እኔም አላነበብኩትም።ነገር ግን ሩሀማ የተባለች ጓደኛዬ በደምብ እየነገረችኝ ነበር፤ይሄ መጽሐፍ "A Little Life" ይሰኛል።በአሜሪካዊቷ ፀሀፊ ሃንያ ያናጊሃሪ በ2015 ዓ.ም የተፃፈ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ መጽሐፍ ነው።መጽሐፉ 720 ገፆች ያሉት ሲሆን በኒውዮርክ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ ዊያልም፤ጄቢ፤ማልኮምና ጁድ የተባሉ የ4 ጓደኛሞችን ሕይወት በጥልቀት ይተርካል።ዊልያም ተዋናይ መሆን ይፈልጋል፣ ጄቢ አርቲስት ነው፣ ማልኮም አርክቴክት ነው፣ ጁድ ደግሞ ጠበቃ ነው።በተለይ ይሄ ታሪክ ጁድ ሴንት ፍራንሲስ የተባለ አንድ ገፀባህርይ ወይም ጠበቃ ላይ ትኩረት ያደርጋል።
ጁድ በልጅነቱ በጣም ተሰቃይቷል።የሌሎች ሰዎች መጠቀሚያ ሆኗል።በዚህ የተነሳ ራሱን ለመጎዳትና ለማጥፋት የሚሞክር ሰው ነው።የሚገርመው በልጅነታችን የተፈጥሩ ነገሮች አድገንም ተፅዕኖ እንደሚፈጥሩ የተረዳሁት በጁድ የህይወት ተግዳሮቶች ነው።በተጨማሪም ጓደኞቹ ጁድን ለመርዳት ቢሞክሩም ነገር ግን የእሱ ያለፈ ሕይወት እና ሥቃይ ለሁሉም ፈተና ሲሆን ያሳያል።ነገር ግን መጽሐፉ ምንም እንኳን አሳዛኝ ቢሆንም በጁድና በጓደኞቹ መካከል ያለው ቅርበት፤ፍቅርና መከባበር ልዪ ስሜት እንደሚሰጥ ሩሚ ጓደኛዬ ነግራኛለች።ሩሚዬ በጣም በጣም አመሰግናለሁ፤የኔ ጣፋጭ..
ይሄ መጽሐፍ በ2015 የማን ቡከር ሽልማት(Man Booker Prize) እጩ መሆን ችሏል።በተጨማሪም ከ205 ሚሊዮን በላይ ቅጂዎች በመሸጥ፤ በአለማችን አሳዛኝ መጽሐፎች ተረታ በ1ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።መጽሐፉን በሶፍትኮፒ ከፈለጋችሁ ከታች ባለው ሊንክ ማግኘት ትችላላችሁ፤መልካም ንባብ።
📚Pdf፦
https://t.me/Hulu_Books/335አነበዋለው👍 አላነበውም❤️ ላስብበት⚡️