ በመርዳት ማበረታታት ሊሆን የችላል፡፡

8..ለልጅዎ ውጤታማነት ተገቢውን ድጋፍና ክትትል በማድረግ ያበረታቱ፤የአጠናን ዘዴዎቻቸውንም ይፈትሹ

የተለያዩ የመማር ወይም የጥናት ዘዴዎችን ለልጆችዎ በማመላክትም ማበረታታት ይችላሉ፡፡ ልጆች መጽሀፍና ደብተሮቻቸው ላይ አፍጥጠው እንዲታዩ ብቻ ማስገደድ ልጆችን ከማሸማቀቅና ከማሰልቸት የዘለለ ሚና ላይኖረው ይችላል፡፡ ልጆች ጥናታቸውን በተገቢ መልኩ እንዲያካሂዱ የሚመቻቸወን የጥናት ዘዴ ተግባራዊ እንዲያደርጉ ከነሱ ጋር በጋራ መወያየት እና መመካከር ያስፈልጋል፡፡ የልጅዎችዎን መምህርም በዚህ ዙሪያ እያወያዩ ፤ ጥናት ፕሮግራም በማዘጋጀት ክትትልና ድጋፎችን በማድረግ   ማበረታታት ልጅዎን የላቀ ውጤት ባለቤት እንዲሆን  ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡

ስለዚህ ሁላችንም ልጆቻችንን በተገቢው ሁኔታ ሳንታክት በማበረታታት  ስኬታቸው ዕውን ይሆን ዘንድ ሁሌም ከጎናቸው ልንሆን ይገባል፡፡


እናመሰግናለን
ውድ እና የተከበራችሁ ወላጆች/አሳዳጊዎች፡-
ህዳር 27 ቀን 2017 በሁሉም ካንፓሶቻችን ተካሂዶ በነበረው የት/ዘመኑ የመጀመሪያው የወላጅ-መምህር ኮንፍረንስ “ስለልጄ ለመወያየት ከጥሪ በላይ አያስፈልገኝም” በሚል የጥዋት ብርድ ተቋቁማችሁ፤ የስራ ሰዓታችሁም ሳይበግራችሁ ጭምር በነቂስ በመውጣት በሩብ ዓመቱ በት/ቤቶቻችን ልጆቻችሁ ስለነበራቸው አጠቃላይ የትምህርት አቀባበል እና የስነ-ምግባር ሁኔታ ከመምህራን ጋር በመወያየት ላሳያችሁት ቁርጠኝነት እጅግ አድርገን ከልብ እናመሰግናለን፡፡

በዚህ ልክ ተግባብተን እና ተጋግዘን በጋራ ከሰራን በእርግጥም የልጆቻችን ሁለንተናዊ ከፍታ ዕውን ይሆናል፡፡

አል-ዓፊያ ት/ቤቶች ፅ/ቤት




የወላጅ-መምህር ግንኙነት
የወላጅ - መምህር ግንኙነት ልጆች በትምህርታቸው ስኬታማ ይሆኑ ዘንድ በእጅጉ አስፈላጊ ነው፡፡የወላጅ-መምህር ግንኙነት የተማሪን ውጤታማነት ለማረጋገጥ በሁለት ወሳኝ ባለድርሻ አካላት መካከል የሚኖረውን ትብብር ለማጠናከር ከሚረዱ እስትራቴጂዎች አንዱ ወሳኙ ነው፡፡ 

ወላጆች ከልጆቻቸው መምህራን ጋር ያላቸው ግንኙነት ስለሚኖረው ፋይዳ በርካታ ጥናቶች ተካሂደዋል፡፡ ከጥናቶቹ መረዳት እንደሚቻለው በልጆቻቸው ትምህርት ዙሪያ የነቃ ተሳትፎ የሚያደርጉ ወላጆች በዚያው መጠን የልጆቻቸው ውጤትም በከፍተኛ  ደረጃ እንደሚሻሻል ነው፡፡

ውጤታማ የወላጅ - መምህርን ግንኙነት እንዲኖር መጀመሪያ መሆን ያለበት ከልጅዎ መምህር ጋር የሚኖርዎት ውይይት መረጃ መሰብሰብ ላይ ብቻ የሚገደብ አለመሆኑን ጠንቅቆ መረዳት ነው፡፡ የወላጅ-መምህር ግንኙነት ፋይዳው ልጅዎን በትምህርት ቤት ዙሪያ ሳለ የሚታይበትን የባህሪ ሁኔታ በሚመለከት መረጃ ከመሰብሰብም በላይ ነው፡፡

የወላጅ መምህር ግንኙነት ወላጆችና መምህራን አንድን ተማሪ አስመልክተው በት/ቤትም ሆነ ከትምህርት ቤት ውጭ ምን ዓይነት የትምህርት ብቃት(capacity) እንዲሁም ባህሪ(behavior) እንዳለው ጠቅላላ መረጃ የሚለዋወጡበት መድረክ ነው፡፡ አንድ ተማሪ በትምህርት  ቤትም ሆነ በቤት ውስጥ ያለውን ጠንካራ ጎን እንዲሁም መስተካከል ያለበትን ድክመት በግልጽ ተወያይተው የጋራ መፍትሄ የሚያበጁበት ነው፡፡የወላጅ -መምህር ግንኙነት (parent-teacher communication):: ወላጆች ልጆቻቸው ቤት ውስጥ እንዴት ለትምህርታቸው ትኩረት መስጠት እንደሚገባቸው ተገቢውን ምክርና ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው የወላጅ-መምህር ግንኙነት የሚያበረክተው አስተዋፆም በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡

ሆኖም ግን በርካታ ወላጆች ይህን ሁሉ በሚገባ የተረዱት አይመስልም፡፡ እነሱ መስራት የሚገባቸውን ተግባራት ሁሉ የትምህርት ቤት መምህራን ብቻቸውን እንዲወጧቸው ሲጠብቁ በተደጋጋሚ ይስተዋላል፡፡ ልጆች ቤት ውስጥ የሚደረግላቸው የቤተሰብ ድጋፍ እና ክትትል እጅግ ከፍ ያለ ሚና ሲዘነጉ ይስተዋላል፡፡

ስለ ልጆች አጠቃላይ ሁኔታ ከሌላው ሰው ቀድመው የሚረዱት ወላጆቻቸው ናቸው፡፡የልጆችን ባህሪ፣ የትምህርት አቀባበላቸውን እንዲሁም ያላቸውን ዝንባሌ ጠንካራና ደካማ ጎናቸውን ጭምር ከመምህራን በፊት የሚያውቁት ወላጆች ናቸው፡፡ መምህራን የዚህን ያህል ርቀት ተጉዘው የተማሪውን የልብ ትርታ ለመረዳት ብዙ ጊዜ ሊያስፈልጋቸው ይችላል፡፡

