ባንካችን ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት በካፌ የሚሰጠውን ማዕከል በድምቀት አስመረቀ!
ባንካችን አቢሲንያ በዋናው መስሪያ ቤት በሚገኘውና ከጫካ ቡና ጋር በመተባበር የከፈተውን ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት በካፌ የሚሰጠውን ማዕከል በትላንትናው ዕለት ጥር 22 ቀን 2017 ዓ.ም የባንካችን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ በቃሉ ዘለቀ፣ የጫካ ቡና ባለቤት አቶ ብስራት በላይ እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በታላቅ ድምቀት አስመርቋል፡፡
ይህ ዘመናዊ የባንክ አገልግሎት በካፌ በውስጡ በሚገኙ የኢንተርአክቲቨ ቴለር ማሽኖችና (ITM) የራስ አገዝ አገልግሎት መስጠት በሚችሉ ታብሌቶች አማካኝነት ደንበኞች ከቅርንጫፎች ማግኘት የሚችሉትን የባንክ አገልግሎት ማግኘት ይችላሉ፡፡
በተጨማሪም በማዕከሉ ውስጥ በሚሰጠው የካፌና የሬስቶራንት አገልግሎት ከጥሬ ገንዘብና ከወረቀት ንክኪ ነጻ (Cashless and Paperless) መልኩ በተለያዩ የዲጅታል አማራጮች የአገልግሎት ክፍያ የሚስተናገድ ይሆናል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ሊንኩን ይጠቀሙ፡-
https://surl.li/ypzbwf