..
...እብዱ ዮሐና
ምዕራፍ አራት(4)
ዮሐና የእግዚአብሄር ልጅ አካል ላይ በደረሰው ስቃይ አብሮት ሲሰቃይ፣ እንዲሁም በመንፈስ አብሮት በደስታ ሲሞላ | ሰዓታት አለፉ:: ከተቀመጠበት ቦታ ሲነሳ እኩለቀን ሆኖ ነበር፡፡ ፀሀይዋ አሁን አናት ትበሳለች፡፡
ዙርያውን ተመለከተ፡፡ ነገር ግን ከብቶቹን ማየት አልቻለም፡፡ በዚያ ለጥ ባለ የለምለም ሳር ሜዳ ላይ እንዴት ከዓይኑ ሊሰወሩ እንደቻሉ ግራ ተጋብቶ በየቦታው ፈለጋቸው:: ከመስኮቹ ባሻገር እንደ እጅ መዳፍ መስመሮች ከሚጥመዘመዘው ጐዳና አጠገብ ሲደርስ ከርቀት ጥቁር ልብስ የለበሰ አንድ ሰው በአትክልት ስፍራዎቹ መሀል ቆሞ አየ፡፡ በጥድፊያ ወደ ሰውየው አመራ።
ወደ ሰውየው ቀርቦ ሲመለከት፣ ከገዳሙ መነኮሳት አንዱ መሆናቸውን አወቀ፡፡ ዮሐና ጐንበስ ብሎ እጅ ከነሳ በኋላ፣ ከብቶቹን በዚያ የአትክልት ሥፍራ ውስጥ አይተው እንደሆነ ጠየቃቸው፡፡
መነኩሴው ንዴታቸውን ለመቆጣጠር እየሞከሩ ትክ ብለው አዩትና በኃይለ ቃል «አዎን አይቻቸዋለሁ፡፡ እዚያ ማዶ ናቸው፡፡ ና ተከተለኝ፡፡ የት እንደሚገኙ አሳይሃለሁ» አሉት፡፡
ዮሐና መነኩሴውን እስከ ገዳሙ ድረስ ተከተላቸው፡፡ በገዳሙ ውስጥ ከብቶቹን በአንድ ሰፊ ግርግም ውስጥ በጠፈር ታስረው በአንድ ሌላ መነኩሴ ሲጠበቁ አያቸው፡፡ መነኩሴው እንስሳቱ በተንቀሳቀሱ ቁጥር የሚመልሱበትና የሚዥሉጥበት ትልቅ ዱላ ይዘዋል፡፡ ዮሐና ከብቶቹን ለመውሰድ ወደዚያ ሲጠጋ መነኩሴው ካባውን ጨምድደው በመያዝ ፊታቸውን ወደ ገዳሙ ደጃፍ አዞሩና በጩኸት «ወንጀለኛው ልጅ ይኸውና! ይዤዋለሁ» አሉ፡፡
በጩኸታቸው የተነሳ ቄሶችና መነኩሳት ከተለያየ ማዕዘን እየሮጡ ብቅ፣ ብቅ አሉ። ከተቀሩት ባልደረቦቻቸው በለበሱት ምርጥ ልብስና በመራራ ባህሪያቸው የሚለዩት ቄስ-ገበዝ ከፊት ሆነው ይመሯቸዋል፡፡ የዘረፉትን ምርኮ ለመቀራመት እንደሚረባረቡ ወታደሮች ዮሐናን ከበቡት፡፡
በዚህ ጊዜ ዮሐና ቄስ-ገበዙን እየተመለከተ ረጋ ብሎ፣ «ወንጀለኛ ያላችሁኝ ለምንድ ነው? ለምንስ ያዛችሁኝ? እንደ ወንጀለኛ የምታይበት ምንም የፈፀምኩት ስህተት የለም» አላቸው፡፡
የቄሶቹ የበላይ እንደ መጋዝ በሚገዘግዝ ድምፅ፣ «ከብቶችህ የገዳሙ ንብረት በሆነ መስክ ላይ ሳር እንዲግጡ አድርገሃል» አሉት:: ከብቶቹ ተክሎቻችንን ተነጣጥሰው አበላሽተውታል፡፡ የወይን እርሻችንንም አውድመ ውታል፡፡ የያዝናቸውም በከብቶቹ ለደረሰው ጥፋት ኃላፊ በሆነው እረኛ ምትክ ነው፡፡›› ሲናገሩ ፊታቸው ላይ የሚታየው ንዴት ጨመረ።
«አባቴ ...» አለ ዮሐና፣ በሚያስተባብል ድምጽ። ግን እኮ ከብቶቹ
ምንም የማያውቁና መናገር የማይችሉ ፍጡራን ናቸው፡፡ እኔም ብሆን......
.............ይቀጥላል ...........
👍👍👍👍👍👍👍👍
https://t.me/Asresee
https://t.me/Asresee
https://t.me/Asresee