አንድ መምህር የሚያስተምራቸውን ተማሪዎች ሁሉ በሚገባ ተረድቶ ተገቢ መፍትሄ ማበጀት እንዲህ ቀላል ስለማይሆን ወላጆች የተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎችን (means of communication) በማመቻቸት የልጆቻቸውን ባህሪ፣ጠንካራ እና ደካማ ጎን ከልጆቻቸው መምህራን ጋር በመወያየት መምህሩ/ሯ ተማሪውን በሚገባ ተረድቶ የተሻለ ድጋፍ ያደርግለት ዘንድ ከነሱ የሚጠበቀውን ካደረጉ በርግጥም ኃላፊነታቸውን ለመወጣት ጥረት አድርገዋል ማለት ይቻላል፡፡

የወላጅ-መምህር የቅርብ ግንኙነት ልጆች በትምህርት ቤትም ሆነ ከዚያ ውጭ ባለ ህይወታቸው ስኬታማነትን ይጎናፀፉ ዘንድ በጣም እስፈላጊ ግብዓት መሆን ይችላል፡፡በወላጅ እና መምህራን መካከል በተማሪው ዙሪያ የሚመክር የግንኙነት መስመር ሲኖር ተማሪውም እሱን የላቀ ደረጃ ለማድረስ ሁኔታዎችን በማመቻቸት ላይ የሚንቀሳቀስ ጠንካራ የትብብር መድረክ መኖሩን እንዲረዳ ያስችለዋል፡፡

በተመሳሳይ ወላጆችና መምህራን በቅርብ እነደሚገናኙና እነደሚወያዩ የተረዱ ልጆች ብዙውን ጊዜ ከሌሎቹ የተሻለ ከፍተኛ የኃላፊነት ስሜት ይሰማቸዋል፤ በውጤታቸውም ብልጫ ይኖራቸዋል፡፡ከዚህም ባሻገር በትምርት ቤት ውስጥም በባህሪያቸው የተመሰገኑ ጎበዝ ተማሪዎች ይሆናሉ፡፡

የወላጅ- መምህር ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችሉ በርካታ መንገዶች አሉ፡፡ የተወሰኑትን እንመልከት፡-

1. በወላጆችና መምህራን መካከል የሚደረጉ ግንኙነቶች ዓላማቸው የልጅዎን የትምህርት ውጤት ማሻሻል መሆኑኑን ይረዱ፡፡ልጅዎ ነገ የተሻለ ዜጋ ሆኖ ይቀረጽ ዘንድ ዛሬ እየተደረገ ያለ ጥረት መሆኑን ለአፍታም ሊዘነጋ አይገባም፡፡

2. ስለ ልጅዎ የትምህርት ውጤት ሲነሳ ጠንካራ ጎን ላይ ብቻ ትኩረቶን ከማድረግ ተቆጥበው መሻሻል የሚገባውንም በመለየት መወያየት በእጅጉ አስፈላጊ መሆኑን ልብ ይበሉ፡፡

3. ስለ ልጅዎ ለመወያየት ሁል ጊዜ ኮንፍረንስ ብቻ አይጠብቁ፡፡ከልጅዎ መምህር ጋር መገናኘትና መወያየት መደበኛ(regular) ተግባርዎ ያድርጉ፡፡ በዚህም ልጅዎ ላይ ጤናማ ያልሆነ ክስተት ቢፈጠርኳ በጊዜ ተረድተው አፋጣኝ የመፍትሄ  እርምጃ መውሰድ ይችላሉ፡፡

እነዚህን ተግባራዊ ማድረግ ከቻሉ ከልጅዎ መምህር ጋር ያልዎት ግንኙነት እየተጠናከረ ይመጣል፤ሁሌም የሚያልሙት የልጅዎ ስነምግባርም ሆነ የትምህርት ውጤት ከፍታም እውን መሆን ይችላል፡፡
ጠንካራ የወላጅ መመምህር ግንኙነት ለተማሪዎች ውጤታማነት


ክፍል 3 (የመጨረሻ ክፍል)

11. ሚዲያ በልጆች የስሜት እና በጤናማ ማህበራዊ ግንኙነት መዳበር ላይ ተፅዕኖ ያደርጋል/IMPACT on SOCIAL-EMOTIONAL DEVELOPMENT/

የስሜት መዳበር እንደሌሎች የመዳበር ዘርፎች በሂደት የሚያድግ ሲሆን እደገቱ ስኬታማ እንዲሆን የቤተሰብ፣ መምህራን እና የሊሎችም ሚና በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ የስሜት መዳበር በአእምሮ መዳበር አማካኝነት የሚከሰት ለውጥ ሲሆን የራስን ስሜት መረዳትና መቆጣጠር መቻልን እንዲሁም ለሌሎች ርህራሄ እና ፍቅር እንዲኖረን የሚዳርግ ነው፡፡ ይህ እድሜ ሲጨምር የበለጠ እየዳበረ የሚሄድ የመዳበር ዘርፍ ነው፡፡ ነገር ግን ለእደገቱ ወሳኝ የሆነ ሁኔታ እስካልተፈጠ ድረስ ለውጡ የሚታሳብ አይደለም ይሉቁንም የራሳቸውን ስሜት ብቻ የሚያስቀድሙ እና ለሌሎች ደንታ የሌላቸው ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ በዚህ ረገድ ሚዲያ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስድ ሲሆን ይህም የሚሆን ለረዥም ሰዓታት በትዕንት መስኮት ጊዜን ማሳለፍ በእውነተኛው ህይወት የሰዎችን ስሜትና ሁኔታ ለመመልከት ጊዜ እንዳይኖራቸው ስለሚያደርግ ነው፡፡

የልጆች ስሜት አወንታዊ በሆነ መንገድ እንዲደብር ከሰዎች ጋር መገናኘትና መስተጋብር መፍጠር አስፈላጊ ነው። ሚዲያ በልጆች ስሜታዊና ማህበራዊ መዳበር ላይ የሚዳርሰው አሉታዊ ተፅዕኖ በተመለከተ በስድሰተኛ ክፍል ተማሪዎች የሰዎችን በፎቶና ቪዲዮ ስሜታቸውን የመረዳት ችሎታ ጥናት ተካሂዶ ነበር፡፡ ከነዚህ ተማሪዎች የተወሰኑት ለአምስት ቀናት ትዕይንቶችን በሚዲያ መስኮት እንዲመለከቱና የተቀሩት ደግሞ ምንም አይነት ትዕይንት በሚዲያ እንዳይከታተሉ በማደረግ ያላቸወን የሰዎች ስሜት የመረዳት ችሎታ ለመለካት የተቻለ ሲሆን ውጤቱ እንደሚያሳየው ለአምስት ቀናት ሚዲያ ያልተከታተሉ ልጆች ከጥናቱ በፊት ከነበራቸው የሰዎችን ስሜት የመረዳት ችሎታ የበለጠ መሻሻል ሲያሱ ለአምስት  ቀናት ሚዲያ የተከታተሉት ግን በተቃራኒው በፊት ከነበራቸው ስሜትን የመረዳት ችሎታ ያነሰ ሁኖ ተመዝግቦል፡፡  ከሚዲያ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ከሰዎች ጋር የሚኖርን የርስበርስ ግንኙነት እንዲቀንስ በማድረግ በሰዎች ላይ የስሜት ምልክቶችን መከታተል እንዳይችሉ እና የሰዎችን ስሜት የመረዳት ችሎታም እንዲቀንስ የሚያደርግ ሲሆን ወጤቱም የስሜት መዳበርን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጎዳ የጥናቱ ተመራማሪዎች አስተውቀዋል፡፡


ሚዲያ የሚያደርሰውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስ እና ለማስቀረት ወላጆች ሊተገብሯቸው የሚገቡ ነገሮች

ሚዲያ በልጆች ሁለንተናዊ እድገት ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስና ያለውን አወንታዊ አስተዋፅኦ ለመጨመር ወላጆች ጥረት ማድረግ እንደሚገባቸው በጉዳዩ ሰፊ ጥናት ያደረጉ ሙህራኖች ያሳስባሉ፡፡ ነገር ግን የሚዲያን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስና አወንታዊ አስተዋፅኦ የማሳደግ ተግባር በወላጆች ብቻ የሚሳካ ተግባር ሳይሆን የመምህራን፣ የሚዲያው ባለቤቶች፣ የመንግስት ፖሊሲ አውጭዎችና አስፈፃሚዎችን ቁርጠኝነት የሚፈልግ ነው፡፡ ከዚህ በታች የቀረቡትን ምክሮች ወላጆች በመተግበር  ሚዲያ የሚያደርሰውን አሉታዊ ተፅዕኖ በመቀነስ አወንታዊ አስተዋፅኦውን ለመጨመር የበኩላቸውን ድርሻ መወጣት ይገባቸዋል፡፡

1. ልጆች በተለይ እድሜያቸው ከሁለት ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት ማንኛውም የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ የሚመለከቱበትን ጊዜ መቀነስ

2. የኤሌክትሮኒክስ መጫወቻዎችን መቀነስና በምትኩ ሌሎች መጫወቻዎችን እንዲጠቀሙ ማድረግ

3. የተለያዩ የፈጠራ ችሎታን የሚያሳድጉ መጫወቻዎችን እንዲጠቀሙ ማበረታታት ለምሳሌ የሚገጣጠሙ፣ የሚደረደሩ እና በተግባር ልጆች እያዩና እየነካኩ ሊጫወቱባቸው የሚያስችሉ መጫወቻዎች

4. በምግብ ሰዓት ቴሌቭዥን መዝጋት እንዲሁም ሌሎች ሚዲያዎችንም እንዳይጠቀሙ ማድረግ መረሳት የለበትም

5. በመተኛ ክፍሎቻቸው ልጆች ቴሌቭዥን ፣ኮምፒውተር፣ የኢንተርኔት አገልግሎት እንዳያገኙና እንዳይጠቀሙ ማድረግ።

6. ልጆችን ከኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎች ውጭ የሆኑ የመዝናኛ ተግባራትን ማለትም ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በማድረግ የሚጫወቱባቸው፣ የአእምሮ ተግባራትን የሚፈልጉ ጨዋታዎች እና ተግባራት በመስራት እንዲያዘወትሩ ማበረታታት

7. ለልጆች እድገት አስፈላጊ የሆኑ እና ትምህርት ሰጭ የሆኑ የቴሌቪዝን ፕሮግራሞች በመምረጥ አንድላይ ከልጆች ጋር ሁነው መመልከት የሚገባ ሲሆን በሚመለከቱበት ጊዜም ልጆች የተመለከቱትን ነገር ምን ያህል እንደተረዱት መጠየቅ፣ ማብራሪያ መስጠት ያስፈልጋል፡፡

8. በሚዲያ አጠቃቀማቸው ወላጆች ለልጆች ጥሩ አርዓያ እና ምሳሌ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ልጆችን በቤት ውስጥ አስቀምጦ የአዋቂ ይዘት ያላቸው ፊልሞች፣ፕሮግራሞች የመመልከት ሁኔታ በየቤቱ ይስተዋላል ፡፡ ይህን በማስወገድ ተገቢ ወደሆኑ ተግባራት ማምራትና ማከናወን ይገባል ፡፡ ለምሳሌ ማንበብ፣ የተለያዩ የወረቀት ስራዎችን መስራት ወዘተ ይህን ልጆች በሚመለከቱበት ጊዜ እነሱም ተመሳሳይ ነገር ማድረግ ይፈልጋሉ ፡፡

9. ወላጆች የራሳቸውን የሚዲያ አጠቃቀም መገደብ በምትኩ ለልጆችም ጊዜን በመመደብ የተለያዩ ታሪኮችን፣ ተረቶችን ማውራትና የልጆችን አዕምሮ የሚያሳድጉ የተለያዩ ጥያቄዎችን እና ተግባራትን መስጠት ይገባል፡፡

10. ወላጆች ከጎረቤቶቻቸው እና ከአካባቢ ሰዎች ጋር ስለልጆቻቸው የሚዲያ አጠቃቀም፣ የሚዲያ ተፅዕኖ በማንሳት መወያየትና የጋራ የሆነ መግባባት ላይ መድረስ ይገባቸዋል፡፡ ምክኒያቱም ልጆች በቤታቸው የሚያዩት ፊልሞች ቢከለከሉ ሌላኛው ቤት ውስጥ በመሄድ የማየት ሁኔታ ስለሚኖር ተመሳሳይ የሆነ መግባባት ላይ መድረስ ይገባቸዋል፡፡

11. ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር በመሆን ስለተለያዩ የቤተሰብ፣ አገራዊ፣ አካባቢያዊ ጉዳዮች በማንሳት የመወያየት ልማድ ሊያዳብሩ ይገባል፡፡

T.A (MA in Developmental       Psychology)

Sources
Heather L. Kirkorian, Ellen A. Wartella, (2008) Media and Young Children’s Learning: 18 / NO. 1 / Retrived in http://
www.futureofchildren.org

Children, Adolescents, and the Media, October 2005 Revised February 2014 by Jane Anderson, MD Revised July 2016 by Jane Anderson, MD

The Impact of Media Use and Screen Time on Children, Adolescents, and Families American College of Pediatricians – November 2016


ክፍል 2…

3. በልጆች ባህሪይና ትኩረት ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ/IMPACT on BEHAVIOR and ATTENTION/

ልጆች በቀን ውስጥ ለረዥትም ሰዓታት የተለያዩ ትዕይንቶችን በሚዲያ የሚመለከቱ ከሆነ በባህሪያቸውና በነገሮች ላይ ትኩረት የማድረግ ብቃታቸውን አሉታዊ ተፅዕኖ በማሳደር ለእንቅልፍ መዛባትን በማስከተል የአእምሮ እድገታቸው ላይ የከፋ ጉዳት ያደርሳል፡፡  እ.አ.አ በ2016 የተደረገ ጥናት እንደሚያሳየው በስክሪን ነገሮችን የመመልከት ጊዜ እና ዝቅተኛ የመኝታ ሁኔታ እና የባህሪ ችግሮች እንደሚያያዙ አረጋግጧል፡፡ በታዳጊ እድሜያቸው ቴሌቪዥንን የሚመለከቱበት የሰዓት ብዛትና ለወደፊት ከሚኖር የትኩረት ችግር ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለ ሲሆን በተለይ እድሜያቸው አንድ እና ሶስት አመት የሆናቸው ልጆች በቀን ውስጥ ለሰዓታት ቴሌቪዥን የሚመለከቱ ከሆነ እነዚሁ ልጆች ሰባት አመት ሲሞላቸው ለትኩረት ችግር እንደሚገጥማቸው በዚህ ጥናት የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

4. ለወሲብ ተጋላጭ የሆኑ ባህሪያቶችን እንዲላመዱ አስተዋፅኦ ያደርጋል ፡፡ IMPACT of MEDIA on SEXUAL RISK BEHAVIORS

በፊልሞች፣ በቴሌቪዥን፣ እና በሙዚቃ ክሊፖች በአብዛኛው ወሲባዊ መልዕክቶች በግልፅ የሚሰራጩ ቢሆነንም አነዚህ መልዕክቶች የተሳሳቱና ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ የሚመሩ ናቸው፡፡ እንዳለመታደል ሁኖ እነዚህ መልዕክቶች በታዳጊዎች እውነተኛ እንደሆኑ ተድሮጎ ተቀባይነት ማግኘታቸው ነው፡፡ በሚዲያ የሚተላለፉ ፕሮግራሞች እና የማስታወቂያ ይዘቶች በብዛት ወሲብ ነክ ናቸው፡፡ ወጣቶችም ሚዲያን እንደ ዋነኛ የወሲባዊ ባህሪያት የመረጃ ምንጭ አድርገውታል፡፡  በዚህም ምክንያት ታዳጊዎች ባገኙት የተሳሳተ የወሲብ መረጃ በራሳቸው ህይወት ያለጊዜያቸው በመሞከር ለተለያዩ ችግሮች ይጋለጣሉ፡፡
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ወሲባዊ ይዘት የተቀላቀለባቸው የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን አብዝተው የሚያዩ ወጣቶች ከማያዩ ወጣቶች የበለጠ ያለጊዜያቸው የተለያዩ ወሲባዊ ተግባሮችን ለመጀመር ይነሳሳሉ፡፡ታዳጊ ወጣቶች ከፍተኛ ደረጃ የወሲብ ይዘት ላለው ነገር የተጋለጡ ከሆነ ከሌሎች ካልተጋለጡ ወጣቶች  ጋር ሲነፃፀሩ ሁለት እጥፍ በቀጣዮች ሦስት አመታት የማርገዝ እድል አላቸው፡፡ አነዚህ ጥናቶች በተጨማሪ እንደሚያሳዩት ወሲብ ነክ የንግግር ልውውጥ በቴሌቪዥን መስኮት የሚመለከቱትም ልክ ወሲባዊ ተግባራትንም እንደሚመለከቱ ወጣቶች ተመሳሳይ ችግር ይጋለጣሉ፡፡

5. አልኮልና ሲጃራ ተጠቃሚነት ያስከትላል፡፡ /IMPACT on TOBACCO and ALCOHOL USE/

ከመጠን ያለፈ የቴሌቪዠን፣ ፊልሞችን እንዲሁም የኮምቢውተርና የቪዲዮ ጌሞችን መመልከት ለአልኮልና ሲጃራ ሱሰኝነትን ያስከትላል፡፡ በቅርቡ የተሰራ ጥናት እንደዘገበው ወላጆች ልቅ የሆነ ፊልሞችን ልጆቻቸው እንዳይመለከቱ በማገዳቸው ምክንያት ሲጃራ ለመጨስ የመመከር ሂደት መቀነሱ ተረጋግጦል፡፡

6.በእንቅልፍና አመጋገብ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል/ IMPACT on SLEEP and NUTRITION/

ሚዲያን መጠቀም በቂ እንቅልፍ እና ጥሩ እንቅልፍ እንዳይኖር ማለትም በእንቅልፍ ልብ መንቃት፣ ቅዠት፣ የተዛባ የእንቅልፍ ልማድ እንዲከሰት ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ይህም በልጆች በሽታን የመቋቋም ችሎታን እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ የምግብ የመፈጨት ሂደትን በማስተጓጎል ልጆችን ከመጠን ላለፈ ውፍረት ይዳርጋቸዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ልጆች በሽታን የመቋቋም ብቃታቸውን እንዲቀንስ እና ለተለያዩ በሽታዎች በቀላሉ የመጠቃት እድላቸው ከፍተኛ እንዲል የሚያደርግ ሲሆን የትምህርታቸው ውጤታቸውም  እንዲቀንስ አሉታዊ አስተዋፅኦ ያደርጋል ፡፡
በአንድ ጥናት ልጆቻቸው በመዋለ ህፃናት የሚማሩ 495 ወላጆች ስለልጆቻቸው ቴሌቪዥን የመመልከት ልማድና እና የመኝታ ሁኔታ ተጠይቀው ነበር፡፡ ከነዚህ  ውስጥ 25 ፐርሰንት የሚሆኑት ወላጆች የተገኘው መረጃ በልጆች መኝታ ክፍል ቴሌቪዥን እንዳለ አሳይቶል፡፡ ይህም ልጆች ለረዥም ሰዓታት ቴሌቪዥን የመመልከት ልማድ እንዲኖራቸውና በቂ የእንቅልፍ ጊዜ እንዳይኖራቸው በማድረጉ ነው፡፡ የእንቅልፍ መዛባት ችግር የሚያያዝ የበለጠ የበዛበት ምክንያት የቴሌቪዥን ምልከታው የጨመረው በልጆቹ መኝታ ቤት በመገኘቱ ምክንያት እንደሆነ የጥናቱ ተመራማሪዎች  ተናግረዋል፡፡
የእንቅልፍ ማጣት ችግር ከመጠን በላይ ለሆነ ውፍረት፣ ከስኮር በሽታ፣ ከትምህርት ችግር፣ እና ከተለያዩ የባህሪ ችግሮች ጋር እንደሚያያዝ ጥናቶች በተደጋጋሚ ይዘግባሉ፡፡

7. ሚዲያ በትምህርት ውጤት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ያሳድራል /IMPACT on ACADEMIC PERFORMANCE

ከመጠን ያለፈ የሚዲያ መጋለጥ በትምህርት ውጤት ላይ አሉታዊ የሆነ ተፅዕኖ እንደለው ይታወቃል፡፡ ይህን አስመልክቶ ዘመሪመን እና ክሪስታኪስ የተባሉ ተመራማሪዎች አስከሰባት አመት የሚሆናቸውን ታዳጊ ልጆች የቴሌቪዥን ምልከታ በአስተሳሳብ እና በአእምሮዊ እድገታቸው ላይ የሚሳድረውን ተፅዕኖ ለመገምገም የሚከሩ ሲሆን የግምገማ ውጤቱ እንደሚያሳያው ልጆች ሶስት አመት ከመሆናቸው በፊት ለብዙ ሰዓታት በቀን ውስጥ ቴሌቪዥን የሚመለከቱ ከሆነ በአእምሮ እድገታቸው ላይ የከፋ ጉዳት እንደሚያደርስና ነገሮችን አንብቦ ለመረዳት እንደሚቸገሩ እና በትምህርታቸውም ዝቅተኛ ውጤት እንደሚያሰመዘግቡ ጠቁመዋል፡፡

8. ሚዲያ ለድብርት ያጋልጣል/ IMPACT on DEPRESSION/

ትዕይንቶችን በሚዲያ መስኮት ለረዥም ጊዜ መጠቀም ከድብርት ጋር እንደሚያያዝ ብዙ ጥናቶች አሳይተዋል፡፡ በሃገረ ዴንማርክ በተመሳሳይ የዕድሜ ክልል የሚገኙ 435 ወጣቶች ላይ ለረዥም ጊዜ በተካሄደው ጥናት እንደሚያሳየው በእያንዳንዱ ተጨማሪ ሰዓት ወይም ቀን ቴሌቪዥን መመልከት በጎልማሳነት የእድገት ወቅት ለከፍተኛ ድብርት እንደተጋለጡ ተጠቁሞል፡፡

9. ሚዲያ ለጠብ አጫሪነትን እና ለሁከት ፈጣሪነት ያጋልጣል/ IMPACT on AGGRESSIVE BEHAVIOR and VIOLENCE/

ጥናቶች እንደሚያሳዩት በትዕይንት መስኮት ሁከትና ብጥብጥ ያለቸውን ነገሮች መመልከት በእውነተኛው ህይወትም የጠብ አጫሪነት እና ሁከት ፈጣሪነት ባህሪያት እንዲጨምር ምክንያት ሊሆን እንደሚችል ነው፡፡ በኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎች የሚተላለፉ ፊልሞችና ድራማዎች በአብዛኛው በይዘታቸው የጠብ አጫሪነት፣ የሁከት፣ የጥፋት፣ የድብድብ፣ ወዘተ ትዕንቶችን የተካተቱበት በመሆኑ የልጆችን አስተሳሰብ ከፍተኛ ተፅዕኖ በማሳደር እውነተኛው አለም የጥፋትና የሁከት እንደሆነ እንዲያምኑ ምክንያት በመሆን ለጠብ አጫሪነትና መሰል ባህሪያትን እንዲያሳዩ ምክያት ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ሁሉም ህፃናት እንደዚህ አይነት ባህሪያት ያሳያሉ ማለት ሳይሆን ዝንባሌ እንዲኖራቸው ምክንያት ሊሆን ይችላል ለማለት ነው፡፡ ሌሎች ነገሮች ለምሳሌ በአካባቢያቸው የጠብ አጫሪነትና ሁከትን የሚያበረታቱ ሁኔታዎች ከተጨመሩ ከሌሎች ልጆች አንፃር የጎላ የባህሪ ችግሮችን የማሳየት እድላቸው ከፍተኛ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

ከቴሌቪዥን በተጨማሪ በስማርት ስልኮችና እና በኮምፒውተር ላይ የሚጫኑ ሁከት እና ብጥብጥን የሚያንፀባርቁ ጌሞች/ጨዋታውች/ በልጆች ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖን ያሳድራሉ፡፡
.....ክፍል 3 ይቀጥላል


ሚዲያ በልጆች አእምሮዊ፣ ስነልቦናዊ፣ ስሜታዊ፣ ማህበራዊ እድገት ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ተፅዕኖዎች ለመቀነስ ወላጆች ሊተገብሯቸው የሚገቡ ምክሮች።

ክፍል 1…

እንደሚታወቀው በሀገራችንም ሆነ በዓለማችን ሚዲያ በልጆች አስተዳደግ እና ሁለንተናዊ ማንነት ላይ ከባድ አደጋ ከሆነ ሰነባብቷል፡፡በየቤቱ በርካታ ልጆችን አንዳንዴ አዋቂዎችን ሳይቀር አጉል ጠልፎ እየጣለ አያሌ ቤቶችን እያናጋ፤ ሰላምንም እያደፈረሰ ይገኛል፡፡ታዲያ እኛም ለዛሬ በዚህ ዙሪያ ጠቃሚ ግንዛቤ ያስጨብጣል ያልነውን መረጃ ለናንተ ለወላጆች እነደሚከተለው አቅርበነዋል።

መረጃው ጥናትን መሰረት አድርጎ በዘርፉ በለሙያ የቀረበ በመሆኑ ሁላችንም አንብበን ከልጆቻችን ጋር በመወያየት የመፍትሔ አካል መሆን ይጠበቅብናል።
መልካም ንባብ፡፡

የመገናኛ ሚዲያዎች በሁለት ዋና ክፍሎች የሚመደቡ ሲሆን አንደኛው ኤሌክትሮኒክ ሚዲያ በመባል የሚጠራ ሲሆን እንደ ቴሌቪዥን፣ ኮምፒውተር፣ ስማርት ስልኮችን፣ ወዘተ በመጠቀም  ፊልሞችን፣ ድራማዎችን፣ ፕሮግራሞችን፣ ጨዋታዎችን፣ ሙዚቃዎችን እና የሙዚቃ ኪሊፖችን የሚተላለፉበት ነው፡፡ ሌላኛው ፕሪንት ሚዲያ የሚባል ሲሆን በወረቀት ላይ የሰፈሩ ፁህፎች፣ ታሪኮች፣ ዜናዎች፣ ልቦለዶች፣ ወጎች፣ መረጃዎችን፣ ወዘተ የሚያካትት ነው፡፡

ሁለቱም የሚዲያ አይነቶች በልጆች ላይ አወንታዊ እና አሉታዊ ተፅዕኖዎችን ያሳድራሉ፡፡ አዎንታዊ ተፅዕኖዎች ለምሳሌ የልጆችን ስነምግባር፣ ስነልቦና፣ የፈጠራና ችግር የመፍታት ችሎታዎች የሚያሳድጉ የተለያዩ ትምህርቶች፣ ምክሮች፣ መረጃዎች በሚዲያ አማካኝነት ሲተላለፉ ነው፡፡

ሚዲያ በዚህ ትውልድ ልጆችና ወጣቶች ዘላቂ ተፅእኖ አለው፡፡ ምክያቱም በሚዲያ የሚተላለፉ ይዘቶች በቀላሉ መደጋገም ስለሚችሉ በቀላሉ በልጆችና በወጣቶች አእምሮ የመቀመጥ እድላቸው ሰፊ ነው፡፡ የሚቀርቡት ይዘቶች የልጆችን ትኩረት ለመሳብ በማራኪ መልኩ መቅረባቸው ሌላኛው ምክንያት ነው፡፡
የኤሌክትሮኒክ ሚዲያ በተለይ ቴሌቪዥን በልጆች ላይ  የሚያሳድረው ጉልህ ተፅዕኖ መተቸት የተጀመረው ቆየት  ላለ ጊዜ ነው፡፡ ከነዚህም ትችት ውስጥ አንደኛው በለጋ እድሜያቸው ልጆች ለሚዲያ መጋለጥ የአስተሳሰብ እድገታቸው እና የትምህርት ውጤታቸው ላይ የሚያስድረው ተፅዕኖ ነው፡፡ በአጠቃላይ ከተለያዩ ጥናታዊ ውጤቶች የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ሚዲያ በልጆች ሁለንታዊ መዳበር ላይ የሚከተሉትን አሉታዊ ተፅዕኖዎች ያሳዳራል፡፡

እነሱም፡-
1. ሚዲያ ታዳጊ ልጆች ጤናማ ተግባራት ለማከናወን የሚኖራቸውን ጊዜ ይቀንሳል/ Media use decreases time spent in more healthful activities/

ጤናማ የሆኑ ተግባራት የምንላቸው ከቤተሰብ ፣ ከጓደኝ ጋር የሚኖረን  መስተጋብር በመስተጋብሩም ውስጥ ልጆች የሚያገኞቸው ጠቃሚ ነገሮች ለምሳሌ የፈጠራ ችሎታ መዳበር፣ ችግሮችን የመፍታት ክህሎት፣ አካላዊ እንቅስቃሴ ፣ የማንበብ፣ በቤት ውስጥ ወላጆችን ማገዝ፣ በቂ እንቅልፍ ማግኝት ናቸው፡፡ እነዚህ ጠቃሚ ተግባራት አብዛኛውን የልጆች ጊዜ በመውሰድ ቀድመው መዳበር የሚገባቸው ሲሆን ለብዙ ሰዓት ሚዲያዎችን መጠቀም ለነዚህ ተግባራት የሚኖርን ጊዜ እንዲቀንስ አስተዋፅኦ ያደርጋል፡፡

2. ሚዲያ በልጆች የጨዋታ እና የመዳበር ሁኔታ ላይ ተፅዕኖ ያሳድራል፡፡ /IMPACT on PLAY and DEVELOPMENT/

ታዳጊ ልጆች የወላጆቻቸውን ስልኮች በመጠቀም ለረዥም ሰዓት በስክሪን ላይ መጋለጣቸው በጣም እየጨመሩ በመምጣቱ ተመራማሪዎች በታዳጊ ህፃናት ላይ የሚኖረውን አሉታዊ ተፅዕኖ መገምገም ጀምረዋል፡፡ ለምሳሌ በቅረቡ የወጡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ልጆች ተገቢ ክህሎቶችን፣ የሚጠበቁ ተግባራትን ፣ ችሎታወችን ከማከናወን ይልቅ የስክሪን ላይ የተመለከቷቸውን የገፀ-ባህርያት ድርጊቶችን፣ እንቅስቃሴዎችና ንግግሮችን አስመስለው ማሳየት እንደሚቀናቸውና በእድሜያቸው የሚጠበቁ መሰረታዊ ክህሎቶችንና ተግባራትን ለምሳሌ ጫማቸውን እራሳቸውን ችለው ማሰር፣ ብስክሌት መንዳት፣ መዋኘት፣ ፊታቸውና እጃቸው መታጠብ፣  መፀዳዳት ወዘተ ላይ ዝቅተኛ የሆነ ክንውን አሳይተዋል፡፡

የሚገርመው በአንድ መዋለ ህፃናት ላይ የተሰራ ጥናት እንደሚያሳየው በጥናቱ ከተሳተፉት ህፃናት 58% የሚሆኑት የኮምፒተር ጨዋታዎችን እንዴት መጫወት እንዳለባቸው ህጎችን ጠንቅቀው የሚያውቁ ቢሆኑም ከነዚህም ውስጥ ጫማቸውን እንዴት ማሰር እንደሚችሉ የሚያውቁት 9% ብቻ ናቸው፡፡ ይህ የሚያሳየው ልጆች ለሚዲያ ያላቸው መጋላጥ በመጨመሩ እና የልጆች ሁለንተናዊ መዳበር አሉታዊ ተፅዕኖ በማሰደሩ ነው፡፡  ምንም እነኳን ልጆች የኤሌክትሮኒክ ሚዲያዎችን እንደ ቴሌቪዥን ጨዋታዎች፣ ስማርት ስልኮች፣ ኮምፒውተርን ላይ በተጫኑ ጨዋታዋችን በመጠቀም የሚጫወቱ ቢሆኑም እነዚህ ጨዋታዎች የልጆችን ከማዝናናት ባሻገር የልጆችን አእምሮ፣ አስተሳሰብና የፈጠራ ችሎታ የሚያሳድጉ አይደሉም፡፡ ይልቁንም በተጨባጭ እውነታና በአካባቢያቸው የሚገኙ ነገሮችን በመጠቀም ልጆች እንዲጫወቱ ማድረግ  የልጆችን ሁለንተናዊ እደገት እንዲጨምር ያደርጋል ምክንያቱም ልጆች በቀጥታ ከመጫወቻዎቹ ጋር ያላቸው መስተጋብር ሰፊ እና ሁሉንም የስሜት ህዋሶቻቸው በንቃት መረጃን መሰብሰብ ስለሚችሉ ነው፡፡ በተቃራኒው በሚዲያዎች አማካኝነት የሚጫወቱ ከሆነ ያላቸው ተሳትፎ ዝቅተኛ ስለሚሆን በጨዋታው ብቻ ተወስነው ሌሎች ለእድገታቸው አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ተግባሮችን ማከናወን ስለማይችሉ መረጃ ተቀባይ ብቻ እንዲሆኑ ስለሚያደርጋቸው ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ በሃገረ እንግሊዝ በመምህራን ማህበር አማካኝነት በቅድመ የልጆነት ወቅት የሚገኙ ታዳጊ ልጆች በኤሌክትሮኒክ ሚዲያ ብዙ ሰዓት መጠቀማቸው መሰረታዊ ክህሎቶችን ማከናወን ላይ ዝቅተኛ ችሎታ እንደሚያሳዩ አበክረው ይመክራሉ፡፡ እነዚህ ልጆች የተለያዩ ነገሮች በመደርደር መጫወትና እንዲሁም ለተለያዩ የትምህርት ቤት ተግባራትን ለመስራት ብዕርና እርስሳስ መጠቀም በደንብ እንደማይችሉ ጥናታቸው አረጋግጧል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ ሁለት ጥናቶችን በአካባቢ በሚገኙ ቁሳቁሶች በመጠቀም የሚዘጋጁ መጫወቻዎች ለታዳጊ ልጆች የቋንቋ መዳበር ጠቃሚ እንደሆኑ አረጋግጠዋል፡፡የመጀመሪያ ጥናት እደሜያቸው ከ18 እስከ 30 ወር የሆናቸው ታዳጊ ህፃናት ከወላጆቻቸው ጋር ነገሮችን በመደርድር የሚጫወቱት የቋንቋ ወጤታቸው የተሻለ ሲሆን በሌላኛው ጥናት የኤሌክትሮኒክ ሚዲያ የሚጠቀሙ ታዳጊ ልጆች ዝቅተኛ የንግግር የቋንቋ ክህሎት አሳይተዋል፡፡

አዋቂዎች መረጃን ከቴሌቪዥን ላይ በመመልከት የሚፈልጉት መረጃ መርጠው መውሰድ የሚችሉ ሲሆን የወሰደቱን መረጃ እውነተኛ ይሁን ምናባዊ መለየት ይችላሉ፡፡ ልጆች ግን ያዩት ነገር መርጠው መውሰድ አይችሉም፡፡ የሚያዩትን ነገር እውነተኛ በገሃዱ አለም ያለ ይሁን በምናብ የተፈጠረ መሆኑን መለየት ይቸገራሉ፡፡ በዚህም ምክንያት ታዳጊ ህጻናትም በቴሌቨዥን መስኮት ያዩትን ባህሪዎች ትርጉም ባለው መልኩ  አስመስለው ማሳየት ይችላሉ፡፡ ታዳጊ ልጀች በምስል ለሚታዩ ነገሮች ከፍተኛ ትኩረት የሚያደርጉ ሲሆን በአብዛኛውም ከምስሉ ጋር የቀረበውን ታሪክ ወይም ንግግር ለመረዳት ይቸገራሉ፡፡ ታዳጊ ልጆች በቴሌቪዥን መስኮት ያዩዋቸው የሚያሰፈሩ ምስሎች በወስጠ አእምሮዋቸው ለረዥም ጊዜ መቀመጥ ስለሚችሉ ለተለያዩ የመኝታ ችግሮችና ለቅዠት ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

........ክፍል 2 ይቀጥላል


PREPARATION AND EXAM DAY CHECKLIST
All of the points below have been shown to help students do their best in exams. Think of the reasons for each of the statements. Discuss them with your children.
Well before the exams,
•  Students should check the exam timetable to make sure they arrive for exams on the correct day, at the correct time. This is entirely their responsibility.
•  Students should make a revision/study timetable.
•  Students should revise every part of their lessons.
•  Students should make notes and summaries of the important parts.
•  Students should find out about the exam. (Timing, number of questions, choice etc.)
•  Students should have extra pencils or pens etc. 
•  Students should eat regularly and get enough sleep before exams.

The evening before the exam
•  Students should not plan to revise a lot of work. This bulk of their revision should have been completed earlier.
•  Students should read over their summaries
•  Students should try to relax
•  Students should get everything ready for the next day; equipment, clothes, etc.
•  Students should get a good night’s sleep.

The day of the exam
•  Students should get up in plenty of time and try not to be rushed.
•  Students should not do revision other than looking over summaries of important points.
•  Students should eat a good breakfast.

During the exams
•  Students should check that the exam paper they are given is the right one.
•  Students should write their name on their exams / answer sheets.
•  Students should read all the questions.
•  Students should check the time regularly during the exam.
•  Students should check the back page of all exam papers to ensure they have finished all of the questions.
•  Students should leave enough time to read over all of their answers.
WISHING OUR STUDENTS THE BEST OF LUCK ON THEIR EXAMS!




ለፈተና ለመዘጋጀት የሚጠቅሙ 9 ነጥቦች

ውድ እና የተከበራችሁ የት/ቤቶቻችን ወላጆች፡-

ከሰኞ ህዳር 16 ቀን 2017 ጀምሮ ትምህርት ዘመኑ የመጀመሪያው መንፈቀ-ዓመት አጋማሽ ፈተና መሰጠት ይጀምራል።ታዲያ በዚህ ወቀት ለተማሪዎች የፈተና ዝግጅት  ጠቃሚ መሆናቸውን በባለሙያዎች የሚመከሩ 9 ጠቃሚ ነጥቦችን ልንነገራችሁ ወደናል፤መልካም ንባብ፡፡

1. ቁርስና ጠቃሚ ምግቦች
ሰውነታችን በአግባቡ ሥራውን እንዲሰራ ኃይል ያስፈልገዋል፤ አንጎላችን ደግሞ ትኩረት እንዲኖረውና የማስተዋል አቅማችን እንዲጨምር በቂ የሆነና ያልተቆራረጠ የኃይል አቅርቦት ይፈልጋል።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቁርሳቸውን ተመግበው ወደፈተና የሚገቡ ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ያስመዘግባሉ። የተመጣጠነ ምግብ ተመግበው ለፈተና የሚቀርቡት ደግሞ የበለጠ የማስታወስና የማስተዋል አቅም ይኖራቸዋል።

ስለዚህ ሁሌም ቢሆን ፈተና ያለባቸው ተማሪዎች እንደ የገብስ ገንፎ፣ ዳቦ፣ ሩዝና ድንች ያሉ በካርቦሃይድሬት የበለጸጉ ምግቦችን በቁርስ ሰዓት ተመግበው ቢወጡ ይመከራል።
እርጎ፣ እንቁላል፣ አሳ፣ ጎመን፣ ቲማቲምና አቮካዶ ዓይነት ምግቦችም እጅጉን ጠቃሚ ናቸው።

2. በጠዋት ወደ ጥናት መግባት
ሁሌም ቢሆን ነገሮችን አስቀድሞ መጀመርን የመሰለ ነገር የለም። ለፈተናም ቢሆን ጥናት በጠዋት ተነስቶ መጀመር በፈተና ወቅት የተረጋጋ መንፈስ እንዲኖረን ይረዳል።
ጠዋት ላይ ጭንቅላታችን እረፍት አድርጎ በአዲስ መንፈስ ሁሉንም ነገር ስለሚጀምር፤ በዚህ ሰዓት ማጥናት ውጤታማ ያደርጋል። በተለይ ደግሞ የክለሳ ጥናቶችን ለከሰዓት ማሸጋገር ተገቢ አይደለም።

3. ከፋፍሎ ማጥናት
የክለሳ ጥናትን ከፋፍሎ ማካሄድን የመሰለ ነገር የለም። አንድ የትምህርት ዓይነት ላይ 10 ሰዓት ሙሉ ከማሳለፍ በየቀኑ አንድ ሰዓት በማጥናት በ10 ቀን መጨረስ ይበልጥ ውጤታማ ያደርጋል።
ያጠናነውን ነገር ለማስታወስና በቀላሉ ለመሸምደድ ጭንቅላታችን ጊዜ ይፈልጋል። ከፋፍሎ ማጥናት ደግሞ ለዚህ ፍቱን መድሃኒት ነው። ከፋፍሎ ማጥናት እጅግ ውጤታማው መንገድ እንደሆነም በመላው ዓለም የተሰሩ የተለያዩ ጥናቶች ያለመክታሉ።

4. ራሳችሁን ቶሎ ቶሎ ፈትኑ
የሥነ አዕምሮ ጥናት ባለሙያዎች እንደሚሉት የማስታወስ ችሎታን ለማዳበርና በራስ መተማመናችንን ለመጨመር ራስን መፈተን ውጤታማ ያደርጋል።
ከዚህ በተጨማሪ እየተዘጋጀንበት ያለነውን ጉዳይ በደንብ እንድናውቀው ከማድረጉ በተጨማሪ የረሳናቸው አልያም የዘለልናቸው ርዕሶችን ለመለየት ይረዳናል።

5. መምህር መሆን
ከባዱን የክለሳና ራሳችሁን የመፈተን ሥራውን ካከናወናችሁ በኋላ ጓደኞቻችሁን ሰብሰብ አድርጋችሁ በጭንቅላታችሁ የሚመጣውን ነገር በሙሉ ንገሯቸው። ራሳችሁን በመምህር ቦታ አድርጋችሁ እውቀታችሁን ለማካፈል ሞክሩ።
ምን ያህል እንደምታስታውሱ ለማወቅ ከመርዳቱ በተጨማሪ ጓደኞቻችሁንም ትጠቅሟቸዋላችሁ።

6. ከተንቀሳቃሽ ስልኮች መራቅ
ስልኮች በጣም ብዙ ጥቅም አላቸው። ነገር ግን በጥናት ወቅት ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው ነው የሚያመዝነው። በተለይ ደግሞ ማህበራዊ ሚዲያዎችን የምትጠቀሙ ከሆነ።
ብዙ ጥናቶች እንዳረጋገጡት ብዙ ጊዜያቸውን ስልካቸው ላይ የሚያሳልፉ ተማሪዎች የትምህርት ውጤታቸው ሁሌም ቢሆን ዝቅ ያለ ነው።

7. ቋሚ እረፍትና አካላዊ እንቅስቃሴ
ውጤታማ የክለሳ ጥናት ማለት እረፍት አልባ ጥናት ማለት አይደለም። በጥናታችን መሀል መሀል ላይ ጥሩ አየር ለማግኘትና ሰውነታችንን ለማፍታታት ወጣ ብሎ እንቅስቃሴ ማድረግ የማስታወስ ችሎታችንን በደንብ ከፍ ያደርገዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ሰውነታችን እና ጭንቅላታችን በእጅጉ የተሳሰሩ በመሆናቸው እንቅስቃሴ ስናደርግ የደም ዝውውራችን ይስተካከላል፤ ይህ ደግሞ በቂ ኦክስጅን ወደ ጭንቅላታችን እንዲሄድ ይረዳል።
አካላዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ተዘርዝሮ የማያልቅ ጥቅሞች ያሉት ሲሆን ጭንቀትን መከላከልና በራስ መተማመንን መጨመር ከነዚህ መካከል ይጠቀሳሉ።

8. እንቅልፍ
ከፈተና በፊት ያለችውን ምሽት ጥሩ እንቅልፍ አግኝቶ ማሳለፍ ተገቢ እንደሆነ ብዙዎች ይስማማሉ። ነገር ግን ጥሩ እንቅልፍ ፈተናው ሲቃረብ ብቻ ሳይሆን ከሳምንታት በፊት ገና ዋናው ጥናት ሲደረግና ክለሳ በሚደረግበት ወቅትም እጅግ ወሳኝ ነው።
በጠዋት ተነስቶ ውጤታማ የክለሳ ጥናት ካደረጉ በኋላ በጊዜ ተኝቶ ጥሩ እንቅልፍ ማግኘት ሰውነታችንና ጭንቅላታችን በደንብ ተግባብተው እንዲሰሩ ይረዳቸዋል። ሌሊቱን በሙሉ ለማጥናት ሙከራ አታድርጉ ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች። ምክንያቱም ራሳችን ላይ ጫና እያሳደርን ስለሆነ።

9. መረጋጋትና በጎ በጎውን ማሰብ
ተማሪዎች እስካሁን የተዘረዘሩትን ነገሮች ሁሉ ተግባራዊ ካደረጉ ምንም የሚያሳስባቸው  ነገር ሊኖር አይገባም። ዘና ብለው ወደ ፈተና መግባት ብቻ ነው የሚቀራቸው፡፡ ምናልባት ጥሩ ያልሆነ አጋጣሚ ቢገጥማቸው እንኳን እሱን ረስተው  ለቀጣዩ በጥሩ መንፈስ ለመዘጋጀት መሞከር ነው ፡፡

ምንጭ፡BBC NEWS አማርኛ
በመጠኑ ተስተካክሎ የተወሰደ

ውድ ወላጆቻችን፡-
በእያንዳንዱ የፈተና ጊዜ ልጆቻችሁን ማገዝ እና ማበራታታት እንዲሁም  ሞራል  መስጠት አትርሱ።


ውድ ተማሪዎቻችን ፡-

መልካም ፈተና!!!


ለአል-ዓፊያ ወላጆች በሙሉ

የተማሪዎች ክፍያ የሚከፈለው በዳሽን ባንክ በተማሪዎች መለያ ቁጥር(በተማሪዎች ስም) ብቻ መሆኑን ከወዲሁ እናሳውቃለን።

ክፍያውን ከከፈሉ በሗላ የባንክ ስሊፑን ማምጣት ሳይጠበቅባችሁ ደረሰኙ ከት/ቤት ተማሪዎች መውስድ ይችላሉ::


Репост из: የአል-ዓፊያ ት/ቤቶች ማህበረሰብ_Al-Afia Community
የሁለተኛው ሩብ ዓመት የተማሪዎች የት/ቤት ክፍያን ይመለከታል

ውድ ወላጆች የሁለተኛው ሩብ ዓመት ክፍያ ከኅዳር 15 እስከ ኅዳር 30 ባለው ጊዜ ዉስጥ ተከፍሎ መጠናቀቅ ይኖርበታል::

በመሆኑም በክፍያው  ቀናት  ከሚከሰት አላስፈላጊ መጨናነቅ  ለመቀነስ ክፍያውን አሁኑኑ መክፈል ይችላሉ::

ክፍያው በተማሪዎች መለያ ቁጥር በባንክ ሲሆን የተማሪው/ዋ መለያ ቁጥር ከት/ቤት በወላጅ መምህር መፅሐፍ የሚላክሎት ይሆናል::

ለበለጠ መረጃ ልጅዎን የሚያስትምሩበትን ቅርንጫፍ ት/ቤት መጠየቅ ይችላሉ::

የአል ዓፊያ ት/ቤ/ጽ/ቤት


Репост из: የአል-ዓፊያ ት/ቤቶች ማህበረሰብ_Al-Afia Community
#WerabeUniversity

ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ መርሐግብር ተማሪዎች እንዲሁም በ2016 ዓ.ም በወራቤ ዩኒቨርሲቲ በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው ህዳር 19 እና 20/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

☞ ከ8ኛ-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
☞ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣
☞ አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
☞ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

በአንደኛ ሴሚስተር ምዝገባ ፈፅማቹ በተለያዩ ምክንያቶች ትምህርታችሁን ያቋረጣችሁ ተማሪዎች፥ የዊዝድሮዋል ቀሪ ፎርማችሁን በመያዝ ህዳር 23 እና 24/2017 ዓ.ም መመዝገብ ይኖርባችኋል፡፡

በ2017 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደፊት ይገለፃል ተብሏል።

ለዘንድሮ ፍሬሽማን ተማሪዎች 👇
https://t.me/atc_news/25985

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news



Показано 20 последних публикаций.